
ከውይይት የተጠቀሰ፤ ሰላም፤ ትንሽ ላክልበት። ቃል ሥጋ ሆነ! በሌላ አገላለጽ መንፈስ ወይም መለኮት ስጋ ለበሰ deity or spirit embodied in flesh in human form “God incarnate” የለበሰው ስጋው ተራ ስጋ ሳይሆን ጸጋንና እውነትንም የተሞላ ነው በዚህ ሙላት በእኛ አደረ እኛም ክብሩን አየን። ስጋ ከመሆኑ በፊት ምን ነበረ? ዮሐንስ ምዕራፍ 1: 1. በመጀመሪያው ቃል (The Word ፡logos ሎጎስ ማለት የእ/ር ሀሳብ አስተሳሰቦች ስብስብ፤ ምክንያት፤ ንግግር የኮሙኒኬሽን፤ የቃላት መግለጫ ሐሳብ ሎጎስ) ነበረ። ቃልም (ሎጎስ: የእ/ር ሐሳቡ) በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ቃልም (ሎጎስ: የእ/ር ሐሳቡም) እግዚአብሔር እራሱ ነበረ።
John 1:1. Within a beginning there was The Word (logos: The Thought; The Collection of Thoughts; The Idea; The Reason; The Discourse; The Communication; The Verbal Expression). And the Word (logos: the thought; the expression) was (and continued being) facing, directed and moving toward (or: with) God. And the Word (logos: the thought; the idea; the reason; the expression) continued being God. [or: Originally the Word was existing and continued to be, and the Word was being {projected} toward God. And the Word, It was existing being God (idiomatically: And the Word was just what God was; And the Expression was {an extension of} Deity). JMT
” ቃል ሥጋ ሆነ “ይላል። ዮሐንስ 1 ፡14 የእ/ር ሐሳቡ ስጋ ሆነ። ኢየሱስ ሲወለድ ማለትም “እግዚአብሔር የነበረው ቃል” እና “ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ” የሚለው ቃል የሥጋ ቅርጽ ወይም መልክ ያዘ ወይም ሆነ የሰውነት ቁመናም የያዘ ሆነ። took the form of human flesh። መንፈስ በዚያን ቀን ሥጋ ሆነ። በእ/ር አጀንዳ ውስጥ የዚህ ክስተት አንድምታ እጅግ በጣም ሰፊ ግብ ነበረው።
ማወቅ ያለብን የእ/ር ትልም ወይም ንድፍ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን የሚለውን ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የአካሉ ራስ ብቻ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው በማንኛውም ጤናማ ውልደት ወይም ልደት የአካሉ የመጀመሪያ የሆነው ጭንቅላቱ በመጀመሪያ የእናቱን ማኅፀን በመክፈት ይወጣል። ከዚያ አካሉ እንደሚመጣ እናውቃለን እ/ር በዘረጋው የውልደት ስርአት እናስተውላለን። በነዚህ መንፈሳዊ ነገሮችም ላይ ክርስቶስ በመጀመሪያ ቃል የተፀነሰው ስጋ ሆኖ የተወለደ ቢሆንም ከዚያ በኋላ ግን የመውለድ ሂደቱ ለአካሉ አላቆመም። ሙሉ በሙሉ መወለድ መላው የእርሱ አካል እስከሚወጣ ድረስም በሂደት ላይ ነውና አልተጠናቀቀም አካሉ ሁሉ ቃል ሥጋ ሆነ ይባላል። ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና።
በቀደም እንዳነሳሁት ክርስቶስ ለብዙ ነገር የበላይ ራስም ነው። የአሕዛብም ራስ፤ የሕይወትንም ራስ ፤ የማዕዘን ራስ፤ የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፤ የቤተ ክርስቲያን ራስ፤ የመዳንንም ራስ፤ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ያመጣ የመዳናችን ራስ፤ የጥበብና የእውቀት ራስ፤ እርሱ የሁሉ ራስ ነው አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ የመሆኑ ሚስጥር ግን ታላቅ ነው፤ የአንድ አካል ! “ ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5/32”
ወደ ሮሜ ሰዎች 12/5 እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6/17 ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/12 አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤ወደ ገላትያ ሰዎች 3/28 አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።ወደ ገላትያ ሰዎች 3/27 ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1/18 እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው። የራሱ አካል ለሆነችው የቤተክርስቲያን ማለትም የክርስቶስ አካል [በእርሱ ሙሉ ሆናችኋል! ye are complete in him!] ይላታል። ራስ በሆነው በእሱ የመሎኮት ሙልአት ሁሉ በእርሱ ውስጥ ቲፍ ብሎ ተሞልቶዋል ማለት አካል ማለት ከአንገት በላይ ካለው የጭንቅላት የአካል ክፍል ብቻ ሳይሆን ይሄ በንፈሳዊ የክርስቶስ አካል ልጅነት በጥቅሉ ልጆችን ሁሉ የሚጨምር ነው የአካሉ ሙልአት ናችሁና። የጭንቅላት ብቻውን ብታዩ ሙሉ አካል ነው ልትሉ አትችሉም። ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ በውስጣችሁ ተሞልታችኋል። ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡7 በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ Phil 2፡7 and was #made in the likeness of men: መጽሐፈ መክብብ 11፡5 የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡3 ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።ወንድም ቢኒ።