
ከውይይት የተጠቀሰ፤Binyam TA ወደ አባቴ እመለሳለሁ ሲል አባት መንፈስ ነው በክርስቶስ አእምሮ እናስተውለው ወደ አባቴ ማለቱ ወደ መንፈሴ እመለሳለሁ ማለቱ ነው። ቀድሞ በመንፈስ ክቡር ነበር። ከአብ ወይም ከአባት ወጥቼ መጥቻለሁ ሲል ከመንፈስ ወጥቼ መጥቻለሁ ማለቱ ነው። በመጀመሪያው ቃል ወይም መንፈስ ነበረ፥ ቃልም መንፈስም እግዚአብሔር ነበረ። ቃልም ወይም መንፈስም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ ። ስሙንም #አማኑኤል ይሉታል ትርጓሜውም። #እግዚአብሔር #ከእኛ #ጋር የሚል ነው። ከደቀ መዛምርቱ አንዱ ጠርጣራው ቶማስ እያማረረ ጌታን ጠየቀ “ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም መንገዱንስ እንዴት እናውቃለን” እኔ ነኝ መንገዱ፤ እየሱስም ደገመ፤ እኔ ነኝ እውነቱ፤ እየሱስ ሰለሰ እኔ ነኝ ህይወቱ፤ ማርታ በሃዘን በተሞላ አነጋገር”በመጨረሻው ቀን በትንሳኤ እንዲነሳ አውቃለሁ አለችው” እየሱስም መለሰ “ትንሳኤ እኔ ነኝ፤ ህይወት እኔ ነኝ” ;;
መጽሃፍት ትመረምራላችሁ መጽሓፍት ሁሉ ግን ስለኔ ይናገራሉ ህይወት እንዲሆንላችሁ ግን ወደኔ ልትመጡ አትወዱም። ምን ምን? መጽሓፍት ሁሉ ግን ስለኔ ይናገራሉ ? ሁሉ ስለኔ የሁሉ ትርጉም ሁሉ ነው። “እኔ ነኝ” “I am” መጨረሻ የለውም የወይኑ ግንዱ እኔ ነኝ፤ በሩእኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ የአለም ብርሃን እኔ ነኝ ፤ አልፋ እኔ ነኝ ፤ ኦሜጋ እኔ ነኝ ፤ የመጀመርያው እኔ ነኝ፤ የመጨረሻው እኔ ነኝ፤ የምዋጀው እኔ ነኝ ፤ ብርታትህ እኔ ነኝ ፤ የሚኖረው እኔ ነኝ ፤ ሞቶ የነበረው እኔ ነኝ ፤ ትንሳኤው እኔ ነኝ ፤ የዘጋሁትን ማንም የማይከፍተው የከፈትኩትን ማንም የማይዘጋው እኔ ነኝ ፤ የዳዊት ስርና እኔ ነኝ ፤ የንጋት ኮከብ እኔ ነኝ፤ ስሙም ድንቅ መካር እኔ ነኝ ፥ ኃያል አምላክ እኔ ነኝ ፥ የዘላለም አባት እኔ ነኝ ፥ የሰላም አለቃ እኔ ነኝ “ያለውና የሚኖረው እኔ ነኝ:
እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ… እኔ እኔ ነኝ በላቸው” [I AM that I AM, tell the pepople that I AM hath sent you] እነሆ ለስነቱ መጨረሻ የለውም ። “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2:9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤የዮሐንስ ራእይ 1:8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።” አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ ያለኝ እኔ እኔ፤ የታመነውና እውነተኛው ምስክር እኔ ነኝ፥።የዮሐንስ ራእይ 4:10-11 ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም[ለደስታህ ተፈጥረውማልና for thy pleasure they are and were created.] ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።
ከመጀመርያው የተናገርኩት ነኝ
ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም። “ የዮሐንስ ወንጌል 8/25 እንግዲህ፦ አንተ ማን ነህ? አሉት። ኢየሱስም፦ ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርሁት ነኝ። ….27 ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም። ወንድም ቢኒ።