በሰው ውስጥ ሁለት አይነት እይታ አለ አዳማዊና ክርስቶሳዊ


ከውይይት የተጠቀሰ፤ Willy Mac ክፍል አንድ። ሰላም። በሰው ውስጥ ሁለት አይነት እይታ አለ አዳማዊና ክርስቶሳዊ የአዳምን ሁላችንም ስለምናውቀው ትንታኔ ብዙም አያስፈልገውም የክርስቶስ እይታ ግን የነገሮችን እውነተኛ ተፈጥሮ ስለሚረዳና ስለሚያውቅ ዓይኑ እንደምታይ አይፈርድም ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም። አንተ ጣል ያደረካት ጥቅስ ጥሩ ናት በደንብ ብናስተውላት ግ ን ክችግሩ ምንጭ ዘንድ ትጠቁመናለጭች ። 1 ዮሐ 3: 4 እንዲህ ይላል:4 ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን[ህግን መተላለፍ] ደግሞ ያደርጋል: ኃጢአትም ዓመፅ[ህግን መተላለፍ] ነው። 1John 3:4O Whosoever committeth sin transgresseth also the law[ህግን መተላለፍ]; for sin is the transgression of the law ኃጥያት ህግን መተላለፍ ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 3፡ 23 ሁሉ ኃጢአትን sinned [hamartano ham-ar-tan’-o to miss the mark (and so not share in the prize) ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር[የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነው። የሐዋርያት ሥራ 7/55] ጎድሎአቸዋል፤ ። አሁን አንተ በአንድ መአዝን ያለውን እይታ አንስተካል እይታው ግን ሰፊ ነው። ለመሆኑ ከፀጋ በታች እንጂ ከህግ በታች አይደላችሁም ምን ማለት ነው? ከፀጋ በታች እንጂ ከህግ በታች አይደላችሁም የሚለው ቃል እንደ እይታቸው ልክ ብዙ ወገኖች ፍቻቸውም ይልለያያል። አንዳንዶች ባለአእምሮ ወይም ቃል በቃል የሚተሮጉሙ ሊትራሊስት በመባል የሚታወቁት አማኞች የተፈጥራዊ ሰው እይታ literalist [A person who translates text literally or not spiritually discerned] ይህ እይታ በአብዛኛው ፊደል ቃል በቃል የሚወስድ ወገን ሲሆን። ያላቸው እይታ ሌላው ቀርቶ የዮሃንስ ራእይን ምንም እንካን ጌታ ለባርያው በመላኩ በኩል በምልክት ጌታ ቢያጽፈውም ሁሉ ነገር ተፈጥራዊ እንጂ መንፈሳዊ እይታ የለውም ብለው ቃል በቃል ይረዱታል። [not figurative or metaphorical] የሚል አቃም ያሳያሉ። ይህም ሁሉ ነገር መንፈሳዊ ነው ከሚሉ ወገኖች ጋርም የአመለካከት ልዩነት በዚህ ምክኛት አለ። ከፀጋ በታች እንጂ ከህግ በታች አይደላችሁም በሚለው በዚህም ላይ ሃሳባቸው ተመሳሳይ ሆኖ ለሁለት የተከፈለ እይታ አላቸው። አንደኛው ወገን
“በሕጉ መሠረት” ህግን የመጠበቅ ግዴታን ያመለክታል ይላሉ። ነገር ግን ህጉን የማክበር አቅምና ግዴታ ከሌለን ለምን ኃጢአት እንዳንሠራ ይከለክለናል? የኃጢአት የዘወትር ፍቺው በጳውሎስ ጽሑፎች ውስጥም ሆነ በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ህግን መተላለፍ ነው። የአማርኛ ትርጉሞች በስተት ቀጥተኛ ትርጉሙን ደብቀውታል እንጂ በዋናው ቃንቃ ሆነ በእንግሊዝኛው ህግን መተላለፍ ኃሃጥያት ነው ይለዋል። 1 ዮሐ 3: 4 እንዲህ ይላል:4 ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን[ህግን መተላለፍ] ደግሞ ያደርጋል: ኃጢአትም ዓመፅ[ህግን መተላለፍ] ነው። 1John 3:4O Whosoever committeth sin transgresseth also the law[ህግን መተላለፍ]; for sin is the transgression of the law ኃጥያት ህግን መተላለፍ ነው።
የዮሃንስ ዓረፍተ-ነገር ከጳውሎስ አስተሳሰብ ጋር ሙሉ ለሙሉ ስምምነት እንዳለው ማሰተዋል አለብን። በሮሜ3 በሕግ ምክንያት የኃጢአት እውቀቱ ይመጣልና ብለዋል። ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና። ( ሮሜ 3 20 ) እና “ነገር ግን በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ፦ አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና።” ( ሮሜ 7 7). ሕጉ ኃጢአትን ምን ማለት እንደሆነ ይገልፃል። ክርስቶስ የህግ ፍፃሜ ነው። በክርስቶስ ባለው ፍቅርም የሕግ ፍጻሜ ነው።እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ። በፍቅር የሚኖር ህግን ሁሉ ፈጽመዋልና። “ወደ ሮሜ ሰዎች10፥4የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።” “13፥10 ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።” ጽድቃችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነውና ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም የተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ ፃድቃን የሆነው ከእርሱ ነው እንጂ ከኛ አይደለም።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1/30-31 ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።
ታዲያ ኃጥያት ማለት ህግን መተላለፍ ከሆነ።ጳውሎስ በሮሜ 6:14 ራሱን እንዴት ተቃርኖ ፃፈ ወይስ ምን እያለን? በእርግጥ እሱ እያለ ያለው ህግን የማክበር ሃላፊነት ከእንግዲህ የለብንም ማለቱ ነው? ማለትም ከኃጢአት መቆጠብ የለብንም እያለ ነው? እዚህ ላይ ነው ከህግ በታች አይደለንም የሚለው ሃሳብ ለብዙ ሰዎች ግንዛቤው ትክክል ያልሆነው።
“በሕግ ሥር” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ሕግ ወደ እናንተ ያለው አቅጣጫ አመለካከትን ነው እንጂ እናንተ ወደ ሕግ ያላቹሁን አመለካከት አይደለም። በህግ በኃጢአት (በወንጀል) የተከሰሰ አንድ ኃጢአተኛ “በህጉ ስር” ነው። አጥፊው ለወንጀሉ ሲባል ከህግ ስር ሆኖ ካሳ ለተጎጂው እንዲከፍል የሚያስገድደው ህጉ በእሱ ላይ በተቃውሞ ይቆማል። ዕዳውን ሙሉ በሙሉ በእጥፍ በመክፈል ወይም ዕዳውን ሰርቶ በመክፈል ወይም የቅርብ ዘመድ እዳውን ከፍሎ ከዕዳ የሚገላግለው አንድ ሰው ከአገሩ ከወገኑ ካለው “በሕግ ሥር” የነበረው ሰው ነፃ ወጥቶ አሁን እዳው ስለተከፈለ ከዚህ ቡሃላ”በሕግ ሥር” አይደለም “ከጸጋ በታች ነው.” ተብሎ ይፈታል። እንዲህ ባለው ሁኔታ ፍርድ ቤቱ በይኖ ጉዳዩን ይዘጋዋል። ምክንያቱም ምንም ዓይነት ተጨማሪ ሥራ ስለማይኖር እና ምንም ተጨማሪ ፍላጎት ህጉ ከሌለው ከፀጋ በታች ባሉት ላይ ህጉ ስልጣን የለውም። አንድ ሰው ወንጀል (ኃጢአት) ሲፈጽም ብቻ ነው “በሕግ ሥር” ተብሎ ህጉ ዳኛ ፊት እንዲቀርብ ያስገድደዋል። …..2 ወንድም ቢኒ።
ክፍል ሁለት፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን እንደ እ/ር ቃል ለምሳሌ, አንድ ሌባ 1,000.000 ብር በመስረቁ ተፈርዶበት ከሆነ የእግዚአብሔር ሕግ ሁለት እጥፍ ለተጎጂው እንዲመልስለት ይፈረድበታል (ዘጸአት22/4 …።የሰረቀውን ያህል ሁለት እጥፍ ይክፈል።) ለተጠቂው ሁለት እጥፍ $ 2,000,000 ገንዘቡን ለመክፈል ባይኖረው በዳኛው በተወሰነው መሰረት ረጅም ጊዜ ዕዳውን በስራ መክፈል ይኖርበታል። ሌባው ለ3 አመታት በስራ እንዲቀጣ ከተፈረደ ሌባው “በህጉ መሠረት” ለ3 አመታት “በሕግ ሥር” ነው ይባላል። የህግ እስረኛው የፍርድ እገዳ በመክፈሉ ምክኛት ሲጠናቀቅ ወደ ፍርድ ቤት ይመለሳልና ጉዳዩ ይታያል። ዕዳውን መክፈሉን ወይም አለመክፈሉን ዳኛው ያጣራና የመጨረሻውን ብይን ይወስናል። ዳኛው ጉዳዩን መረምረው እዳውን መክፈሉን እርግጠኛ ሲሆኑ ይህ ሰው ዕዳው ተከፍሏል ስለዚህ “በጸጋው ሥር ” ነው ከእንግዲህ “በሕግ በታች” አይደለም ብለው ይበይናሉ ምክንያቱም ዕዳው ተከፍሏል።
ሕጉ ሁሉንም ሰዎች የኃጢአት ባለእዳ ናችሁ ብሎ ሃጥያተኞች ያረገናል። ይሁን እንጂ ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን “ከሕግ ሥር” ወይም “ከሕግ በታች” አይደለንም። ለምን? ምክንያቱም ስለ እኛ ጌታ ኢየሱስ ዕዳችንን ስለከፈለልን እና ህጉ ስለረካ ነው። እንግዲህ ፍሬ ሃሳቡ ምንድር ነው? ኢየሱስ ዕዳችንን ለመክፈል አቅም ኖሮት ቢከፍልንን በኃጢአት እንቀጥላለን? በጭራሽ! ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን? እ/ር ያርቀው አያድርገው እና! ክርስቲያኖች፤ የእ/ር ልጆች ጸጋ የኃጢአት መንጃ ፈቃድ አለመሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል። ጸጋ የኃጢአት ዕዳ የተከፈለለት አንድ ሰው ሁኔታ ብቻ ነው። ስለዚህ ሕጉ በአሁን ጊዜ በእርሱ ላይ የነበረው እዳ የተከፈለለት በመሆኑ ጸጋ እንዳይከሰት ከለላ ሆኖታል። የኃጢአት ትርጉም አልተለወጠም ኃጥያት ማለት ህግን መተላለፍ ነው። እግዚአብሔር አምላክም የሃጥያት ትርጉም ሰው እንዲቀይር ስልጣንን አልሰጠውም። ሕጉን ለማጥናት ጊዜ ብንወስድ እግዚአብሔር የኃጢአትን ትርጉምና እውቀት ሊሰጠን የእርሱን ህግ ሰጥቶናል። አንድ ጊዜ ሕጉን ስናውቅና ስንቀበል ሕሊናችን ማስተዋል ይችላል የእግዚአብሄርን ህግ በአግባቡ በግል ሕይወት እንዴት እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል አቅልሎታል ፍቅር የህግ የነብያት ሁሉ ፍፃሜ ነው። በፍቅር የሚኖር ክፉን አያደርግምና ህኝ ሁሉ ፈጽመዋል። በአሮጌው ኪዳን ለዕብራውያን ህግ በድንጋይ በጽላት ላይ የተፃፈ በውጪ የተፃፈ ነበር። በአዲሱ ኪዳን ግን እንዲህ ይላል። ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው በስጋ በጽላት ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ። “ወደ ዕብራውያን 10/15-16 መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ብሎ ከተናገረ በኋላ፥” በክርስቶስ ያለ ፍቅር የህግ ፍፃሜ ነው።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4/16 እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3/9 ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ #ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ #ከእግዚአብሔርም#ተወልዶአልና#ኃጢአትን[ sin is the transgression of the law ኃጥያት ህግን መተላለፍ ነው።] #ሊያደርግ አይችልም። ያውልክ እንግዲህ ከእግዚአብሔር መወለድህ የአባትህ ባህርይ ስለሆነ እንደአባትህ ተቀድሰህ ትኖራለሕ ። ወንድም ቢኒ።

The way of the eagle in the heavens , Let us see the two views of life in man, Adam view and Christ view: we may say the frog’s view and the eagle’s view. The frog’s view represent Adams limited view of the spirit realm, To the frog’s view : the universe is limited by the muddy pool in which it lives; the frog never sees beyond the muddy water and the pond, and is thus totally ignorant of the lakes, the rivers, & to the unbounded universe, In contrary the eagle’s view represent divine perspective of GOD [Christ] we all are #one in him John 17:20 , He can see from the highest heavens throughout the whole earth ፣ “For the eyes of the Lord run to and fro throughout the whole earth. 2Chr 16/9”
• We can also see God represent his divine act with eagles Exod 19/4 Ye have seen what I did unto the Egyptians, and how I bare you on eagles’ wings, and brought you unto myself.
• “They Shall Mount Up With Wings of Eagles” Eagles saints! Of course, the way of the eagle in the heavens. (Prov 30:19O Bro. Bini.

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal