
ከውይይት የተጠቀሰ፣ ሰላም ወገኖች። ማንም ሲናገር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር እንጂ እንደ ፖስተርዮ እንደነብዮ አይልም። ለእግዚአብሔር የታመነ ነብይ ይሁን ወይም ፓስተር ወዘተ የሚመዘነው በእግዚአብሔር ቃል ነው። እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እኛ የተጠራነው በጎነቱን እንድናገር ነው። ቃሉ ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ ነው ይለናልና ሆኖም የእግዚአብሔርን ሉአላዊነት ማወቅ ለሚሹ እብደቃሉ እውነትን እናገራለን። ልጆች አሁን አንድ እግዚአብሔር አባት እንዳለ እየተረዱ ነው። 3 እግዚአብሔሮች የዳቪንቼ ንድፍ ስእል አምላኪዎች ምናን ውስጥ የሚዋኙ ዝፕንድ ነው። ፫ እግዚአብሔሮች በ325 ግም ሊቃውንቱ ሲተረጉሙ ወደ መፅሀፍ ቅዱስ የገባ አረም ነው። እግዚአብሔር ፍቅር ነው እውነት ነው እግዚአብሔር የሚባላ እሳትም በመአት የተሞላ ነው። “እብ12:29 አምላካችን በእውነት #የሚያጠፋ እሳት ነውና።” አንድ እግዚአብሔር መልካም መልካሙን ብቻ የሚያደርግ ሰይጣን የተባለ ክፉ ክፉ የሚያደርግ የእግዚአብሔር ተገዳዳሪ ተደርጎ ማሰብ በቴክኖን ጨቅላ ልጆች ዘንድ ነው በሂዮስ የበሰሉ ልጆች ዘንድ ሁሉን በሁሉ የሚሰራው አንድ አባት እግዚአብሔር ያስተውላሉ። ኅይል የእግዚአብሔር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ምንም ቢያደርግ የልቡ መነሻ ፍቅር ነው። ፍቅሩን ለሚያከብሩ ምህረቱን ቸርነቱን፣በጎኖቱን፣ ማዳኑን፣ የዋሁነቱን፣ ጥበቡን፣ ፀጋውን፣ ወዘተ …. ይለማመዳሉ ፍቅሩን የሚያሰቃዮ ያው ፍቅር የሆነ ጌታ የሚባላ እሳት ሆኖ ይለማማመዱታል። ማንም ፍፁም እስከሌለ ድረስ ሁሉ ሰው በእሳቱ ይቀመማል። እግዚአብሔር በቀኙ አሰራር የብርሃን ፍሬ ዝርዝሮች ይሰራል የግራው(የእ/ር ፅልመተ ጎኑ the Dark Side of God) መአቱ ይገለጣል። እውነት የሆነውን ልናስብ ልንናገር ግድ ይለናል።
እ/ር ተቃራኒ ሃይላትን የፈጠረው። በትንቢተ ኢሳይያስ 45፡7 ብርሃንን ሠራሁ፥ #ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ #ክፋትንም እፈጥራለሁ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
ትንቢተ አሞጽ 3:6 ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ #ክፉ ነገር በከተማ ላይ የመጣ እንደ ሆነ #ያደረገው#እግዚአብሔር አይደለምን? ክርስቲያን ተቃርኖ ፀረ ልኡላዊ እግዚአብሄር ሃሳብ የሆነውን ያደረገው #እግዚአብሔር አይደለምን? የሚለውን ያደረገው ሰይጣን አይደለምን? ብሎ በእግዚአብሔር ላይ ይዋሻል። ኦሪት ዘጸአት 4:11 እግዚአብሔርም፦ የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው? ዲዳስ ደንቆሮስ የሚያይስ ዕውርስ ያደረገ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
አዎን ሁሉን መፍጠሩን እ/ር ሃላፊነቱን ወስደዋል:: እራስ በራሳቸው የሚቃረኑትም ጭምር ማለት ነው። ለማሰብ ያህል መራራና ጣፋጭ፤ ሃዘንና ደስታ፤ ድሃና ባለጠጋ፤ ጨለማና ብርሃን፤ መልካምና ክፉ፤ ህግና ጸጋ፤ ተፈጥራዊ ነገሮች ና መንፈሳዊ ነገሮች፤ ሞትና ህይወት፤ እስራትና ነጻነት፤ ለምን ብሎ እ/ር እንደዚህ በጥብቅ የሚቃረኑ ሃይላትን ፈጠረ?
አዎን ማየት ያለብን እ/ር መንገዱን ሊያስተምረን ተቃራኒ ሃይሎችን መፍጠር ነበረበት። መልካምን እንዴት እንረዳው ነበረ ክፉ ባይኖር ኖሮ? የእ/ርን ረቂቅ ጥበቡን በመጠኑም ቢሆን ልንገነዘበው ይገባል። ፉጡራኑን ወደ ብስለት ለማምጣት በምን እደሚያሳልፈን ስናስተውል ይደንቃል:: ተፈጥሮውና ባህርዩ በሰው ውስጥ ይገለጥ ዘንድ የሚጠቀመው ተቃራኒ ሃይላትን ነው:: “መዝሙረ ዳዊት 119፡71 ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።” መጽሐፈ ኢዮብ 36፡15 …. በመከራም ጆሮአቸውን ይገልጣል። Job 36፡15 He… openeth their ears in oppression.
አንድ ሰው በእብራዊን ቋንቋ የጌታን ድምጽ ሰማሁ ካለ ፈጽሞ ሰምቶ ፈጽሞ መታዘዙን የሚያሳይ ነው። ሰምቶ ካልታዘዘም ፈጽሞ አልሰማም። በመገለጥ እንዲሰማም በሌላ ሂደት ያልፋል። “በመከራ ጆራቸውን ይከፍታል። እዮብ36፡15 በእብራይስጥ መከራ የሚለው ውጥረት ይለዋል። አንዳንድ ጊዜ ለምን ይሄ ሁሉ ውጥረት በመንገዳችን እንደ ሚያልፍ እንደነቃለን። እንደ ዛም ሆኖ ነገር ሁሉ ተያይዘው ለበጎ እንዲደረግ እንረዳለን። በብዙ መከራ ማለፋችንም ለብዙ አላማ እንደሆነ እናውቃለን። ከዛ ውስጥ አንዱ ጆራችን እዲከፈት ነው። ጳውሎስ የደቀ መዛምርቱን ልብ በማበረታታትና በእምነታቸወ ጸንተው እንዲሩ በመምከር “ወደ እ/ር መንግስት ለመግባት በብዙመከራ (ግሪክ፦ pressure, እደአገባቡ ቃሉ ሲተረጎም ውጥረት ግፊት መገፋፋት ተጽኧኖ የሚያመጣ ውጥረት )ማለፍ አለብን “” ሐዋ14፡22 ይህም ውጥረት ከአሮጌው አውጥቶ ወደ አዲሱ ተጭኖ ያስገባናል። እ/ር አምላክ ጥበበኛ ነው። አንዱን ውጥረት ከአንድ ነገር ለማውጣትና በተመሳሳይ ሰአትም የስጋን ፈቃድ ሰብሮ የመንፈስን ድምጽ ወደ መስማት ግዛት ያመጣናል።” ወንድም ቢኒ።