እግዚአብሔር መንፈስ ነው ከመንፈስ እግዚአብሔር የተወለደ መንፈስ ነው! አንዳንዱ ሰው ከመንፈስም የተወለደ ሥጋ ነው ብሎ ገልብጦ ይረዳዋል።


ከውይይት የተጠቀሰ፣ ክፍል 1፡ ሰላም ሁላችሁም ደስ ትላላችሁ ስለሁላችሁም እ/ር ይመስገን፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥የዮሐንስ ወንጌል 4/24 ልጆቹም እሱን ይመስላሉ እንጂ ሌላ አይመስሉም። መቼም ነገር ሳይንዛዛ በአጭር ቃል እንቅጩን እንደጌታ የሚያስቀምጠው የለም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ #ከመንፈስም #የተወለደ #መንፈስ ነው። የዮሐንስ ወንጌል 3/6 አለቀ እግዚአብሔር መንፈስ ነው ከመንፈስ እግዚአብሔር የተወለደ መንፈስ ነው! አንዳንዱ ሰው ከመንፈስም የተወለደ ሥጋ ነው ብሎ ገልብጦ ይረዳዋል።
እግዚአብሔር ዘፍጥረት 1 ላይ ሁሉ እንደ #ወገኑ #ዘሩን ያዘጋጅ ይብዛ አላለም? በምድርም ላይ #እንደ #ወገኑ #ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።እግዚአብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን፥ ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውንም ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።እግዚአብሔርም አለ፦ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን #እንደ #ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፤ እንዲሁም ሆነ።
ታዲያ ሰው ጋር ሲደርስ እንደ ወገኑ እንደ እግዚአብሔር የማይዘጋጅበት ምን ምክንያት አለ? እግዚአብሔር ቃል ነው ቃልም መንፈስና ህይወት በውስጡ አለው እንደ ወገኑ ከመንፈስ እግዚአብሔር ዘር የተወለደም መንፈስ ነው! እነርሱ ከእግዚአብሔር ወገን ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወገን ወይም ከወንድ ፈቃድ ወገን አልተወለዱምና ።የዮሐንስ ወንጌል 1/13
መንፈሳዊው የስንዴ ቅንጣት ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ወድቆ ሞተ ህይወት የሚለቀቀው በሞት ውስጥ ነውና ብቻውን አልቀረም፤ ብዙ መንፈሳዊ የስንዴ ዘለላዎችን ተንዠርግጎ ፍሬ አፍርተዋል።
ወንድማችን ስለ መንፈስ ቅዱስ በመሃል ባነሳው ሃሳብ በሁኔታ የተወሰነ እንዳልሆነ ለማስመር እሻለሁ። በአጭር አማርኛ በመንፈስ ቅዱስን #ታትመናል #sealed ! እንደ ብሉይ ኪዳን የሚወርድና የሚነሳ አይደለም። መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ ካለ አለ ነው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡13 ye were #sealed with that holy Spirit”በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ ሲል መንፈስ ቅዱስንም #ስጦታ ነው። እ/ር ደግሞ በስጦታው ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም። እንዳውም አሁን የመንፈስ ቅዱስን ቀብድ ነው የተቀበልነው ሙላቱን እንወረሰዋለን።
የዮሐንስ ወንጌል 14፡15-16 … #ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ 17 እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው #የእውነት #መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። 18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች #አልተዋችሁም[ኢየሱስ ክርስቶስ}፤ #ወደ #እናንተ #እመጣለሁ[ማ? ኢየሱስ ክርስቶስ}። 19 ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ #ዓለም #አያየኝም[ማንንን? ኢየሱስ ክርስቶስ]፤ እናንተ ግን #ታዩኛላችሁ[ማንንን? ኢየሱስ ክርስቶስ]፤ ]፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ። 20 እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን #ታውቃላችሁ
ማወቅ ያለብን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ አጽናኙ ነው። …..ክፍል 2 ወንድም ቢኒ።

ክፍል 2 ፡ማወቅ ያለብን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ አጽናኙ ነው። “I will NOT leave you abandoned[comfortless], or send you off as orphaned ones. I am repeatedly (habitually) and progressively coming toward you [in the form of the comforter and spirit of truth] men. (Jn 14:18
ጌታችን ምን እንዳለ በግማሽ ሳይሆ በሙሉ ትኩራታቹሁ አሁን አስተውሉ። መንፈስ ማን እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሆነ ግልጽ ያደርግልናል። የስላሴ 3ኛ አካል ነው ? ወይስ ጌታ እራሱ ወደ ቀድሞው የመንፈስ ክብሩ ተመልሰዋል ጌታ እራሱ ይናገር።
20እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን[አጽናኙ በሚመጣበት ቀን] ታውቃላችሁ።
“IN THAT DAY [the day when the comforter comes] you shall know that I am in My Father, and you in Me, and I IN YOU” (Jn 14:20
“John 14/28 Ye have heard how I said unto you, I am going, and I AM COMING TO YOU” የዮሐንስ ወንጌል 14/28 እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ።
አስተዋላችሁ ጌታ ምን አለ ? I am going, and I AM COMING TO YOU! እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ!
አሁን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ ተብሎ መጠራቱን በእ/ር ቃል እናረጋግጥ። nother Comforter[ጳራቂላጦስ] ሌላ አጽናኝ[ጳራቂላጦስ] ይሰጣችኋል ያለው ጳራቂላጦሱ ማን እንደሆነ እናያለን።
የዮሐንስ ወንጌል 14/15-16 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ[ pray] ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] ይሰጣችኋል፤
John 14/15 If ye love me, keep my commandments.16 And I will pray the Father, and he shall give you another Comforter[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.], that he may abide with you for ever;
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፡1 ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
1John 2/1 My little children, these things write I unto you, that ye sin not. And if any man sin, we have an advocate[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] with the Father, Jesus Christ the righteous: ያውላቹ እንግዲህ ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ጳራቂላጦስ አጽናኙ እራሱ ነው። በተረፈ በጌታ ፍቅር ሰላም ለአንተ ይሁን። …።ክፍል 3 ወንድም ቢኒ።

ክፍል 3፡ መንፈስ ቅዱስን የሰደበ የማይሰረይ ሃጥይት ነው ብሎ ነገር የለም አራሚ ፍርድ በገዛ ዘመኑ ይቀበላል እንጂ። ባለፈው እንዳልኩት በአዲስ ኪዳን ”ዘልአለም Eteernal, Everlasting” የሚለው ቃል ከዋናው የግሪኩ ቅጂ ላይ “aionions” ከሚለው ቃል የተረጎመ ነው የቃሉ ስር ወይም፡ ንብረትነቱ “EION” ነው። ትርጉሙም “ዘመን age” ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ናቸው ማለት አይደለም ። aion(the noun form) ሰዋሶው ወይም ነባር ስም ሲሆን aionions (the adjective form ቅጽል ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሶው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንት ሰዋሰው ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት፦ እለታዊ, አመት ፦አመታዊ እንደሚባለው መለት ነው። Greek word “aion” (Strongs #165) or its adjective form “aionios” (#166).በመረዳት ብርሃን ማስተዋል ያለብን ዘመን ማለት ዘልአለም ማለት አይደለም። ብዙ ጊዜና ብዙ ወቅቶች አሉ። ነገር ግን አንድ ዘልአለም ብቻ አለ። ዘልአለም ጅማሬ የለው ፍፃሜም ቢሆን የለውም። ነገር ግን ጊዜ ዘመን ወቅቶች ሁሉም ጅማሬ አላቸው ፍፃሜም አላቸው። ጊዜ ሲያበቃ ዘልአለም ይጀምራል የሚለው አባባል ፈጽሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም ዘልአለም ጅማሬ የለውም የሚያበቃም አይደለም። ዘልአለም ጊዜ ሲመጣ የሚጀምር አይደለም። ዘመናት በዘልአለም ውስጥ የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ልክ ሴኮንድ በደቂቃ ውስጥ ቦታ እንዳለው ደቂቃም በሰአት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው ሰአትም በአመታት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው። አመታት እና ዘመናት ያልቃሉ በዘልአለም ውስጥም የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ጊዜ እናስተውል ዘንድ በነዚህ ቃላቶች መካከል ያለው ልዩ ነት ግልጽ እይታ ሊኖረን ወሳኝ ነው። ዘመን የሚመደበው በጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘልአለም ግን ጊዜ አልባ ነው። በመጽሐፍ ስለ ዘመን የተናገሩትንና ሰለ ዘልአለም የተናገሩትን ለይተን ማስተዋሉ የእ/ርን ጠቅላላ ምክር እናስተውል ዘንድ እጅግ ይጠቅመናል።በጣም የሚያሳዝነው አብዛኛዎቹ የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች ብዙ የሚመሰገኑበት ቢኖርም ዘመንን በተመለከተ ሲተረጉሙ ግድ የለሽ ሆነው ዘልአለም እያሉ በመተርጎማቸው በእ/ር ህዝብ ላይ ለዘመናት ትልቅ ግራ መጋባትን አስከትለዋል። ይህም ብዙ ትውልዶችን ለአያሌ ዘመናት የተዛባ መረዳት ውስጥ ቆልፎ አስቀምጠዋቸዋል። ለመጥቀስ ያህል የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች KJV ላይ እዲሁም በዚህ መጽሐፍ ተጽኖ ስር የተተረጎሙ ሁሉ ላይ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ስለሚሳደብ ሰው የተናገረውን ቃል እንዲህ ያስቀምጡታል። እግዚያብሄር ያሳያችሁ አንዱ ቃል ወደ ስንት ተበታትኖ እንደ ተተረጎመ age {2 ጊዜ beginning of the World {2} ጊዜ, for ever and ever,(8) course{1}ጊዜ World {32} ጊዜ eternal {42}ጊዜ, world began{1}ጊዜ forever{27}, for evermore{2},
እነዚህ ሁሉ ዘመን ወይም እንደ አገባቡ ከዘመን ዘመን፤ ለዘመናት፤ ለዘመኑ፤ ወዛተ ተብሎ በቀላሉ በዚህ መልክ መተርጎም ነበረበት። “ማርቆ3/29 መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን “የዘልአለም” ሃጥያት ይሆንበታል እንጂ አይሰረይለትም” ከዚህ የተሳሳተ ትርጉም የተነሳ የተሳሳተ ጽንሰ ሃሳብ ተወልደዋል። ለዘልአለም ይቅር የማይባል ሃጥያት አለ ብለን እንድናስብ አድርጎን ነበር። ነገር ግን የቃሉ ፍቺ በትክክል እንዲያቀብል አድርገው ከተረጎሙት ከጥቂት የእንግሊዝኛም ትርጉሞች መካከል Emp hatic Diaglott የተባለው ትርጉም ትክክለኛውን ትርጉምi እዲህ ያስቀምጠዋል። “Whoever may blasphemy the Holy Spirit no forgiveness to the age but is exposed to anian lasting judgment mar3/29” “መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ “ለዘመኑ” ይቅር አይባልም። ነገር ግን ”ለዘመኑ“ ፍርድ ይጋለጣል።“ እንደ ምናስተውለው ይቅር የማይባለው ለፍርድ የሚጋለጠው ለዘመኑ ፍርድ እንጂ ለዘልአለም ፍርድ አይደለም። በማትዮስ 12/32 ያለው ደግሞ እንዲህ ተብሎ ተተርጉመዋል ”በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ ”አለም“ ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም። አለም የሚለው ቃል ከግሪኩaion ማለትም ዘመን age ተብሎ መተርጎም ከነበረበት ቃል የመጣ ነው። ቃሉ መተርጎም የነበረበት “መንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ “ዘመን” ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም” ነው። ጌታ እየሱስ የተወለደው በህግ ዘመን ስለ ነበር በዚህ ዘመንም ቢሆን ማለቱ የህግን ዘመን ለማሳየት ሲሆን በሚመጣው ዘመን ቢሆን ሲል ደግሞ አሁን እኛ ያለንበትን የፀጋውን ዘመን ማለቱ ነው። ይህን ካስተዋልን ስለ ዘመንና ስለ ዘልአለም ያለውን ብዥታ ያጠራልናል። በግሪክ aion(ሰዋሰው noun) በግልጽ “ዘመን ወይም ያልተወሰነ ክፍለ ጊዜ ነው an age or an indefinite period of time, Young’s Concordance” ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal