ክፍል1 Rahel Guta Ye Eyesus ሰላም ይሁንልሽ። ዋናው ሁላችንም የእ/ር ፈቃድ ይሁንብን ይውረሰን። ካነሳሽውና ከተቆጣሽ አይቀር ሁላችንም እ/ር እንደ ገለጠልን የተለያየ የመረዳት እንከን እንዳለንና በተረዳንበት ልንመላለስ የግድ ቢሆንም ይህችን እናስተውል። እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፤ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ። ይላልና እስቲ ወደ ስጋ ግዛት ወርደን ማለትም በስጋ ስራ ትችት መመላለስ ሳይሆን በቃሉ ተደግፈን እንነጋገር። ቃሉ ካለ ሁላችንም እንታረማለንና አስተምሪን። ትንቢተ ሚልክያስ 3/16 የአለም መሰረት ሳይጣል ልጆች ነበሩ? መልሱ መንፈሳዊውን ነገር እንደ ማየት አቅማችን ይወሰናል። ልጆች ያለ አባት ልጅ ሊባሉ አይችሉም አባትም ካልወለደ ልጆች ከሌሉት አባት ባልተባለ። የመጀመርያው አዳም የሕይወት እስትንፋስ ከአባት ውስጥ ያገኘ አይደለምን? ወይስ እነ እንሦቹ የአባት የሕይወት እስትንፋስ የለውም? የአለም መሰረት ሳይጣል ልጆች ነበሩ? መልሱ መንፈሳዊውን ነገር እንደ ማየት አቅማችን ይወሰናል። ልጅነት አለም ሳይፈጠር በፊት በመንፈሳዊው አለም በክርስቶስ ውስጥ ከሁላችን ጋር የነበረ ክብር ነው።
መጽሐፈ ኢዮብ 38: 4 ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር።5 ብታውቅስ መሠፈሪያዋን የወሰነ፥ በላይዋስ የመለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው? 6-7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ #የእግዚአብሔርም #ልጆች #ሁሉ እልል ሲሉ፥መሠረቶችዋን በምን ላይ ተተክለው ነበር?የማዕዘንዋንስ ድንጋይ ያቆመ ማን ነው?
1ኛ, *በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን ባቻ ሳይሆን መተርጎም ያለበት በክርስቶስ ኢየሱስ “ውስጥ” ተፈጠርን ነው።[created in(within) Christ Jesus ] ‘ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካም ሥራ እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ “ውስጥ” የተፈጠርን [created in(within) Christ Jesus ]የእግዚአብሔር ፍጥረቱ ነን። ‘ኤፌሶን 2:10
ፍጥረቱ ሁሉ በእዛ ክብር ውስጥ ነበሩ። ከማይታየው የሚታየውን ፈጠረ ሲል የማይታየው እራሱ እግዚአብሔር ነው ከማንነት ወስዶ የሚታየውን ሰራ። ሁሉ ከሱ ወጥተዋልና ምንም እንካ እንደሁላችን በክርስቶስ ውስጥ ቢፈጠሩም እግዚአብሔር ወደሚታየው አካላዊ አለም ሲያመጣንወደ ሮሜ ሰዎች 8/20
እንደወደደው ፍጥረትን ሁሉ ለከንቱነት አስገዝቶ ከእግዚአብሔር ክብር ከክርስቶስ አጉድሎ እንደገና ወደ ቀድሞው ክብራቸው እንደገና በክርስቶስ ሁሉን እየመለሰ ነው። ፍጥረት በፈቃዱ አልወደቀም በፈቃዱም አይድንም ከመንፈሳዊ ሞት የሚያድን እግዚአብሔር ብቻ ነው። ምሳሌ20: 24 የሰው አካሄዱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው እንግዲያስ ሰው መንገዱን እንዴት ያስተውላል?
24 Man’s goings are of the Lord; how can a man then understand his own way? ይስተዋል። ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ #እግዚአብሔር #ስላስገዛው ነው እንጂ #በራሱ #ፈቃድ #ፈቅዶ #አይደለም፤ እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን ለእግዚአብሔር ባለመታዘዝ ሚስጥር ዘግቶታልና። አሁን ተስፋው ፍጥረት ራሱ ከጥፋት ባርነት ነፃ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው። ለዚህም ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።ወንድም ቢኒ።
ክፍል2። እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን በልጅነት ክብር በሙልአት እንወረስ ዘንድ እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።
በአባቱ መንፈሳዊ ልእለ ተፈጥሮ ፈቃድ በአባቱ ቤት በህይወት በትድላና በደስታ የሚኖረው በቤት ያለው ልጅ እና ከአባቱ ህይወት ተድላና ደስታ የጠፋው ልጅ ሁለቱም ለአባታቸው ልጆች ናቸው “የሰውን ልጆች ወደ አሰር ታወርዳለህ የሰውን ልጆንም ተመለሱ ትለህ” , #የጠፋው ልጅም የጠፋው የሚል ቅፅል ስም ተጨመረበት እንጂ ልጅ የሚለው ስያሜ አልተፉቀም ከአባት የሕይወት እስትንፋስ የተገኘ ነውና። የአሳማው አሰሩ ሲበዛበት የአባቱን መልካም ልብ እንዲያስታውስ ወደ ልቡ እንዲመለስ ይሆናል ወደ አባቱም ደስታና ዕረፍት ይገባል። አባትም “ልጄ ሞቶ ነበር አሁን ወደ ህይወት መጣ” ብሎ ደስ ይለዋል። ትንሽ ቅር የሚለው በቤት ያለው ያልበሰለው የአባት የልብ ትርታ በሙልአት ያልገባው ልጅ ነው።
በትልቁ ከእግዚያብሄር ህይወት የጠፋው ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረና። የሉቃስ ወንጌል3:38… አዳም የእግዚአብሔር ልጅ። 38…which was the son of Adam, which was the son of God.
“የሰዎችን ልጆች ወደ አሳር አውረድካቸው የሰው ልጆች ሆይ ተመለሱ ትላለህ” ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ህይወት ወራሾች ነን፥ እስከ እግዚአብሔር ሙልአት የመድረስልችን ምስጢር ለእኛ ሳይሆን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ፍጥረትን ከከንቱነት ወደ ልጅነት ክብር አንድ ለማድረግ ለማዋሀድ ነው። በዚህ ህይወት በሙልአት እንወረስ ዘንድ
ፍጥረት በሙልአት ባያስተውለውም በናፍቆት ኅይል የእግዚአብሔር ልጆችን በክብር መከሰትን ለነፃነቱ ሲል ይራባል።
ልጆች ቀድሞ ወደ ጎደለባቸው የእግዚአብሔር ክብር ወደ ራሳቸው የክርስቶስ አእምሮ እንዲነጠቁና በክርስቶስ የተሰወረውን የእውቀትና የጥበብ መዝገብ ለፍጥረት ጥቅም እንዲበዘብዙ ከዙፋኑ ማለትም ከስልጣኑ ፊት ከሚፈሱልን
በሰባቱም የእግዚአብሔር መንፈስ ሙልአት በእግዚአብሔር መንፈስ፥ በጥበብ መንፈስ ፤ በማስተዋል መንፈስ፥ በምክር መንፈስ፤ በኃይል መንፈስ፥ በእውቀት መንፈስ፤ እግዚአብሔርን በመፍራት መንፈስ መገለጣችንን በናፍቆት ይጠባበቃል።
ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ እግዚአብሔር ስላስገዛው ነው እንጂ በራሱ ፈቃድ ወዶ አይደለም፤ እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን ለእግዚአብሔር ባለመታዘዝ ሚስጥር ዘግቶታልና።
አሁን ተስፋው ፍጥረት ራሱ ከጥፋት ባርነት ነፃ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው። ለዚህም ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።
እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን በልጅነት ክብር በሙልአት እንወረስ ዘንድ እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን። ወንድም ቢኒ።