ልጆች ያለ አባት ልጅ ሊባሉ አይችሉም አባትም ካልወለደ ልጆች ከሌሉት አባት ባልተባለ። የማይጠፋው አባት ከማይጠፋው ዘሩ የወለድን ምስጉን ነው።እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም። የውጨኛው ሰው ቢጠፋ የውስጠኛው ሰው እለት በዕለተ ይታደሳል ከክብር ወደ ክብር ይለወጣል። ልጆች ከስጋ ድንካናቸው ድካም ወደ መንፈስ ብርታት ዘወር የማለት ስልጣና መንፈሳዊ አቅም አላቸው። ሀይል በሚሰጣቸው በውስጣቸው ባለው ህያው ክርስቶስ ይበረታሉ። ክርስቶስ በእነሱ ስለ እነሱ በእነሱ ውስጥ ብርቱ ነው። በውስጣቸው ባለው በእግዚአብሔር ጥበብ ክርስቶስ የፊታቸው ድፍረት ትለወጣለች። ኢሳያስ 40:27 ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ። መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?
27 Why sayest thou, O Jacob, and speakest, O Israel, My way is hid from the Lord, and my judgment is passed over from my God?
28 አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም።
28 Hast thou not known? hast thou not heard, that the everlasting God, the Lord, the Creator of the ends of the earth, fainteth not, neither is weary? there is no searching of his understanding.
29 ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።
29 He giveth power to the faint; and to them that have no might he increaseth strength.
30 ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ
30 Even the youths shall faint and be weary, and the young men shall utterly fall:
31 እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።
31 But they that wait upon the Lord shall renew their strength; they shall mount up with wings as eagles; they shall run, and not be weary; and they shall walk, and not faint.