ጌታ በጥላው ማን ነው? የዮሐንስ ወንጌል 5/39 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤
ወንድም ቢኒ።
በዘፍጥረት: እርሱ እንደ መልከጼዴቅ ነው
በዘፀአት እርሱ የእኛ ፋሲካ ነው
በዘሌዋውያን- እርሱ ቄስ [ካህን]ነው
በዘዳግም: እርሱ እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ነው
በኢያሱ እርሱ ድል አድራጊው ነው
በመሳፍንቶች: እርሱ ፈራጃችን ነው
በሩት: እርሱ ቤዛችን የሚዋጀን ነው
በዕዝራ: እርሱ የእኛ የህይወታችና የእምነታችን ደራሲና ጸሐፊ ነው
በነህምያ: እርሱም የተሰበረውን ልብ ጠጋኝ ነው
በአስቴር: እሱ ንጉስ ነው
በኢዮብ: እርሱ የመታመናችን ዋጋ ነው
በመዝሙረ ዳዊት: እርሱ መዝሙራችን ነው
በምሳሌ: እርሱ የእኛ እውቀት ነው
በመክብብ: እርሱ የእኛ ጥበብ ነው
በማሕልየ መሓልይ: እርሱ ፍቅራችን ነው
በኢሳይያስ: የሰላም ልዑል ነው ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥
በኤርምያስ: እርሱ የእኛ የእ/ር የዘላለም ጽድቅ ነው
በሰቆቃው: እርሱ መልሶ አዳሻችን ነው
በሕዝቅኤል: እርሱ ሕያው ፍጡር የተመሰለ ነው
በዳንኤል: እሱ አራተኛ ሰው ነው
በሆሴዕ: – እሱ ታማኝ ባል ነው
በኢዩኤል- እሱ የጌታ ቀን ነው
በአሞፅ: እርሱ ፍርድ ነው
አብድዩ: እርሱ አዳኛችን ነፃ አውጫችን ነው
በዮናስ: እርሱ ሁሉን አጠፋለሁ ሲል ሁሉን እምራለሁ ንስሃንም እሰጣለሁ የሚለው ቃሉ ስራ ነው
በሚክያስ የሚያረሰርስ ጠል ነው
በናሆም: እርሱ ተሟጋች ጠበቃችን ነው
በዕንባቆም: እርሱ ራዕያችን ነው
በሐጌ: እርሱ የመጨረሻው የሚወርሰን ክብር ነው
በዘካርያስ: ረቂቅ ስራው በመንፈስነቱ እንጂ በኃይልም በብርታትም አይደለም
በሚልክያስ: እርሱ የፅድቅ ፀሐይ ነው