
ከጥያቄና መልስ የተወሰደ። ተባረክ ወንድሜ። ልክ ነህ ኪንግደም እራሱ የመጨረሻው የብስለት እርከን አይደለም። ሁሉም ገና ከከብር ውደ ክብር እየተለወጥ ያንን መልክ መቸ በሙላት ነካውና? በልጅነት ጉዞ ውስጥ ነገ የእውነት መንፈስ እንዴት እንደሚመራን አናውቅም። እውቀትም ቢሆን ይሻራልና ምክንያቱም ከእውቀት ከፍለን አሁን እናውቃለንና፥ ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው እውቀት ይሻራል።በእርግጥ የቀድሞ አባቶች በታሪክ ነበሩ። የህይወታቸው ደራሲ ግን በዛ ውስጥ ሊያስረዳን የሚፈልገው ብዙ ለእኛ የሚናገረን አለው ባይ ነኝ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10/11 ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ።
ከዘፍጥረት ጀምሮ ብዙው ተምሳሌታው መለእክት አለው ለምሳሌ በዘፍጥረት በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ። ይህ በራእይ ስትመጣ ተምሳሌት ሆኖ ይታያልይ። የህይወት ዛፉም ክርስቶስ ሆኖ ይታያል። በአጭሩ ስለስጋዊ አእምሮ እንዳለ ሆኖ ያንን ቢስትሊ ኔቸር እኢነርጃይዝ የሚያረገው መንፈስ እንዳለው ቃሉ ይናገራል። በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2/1-2 ያም ቢሆን የእ/ር ሴታፕ ነው። እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ሲዘጋው እንዳይታዘዙ የተጠቀመው የላከባቸው መንፈስ አለ። ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው[ማ? እ/ር] ነው እንጂ በፈቃዱ[ማ? ፍጥረት በፈቃዱ] አይደለም፤።እ/ር ፍቅር ቅዱስ ፃድቅ ወዘተ…ነው። በዛው ልክ ግን እ/ር በግርማው የሚያስፈራ በመአት የተሞላ አምላክ ጭምር ነው። ከእ/ር ዘንድ እነዚህ መናፍስት ሊላኩ እንደሚችሉ ከስር ቃል አስቀምጥላሁ። የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው? ከሚገልጥልን በቀር ማስተዋል አይቻልም መንፈሳዊው ነገር ከሰው ማስተዋል በላይ ግዙፉ ነውና። ቢሞከርም ከውቂያኖስ ይልቅ ጠሊቅ ከሆነው ምክሩ በማንኪያ ጨልፈን እደመረዳት ያህል ነው። ስለ ተቃራኒ ሃይላት ስናስብ መገንዘብ ያለብን ከሚቋቋመን ተቃራኒ ነገር የምንማረው ነገር አለ። ለዚያም ነው እ/ር ተቃራኒ ሃይላትን የፈጠረው። በትንቢተ ኢሳይያስ 45፡7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አዎን ሁሉን መፍጠሩን እ/ር ሃላፊነቱን ወስደዋል:: እርስ በራሳቸው የሚቃረኑትም ጭምር ማለት ነው። ለማሰብ ያህል መራራና ጣፋጭ፤ ሃዘንና ደስታ፤ ድሃና ባለጠጋ፤ ጨለማና ብርሃን፤ መልካምና ክፉ፤ ህግና ጸጋ፤ ተፈጥራዊ ነገሮች ና መንፈሳዊ ነገሮች፤ ሞትና ህይወት፤ እስራትና ነጻነት፤ ለምን ብሎ እ/ር እንደዚህ በጥብቅ የሚቃረኑ ሃይላትን ፈጠረ?
አዎን ማየት ያለብን እ/ር መንገዱን ሊያስተምረን ተቃራኒ ሃይሎችን መፍጠር ነበረበት። መልካምን እንዴት እንረዳው ነበረ ክፉ ባይኖር ኖሮ? የእ/ርን ረቂቅ ጥበቡን በመጠኑም ቢሆን ልንገነዘበው ይገባል። ፉጡራኑን ወደ ብስለት ለማምጣት በምን እደሚያሳልፍ ስናስተውል ይደንቃል:: ተፈጥሮውና ባህርዩ በሰው ውስጥ ይገለጥ ዘንድ የሚጠቀመው ተቃራኒ ሃይላትን ነው:: “መዝሙረ ዳዊት 119፡71 ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።” መጽሐፈ ኢዮብ 36፡15 …. በመከራም ጆሮአቸውን ይገልጣል። Job 36፡15 He… openeth their ears in oppression.
ወደ ሮሜ ሰዎች 8/20 ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፤
Rom 8/20 For the creature was made subject to vanity, not willingly, but by reason of him[God] who hath subjected the same in hope,
2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2/11-12 ….. እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 18/10 በነጋውም ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው፥ ።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 18/19እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን የሚያታልል ማን ነው? አለ። አንዱም እንደዚህ፥ ሌላውም እንደዚያ ያለ ነገር ተናገረ።
20መንፈስም መጣ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አታልለዋለሁ አለ። እግዚአብሔርም፦ በምን? አለው።
21እርሱም፦ ወጥቼ በነቢያቱ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ። እግዚአብሔርም፦ ታታልለዋለህ ይቀናሃል ውጣ፥ እንዲህም አድርግ አለ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 11/32 እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና። ወንድም ቢኒ።