
ከጥያቄና መልስ የተወሰደ።Simply Hell and Gangnam is a symbol of judgment NOT wher Trinitarians or any man go’s it is a symbol of judgment . And God’s judgments are Correctional judgment by Nature, If you wane go to visit, Gehenna is a small valley in Jerusalem. In the Hebrew Bible, Gehenna was initially where some of the kings of Judah sacrificed their children by fire. Thereafter, it was deemed to be cursed. If you plan to go and visit location in Jerusalem, is south of Mount Zion. Geography 31°46′6.262″N 35°13′49.58″E
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጭምር አምኖበታል። ወንድም ቢኒ።

የሲኦል እና የገሃነም ፍቺ ከነ ፍፃሜው።
Brother Binyam T. Alemayehu 02/06/2018
በእብራይስጥ ትክክለኛው ገሃነም Gehenna [የሄኖም ሸለቆ Ge-Hinnom “valley of Hinnom”]የአሮጌው ኪዳኑ “hell” ወይም ገሃነመ እሳት ስያሜ ምንጭ የመጣበት በእዮርሳሌም፡ በስተደቡብ ይገኝ ከነበረ “የሄኖም ሸለቆ” ከተባለው ነው። በእንግሊዝኛው “Hell” በአማርኛ “ገሃነም” “ሲኦል” ተብሎ የተተረጎመው ነው። ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮ ይለማመዱ የነበሩ ነገስታት በነበሩት በአክአዝና በምናሴ ዘመነ መንግስት ሞሎክ ለተባለ ለአሞናውያን ጣኦት ሰዎች በጭካኔ ወንድ ልጁን እና ሴት ልጁን መስዋእት አድርገው በዚህ ሸለቆ ያቀርቡበት ነበር። ይደረግ የነበረው ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮም የተነሳ ኢዮስያስ ይህን ሸለቆ ርኩስ ሆኖ እንዲቆጠር አደረገ። ይህም ስፍራ ለዘመናት የከተማው ቆሻሻ መጣያ ና ማቃጠያ ቦታ ሆነ ቡሃላም የፍርድ ቅጣት ተምሳሌት ሆኖ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ተጠቅሞበታል። ከዚህ ሸለቆ አጠገብም ከፍ ባለው አቀበት ወይም ከፍታ ላይ ነበር እዮርሳሌም የተገነባችው።
መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 23/10 ማንም ሰው ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት እንዳያሳልፍ በሄኖም ልጆች ሸለቆ የነበረውን ቶፌትን ርኩስ አደረገው።[የቀድሞው ትርጉም]
‘በሄኖም ሸለቆ የነበረውን ቶፌት የተባለውን ማምለኪያ አረከሰ፤ ይኸውም ማንም ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ እንዳያቀርብበት ነው። ‘2 ነገሥት 23:10[መደበኛው ትርጉም]
2Kgs 23/10 And he defiled Topheth, which is in the valley of the children of Hinnom, that no man might make his son or his daughter to pass through the fire to Molech.[KJV]
ኤርምያስ 7:30-32/ የይሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉን ነገር ሠርተዋል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ርኵሰታቸውን አኑረዋል። 31 እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያለችውን የቶፌትን መስገጃዎች ሠርተዋል።32 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ስፍራ ከማጣት የተነሣ በቶፌት ይቀበራሉና የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።[የቀድሞው ትርጉም]
‘እኔ ያላዘዝኋቸውን፣ ከቶም ያላሰብሁትን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት አቃጥለው ለመሠዋት በሄኖም ልጅ ሸለቆ የቶፌትን መስገጃ ኰረብቶች ሠሩ። ስለዚህ አስተውሉ፤ ይላል እግዚአብሔር ፤ ስፍራ እስከማይገኝ ድረስ ሙታንን በቶፌት ስለሚቀ ብሩ፣ የዕርድ ሸለቆ እንጂ ከእንግዲህ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል። ‘ ኤርምያስ 7:31-32 [መደበኛው ትርጉም]
30 For the children of Judah have done evil in my sight, saith the Lord: they have set their abominations in the house which is called by my name, to pollute it.
Jer 7/31 And they have built the high places of Tophet, which is in the valley of the son of Hinnom, to burn their sons and their daughters in the fire; which I commanded them not, neither came it into my heart.
32 Therefore, behold, the days come, saith the Lord, that it shall no more be called Tophet, nor the valley of the son of Hinnom, but the valley of slaughter: for they shall bury in Tophet, till there be no place.[KJV]
እግዚአብሔር በነብይ ኤርምያስ የእ/ርን ቁጣ በትንቢት ተናገረ ፍርድ በእዮርሳሌም ሲመጣ “የዕርድ ሸለቆ” ተብሎ እንደ ሚጠራ ተነበየ።
ትንቢተ ኤርምያስ 19/6 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡[የቀድሞው ትርጉም]
Jer 19/6 Therefore, behold, the days come, saith the Lord, that this place shall no more be called Tophet, nor The valley of the son of Hinnom, but The valley of slaughter.
እ/ር በትንቢት ሲናገር ፍርድ በእዮርሳሌም ሲመጣ “የሸክላ ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፤ ይህን ሕዝብና ይህቺን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤” ብለዋል ብለህ ንገራቸው አለው።
‘“ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፤ እንዲህም ትላቸዋለህ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሸክላ ሠሪው ገንቦ እንደ ተሰበረና ሊጠገን እንደማይቻል፣ ይህን ሕዝብና ይህቺን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤ የቀብር ቦታ ከመታጣቱ የተነሣ ሙታናቸውን በቶፌት ይቀብራሉ። ‘ኤርምያስ 19:10-11
ከዛም እዮርሳሌም ትንሽ ቆይታ በባቢሎናውያን ሰራዊት ጠፋች። ከአንድ ክፍለ ዘመን ቡሃላ በነህምያ ዘመን ድጋሚ ተሰራች። ላለፉት 2000 ሺ አመታት በተደጋጋሚ ጠፍታ ነበር። የደገመች ተሰራች። ከተማዋም አሁን ቆማለች። የኤርምያስ ትንቢት የመጀመርያው የፍርድ ገጽታ ነው የተፈፀመው። የዚህ ትንቢት ሙሉ ጥፋት የሚያካትተው ቅሪት አለው።
ጌታ እየሱስም ከገሃነም ጋር ተያይዞ የተነገረውን ትንቢት በእዮርሳሌም ላይ የተነገረውን ጭምርና በተምሳሌነትም ደጋግሞ ተናገረው። በገሃነም ምሳሌም 11 ግዜ ተጠቅሞበታል። ( በማቴ 5:22 , 29 , 30 ; 10:28 ; 18: 9 , 23:15 , 33 ; ማርቆስ 9 43 , 45 , 47 ; ሉቃስ 12 5 ያንብቡ ።)
‘ “እናንተ እባቦች፤ የእፉኝት ልጆች! ከገሃነም ፍርድ እንዴት ልታመልጡ ትችላላችሁ? ስለዚህ ነቢያትን፣ ጠቢባንንና መምህራንን እልክላችኋለሁ፤ ከነዚህም አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹንም በምኵራቦቻችሁ ትገርፏቸዋላችሁ፤ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዷቸዋላችሁ። ስለዚህ፣ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው ንጹሕ ደም ሁሉ እናንተ ተጠያቂዎች ናችሁ። እውነት እላችኋለሁ፤ ላለፈው ነገር ሁሉ ይህ ትውልድ ይጠየቅበታል። ‘ማቴዎስ 23:33-36
ቡሃላ ወረድ ብሎ በእዮርሳሌም ላይ የፍርድ ቃሉን ሲናገር እናያለን።
‘ “አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ አንቺ ኢየሩሳሌም! ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ! እናንተ ግን ፈቃደኛ አልሆናችሁም፤ እነሆ፤ ቤታችሁ ወና ሆኖ ይቀርላችኋል! እላችኋለሁና፤ ‘በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው’ እስከምትሉ ድረስ ዳግመኛ አታዩኝም።”’ማቴዎስ 23:37-39
ኤርሚያስ የእዮርሳሌምን ጥፋት ከገሃነም ሸለቆ ላይ እንደተሰበረው የሸክላ ገንቦ እንደምትሰባበር ከፍርድ ጋር ካያያዘው ቡሃል ገሃነም የእ/ር ቃል የሚቃወሙት ላይ የመለኮት ፍርድ ተምሳሌት ሆነ ። ጌታም እዮርሳሌም እንደምትጠፋ ደግሞ ተነበየ።
ስለዚህ፣ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው ንጹሕ ደም ሁሉ እናንተ ተጠያቂዎች ናችሁ። እውነት እላችኋለሁ፤ ላለፈው ነገር ሁሉ ይህ ትውልድ[genea, “ዘር race, ዝርያ offspring”] ይጠየቅበታል። ‘ማቴዎስ 23:34-36
ጌታ እየሱስ አማኞች እየሩሳሌም በውጭ ጦር ስትከበብ ከከተማዋ ፈትለክ ብለው እንዲያመልጡ አስጠነቀቃቸው። እነሱም ከ 66-67A.D. ገደማ ተበተኑ። በ70AD ላይ ታይተስ የተባለ የሮማ ጀነራል እዮርሳሌምን አጠፋት። አሁንም የትንቢቱ ሙልአት ገና በመሆኑ አማኞች የእየሱስን ቃል ሊያስቡበት ይገባል። አማኞች እየሩሳሌም በውጭ ጦር ስትከበብ ከከተማዋ ፈትለክ ብለው ሊያመልጡ ይገባል እ/ር ያድነናል ብለው መቀመጥ የለባቸውም ይህ ትንቢት ከላይዋ ነው እና። የነብዩ ኤርሚያስ ትንቢት ግልጽ ነው ዳግም ልትስራ እስከማትችል በገሃነም ሸለቆ ላይ እንደሰበረው የሸክላ ገንቦ እንደምትሰባበር ተናግረዋልና አማኞች የወረራ ምልክት ካዩ ሊዘናጉ አይገባም። ምናልባትም ከተማይቱ መርገሙየሚሰበርላት “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” ብላ ክርስቶስን ከተቀበለች ብቻ ነው።
ስለዚህ ጌታ ጋሃነም የሚለውን የእብራይስጥ ቃል ተጠቅሞ ለግሪኮችና ለሮማዊያን ዝምድና የሌለው ቃል ቢሆንም ለ11 ግዜ በእርሱ ቃል የማይታመኑትን እነሱም እያስጠነቀቀ ካላመኑ የኤርሚያስ ትንቢት እንደ ሚፈፀምባቸው እየነገራቸው ነበረ። እነሱም በግላቸው በጅምላ ፍርዱ ላይ ተካተው ሊገኙ እንደሚችሉ ኤርሚያስ እንደ ተነበየው “የእርድ ሸለቆ” እንደ ሚሆን አስጠነቀቃቸው።
ሌላው ጌታ ከተናገራቸው የገሃናም ተምሳሌት ፍርድ መካከል ሊታዩ የሚገባቸው አንዱ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤” የሚለው ቃል ነው።
‘ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጒለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤ ‘ማርቆስ 9:47-48
ጌታ የጠቀሰውና የተነተነው የነብዩ ኢሳያስን ትንቢት ነበር። ‘“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”’ኢሳይያስ 66:24
ኢሳያስ እየተናገረ የነበረው ስለ አሮጌዋ እዮርሳሌምና ስለ አዲስትዋ እዮርሳሌም ነበር።
‘“ወዳጆቿ የሆናችሁ ሁሉ፣ ከኢየሩሳሌም ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ስለ እርሷም ሐሤት አድርጉ፤ ለእርሷ ያለቀሳችሁ ሁሉ፣ ከእርሷ ጋር እጅግ ደስ ይበላችሁ። ‘ኢሳይያስ 66:10
‘“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ የእናንተና የዘራችሁ ስም እንደዚሁ ጸንቶ ይኖራል” ይላል እግዚአብሔር ፤ ‘ኢሳይያስ 66:22
ስለዚህም ነበር ጌታ ገሃናምን የተጠቀመው ይደረግ የነበረው ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮም ርኩሰት በዛ ዘመን ቆሞ ነበርና በዚያ ዘመንም ይህም ስፍራ ለዘመናት የከተማው ቆሻሻ መጣያ ና ማቃጠያ ቦታ ሆነ ቡሃላም ብዙ የሞቱ እንስሶች እና የሰዎች አካል ሳይቀር ይጣልበት ነበርና የበሰበሰም የበዛበት ያለማቋረጥ በትላትሎችም የተሞላ ነበረ። ጠረኑን ለመቋቋም ሲባል ቆሻሻውንም ለማቃጠል ሁልጌዜ የማይጠፋ ፍምና እሳት ይታይበት ነበረ። በዚህም የፍርድ ቅጣት ስፍራ ምሳሌ ሆኖ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና” የሚለውን ተጠቅሞበታል።
‘ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጒለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤ ‘ማርቆስ 9:47-48
ሌላው ሲኦል የሚለው ቃል በመጀመርያ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ የሚገኘው ፔንታቱክ [ባለ አምስት ቅጽ መጽሓፍት(ማለት ነው)] ተብለው በሚታወቁት አምስቱ የሙሴ ጹሁፎች መካከል በኦሪት ዘኍልቍ 16/30 ሲሆን ከዛ ቡሃላ በብዙ ቦታ ላይ ተጽፈዋል። ይህም አንድ የእብራይስጥ ቃል እናም ሰዎስት የግሪክ ቃል በእንግሊዝኛው “Hell” በአማርኛ “ሲኦል” በማለት የተተረጎመው ነው። በአብዛኛው በብሉይ ወይም በአሮጌው ኪዳን በሁሉም የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ሁሉ “SHEOL” የሚለው ቃል ተጠቅመውበታል ትርጉሙም ድርብ ሳይሆን ነጠላ የሆነ “የሙታን ቦታ” “the place of the dead.” ማለት ነው። ሌላው ትርጉሙ የሙታን መቃብር grave, ጉድጋድ pit የሙታን ግዛት the realm of the dead።
ኦሪት ዘኍልቍ 16/30 እግዚአብሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እንደ ናቁ ታውቃላችሁ። Num 16/30 But if the Lord make a new thing, and the earth open her mouth, and swallow them up, with all that appertain unto them, and they go down quick into the pit[ sh’owl sheh-ole’] then ye shall understand that these men have provoked the Lord.
ሌሎች ተዛማች ሊጠኑ ሊታዩ የሚገባቸው ሃሳቦች ቢኖሩም እነዚህ ምንም ይሁኑ ምንም የሲኦል እና የገሃነም ፍፃሜው በጥቂቱ ካለፈው ፁሁፍ “እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞትና የእሳት ባህር ፍቺ” ከሚለው ላይ ፍፃሚያቸውን እናያለን።
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞትና የእሳት ባህር ፍቺ የተወሰደ።
“ስለዚህ ሃሳብ በብዙ ሰዎች ብዙ ተጽፎ አንብቢያለሁ ሚዛን የሚደፋና፡ብሎም የማይደፋም ቀልሎ የተገኘም አጋጥሞኛል። በእ/ር ቃል ሲመዘን ማለቴ ነው። በዚህ ሃሳብ ላይ በብዙ ሰዎች ዘንድ ሰፊ የሆነ ግራ የተጋባ አመለካከት እንዳለ ግልጽ ነው። ለብዙወገኖች ይጠቅማል በማለት ይህን የመረዳት ብርሃን አብረን እንድናየው እወዳለሁ መልካም ነገር አለውና። ከቀድሞው አባቶች ሲኦል ዘልአለማዊ ነውን? (is hell eternal or will GOD’S plan fail?) በRev-Charles pridgeon ከነቮበር ወ 1920 እትም መጽሐፋቸው። የእሳት ባህርን በተመለከተ ከገለጡት እጅግ ከሚያስደንቀው የመረዳት ብርሃን የተሞላበት የሊቅ ወይም
የእስኮላር ስራቸው ለተሻለ ግንዛቤ ለብዙ አስተዋዮች እንደ ታገዙበት ሁሉ እኔም ከታገዝኩበትና ከተረዳሁበት መካከል ለወገኖች ጥቅም ልጠቅስ እወዳለሁ። “የእሳት ባህርና ዲኑ (BRIMSTONE) የሚያመለክቱት እሳቱ ከዲኑ ጋር ሲነድ ነው። ዲን፡brimstone ወይም ድኝ፡ sulphur የሚለው የእሳቱ ባህርይ ነው።
የግሪኩ ቃል THEION ሲተረጎም ዲን፡brimstone ተብሎ የተተረጎመ ሲሆን ያው የግሪኩ ቃል እራሱ THEION መለኮት ማለት ነው። በጥንታውያን ግሪኮች መካከል ድኝ ፡sulphur የተቀደሰ ነበረ። እናም ለማጠን፤ ለማንፃት፤ ለማጥራት ለአምላካቸው ያውሉት ነበር። ለዚህም አላማ ያጥኑ ነበር። homer’s lliad[16:228] አንድ ሰው በእሳትና በዲን ዋንጫውን እያፀዳ እንደሆነ ሊናገር ይችላል። THEION ከሚለው ቃል የተሳበው ግስ {ግስ፡ ማለት የቌንቋ አረባብ የዘርና ነባር መሰረት ቃል ነው። } THEIOO ሲሆን ማለትም ማወደስ፤ መለኮትን መስራት፤ ለአምላክነት መለየት ማለት ነው። [liddel and scott Greek English Lexicon, 1897 Edition] ተመልከት/ቺ።
ለማንኛውም ግሪካዊ ወይም በግሪክ ቋንቋ ለሰለጠነ ሰው “የእሳት ባህርና ዲን” ሆኖ መረዳት የነበረበት “የመሎከት የማጣርያ ብህር፣
a lake of divine purifcation” ነበር። ፍርድ የሚለው ሃሳብ መከልከል የለበትም። እ/ር መንገዱ ሁሉ እውነትና ፍርድ ነውና። በጥንታዊ ግሪክ ቋንቋ መለኮታዊ ማጣርያና ለመለኮት ማዋል የሚል ነው ፍቺው። በተራው አገላለጽ ይህ የቃሉ ትርጉም ገንጥለው አውጥተውታል። አመፀኛ ሃፍረት የለውም ተብሎ እንደ ተፃፈ ምንም ነገር ሳያስቀሩ ግን የዘልአለም ስቃይ ጋር አዛምደውታል።” የተጠቀሰው ተፈፀመ።
በነገራችን ላይ THEION የሚለው ቃል የተሳበው theo ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን እግዚአብሔር (መለኮት) GOD እየተባለ በአብዛኛው የተተረጎመው ቃል ነው። ቲዮሎጂ {Theologi or Theology is the study of GOD} የስነ መለኮት ጥናት ወይም ስለ ስነ መለኮት ማጥናት ከዚህ ሃሳብ የተገኘ ነው።
የእ/ርን አሰራርና አደራረጉን ለማወቅ አንድ ሰው ቃሉን እያጠና መንፈስም መረዳትን እያበዛለት ሲመጣ የቃሉን መንፈሳዊ አመልካች በትክክል ማስተዋል ሲጀምር በመጽሐፉ ፀሐፊ በእ/ር የዘልአለም አጀንዳ በቅዱሱ ልእለ ተፈጥሮ ውበትና እንዲሁም በታላቅ ጥበቡ፤ በፍቅሩ ብልጽግና ይነደፋሉ። እ/ርንም ውድድድ ያደርገዋል። በእ/ር ዘንድ ያለው ፍርድ ለማቅናት እንደሆነ ማስተዋል ይጀምራልና።
ሰዎች ለመከራ ይቀጣሉ። እ/ር ግን በፍርዱ ያቀናል ያፀዳል።በግሪኩ ቃል የጠራ ወይም የነፃ pur በዚህ ዘመን እንግሊዝኛ ማጽዳት ወይም ማጥራት ፡ ንፁህ ማድረግ PURGE and PURIFY ለሚሉት ቃላት ስር ወይም ምንጭ ነው። የእ/ር እሳትም የሚያደርገው ይህንኑ ነው። የእ/ር ባህርይና ተፈጥሮ ያሳያል። በዛሬው ጥናታችን በጥቂቱ የእሳቱን ባህሪ በመፅሐፍ ቅዱስ የእውነት ቃል እናጠናለን። ይህን እሳት እየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለኩሶታል። በእሳት የሚያጠምቅ ሆኖም መጥተዋል። ለሚከተሉት ሁሉ እንደ እሳት መምጣቱን ቀጥለዋል። ገናም ለፉጡራኑ ሁሉ ይመጣል። አሜን ጌታ ሆይ ማራናታ አብዝተህ ቶሎ ቶሎ ምጣ። አሜን።
የሲኦል እና የገሃነም ፍቺ ከነ ፍፃሜው።
Brother Binyam T. Alemayehu 02/06/2018
Binyam TA በተቻለ አቅም በተጀመረበት አርእስት ወይም ተመሳሳይ ሀሳብ ብንቆይ መልካም ነው። ህይወታችን ባህርያችን ፀባያችን ወዘተ.. ክርስቶስ ሊሆን ተወስነዋል ይህ መሰረታዊ ነው። በተጀመረው አርእስት ለመጨመር ያህል። በዚህ ቦታ ላይ ሁለተኛው ሞት ማለት የመጀመርያው ሞት እና ሲኦል በእሳት ባህር ውስጥ ሲደመሰሱ ማለት ነው። “በራእይ 20/4 ሞትና ሲኦልም የእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም “የእሳት ባህር” [ይህ ሃሳብ ሲተረጎም ለሁለተኛ ጊዜ የተጨመረ ነው።] ሁለተኛው ሞት ነው።” “death and hell were cast into the lake of fire. THIS IS THE SCOND DATH.”k.j.v.
ትክክለኛው ትርጉም ለአንባቢያን እንዲገባ መሆን የነበረበት “ሞትና ሲኦልም በእሳት ባህር ውስጥ ተጣሉ። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።” እንደ ምናስተውለው ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባህር ሲጣሉ ሁለተኛው ሞት ይባላል። ይሄ መንፈስ ቅዱስ እራሱ ሲያጽፈው ሁለተኛው ሞት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ፍቺ ነው። አስተውሉ ሁለተኛው ሞት ማለት ሰዎች በማይጠፋው እሳት ለዘልአለም ሲቀቀሉና ሲሰቃዩ ማለት አይደለም። አሊያም እንደ ሚባለው ክርስቶስን ያልተቀበሉ ከሞት ቡሃላ የሚጠብቃቸው ኑሮ አፈ ታሪኩ የዘልአለም ሞትና ስቃይ አይደለም። አሁን አይናችን ተከፍቶ ማየት ችለናል ሁለተኛው ሞት ማለት የአንደኛው ሞትና የሲኦል የሞት ግዛት ሁሉ በእሳት ባህር ውስጥ ተጥለው ሲደመሰሱና ሲጠፉ ማለት ነው ። በህይወት መጽሐፍ ያልተገኘ ሁሉ የመተላለፍና የሃጥያትና የሲኦል ተፈጥሮ ማንነቱ የተናወጣቸው አመል ሁሉ የአመፃ ሚስጥር ሁሉ ወደ የመለኮት የማጣርያ የእሳት ባህር ይጣላሉ።
“እ/ር መንፈስ ነው። ዮሃ 4/24” መንፈሳዊው ነገር ለቁሳዊው አለም ለማስረዳት በአካላዊ ቋንቋ መስሎ ያስረዳናል። የብዙ አማኞች ችግር ይሄ ነው። ለዚህም ነው በመንፈስ መገለጥ እንድንረዳቸው በተምሳሌነት የተጠቀመባቸው ምልክቶች፣ SYMBOLS ቀጥታ ከመተርጎም የመጡ ብዙ ችግሮች የተከሰቱት። መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መጽሐፍ ነው።
አስተውሉት እስቲ “የእሳት ባህር” የሚለውን ቃል እንየው “ባህር ምንድነው?” ስፋትና ጥልቀት ያለው በውሃ የተሞላ ቦታ ነው። ይሄኛው ልዩነቱ በእሳት መሞላቱ ነው። በምልክት ወይም በገላጭ ቋንቋ ጌታ ተጥቅሞ ተናገረው። እስራኤል ቀይ ባህር በጌታ ለሁለት ተከፍሎ መንገድ አድርጎላቸው በውስጡ ባለፉ ግዜ ሐዋርያው በጥምቀት አልመሰለውምን ? 1ኛ ቆሮ 10/2 እነዚህም በመለኮታዊ ማጣርያ በእሳት ባህር የሚያልፉትም እንደዚሁ ነው። ለእ/ር እንዲ ሰለጥኑለት በልምድ ውስጥ ያሳልፋቸዋል።የእ/ር በእሳት የመቀመሙና የመፈተኑ ባህርዩንና አላማውን ስናይ “ወደ እሳት አመጣለሁ እንደ ብርም አነጥራቸዋለሁ። እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ። እነሱም ይጣራሉ እኔም እመልሳላቸዋለሁ፤ እኔም “ህዝቤ ናቸው” እላለሁ። እነሱም “እ/ር አምላካችን ነው” ይላሉ። ዘካ13/9
እንደ ምናስተውለው እንደ ወርቅ በእሳት ከተፈተኑና ከነጠሩ ቡሃላ በጨረሻ እ/ር “ህዝቤ ናቸው” ለማለት አላፈረባቸውም እነሱም በመንፃታቸው “እ/ር አምላካችን ነው” ሲያስብላቸው ይታያል እንጂ እሳቱ ሲያጠፋቸው አይታይም። በአንጥረኛ ወርቁ ወደ እሳቱ የመግባቱ አላማ ወርቁ ወደ ተፈለገበት አላማ ከፍ ወዳለ ውበት ቅርጽ ለማድረስ እንጂ ወርቁን ለማጥፋት አይደለም። ደግሞም ማንኛውም ተምሳሌት ሲነገር የሚወክለውን ገፀ ባህሪን ያመለክታል እንጂ ቀጥታ የተመሰለበትን አያመለክትም። በምድራዊ ቌንቋ ለምሳሌ አንበሳ ነው! ሲባል አንበሳ የደፋርና የብርቱ ምሳሌ ነው። እርሱ በግ ነው ሲባል የዋህ ቅን ሰው ነው ለማለት ነው ወይም ለምሳሌ ማቴ 23/15 ከእናተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የገሃነም ልጆች ስለምታደርጉ … በዚህ ተምሳሌት ጌታ የሚናገረው ስለከፋ ማንነት ወይም ስለክፉው ባህሪና ተፈጥሮ መሆኑ ግልጽ ነው።
በመንፈሳዊ ቋንቋ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ አንበሳውም በጉም እሱ ነው። አንበሳነቱ በሃይል በችሎታ የተሞላ፡ አለምንና ሁሉን ያሸነፈ፡ እንደ በግነቱ በልቡ የዋህና ትሁት መሆኑና መስዋእ፣ ሰላም ወዳድነቱና የሰላም አለቃ መሆኑ የሚወደውን ፍጡራኑን ሁሉ በልባቸው ዙፋን ላይ በፍቅር መግዛቱ ደግሞም ከሁሉ በላይ ለአባቱ ፈቃድ ብቻ ያደረ መሆኑ ከዚያም ባሻገር ወዘተ…ሌላ ምሳሌ ብናይ ስንዴውን[መልካሙን ዘር] በጎተራ ይከተዋልና ገለባውን [የአመፃ ሚስጥሩን] ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል። ያም የሞት የሲኦል የሃጥያት መጨረሻቸው የሚያሳይ ነው። እ/ር እሳት ነው። የመጨረሻውን ጠላት ሞትን በእሳት ባህር ይደመስሰዋልና፡ ሞት ፈጽም ካልተደመሰሰ ህይወት ማለትም እ/ር እንዴት ሁሉን በሁሉ ይሆናል?እውነቱ ግን የግዴታ ሞት ሁሉ በህይወት ይበላል ይዋጣል። ‘አምላካችን የሚያጠፋ[የሚባላ consuming] እሳት ነውና።’ ዕብራውያን ብርሃን ለጨለማ የበላይ ነው፡ እሳቱም ነው ይበላዋልም ህይወትም እንዲሁ ለሞት የበላይ ነውና።እ/ር እርሱ ሁሉን በሁሉ ሲሆን ሃጥያት የለም ሃጥያተኛም የለም፡ የሃጥያት ሃይል ሞት የለም ሲኦልም የለም። ሁሉ በእ/ር ይዋጣል።
መቼም እ/ር ሰውን በእሳት ባህር እንደ ማያጠፋው የታወቀ ነው። በየትም ቦታ የእ/ር ቃል እንደዛ አይልም። ያ የእውነት ተፃራሪ ነው። “ቃልህ እውነት ነው በእውነትህ ቀድሳቸው።” የባቢሎንን ማስፈራርያ ወጥመድ ስብከትን ነው። አስቡት እስቲ ሰውን ማምለጫ በሌለው የዘልአለም ሞትና እሳት ውስጥ ፈጥረህ ና ከተህ የመጨረሻውን ጠላት ሞትን እንዴት ትደመስሳለህ?የእ/ር መለኮታዊ እሳት ሰዎች ሁሉ ይፀዱበታል፤ ይነጥሩበታል፤ ጽድቅን፤ ይማሩበታል እንጂ አይጠፉበትም።