
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ፦በወንድም ቢኒ፦ “ቶሎ መሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ፣ እግዚአብሔር ለእርሱ የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ይህ ነው፤ ኢየሱስም መልአኩን ልኮ ለአገልጋዩ ለዮሐንስ በምልክት ገለጠለት፤ ራእይ 1:1” JOV (Jusus opinonative versions )
[JMT]AN UNVEILING OF JESUS CHRIST (REVELATION)CHAPTER 1:1. An unveiling of Jesus Christ which God gave by Him (in Him; for Him; to Him) to point out to His bond‑servants (love‑slaves) that which is necessary to come to be (to be birthed) in swiftness. And sending as an apostle, through means of the agent (messenger), He indicated by signs (symbols) to (in; for) His bond‑servant John
ወዳጆች ሆይ: በጌታ የተወደዳችሁ ለእናንተ አእምሮን ሁሉ የሚያልፈው የእ/ር ሰላም በክርስቶስ ይሁን። የእርሱ ታላቅ ፍቅርና በረከቶች በዚህ ቅጽበት ለእናንተ ይብዛላችሁ! በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ባለው አካሄዳቹህ ና ጉዞ በጌታ በኃይል እየበረታ ይመጣ ዘንድ ፀሎቴ ነው።
ስሙንም ባርኩ – ጌታ ለእኛ በየዕለቱ ካለው ጫና በላይ በአገልግሎት ሁለ ለማከናወን እንችል ዘንድ ጥንካሬ እና በረከት መስጠቱን ቀጥለዋል። በእውነት ክርስቶስ በውስጣችን ነው በሰው መንፈስ ውስጥ በዙፋኑ ላይ ተንሰራፍቶ ነግሰዋል። ክርስቶስ የእያንዳዳችን እውነታ ነውና በእርሱ ላይ አይናችሁን መትከላችሁን ቀጥሉ። በሁሉም ነገር ውስጥ ኃያሉን ክርስቶስ በውስጣቹ ተመልከቱ! በአለም ካለው በእናንተ ያለው ታላቅ ነው። ጥበብ በልጆችዋ ፀደቀች [ትክል ሆነች] በዲቃላዎች ግን አላፀደቀችም[ትክክል አልሆነችም]
ይህ ክርስቶስ በእኛ ውስጥ እንጂ አንዳንዶች ከጣራ ሊያወርዱት እንደሚሹት የሆነ ሚልክወይ ወይም ጋላክሲ ወይ ከአድማስ ባሻገር የሆነ ቦታ ሩቅ ሰማይ የተደበቀ አይደለም። ክርስቶስ የክብር ተስፋ ነው። የተስፋ ምድርም ነው። የክብር ተስፋችን እያስጨበጠን ያለው አባት ይባረክ። በጸጋው እኛ አሁንም እዚህ በሕያዋን ምድር ላይ የጌታን ክብር በመንፈስ እያየን ነው። ባሉት የፊታችን ቀናትና ከፊት በሚመጡት ጊዜያት የበለጠ የመታደስ የመረስረስ ዘመን ይሆንልን ዘንድ ፀሎቴ ነው። የእርሱ ከሆነው ከመቼውም ጊዜ እየጨመረ ከሚኬደው ሕይወት፤ ብርሃን፤ ፍቅር እና በመንፈሳዊ በረከቶች ሁሉ እናም ኃይል ብሩህ እንዲያደርገንና እና በዙፋኑ ፊት ነቀፋ-አልባ ሆነን መግባት መውጣት መሰማራት እንዲሆንልን በጌታ ፊት ፀሎቴ ነው። በእየሱስ ክርስቶስ ስም[ወኪለ-ተፈጥሮ፤ ወኪለ-ባህይ ፤ወኪለ-ስልጣን፤ወኪለ-ማንነት] ። አሜን ይሁን!
ከየዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ገና ከጌታ ብዙ እንደምማርና ለሁላችንም በእሱ እውነትን ማየት እንዲሆንልን ፀሎቴ ነው። የአንድ ቤት መሰረቱ በትክክል ከተሰራ የቀረው መልካም ሆኖ ሊሰራ የግድ ነው። መሰረቱ ከተበላሸ ግን ቤቱ ሊሰነጠቅ ብሎም ሊፈርስ የግድ ነው። ስለዚህም የዚህ መጽሓፍ መሰረታዊ እይታችን ትክክል ካልሆነ የመረዳት ግንባታውም ምን እንደሚሆን የታወቀ ነውና መሰረታዊ እይታችን ላይ ሚዛኑን የጠበቀ አቅም እንዲኖረን መሰረት ሊሆን የሚገባውን እውነት[ኢየሱስ ክርስቶስ እውነት ነው] ከቃሉ እውነት በቅድሚያ እናስተውል። ከተመሠረተው መንፈሳዊ መሰረት በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። መንፈሳዊ ነገር እንደ ቱባ ክር ነው እውነተኛውን ጫፍ ከያዛቹሁት ቀሪው ዝም ብሎ ይተረተርላችሃልና።
የዮሐንስ ራእይ የመጽሐፉ ዋንኛ ትኩረት መጀመርያውም መሃከለኛም መጨረሻውም የሆነው ፍሬ ነገሩ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው። በዛም ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአካሉ ራስ መሆኑ ሊረሳ አይገባም ስለዚህ ነገሩ ሰፊሃሳብና ጥልቀት ያለው ነው። ስለ መጽሐፉ አፃፃፍ ስናስተውል በምድራዊ አይን እንኳ አንድ ጥሩ ደራሲ በመጀመሪያው የመጽሐፉ ክፍል በመጽሐፉ የተደራስያኑን ጠቅላላ ፍሬ ሃሳቡን በጥሩ ገላጭ ምናባዊ እይታ በአጭሩ ቅንጭብ አርጎ ፍንጭ ካሳየ ጥሩ ፀሃፊ ነው ይባላል።
በየዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ በእምነታችን ደራሲ በክርስቶስ የሆነው ይከው ነው። የራእይ መጽሃፉን ሲጀምር እራሱ የመጽሐፉን ሙሉ መልእክት ቅልብጭ አድርጎ አስቀምጦታል። የአማርኛ ትርጉም ደብቆታል እንጂ ሲጀምር መተርጎም የነበረበት ቀጥተኛ ፍቺው “The Unveiling of Jesus Christ ” ““የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ” ነው። ሙሉ ስሙ መሆን የነበረበት “የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ተብሎ ነበር።፤ An unveiling of Jesus Christ.” Revelation 1:1[jmt] Rev 1:1 The Revelation of Jesus Christ[kjv]” ይህ ሐረግ ሁሉንም ይነግረናልና። መጽሐፉ በአጭሩ ለአንድ ዓላማ ነው የተጻፈው እሱም በቅዱሳኑ ውስጥ በመንፈስ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሸፈነበት የስጋ መጋረጃ የክብሩን የመገለጥን ረቂቃዊ መንፈሳዊ ሚስጥራዊ መንፈሳዊ ሂደቱን ለመግለጥ ለማሳየት ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ ተጓዳኝ አጀቦች ሁሉ በሱ ታላቅ ክብርና ብርሃን ቦግ ብሎ መብራት ምክንያት ተጋልጠው እሱ ሲከብር እነሱ ለእይታ ተጋልጠው በብርሃን ይዋጣሉ። የጨለማ ህልውና በብርሃን ህልውና ይዋጣልና ።
በቀላል ቋንቋ የቀሩት የዚህ የእ/ር ብርሃን ክርስቶስ መገለጥ ገመናቸውን ያጋለጣቸው ትእይንቶች ናቸው። ልክ ማታ ውሃ ጠምቶህ/ሽ ወደ ወጥ ቤት ትሄድና መብራቱን ስታበራ በረሮው ይሁን ሌላው ነገር ሁሉ ግልጥ ብሎ ሲተራመስ እንደሚታይ በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ፤ የቀሩ ሁሉ ወደ መታየት መጥተው ሲተራመሱ ይስተዋላል ። በምስል በምልክት ያፃፋቸው ሁሉ የነገሮች ገፀ-ባህርይ አመልካች ወካይ ምልክቶች እና አመልካቾች ናቸው። እያንዳንዱ ዋይታ፤ እያንዳንዱ ነጎድጓድ፤አርሜገዶን፤ እንስሶች፤ ምስሎች,፤ምልክቶች፤ ባቢሎን፤ዘንዶ፤ወዘተ… ከብርሃኑ መከሰት የተነሳ በምልክት መንፈሳዊውን ሚስጥር ወክለው የተጋለጡ የነገሮች ገፀ-ባህርይ አመልካች ወካይ ምልክቶች እና አመልካቾች ናቸው። ። በአጭሩ በክብር መገለጡ የኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ የመከራዎች ወይም የክርስቶስ ተቃዋሚን መገለጥ ለማሳየት አይደለም። እነሱ የጎንዮሽ ትእይንት ናቸው እንጂ ዋናው የእ/ር ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መንፈስ ክብሩ ተመልሶ ከሰማያት ሁሉ በላይ ከመውጣቱና ሁ-ሉ-ን ከ-ሞ-ም-ላ-ቱ ከመክበሩ በፊት [ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4/10] ማለትም በስጋ አገልግሎት ወራቱ ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸው የታወቀ ነው።[የማቴዎስ ወንጌል 13/34-35] ሃኪሙ ዶ/ር ሉቃስ ሲነግረን “ኢየሱስ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው” ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው? እደሆነ ያስረዳናል ይህም የጀመረውን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም በምሳሌ የማስረዳት ጥበቡ በራእይ መፅሐፍም ቀጥሎበታል።
“ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ፥ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው ሁሉ መጀመሪያውን ነገር ጻፍሁ፤የሐዋርያት ሥራ 1/1-2”
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥እናገራለሁ የሚለው ጌታ ትላንትም ዛሬም ነገው ያው ነው።
ብርሃን ሲገለጥ ጨለማን ያጋልጣልና በብርሃን ማንነቱ ሁሉን ይሞላዋል። ብርሃን ለጨለማ እሳቱ ነው ይበላዋል። መጽሐፉ አዎንታዊና የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥን መንፈሳዊ እውነታዎችን የመገለጡ ረቂቅ ታክቲክ ወይም ዘየ የሚተርክ በምልክት በተምሳሌት እንዲገባን የሆነ መንፈሳዊ መጽሐፍ ነው። እ/ር በምልክት ላከው “sent and signified it, Rev 1:1” እነዚህ ገላጭ ምልክቶች በራሳቸው እውን አይደሉም ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እውን ነው። በገላጭ ምልክት signs and symbols ያሳያቸው ናቸውና። ምልክት ወይም ተምሳሌት የሚነገረው በጥሬው ካለው ትርጉሙ ውጪ ሌላ ነገርን የሚወክል ምስል፤ ቃል ወይም ሃረግ ነው። እውነታው ፍፃሜው የክርስቶስ መገለጥ ነው። የሌሎቹ መገለጥ በራሳቸው ፍፃሜ አይደሉም ወደ ፍፃሜ የሚያቻኩሉና ታይተው ለመዋጣቸውና አንድአንዶቹም ለመጥፋታቸው የተመደቡ ናቸው ይህም እሱ በሙሉክብሩይገለጥ ዘንድ ነው።
Signified signs and symbols are not literal, HE IS THE REALITY! It’s is the An unveiling of REALITY of Jesus Christ. Revelation 1:1[jmt]
መጽሐፉ ስለ አንድ ፀረ ክርስቶስ ሰው መገለጥ አላማ ይዞ የተፃፈ አይደለም። ወይም ያለፉ ታሪካዊ ትውፊቶችን ክስተቶችን ወይም የወደፊት ጥፋት መገለጥ ለማሳየት የተፃፈ አይደለም። እያንዳንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የሚጋለጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሸፈነበት በምልክት የተመሰሉ አግልሎ እንዴት ድል እንደሚነሳቸው የሚያሳይ ነው።
‘እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው። ‘ዮሐንስ 3:17 የመጨረሻው ድሉም ሙሉ መዳን ያመጣ ዘንድ ነው። “እነሆ: ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ.” (ራእይ 21: 5) አሜን!
የእ/ር ፈቃድ ቢሆንና መጽሐፉ “የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ተብሎ ቢተረጎም ኖሮ ይበልጥኑ ልንረዳው ፍንጭ ይሰጠን ነበረነ። የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ An unveiling of Jesus Christ. Revelation 1:1[jmt] Rev 1:1 The Revelation of Jesus Christ[kjv]” መገለጡ “revelation” በግሪኩ “አፖካሊፕስ” apokalupsis,ከሚለው የተረጎመ ነው። “አፖካሊፕስ” “The Apocalypse.” ይህ ቃል በብዙ ስጋዊያን ሰባኪዎች የተሰቃየ የመጽሐፉ ቃል ነው። ቃሉ ዛሬ ዛሬ መለኮትን በፍቅሩ ሳይሆን በአምላካዊ አጥፊነት በመፈረጅ በመሳላቸው ስቃይና እልቂትን የሚያመለክቱ ድርጊቶችን ለመጥቀስ በዚህ ዘመን ጥቅም ላይ ውሏል።
ምክንያቱም ልክ እስራኤል ላይ እ/ር እንዳደረገው ጊዜው ደርሶ ከፊል መንፈሳዊ እውርነት ገና ስላላነሳ ነው። “ወደ ሮሜ ሰዎች 11/8 ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው ተብሎ ተጽፎአል።” በባቢሎን የአመፃ ሚስጥርና ትምህርት ምርኮኞች ስለሆኑ ከምርከዋ ወጥተው እርሱ የእውነት መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ በመራቸው ጊዜ ወደ ሚሄድበት በጉን ለመከተል ኁይል እስጊያገኙ ድረስ ይህ ሊሆን የግዴታ ነው።
ልክ የጋቭሮቭ ፈረሶች አረንጓዴ መነጽር አጥልቀውላቸው ድርቆሹን ለምለም ሳር ነው ብለው እደሚያመነዥኩት በስጋዊያን ሰባኪዎች ዘንድ የራዕይ መጽሐፍ ሲታይ በአሰቃቂ ክስተቶች ዓለምን በተለይም “በታላቁ መከራ” ወቅት እንደሚጠፉ ወዘተ.. ይስሉታል ይናገሩታልምና።
እውነቱ ግን የመጽሐፉ ቀጥተኛ ፍቺው የእሱ “እየሱስ ክርስቶስ መገለጡ” “The Unveiling of Jesus Christ ” ማለት ነው። በቀላሉ የእየሱስ ክርስቶስ መገለጡ የሚያሳይ እንጂ የመከራዎችን ወይም የመከራን ወይም የክርስቶስ ተቃዋሚን መገለጥ ለማክበርና ለማክበድ አይደለም።
ይህ ቃል “መገለጥ” “revelation” በግሪኩ “አፖካሊፕስ” apokalupsis, በመጽሐፍ ቅዱስ በአጠቃለይ መለኮታዊ መገለጥን የሚያሳይ ቃል እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል።
ይህንኑ ቃል ጳውሎስ ሲጠቀምበት ሲፀልይላቸው እኔ እማውቀው ነገር አለ የክብርን አባት ባወቃቹ መጠን የጥበብንና የመገለጥ መንፈሱ መንፈሱ… እንደሚመጣ አውቂያለሁ ለእናንተም ይሆን ዘንድ…. “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:17 የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን [“revelation” በግሪኩ “አፖካሊፕስ” apokalupsis,] መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።”
‘ከማንም ሰው አልተቀበልሁትም፤ ከማንም አልተማርሁትም፤ ይልቁንስ በመገለጥ[“revelation” በግሪኩ “አፖካሊፕስ” apokalupsis] ከኢየሱስ ክርስቶስ ተቀበልሁት። ‘ገላትያ 1:12 ይህ ማለት መንፈሳዊ እድሳት ከማግኘቱ በፊት ተከድኖበት የነበረው በመገለጥ ወዲያው አወኩት እያለን ሳይሆን እውነት ከዚያም በላይ ማንነት ነውና ያም ማንነት እውነት የሆነው እየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ እውነት ተገልጦለት ነው ያወቀው።
‘በመጀመሪያ ቃል Word (ሎጎስ logos) ነበረ፤ ቃልም Word (logos) ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም Word (logos)እግዚአብሔር ነበረ። ’14ቃልም Word (ሎጎስም logos) ሥጋ ሆነ፤ ዮሐንስ 1:1,14 ይሄ ቃልም እውነት ነው። ‘ቃልህ(ሎጎስም logos) እውነት ነው፤ ‘ዮሐንስ 17:17 ስለዚህ እየሱስ ክርስቶስ ስጋ የለበሰው እውነት ቃል(ሎጎስ logos) ነው። ስለዚህ የእውነት፡መገለጥ የእየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው።
ይህም ክብሩ ሊገለጥ ያለው ወደ ክብር ባመጣቸው በልጆች እንደሆነ ይስተዋላል። ‘ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች[የበሰሉ ልጆች huios hwee-os’] መገለጥ [“revelation” በግሪኩ “አፖካሊፕስ” apokalupsis] በናፍቆት ይጠባበቃል። ‘ሮሜ 8:19
ፍጥረት ሁሉ በናፍቆት የሚጠባበቀው የእየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ልጆች ውስጥ በክብር በመገለጥ[“revelation” በግሪኩ “አፖካሊፕስ” apokalupsis] ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ፍጥረትን ሁሉ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነት እንዲደርሱ ነው።
የእየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ማለት በእግዚአብሔርን ልጆች ውስጥ ለፍጥረት ጥቅም በክብር መገለጥ[“revelation” በግሪኩ “አፖካሊፕስ” apokalupsis] ማለት ነው። ይኸውም በመጋረጃው ማለት በአካሉ በልጆች በሥጋው በኩል በከፈተው አዲስና ሕያው መንገድ ነው የሚገለጠው። ‘ይኸውም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል በከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው። ‘ዕብራውያን 10:20 በመጋረጃው በሥጋው ብርሃኑን የክርስቶስን ክብር ደብቆታል መገለጡም ክብሩን ለአለም ይገልጠዋል።
በመጀመርያው ስጋ ሲለብስ በመጋረጃው በሥጋው ብርሃኑን ማለትም የክርስቶስን ክብር ደብቆት እንደ ነበረ አሁንም እንዲሁ በአካሉ ቤተክርስቲያን ተመሳሳይ ነው። የማቴዎስ ወንጌል 17/2 በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።
በእርግጥም ክርስቶስ በእኛ ውስጥ ነው። ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ መሆኑ ነው which is Christ in you, the hope of glory ።መጋረጃው ሥጋው ግን ደብቆታል። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1/27 ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው። Colossians1:27. To whom God wills (purposed; intends) to make known by intimate experience, what [are] the riches of the glory of this Secret (or: the wealth which has it source in this sacred mystery’s manifestation which calls forth praise) within the multitudes (among the nations; in the Gentiles; among the swarms of ethnic groups), which is (exists being) Christ within you folks, the expectation of the glory (or: Christ, which continuously exists within you [is] the hope of the manifestation which calls forth praise),
የራዕይን መልእክት የሚያነብ ልብ በሚያነበብበት ጊዜ በእያንዳንዱ ገጽ ፊቱን ያያል በእያንዳንዳቸው መስመር ከክርስቶስ ጋር በምሳሌ እራሱን ጨምሮ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ካላየን የሚታያየው ሁሉ ከንቱ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደዚህ መጽሐፍ በመቅረብ በክርስቶስ የክብር ባህር መዋኘት እንችላለን። የእግዚአብሄር ክብር የክርስቶስ መልክ ነው። “ሁሉ ሃጥያትን ሰረተዋል የእ/ር ክብር ጎድላቸዋል” በሃጥያት ምንያት የጎደለብን ብር አልነበረም የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ነው። ሃጥያት የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ልንረዳው ይገባል በግሪኩ HARMATIA ሲሆን ይህ እስፖርታዊ ቋንቋ ነው፤ ትርጉሙም ምልክሩን መሳት ነው። MISSING THE MARK በአንድ ቀስተኛ ቀስቶ የቀስቱን ፍላጻውን ካሽቀነጠረ ኢላማውን ወይም አላማውን ከሳተ ውድዱርን የሚያየው ህዝብ ሃማሪቲያ HARMATIA ብሎ በታላቅ ድምጽ ይጮካል። እኛም ኢላማችን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ስለሳትን ሃማሪቲያ HARMATIA ሆነብን አሁን ግን እ/ር ይመስገን በሃማሪቲያ HARMATIA ያጣነው የጎደለብን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ተመለስን። የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነው። የሐዋርያት ሥራ 7/55 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ-ን-ም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፦
በነ ሄኖክ በነ ኖህ፤ ሙሴ፣ ኤልያስ፤ ዳዊት ወዘተ… ሚስጥር ጌታ አድርጎባቸው እንጁ ይክብሩ ተስፋ በውስጣቸው ነበረ ለእኛ ግን ሚስጥሩን ገለጠልን አሁን 7ባቱንም ማህተሞች በህይወታችን በእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ መፍታት ጀምረዋል።
የተቀባ(ክርስቶስ)– የሕይወታችን-እስትንፋስ፥ በእውቀትም ሆነን ሳንሆን በእሱ እንኖራለን።
የመንፈስ ዘሩ በውስጣቸው አልነበረም ማለት ሳይሆን ዘሩ እንዲበቅል አስፈላጊው ንጥረ ነገር ብርሃኑን እግዚአብሔር ካበራበት ህይወት አግኝቶ ይበቅላል።
እዮብ 32:4 የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ(ክርስቶስ ) ሕይወት ሰጠኝ።
8 ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጣል።
8 But there is a spirit in man: and the inspiration of the Almighty giveth them understanding.
ይህ ክርስቶስ አሁን በእኛ ውስጥ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ‘ለእነርሱም እግዚአብሔር የዚህ ምስጢር ክብር ባለጠግነት በአሕዛብ መካከል ምን ያህል እንደሆነ ለማሳወቅ መረጠ፤ እርሱም የክብር ተስፋ የሆነው
በ-እ-ና-ን-ተ ው-ስ-ጥ ያ-ለ-ው ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነ-ው። ‘ቈላስይስ 1:27
Colssians1/27. To whom God wills (purposed; intends) to make known by intimate experience, what [are] the riches of the glory of this Secret (or: the wealth which has it source in this sacred mystery’s manifestation which calls forth praise) within the multitudes (among the nations; in the Gentiles; among the swarms of ethnic groups), which is (exists being) Christ within you folks, the expectation of the glory (or: Christ, which continuously exists within you [is] the hope of the manifestation which calls forth praise),
በመጀመርያው ክብሩን የገለጠው ቃልም ሥጋ በመሆን ነበር። የዮሐንስ ወንጌል 1/14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።
ኢየሱስም የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ሰዓቱ ደርሶአል ብሎ እንዳለውም እንደ ስንዴ ቅንጣት በሞቱና በትንሳኤው እራሱን አባዝቶ ከብረዋል። እውነት እውነት ብሎ በራሱ ምሎ በስንዴ ቅንጣትም እራሱን መስሎ በምድር ወድቆ ሞተ ብቻዋን ከብሮ ሊቀር አልወደደምና፤ በዘር ውስጥ ያለው ህይወት የሚለቀቀው በሞት ውስጥ ነውና። ከሞት ሲነሳም ብዙ ፍሬ ብዙ እሱን የሚመስሉ ልጆችን አፈራ።
23 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ሰዓቱ ደርሶአል።
24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።የዮሐንስ ወንጌል 12
ፍጥረት ሁሉ በናፍቆት የሚጠባበቀው እንደገና የቀድሞውን አይነት አገልግሎት አይደለም። በቤተ ክርስቲያን በኩል አንዳንዶቹን አስቀድሞ እንደሰጠው ሐዋርያትን፥ ነቢያትን፥ በነዚህ አገልግለቶች ብቻ ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነት እንዲደርስ አይችልምና ። የነዚህ አገልግሎቶች ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ የተሰጡ ናቸው። እኛን ከመስራት ውጪ ፍጥረትን ከመበስበስ ባርነት ለማውጣት በራሳቸው ሙሉ ሃይል አይደሉም የእምነት መንፈሱም በመጠን እውቀቱም ከእውቀት ተከፍሎ ነው በዚህ ግዛት የተሰጠው። በእግዚአብሔርን ልጆች በሙልአት በክብር መገለጥ ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ፍጥረት ሁሉ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነት እንዲደርስ ይሆናል። ለልጅነት ሙልአት እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።
ማወቅ ያለብን ልጅነት የብስለት እርከን አለው የመጀመርያው ደረጃ በስሙ[በተፈጥሮው በባህሪው] አምነን ማንነቱን ማንነታችን አርገን ስንቀበለው የሆንነው ትንንሽ ገና ያልበሰሉ የእግዚአብሔር ልጆች[ teknon tek’-non ትንንሽ ልጆች፡ ህፃናት፤ ጨቅላ ህፃናት] እንሆን ዘንድ ነው ሥልጣንን የሰጠን፤ [የዮሐንስ ወንጌል 1/12] ይህም የሕፃንነት እርከን ቢሆንም የእግዚአብሔርም ጸጋ በእኛ ላይ በመሆኑ ፥ ጥበብ ሞልቶብን በመንፈስ ጠንክረን፤ ምንም ልጅጆች ብንሆን ፥ ከምንቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረን፤ የበሰሉ የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን በክብር እንገለጣለን።
የበሰሉ የእግዚአብሔር ልጆች ‘ይህም ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች[የበሰሉ ልጆች huios hwee-os’] ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነት እንዲደርስ ነው። ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች[የበሰሉ ልጆች huios hwee-os’] መገለጥ በናፍቆት ይጠባበቃል። ‘ሮሜ 8:19,21
ለልጅነት ክብር የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም ምንም እንኳን የመንፈሱ ወራሾች ብንሆን በቅድሚያ የተቀበልነው የመንፈሱን ቀብድ ወይም መያዣ ብቻ በመሆኑ በሙልአት እንዳንገለጥ ተገድበናል ይህም የሆነበት ምክንያት ገና ስላልበሰልን ነው። አባት ወደ ብስለት ካመጣን ቡሃላ በመንፈሱን ቀብድ ብቻ ሳይሆን የልጅነት ሙልአት ክብር የመለኮት መንፈስ ሙልአት ይዘን ሳንገደብ በክርስቶስ ክብር እንገለጣለን እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ ለልጅነት አይሰጥምና። የዮሐንስ ወንጌል 3/34 በዚህም ክብር በብቃት ትንቢት መተንበይ አጋንንት ማውጣት ሳይሆን በፍጥረት ላይ የተፈጥሮ ለውጥ እናካይዳለን ያም ማለት ፍጥረትን ከመበስበስ የባርነት ተፈጥሮው ነጻ አውጥተን ወደ እግዚአብሔር ልጆች[የበሰሉ ልጆች huios hwee-os’] ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነትና ህብረት እንዲደርስ እናደርገዋለን።
ልጅነት በሙልአት የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ ለልጁ አይሰጥምና የልጁ መልክ ይዞ መገለጥ ማለት አንዱና ዋንኛው በሰባቱም የእግዚአብሔር መናፍስት አሰራር እንደ እየሱስ ክርስቶስ ይዞ መገለጥ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል። እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤ትንቢተ ኢሳይያስ 11/2 የዮሐንስ ራእይ 3/1 …ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት..ያሉት እንዲህ ይላል፦..አሜን ወንድም ቢኒ Bro. Binyam T. Alemayehu ወንጌልን በፍቅር
TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND