ጥያቄና/መልስ ስጋዊ መንፈሳዊ ሰው ሲባል ምን ማለት ነው?


ስጋዊ መንፈሳዊ ሰው ሲባል ምን ማለት ነው?
ክፍል አንድ: : ሰው በእርግጥ ስጋ የለበሰ ፍጥረት ነው ጌታ እ/ርም ለዚህ ነው ስጋ ለባሽ ብሎ ሰውን የሚጠራው ብረት ለባሽ ብሎ ጠርቶት አያውቅም። ሃዋርያት ስጋ የሰው ማደርያ መሆኑን አስተውለውት ነበር።
“13 ሁልጊዜም በዚህ ማደሪያ ሳለሁ በማሳሰቤ ላነቃችሁ የሚገባኝ ይመስለኛል።
14 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና።2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1”
23 በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤24 ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው።ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጥያቄው መንፈስ ግን ስጋዊ እና መንፈሳዊ ስንል ምን ማለት ነው ? ነው።
እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥የዮሐንስ ወንጌል 4/24 ልጆቹም እሱን ይመስላሉ እንጂ ሌላ አይመስሉም። መቼም ነገር ሳይንዛዛ በአጭር ቃል እንቅጩን እንደጌታ የሚያስቀምጠው የለም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። የዮሐንስ ወንጌል 3/6 አለቀ እግዚአብሔር መንፈስ ነው ከመንፈስ እግዚአብሔር የተወለደ መንፈስ ነው! አንዳንዱ ሰው በውሸት ትህትና ተላብሶ የግግምናው ብዛት ከመንፈስም የተወለደ ሥጋ ነው ገልብጦ ይረዳዋል።
እግዚአብሔር ዘፍጥረት 1 ላይ ሁሉ እንደ ወገኑ ዘሩ ያዘጋጅ ይብዛ አላለም? በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።እግዚአብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን፥ ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውንም ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።እግዚአብሔርም አለ፦ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፤ እንዲሁም ሆነ።
ታዲያ ሰው ጋር ሲደርስ እንደ ወገኑ እንደ እግዚአብሔር የማይዘጋጅበት ምን ምክንያት አለ? እግዚአብሔር መንፈስ ነው እንደ ወገኑ ከመንፈስ እግዚአብሔር የተወለደም መንፈስ ነው! እነርሱ ከእግዚአብሔር ወገን ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወገን ወይም ከወንድ ፈቃድ ወገን አልተወለዱምና ።የዮሐንስ ወንጌል 1/13
አሁን ወደ ጥያቄው ቁም ነገር ጥልቀት እንግባ መቼም ስለ አዲሱ ሰውና አሮጌው ሰው የማያውቅ የለምና አሁን አዲሱ ሰው እንዴት ማደግ አለበት? በመጀመርያ ለመኖርና ለማደግ ምግብ[የእ/ር ቃል] ያስፈልገዋል የበላ ያድጋልና ያልበላ ይጫጫል ብሎም ምንም እንካ ከማይጠፋው ዘር ቢወለድም አንድ ህፃን ተወልዶ ባያድግ ቤተሰቡን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ያስደነግጣል ።
«በጌታችንና በመድሃኒታችን በእየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ» የሚገርም ቃል ነው። ለልጆች ወይም ለአማኞች ሁሉ የማያቃርጥ ተግዳሮት ቢኖርብን በጌታችን ጸጋና እውቀት ለማደግት ያለውሂደት ነው። ማደጋቹ በነገር ሁሉ ይደግ ይገለጥ፤ ራስ ወደ ሆነው ክርስቶስ እደጉ፤ ስለማደግ የእ/ር ቃል ብዙ ያስተምረናል። ከእነዚህ አንዱና ዋንኛው አስፈላጊ ነገር በለልጆች ህይወት ውስጥ ልናድግብትያለ ከመንፈሳችን ውስጥ በሚወጣው ህይወት መኖር መለማመድ ነው፡ ከአይምሮ ብቻ ሳይሆን ከዚያም ባሻገር የክብር ተስፋ ካለው በውስጣችን ከሚፈልቀው መንፈሳዊ የህይወት ወንዞች ከክርስቶስ ህይወት መቅዳት ይበዛልን ዘንድ በዚህም እርሱ እውቅትና መረዳታችን ይሆንልናል።

ይህ በኛ አውን ይሆን ዘንድ የስጋዊው ሰው ሃሳብ መፍረስና አይምሮን ደግሞ መማረክን ሁለቱን ያጣመረ ተግባርን ያዛል። ‹2ኛ፣ ቆሮ 10/5 የሰውንም ሃሳብ በእግዚያብሄርም እውቃት ላይ የሚነሳውንከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳላን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን።> ብዙ ግዜ ይህን ሃሳብ ከውጪ ላሉት እንጠቀምበታለን ። ጠቢብ እራሱን ያያልና ። ተቀዳሚ መልክቱ ግን በእኛ ውስጥ ስጋ በመንፈስ መንፈስም በስጋ ላይ በለው የእሽቅድድም ትእይንት የሚያመለክት ነው። ለምን ስጋዊው አስተሳሰብ መፍረስ አይምሮ ደግሞ ታድሶ ይታዘዝ ዘንድ መማረክ አስፈለገው? ምክንያቱም “ስለስጋማሰብ ሞት ነውና ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ህይወትና ሰላም ነው።ሮሜ 8/6 For to be carnally minded is death; but to be spiritually minded is life and peace.” ስጋዊ አይምሮ መያዝ ሞት ነው። በቀላሉ የሞት ፍቺው ያ ነው። ጌታ ደግሞ ሞትን ሊደመሥሥ ምጥተዋልና። ምንፈሳዊ አይምሮን መያዝ በአንጻሩ ህይወትና ሰላም ነው። የክርስቶስ አይምሮ ህይውትና ሰላም ነውና።

ክፍል ሁለት
እኛ ደግሞ የክርስቶስ አይምሮ አለን፡ <But we have the mind of Christ.1Cor 2/16> የእ/ር ልጅነታችን ከምልክቱ አንዱ በዚህ አይምሮ ለመጠቀም ማደግ መቻላችን ነው። ያም ማለት የክርስቶስ አይምሮ በመንፈስ የሚመራ እንደሆነ እናስተውላለንና እኛም እንደዚሁ ይጠበቅብናል፡፡ <ማቲ3/16 የእ/ር መንፈስ ወረደብት> ከዛም ማቲ4/1 መንፈስም ይፈተን ዘንድ ወደ ምድረ በዳወሰደው፤ ክዛም በመንፈስ ሃይል ተምለሰ፡ አገልግሎቱም የጌታ መንፈስ በኔ ላይ ነው፡ ብሎ ከጀመረ ቡሃላ መንፈስ ከሆነው አባቱ [ዮሃ4/24] ዘንድ ለመሳካቱ ሚስጥር የሆነው ከአባቱ የሚሰማውን የሚያየውን ብቻ ያደርግ ስለነበር ነው። የራሱን ፈቃድ አንዳች እንኻን አያደርግም ነበር። ከመንፈስ ከሰማ ይናገራል ካልሰማ ዝም ይል ነበር በዚህም ድል ነሺ ሆነ። መንፈሳዊ ሰው ማለት ይሄ ነው በተቃራኒው ደግሞ ይህን ምሳሌ የማይኖረው ሰው በሰጋ ፈቃድ ስለሚኖር ስጋዊ ሰው ይባላል።

ኤታ እየሱስ አባቱ ሲያደርግ ካላየም ዝም ይል ነበር አንጂ የራሱን ፈቃድ አላደረገም። < በእግዚያብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእ/ር ልጆች ናቸው ሮሜ8/14> ልጅነትና መንፈስ ቅዱስ የተያያዙ ናቸው። በእ/ር መንፈስ ከመመራት ውጪ የእ/ር ልጅነት የለም፡ ፡

መንፍሳዊ እድገት የአይምሮ ጅምናስቲክ ውጤት አይደለምና፡ መመራታችን በበዛልን ልክ በእድገታችንም ተገቢው ህይደትና ውጤታማም እድገት ይታይበታል። ጌታ<በማቲዮ 6/27 ከእናተ በመጨነቅ(በማሰብ) መቁመቱ ላይ አንዳች መጨመር አይችልም> ብልዋል በተፈጥራዊው ሰው አስቦ ቁመቱ ካላደገ ያም ማለት የምድሩን ካልቻለ ማለት ነው በመንፍሳዊው ላይማ አይታሰብም።< ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው።ዮሃ3/6> ጳውሎስ ይህን ቀጽሎ ሲያስረዳን < በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ ገላ5/25 በዚህ በመንፈስ መኖርና መመላለስ ውስጥ ብዙ የምንማረው የምናውቀው አለ። ስለ መመላልስ፤ ስለመስማት፤ ስለመናግር፤ በእውነት በመንፈስ ያለው የየእለት ህይወት እውን ከሆነልን የከበረ ነገር ነው።

<በሮሜ8/5 እንደ ሰጋ ፈቃድ የሚኖሩ የስጋን ነገር ያስባሉና እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ> አይገርምም ? “የመንፈስን ነገር ያስባሉ ”እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ !እንደ ምናስተውለው ሁለት አይነት ሰዎች ሃሳባቸው የተቀመጠበትን ይናያለን፡ እነዛ ባልተቀደሰ የስጋ ፍላጎት ላይ ሃሳባቸውን ያስቀመጡና የስጋን ምኞቱን የሚፍጽሙ ደግሞም በተቀደሰው የመንፈስ ፈቃድና ፍላጎት የሚኖሩ ሃሳባቸው የተያዘው በመንፈስ ነገር ላይ እንደሆነ እናስተውላለን። በስጋ ግዛት የሚኖሩ ባልተቀደሰው የስጋ ፍላጎት ቁጥጥር ስር ናቸው። በአንጻሩም በመንፈስ ግዛት የሚኖሩ በተቀደሰው በመንፈስ የሚመሩም እንዲሁ ናቸው።

ለመሆኑ በመንፈሳችን ውስጥ ምን ስላለ ነው እ/ር ደጋግሞ ለዚህ የውስጥ ህይወት ህያው እንድንሆን ደጋግሞ በተለያየ መልኩ የሚናገረንና የሚያስተምረን? እ/ር በህይወታችን ምንን ስላስቀምጠ ነው? አዎን መንፈሳዊ ሃብት ወይም መዝገብ ስላስቀመጠ ነው። ‹ በትንቢተ ኢሳ45/3 በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እ/ር እኔ እንደ ሆንኩ እንድታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሃብት እሰጥሃለሁ› ጌታ ነው የሚናገረው ስውር መዝገብ እሰጥሃለሁ የተደበቀችን ሃብት እሰጥሃለሁ፡ ለምን? በስምህ የምጠራህ እ/ር እንደሆንኩ ታውቅ ዘንድ። ምንድን ናቸው እነዚህ በትንቢት የተነገሩ መዝገብና ስውር ሃብቶች?

ክፍል 3
‹በቆላ2/2-3 ልባቸው እንዲጸናና በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደ ሚገኝ ወደ መረዳት ባለጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእ/ርንም ሚስጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ። የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና። › አሁን አወቅን እ/ር ሃብት መዝገብ እያል ግድ የሚለው የእ/ር ጥበብና እውቀትን ነው፡ እነዚህም በየሱስ ክርስቶስ ተሰውረው ተቀምጠዋል። በቆላ1/27ቀደም ብሎ የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናተ ውስጥ ነው ብሎ ለዘመናት ተሰውሮ የየተደበቀውን ሚስጢር ገልጦልናል። አስተዋልን? እ/ር በእኛ ያስቀመጠው ነገር አለ “ክርስቶስ” በእሱ ውስጥ ደግሞ ሃብትና መዝገቡ ታጭቆ አለ ውደ ብስለት ግዛት ማደጋችን ይህን ሃብት መጠቀም ያስችለናል።

ምሳሌ2/3 ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት ለማስተዋልም ድምጽህን ብታነሳ እርስዋንም እንደ ብር ብትፈልጋት እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት የዚያን ጊዜ እ/ርን መፍራት ታውቃለህ የአምላክህንም እውቀትታገኛለህ» ሃብቶች ምን እደሆኑ አስተዋልን እውቀት፤ ማስተዋል፤ የአምላክህን እውቀት ሃሌሉያ ታገኛለህ! ይሄ ሃብት ነው በክርስቶ ተሰውሮ ያለው እለት እለትም ከዚህ በውጣችን ካለው የክብሩ ሃብት እንደ በሰሉ ልጆች መጠቀም እንችል ዘንድ እ/ር ያሳድገናል። ‹1ኛ፣ቆሮ3/7 እንግዲህ የሚያሳድግ እ/ር ነው እንጂ የሚተክል ቢሆን የሚያጠትጣ ቢሆን አንዳች አይደለም።› እንግዲህ የክርስቶስ አይምሮ ካለን ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ያደምጥ እንደ ነበር ማድመጥ አለብን።‹ ቆላ2/18 አካል ሁሉ በጅማትና በማሰርያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠምም እግዚያብሄር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል› የሚያሳድገን መንፈሳዊ ምግብ የምናገኘው በዚሁ መልክ ነው፡ ‹በእ/ር መንፈስ የሚመሩ እነሱ የእ/ር ልጆች ናቸውና› ፡ ልጅነታችን የተመረኮዘውም በዚህ የምንፈሱ ህይወት በመጠቅምና ለማደግም መልሱ ያለው በውስጣችን ካለው መጣመር ነው። መታዘዝ ከመስዋእት ይበልጣል!

መንፈስ ለቤተ/ክ የሚናገረውን ከሰማን ለዘመናችንና ለትውልዳችን ድል ነሺዎች ነን። “እ/ር ግን እውቀትና ጥበብን ይሰጣል” “ጥበብን ለጠቢባን እውቀትን ላስተዋዮች” ዳንኤል ላይ። ለገዛ ዘመናችንም ልንጠቀምበት የተገባውን ምክርና ጥበብ ማስተዋልም የአምላካችንም እውቀት ቢሆን ከኛ አይሰወርም ከእርሱ የተነሳ እናድጋልን ። ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ከእ/ር አፍ ተዘጋጅት በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ› የበላ ያድጋልና መንፈሳዊ እንጀራና ውሃ የሆነውን ክርስቶስን እለት እለት እንመገብ። በማስተዋላችንም ፈጣኖች አንሆናለን። ሃሌሉያ! ‹ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውሃ ነው አይምሮ ያለው ሰው ግንይቀዳዋል። ምሳ»20/5 ብርታታቸው ከእ/ር የሆነና አማካሪያቸውም በምክሩ ድንቅና ግሩም የሆነው እ/ር የሆነ ምንኛ ብጹአን ወይም ደስተኞች ናቸው? አሜን! ጥበብ በልጆችቃ ፀደቀች [ትክክል ሆነች] አሜን! ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal