BUT YOU WILL SEE ME ! እናንተ ግን ታዩኛላችሁ!


BUT YOU WILL SEE ME ! እናንተ ግን ታዩኛላችሁ!

Brother Binyam T. Alemayehu 02/11/2018

ጥሪህን/ሽን ማወቅ በረከት ነው። የተጠራነው ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት ነው።

“1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1/9 ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።” በዚህ ህብረት ና አንድነት ውስጥ ተዘርዝሮ የማያልቅ በረከት አለና።[ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እፀልያለሁ። የዮሐንስ ወንጌል 17/]20-21

ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ሲናገር ከእሱ ጋር ህብረት የሌላቸው ከዚህ ቡሃላ ሊያዩኝ አይችሉም። በተፈጥራዊው አይን የተወሰኑ ናቸውና። በተቃራኒው ህብረት ያላቸውና ጌታ መንፈስ እንደሆነ ያወቁ ጌታን በመንፈስ ማየት ይቀጥላሉ። እሱ ህይወታችን ነውና። አሜን።

የዮሐንስ ወንጌል 14/19 ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ።

20 እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።

21 ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።

John 14/ 19. “Yet a little [while; longer] and the system (world; ordered arrangement) no longer continues viewing (attentively watching) Me, but you men are constantly watching (attentively and contemplatively viewing) Me. Because I, Myself, am continuously living, you men will also be living [other MSS: will also of, or in, yourselves live].[JMT]

John 14:19 “Yet a little while, and the world sees me no more; but YOU WILL SEE ME, and because I live, (in you) you shall live also. At that day (when you SEE ME) you shall know that I am in my Father, and you are in me, and I am in you.”

እናስተውል “ጥቂት ቆይቶ ደግሞ ዓለም አያየኝም፡ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፡ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ፡ እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችህ እኔም በእናንተ ውስጥ እንደሆንሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ. ” ወደ ሰማይ አንቃሮ በመጠባበቅ ማየት ይሻላል ወይስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን የፈቃዱን የእውነት ቃል በመቀበል እራስን ትሁት ማድረግ? ተስፋ ወይስ ተስፋን በእ/ር መጨበጥ ይሻላል?

የማቴዎስ ወንጌል 5/8 ልበ ንጹሖች ብፁዓን[ደስተኞች] ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።

“Matt 5/8 Blessed are the pure in heart: for they shall see God.”KJV

“Matt 5/8. “Those who are clean in the heart [are] happy (and: blessed), because they, themselves, will see God!”JMT

በተራራው ስብከት ላይ ጌታ ከሰጣቸው አይነተኛ መመርያዎች መካከል ይህ ስድስተኛው የመንግስቱ መመርያ ልበ ንጹሖች እግዚአብሔርን ያዩት ዘንድ የተጠበቀላቸው ነው ብሎ ያስተማረው የማይሻረው ህያው ቃሉ ነው። በልባቸው ኑጹሃን እነማን ናቸው? ያልተከፈለ ፤የልብ ጣኦት የሌለው[ ጣኦት ማለት የውሸት የተሳሳተ የአምላክ ምስል ማለት ነው፤] ፤ ያልተበረዘ፤ ያልተቀላቀለ፤ በፍፁም ልቡ እ/ርን የሚወድ፤ በልቡ ትሁት የሆነ የእ/ር ቃል የሚሰማ፤ በልቡ የዋህና ትሁት የሆነ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2/16 እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን። የክርስቶስ ልብ ምን ነበር? የዋህ በልቡም ትሑት ነበረ። ይህም ልብ ለነፍሳችንም ዕረፍት ያመጣል፤ ሰው እ/ርን ሲያይ ነፍሱ ብቻ ሳይሆን የምታርፈው ሰውነቱም  ድና ትቀራለችና።  ያቆብ እንዳለው “ኦሪት ዘፍጥረት 32/30 ያዕቆብም፦ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው።” ከነገሮች ዘወር ብለን በመንፈስ እ/ርን [ክርስቶስን]ማየት መንፈስ ከሚሆን ጌታ እየወረሰን ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።።

የማቴዎስ ወንጌል 11/29 ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤

ይህም ሁሉ በእኛ የሚሰራ በልብ ላይ ስልጣን ያለው እ/ር ነው። ሰው በሃይሉ አይበረታምና።

መጽሐፈ ምሳሌ 20/9 ልቤን አነጻሁ፥ ከኃጢአትም ጠራሁ የሚል ማን ነው?

መዝሙረ ዳዊት 51/10 አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። Ps 51/10 Create in me a clean heart, O God; and renew a right spirit within me.

መዝሙረ ዳዊት 4/7 በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።

መዝሙረ ዳዊት 119/32 ልቤን ባሰፋኸው ጊዜ፥ በትእዛዝህ መንገድ ሮጥሁ።

Ps 119/32 I will run the way of thy commandments, when thou shalt enlarge my heart

መዝሙረ ዳዊት 119/36 ልቤን ወደ ምስክርህ አዘንብል፥ ወደ ስስትም አይሁን።

ትንቢተ ሕዝቅኤል 11/19-20 በትእዛዜም ይሄዱ ዘንድ ፍርዴንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ፥ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ እሰጣለሁ፥ ከሥጋቸውም ውስጥ የድንጋዩን ልብ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።

ትንቢተ ሕዝቅኤል 36/25 ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ፥ ከርኵሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ።

26 አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።

27 መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3/3 እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።

ወደ ዕብራውያን 10/22 ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ፤

 

 

 

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal