
ጥያቄና/መልስ ፤ ስለ ሰው ፈቃድ በተጠየቅው ላይ የተሰጠ ምላሽ
ብራዘር ማክረር ጥሩ ነው። ክራርም ሲያከሩት ይበጠሳልና። መልእክቱን ግን ባንቀላቅለው ጥሩ ነው። ” የምትጠይቁትን አታውቁምና” ያለው እንዳይሆን እ/ር በሰጠን ፕሪንስፐልስ ወይም መመሪያዋች ላይ ፈቃዳችን በሚገባ እንጠቀማለን። ከሀላፊነት ለማምለጥ ስለ ስለበጎ ፈቃዱ አላማ ላይ ግን መፈለግንም ማድረግንም ባለው የበላይነት ላይ ነው ጥያቄው መሆን ያለበት እንጂ በተሰጠህ ስልጣንና ብሎም አብሮ ከሚመጣው ሀላፊነት በአግባው ላለመወጣት ፈቃዶችን አትቀላቅል። ሰው የዘራውን ያጭዳልና።
“የሰው አካሄዱ ከእ/ር ዘንድ ነው ሰው ታድያ መንገዱን ሊያስተውል ይችል ዘንድ እንዴት ያውቃል” ቅዱስ የቃሉ ገለጻ ነው።
ከእ/ር ዘንድ አካየዱ አንዴ በዘልአለም አጀንዳው ሆነበታል ያንንም ሲገልጠው ፍጥረትን ሁሉ ለከቱንት ስላ ስገዛው ይለናልና (ማ? እ/ር) ነው እንጂ በፈቃዱ(በፍጥረት በፈቃድ) አይደለም።” ደግሞም ሰው የእግዚአብሔር ክብር ማለትም ክርስቶስ ሳይጎድለው ይኖር እንደነበር በእርሱ ቀመር ግን ማለትም የህይወትንም ዛፍ ሆነ መልካምንና ኩፋውን የሚያሳውቅ ዛፍ በእኛ ውስጥ ያስቀመጠው እራሱ እግዚአብሔር ነው። ይህንም ለማስተዋል እንደ እ/ር ፈቃድ ይሁንብንና ነገሩ በአላማ ነው ሰፊ ትግስትና ትኩረት የእውነትን ቃል በማመሳከር ልንረዳው ይገባል የሆነ ሆኖ ይህይወት ዛፍ ከሆነው ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ብቻ እየበላን እንድ ንመላለስ ነው የእ/ር ስራ እያነቃን ያለው። ”
“ሰውን ወደ ታች ወደ አሳር አወረድከው” ይላል። ከክብር ወደ ከንቱነት ያወረደው እ/ር ነው። እንዲሁም “የሁሉን ይምር ዘንድ የሁሉን በአለ መታዘዝ ዘጋው” ይላል ታድያ እሱ የተዘጋውን ማንም እንደ ማይከፍተው የከፈተዉን ማንም የማይዘጋው እንደሆነ እያወክ በሀይሉ ላይ። እንደ ጠላቶቹ መዋሸት አይሆንም ብለህ ነውን?
እውነት የሆነውን አሰቡ ብሎናልና አንርሳት። በእርግጥ በምድር ላይ ስንመላለስ በዙርያችን ፈጥሮ ላስቀመጣቸው ሁኔታዎች የበላይ እንድንሆን ዘንድ። አድርገዋል በአጀንዳው ላይ ግን እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነው።
” ሰውን ታስበው ዘንድ ምንድነው? ከኤሎሂም ጥቂት አሳነስከው…” እስከዚህ በደረስ ሰውን መውደዱ ቢገለጥም በዚህ በስልጣን ሲመላለስ ነፃ ፈቃድ እያለው የመስላል ይሄ ግን በእጆቹ ስራ ሁሉ ላይ መሾሙን የሚያሳይ ነው።
እ/ር ለሰጠው ፕሪንስፕል ውፕይም መመርያ ሁሉ በመጠቀም እንዲኖር ነው እንጂ ወደ በጎ በፈቃዱ ስንመጣ ግን ጉዳዩ ሌላ ነው “ስለ በጎ በፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሰራው እ/ር ነው።” ያውልህ እንግዲህ ደመደመው ታዲያ በጎ ፈቃዱ ምንድነው? ትእግስቱም ይለናል ሁሉ በክርስቶስ እ/ርን ውደ ማወቅ እንዲደርሱና እንዲድኑ ነው።” ይለናል። የሁሉ ትርጉም ሁሉ እንደሆነ በአስተዋዮች ዘንድ የታወቀ ነው። ” ሁሉ በአዳም እንደሞቱ ሁሉ በክርስቶስ የህያዋን ይሆናለና እያንዳዱ ግን በገዛ ተራው ይሆናል። ”
እንደ ምናስተውለው ልዩነቱ በአዳም ወገብ ሳሉ ሁሉ በጅምላ ሞቱ በክርስቶስም እንዲሁ ነው ። በክርስቶስ ልዪነቱ እየአንዳዱ በየተራው መሆኑ ነው። ይለናል።
አንተ ስታስበው ከክርስቶስ ውጭ እያለው ፍጥረታዊ ሰው በበደሉና በሀጥያቱ ከሙታን ከሆነ ከሙታን ዘንድ በፈቃድ አለን? እውቀትስ ስፍሯ አላትን? “ሙታን ግን ምንም አያውቁም” ቃሉ የሚያስተምረን ያንን እውነት ነው።
ታዲያ እንዴት ይድናሉ ለምሳሌ በተፈጥራዊው። እንካን ብናይ አልአዛር 4 ቀን በመቃብር የሞተ ሳለ ነፃ ፈቃድ የነበረውን? በፍፁም የውዱ ቃል የትንሳኤው ህይወትን ታጭቆ ቃሉ ሀይል ለብሶ ወደሱ ሲወረወር መጣ መጀመርያ ሙታን የሚነሱት በፈቃዳቸው ሳይሆን በእ/ር በሀይል ብቻ ነውና የመጣው ቃል ህይወትን ሰጠው ልቡና ሳምባውም መስራት ጀመረ በትንሳኤው ና በህይወት በሀይል አቆመው ግንዘቱንም ፍቱለት እና ይሂድ አለው።
ታድያ አልአዛር በነፃ በፈቃዱ ህይወትን ለመቀበልም ሆነ ጌታን አልቀበልም ወግድልኝ ለማለት እዚህ ላይ እውቀት ነበረው ድርሻና ሀይል ውይም ፈቃድ የነበረውን? ለመንፈሳዊ ሙታንም እንዲሁ ነው። “ሀይል የእ/ር ነው” ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለ መታዘዝ ከዘጋ ሸክላ ሰሪው ከሸክላው የላቀ ታላቅ መሆኑ በሁሉ ዘንድ ማስተዋል ይሁን።
ሸክላው ሸክላ ሰሪውን ለምን እንዲህ አድርገህ ሰራህኝ ብሎ ቢጠይቀው የስቃል እ/ርም በሰማይ ይስቃል እኔም በደስታ በተሰበሰቡት እልፍ አእላፋት ደስተኛ መልአክት ጋር ሆኜ እንደ መንፈሳዊ አባቴ እስቃለሁ። ሀይል የእ/ር ነውና በሰማይና በምድር የተወደደውን ያደርጋል የሚከለክለውም የለምና ። ክብር ሁሉ ለቅዱስ ስሙ ይሁን።አሜን!