
ለምን ገናናዋ ቤተክርስቲያን የዘልአለም እና የዘመን ፍቺ አልበራላትም?
ባለፈው እንዳነሳሁት የዘመን ትርጉም ደግሜ ልጥቀሰውና በመረዳት ብርሃን ማስተዋል ያለብን ዘመን ማለት ዘልአለም ማለት አይደለም። ብዙ ጊዜና ብዙ ወቅቶች አሉ። ነገር ግንአንድ ዘልአለም ብቻ አለ። ዘልአለም ጅማሬ የለው ፍፃሜም ቢሆን የለውም።
ነገር ግን ጊዜ ዘመን ወቅቶች ሁሉም ጅማሬ አላቸው ፍፃሜም አላቸው። ጊዜ ሲያበቃ ዘልአለምይጀምራል የሚለው አባባል ፈጽሞ ስህተት ነው።ምክንያቱም ዘልአለም ጅማሬ የለውም የሚያበቃም አይደለም። ዘልአለም ጊዜ ሲመጣ የሚጀምር አይደለም።ዘመናት በዘልአለም ውስጥ የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው።
ልክ ሴኮንድ በደቂቃ ውስጥ ቦታ እንዳለው ደቂቃም በሰአት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው ሰአትም በአመታት ውስጥየራሱ ቦታ እንዳለው። አመታት እና ዘመናት ያልቃሉ በዘልአለም ውስጥም የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ጊዜ እናስተውል ዘንድ በነዚህ ቃላቶች መካከል ያለው ልዩ ነት ግልጽ እይታ ሊኖረን ወሳኝነው። ዘመን የሚመደበው በጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘልአለምግን ጊዜ አልባ ነው። በመጽሐፍ ስለ ዘመን የተናገሩትንና ሰለ ዘልአለም የተናገሩትን ለይተን ማስተዋሉ የእ/ርን ጠቅላላምክር እናስተውል ዘንድ እጅግ ይጠቅመናል።
በጣም የሚያሳዝነው አብዛኛዎቹ የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች ብዙ የሚመሰገኑበት ቢኖርም ዘመንን በተመለከተ ሲተረጉሙ ግድ የለሽ ሆነው ዘልአለም እያሉ በመተርጎማቸው በእ/ር ህዝብ ላይ ለዘመናት ትልቅ ግራ መጋባትን አስከትለዋል።
ይህም ብዙ ትውልዶችን ለአያሌ ዘመናት የተዛባ መረዳት ውስጥ ቆልፎ አስቀምጠዋቸዋል።ለመጥቀስ ያህል የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞችKJV ላይ እዲሁም በዚህ መጽሐፍ ተጽኖ ስር የተተረጎሙ ሁሉ ላይ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ስለ ሚሳደብ ሰው የተናገረውን ቃል እንዲህ ያስቀምጡታል። እግዚያብሄር ያሳያችሁ አንዱ ቃል ወደ ስንት ተበታትኖ እንደ ተተረጎመ አስተውሉ age {2 ጊዜ beginning of the World {2} ጊዜ, for ever and ever,(8) course{1}ጊዜ World {32} ጊዜeternal {42}ጊዜ, world began{1}ጊዜ forever{27}, for evermore{2}, እነዚህ ሁሉ ዘመን ወይም እንደ አገባቡ ከዘመን ዘመን፤ ለዘመናት፤ ለዘመኑ፤ ወዛተ ተብሎ በቀላሉ በዚህ መልክ መተርጎም ነበረበት።
“ማርቆ3/29 መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን “የዘልአለም” ሃጥያት ይሆንበታል እንጂ አይሰረይለትም” ከዚህ የተሳሳተ ትርጉም የተነሳ የተሳሳተ ጽንሰ ሃሳብ ተወልደዋል። ለዘልአለም ይቅር የማይባል ሃጥያት አለ ብለን እንድናስብ አድርጎን ነበር። ነገር ግን የቃሉ ፍቺ በትክክል እንዲያቀብል አድርገው ከተረጎሙት ከጥቂት የእንግሊዝኛም ትርጉሞች መካከል Emp hatic Diaglott የተባለው ትርጉም ትክክለኛውን ትርጉምi እዲህ ያስቀምጠዋል።“Whoever may blasphemy the Holy Spirit no forgiveness to the age but is exposed to anian lasting judgment mar3/29”
“መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ “ለዘመኑ” ይቅር አይባልም። ነገር ግን”ለዘመኑ“ ፍርድ ይጋለጣል።“ እንደ ምናስተውለው ይቅር የማይባለው ለፍርድ የሚጋለጠው ለዘመኑ ፍርድ እንጂ ለዘልአለም ፍርድ አይደለም። በማትዮስ 12/32 ያለውደግሞ እንዲህ ተብሎ ተተርጉመዋል ”በመንፈስ ቅዱስ ላይየሚናገር ሁሉ በዚህ ”አለም“ ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም። አለም የሚለው ቃል ከግሪኩ aion ማለትም ዘመን age ተብሎ መተርጎም ከነበረበት ቃል የመጣ ነው።
ቃሉ መተርጎም የነበረበት “መንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ “ዘመን” ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም” ነው። ጌታ እየሱስ የተወለደው በህግ ዘመን ስለ ነበር በዚህ ዘመንም ቢሆን ማለቱ የህግን ዘመን ለማሳየት ሲሆን በሚመጣው ዘመን ቢሆን ሲል ደግሞ አሁን እኛ ያለንበትን የፀጋውን ዘመን ማለቱ ነው። ይህን ካስተዋልን ስለ ዘመንና ስለ ዘልአለም ያለውን ብዥታ ያጠራልናል። በግሪክ aion(ሰዋሰው noun) በግልጽ “ዘመን ወይም ያልተወሰነ ክፍለ ጊዜ ነው an age or an indefinite period of time, Young’s Concordance”