ስማ/ሚ በኢየሩሳሌም የየሚገነባ ሌላ 3ኛ ቤተ መቅደስ ማለትህ/ሽ ምን ማለትህ/ሽ ነው?


ስማ/ሚ በኢየሩሳሌም የሚገነባ ሌላ 3 ቤተ መቅደስ ማለትህ/ሽ ምን ማለትህ/ሽ ነው?
Brother Binyam T. Alemayehu 1/20/2018

ብዙዎች በክርስትና ውስጥ ያሉና በአይሁድ ሃይማኖት ያሉ “ሶስተኛው ቤተመቅደስ” በቅርቡ ይገነባል ብለው እንደ ሚጠብቁ የታወቀ  ነው። በውኑ ይህ የሚጠባበቁት ትክክለኛ ተስፋ ነውን?

እንደ ጌታ ኢየሱስ ቃል ከሆነ, በዮሐንስ 4:21-24 ላይ ‘ኢየሱስም እንዲህ አላት፤ “አንቺ ሴት፤ በዚህ ተራራም ሆነ በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ እንደ ሚመጣ እመኚኝ። እናንተ ሳምራውያን ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን ድነት ከአይሁድ ስለ ሆነ ለምናውቀው እንሰግዳለን። በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፤ አሁንም መጥቶአል፤ አብም እንደዚህ በእውነት የሚሰግዱለትን ይፈልጋል። እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባል።” ‘

እንደ ምናስተውለው እንደ እግዚአብሔር እቅድ በኢየሩሳሌም የየሚገነባ ሌላ 3ኛ ቤተ መቅደስ ፈጽሞ አይኖርምም። እንደ ጌታ ኢየሱስ የእውነት ቃል ነገሮች ተለውጠው ታይተዋል። ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት መልኩንም ቀይረዋል በቦታ ወይም በአካባቢ ወይም በምድራዊትዋ የኢየሩሳሌም ቤተ-መቅደስ ለአብ የማንሰግድበት ጊዜ መጥተዋል። ስግደቱ ሰው በሰራው መቅደስ የማይሆንበት ዘመን መጥተዋል ህብረቱና አምልኮው በእውነትና በመንፈስ ውስጥ እንዲሆን ወስነዋልና። ጌታ እየሱስ እኔ በሩ ነኝ አለንና በዚህ በንፈሳዊ በር በእርሱ ወደህልውናው ለመግባት ድፍረት አለን። በዚህ በር በመንፈስ እንገባለን እንወጣለን እንሰማራለን። ክብር ለክብር አባት ነው። አሜን።

ለመሆኑ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚሰራው ስልጣን ያላለው ማነው?ዘካርያስ 6:12 ለእርሱም እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘እነሆ፤ ስሙ ቅርንጫፍ የተባለው ሰው ይህ ነው፤ እርሱም በቦታው ይንሰራፋል፤ የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ ይሠራል። 13የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚሠራው እርሱ ነው፤ ክብርን ይጐናጸፋል፤ በዙፋኑ ተቀምጦ ይገዛል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ስምምነት ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም bible.com/1260/zec.6.13.NASV

ቅርንጫፉ ማን እንደሆነ ወደቡሃል እንተነትነዋለን። ‘ለመሆኑ፣ ሰውነታችሁ በውስጣችሁ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆነ አታውቁምን? ይህም መንፈስ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት ነው። እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤ በዋጋ ተገዝታችኋልና፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።’ 1 ቆሮንቶስ 6:19-20

‘በመካከላችሁ እመላለሳለሁ፤ አምላካችሁ (ኤሎሂም) እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ። ማደሪያዬን በመካከላችሁ አደርጋለሁ፤ ነፍሴም አትጸየፋችሁም። ‘ዘሌዋውያን 26:11-12

 

‘ከዚህ የተነሣ እናንተ ከቅዱሳን ጋር የአንድ አገር ዜጋ፣ የእግዚአብሔርም ቤተ ሰብ አባል ናችሁ እንጂ፣ ከእንግዲህ ወዲህ መጻተኞችና እንግዶች አይደላችሁም። በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑ ራስ ድንጋይም ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው፤ በእርሱ ሕንጻ ሁሉ አንድ ላይ ተገጣጥሞ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል። እናንተም ደግሞ እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚኖርበት ማደሪያ ትሆኑ ዘንድ አብራችሁ እየተገነባችሁ ነው።’ ኤፌሶን 2:19-22

የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆንን በግልፅ የሚያስረዳን ግልፅ ቃል አይደለምን? ደግሞ ጌታ ከላይ በዮሐንስ ምዕራፍ 4 ላይ እንደ ተናገረው, በኤፌሶን ምዕራፍ 2 ቁጥር 22 ውስጥ, ይህ ጌታ በመንፈስ ቤተ መቅደሱን እገነባ ነው። እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚኖርበት ማደሪያ ትሆኑ ዘንድ አብራችሁ እየተገነባችሁ ነው።”ስራው በመንፈስ ውስጥ እንዳለ አታይም? ታዲያ ይህ ሁሉ ለወደፊቱ በኢየሩሳሌም ስለሚገነባው 3ኛ ቤተ መቅደስ እየተናገረ ያለው ምንድን ነው?

ጌታ ኢየሱስና ጳውሎስ የተናገሩት ይህ ቤተ መቅደስ በመጽሐፍ ቅዱስ በሕዝቅኤል ምዕራፍ 40-47 እግዚአብሔር  ለነብዩ በራእይ የተሰጠው ነው። አስተውሉ በምዕራፍ 47: 1 ላይ “‘..ከቤተ መቅደሱ መድረክ ሥር ውሃ እየወጣ፣ …ሥር ሥሩን ይወርዳል። ‘ሕዝቅኤል 47:1 ጌታ የተናገረውን ቃል ደግሞ አስታውሱ  ‘በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” ‘ዮሐንስ 7:38 38.

John7/38 “The one continuously trusting and progressively believing into Me, just as the Scripture says, ‘Rivers (floods; torrents) of living water will flow (or: gush; flood) from out of the midst of his cavity (his innermost being or part; the hollow of his belly; [used of the womb]).”

  1. Now this He said about (with regard to) the Spirit [other MSS: Holy (Set-apart) Spirit] of which (of Whom as a source; [other MSS simple read: which]) they – those trusting and believing into Him – were about to be continuously receiving. For the Holy (Set-apart) Spirit was not yet being One having been given [reading with B], because Jesus was not yet glorified (made full of glory or endowed with glory; made to be a manifestation which calls forth praise).

‘በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” ይህን ያለው በእርሱ የሚያምኑ ስለሚቀ በሉት መንፈስ ነበር፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ አልተሰጠም ነበር። ‘ዮሐንስ 7:38-39

 

የቃሉን ግንኙነቱን ታያላችሁ? በሕዝቅኤል ምዕራፍ 47/9 ውስጥ አንብቡ፡ የወንዙን ​​ተፅዕኖ በቁጥር ዘጠኝ ውስጥ ያለውን አስተውሉ “‘ወንዙ በሚፈስበት ስፍራ ሁሉ ብዙ ሕያዋን ፍጡራን ይኖራሉ። ይህ ውሃ በዚያ ስለሚፈስና ጨውማ የሆነውን ውሃ ንጹሕ ስለሚያደርገው፣ ዓሣ በብዛት ይኖራል፤ ስለዚህ ወንዙ በሚፈስበት ስፍራ ሁሉ ማንኛውም ነገር በሕይወት ይኖራል። ‘ሕዝቅኤል 47:9

…” የዚህ ወንዝ አቅጣጫውን ከተከተላችሁ መድረሻው ሙት ባሕር ነው። እንዴት ያለ የሚገርም ምስል ነው። ሕይወት ወደ ሙታን ሳያቃርጥ መምጣቱ እንዴት ያለ ድንቅ መንፈሳዊ ምስል ነው። ባህር በሃትእ በብዙቦታ እንደ ሚመስለው አትርሱ”ሃጥእ እንደ ተቸገረ ባህር ነው” ደግሞም በትንቢተ ኢሳይያስ 57/20 ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፥ ውኆቹም ጭቃና ጕድፍ ያወጣሉና። የሕዝቅኤልን ራዕዮች ወደ አካላዊ ዐውደ-ጽሑፍ ተርጉማቹሁ ካስቀመጣችሁ ከዚህ ትንቢት ነጥብ ጋር በቀላሉ ተላልፋችሃል ጌታ የተናገውም አልገባችሁም። በሉቃስ 24/27 ውስጥ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ የተናገረውን ማስታወስ በቂ ነው። ‘ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ በቅዱሳት መጻሕፍት ስለ እርሱ የተጻፈውን አስረዳቸው። ሉቃስ 24:27

ነብያት ስለእርሱ ተናግረው እንደነበረ ልብ በሉ እና አሁን ደግሞ ይግረማችሁብሎ የእርሱን አካልንም ያካትታል ብሎን ቁጭ።

የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ መሆናችንን እንድናስተውል ሌላ መንፈሳው ገፅታ መጥቀስ እፈልጋለሁ። እንደ ምናውቀው ቤተመቅደስ አጠቃላይ መዋቅሩን እና በውስጡ ያሉትን ቁሳቁሶች በሙሉ ያካትታል። አስታውሱ በወርቃማ መሠዊያው ላይ ዕጣን ማቅረባቸው የተምሳሌቱ ምስል ፍቺ  “የቅዱሳ ጸሎት” ነው (ራዕይ 8፡4) ‘የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳኑ ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ። ‘

አስተውሉ በቅዱሱ ስፍራ ውስጥ መቅረዙ መብራቱ የሚያመለክተው በተለምዶ ቤተ-ክርስቲያን ተብሎ የሚጠራው የተጠሩት አካል ወይም ማህበረሰብ ለማሳየት ነው።(ራዕይ 1፡20). ‘በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምስጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።’

በዕብራውያን 10:19 የቤተመቅደስ መሸፈኛ መጋረጃ በክርስቶስ ሥጋ ቅርፅ እንደ ተመሰለ እንመለከታለን ባለቀለም ፎቶግራፉን እያገኛቹሁት ነው? እኛም የእርሱ ቤተመቅደስ ከሆንን ሥጋችን ከመጋረጃው ጋር ይዛመዳል። ‘ይኸውም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል በከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው። እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ በኢየሱስ ደም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት ድፍረት አግኝተናል፤ ‘

አስተውሉ ቅድስተ ቅዱሳን ያለው በመጋረጃው አልፎ በውስጠተ ውስጣችን (በመንፈሳችን) ነው። የእግዚአብሔር ህላውና መኖሪያ ስፍራም ነው። ደግም ይህ ዋናው መንፈሳዊ አካል የእ/ር ክብር የሆነው ክርስቶስ በእኛ ውስጥ ነው የሚለው ከጥላው ተምሳሌት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ጋርም የሚስማማው ነው። በጥላው ምሳሌው ውስጥ ስታስተውሉ በታቦቱ ውስጥ ነበር የሕጉ ጽላቶች የሚቀመጡት። አሁን ደግም የህይወት መንፈስ  ህጉን በውስጣችን እየፃፈው ነው። የህይወት መንፈስን በመንፈሱ ወደ መንፈሳችን አትርፎ እያፈሰሰው ነው። ማለትም (በልባችን ዋናው አካል ፡ የእኛ ውስጠተኛው ክፍል, በቅድተ ቅዱሳኑ) ።

በእ/ር መንፈስ ማደርያ በጥላው ጊዜ ስታስተውሉ የኪሩቤልም ስፍራዎች በእዚህ መጋረጃ በውስጥ በከል አሉ። ‘ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ፣ በእጅ ጥበብ ባለ ሙያ ኪሩቤል የተጠለፉበት መጋረጃ አበጁ። ‘ዘጸአት 36 35 ይህ የጥላው ተምሳሌት ከመጋረጃችን ውስጠኛ ክፍል ጋር ይዛመዳል ።  እናም ኪሩቤልም እውስጥ ካለው የክርስቶስ አካል ተምሳሌት ነው።   የዮሐንስ ወንጌል 14/20 …. እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።

የዮሐንስ ወንጌል 14/23 ኢየሱስም መለሰ አለውም፦ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።

በምህረቱ ባለጠጋ የሆነው አባት ከምህረት ድህነት አውጥቶ ወደ ባህርዩ ወደ ምህረት ባለጠግነት የብስለት ከፍታ በመንፈሱ እየሰራን ነው። “ምህረትን እወዳለሁ ….ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ ማቴ 9/13” , ማቴ12/7 ከዚህ ቃል እንደ ምናስተውለው ጌታ ምንን ይወዳል? በእርግጥም ምህረትን ይወዳል። ስለ ምንስ ተማሩ አለ? በእርግጥም ምህረትን እንድንማር ይወዳል። እንደሚታየው ግን ብዙዎች ከጌታ ጋር ብዙ ዓመት ተጉዘው ምህረትን መውደዱ ያለ ማስተዋላቸውና ያለ መማራቸው ድንቅ ነው። እ/ር ግን በዚህም ውስጥ አላማ እንዳለው እናውቃለን። አንድ ጊዜ ነው አሉ የወገኖች ህብረት በተጧጧፈ ሁኔታ በመንፈስ ሰክረው በመካከላቸው እ/ር እየበዛ እየቀረበ መጣላቸው። በመሃል አንድ ወንድም ከአካሉ ተገንጥሎ ለብቻው የተቀባ መሆንን ፈልጎ ከህብረቱ ጠፋ። “መጽሐፈ ምሳሌ 181 መለየት የሚወድድ ምኞቱን ይከተላል፥ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል። ና”

የከበረ ነገር ያለበት ወንድም ነበረና እስከ ተወሰነ ርቀት በቀዳው ነዳጅ ተጓዘ ከዛ ግን ድርቀት ሆነ። ከህብረቱም በእድሜም በፀጋም በምህረትም የበለፀጉ የሸመገሉ አንድ አባት ነበሩና ወደ ቤቱ ሄዱና ምህረትን አገለገሉት። እዚያም ሲደርሱ እጅግ ታላቅ ብርድ ስለ ነበረ ብዙ እንጨቶችን ደራርቦ እሳት ይሞቅ ነበር። በሩም ተንኳኳ እሳቸው መሆናቸውን ያይና እንዳኮረፈ በሩን ይከፍተዋል። ሳይነጋገሩ ከቆፈኑ ለማገገም ሁለቱም ከእሳቱ መሞቅ ጀመሩ። እሳቸውም መልክታቸውን መናገር ጀመሩ ይህ ትልቁን እንጨት ታየዋለህን? ሁሉንም እንጨቶች በሃይል ተሰባስበው ካሉበት በብዛት ከሚያቀጣጥላቸው ዋንኞው እሱ ነው። ነገር ግን ከመሃከላቸው እናውጣውና እንየው ብለው በጣም በሃይል የሚቦለቦል እሳት ያለው ትልቁን እንጨት ለብቻው አውጥተው አስቀመቱት በሃይል የሚቦለቦል እሳት ያለው ትልቁ እንጨትም ቀስ እያለ እየከሰመ እየከሰመ ጠፋ። ተነስተውም ለሄድ ሲጀምሩ የሚማር ልብ ስለ ነበረው መልክቱን እዳገኘውና ወደ ወገኖችም ህብረቱም እንደ ሚመለስና ከገወገኖች ጋር ጌታን ለመቋደስ እንደ ጓጋ ነግሮ አመስግኖ ተሰናበታቸው።

በምህረት የተሞላ ማንነት እስኪ መጣብን ድረስ የእ/ር ስርአቶች ምንኛ አስጨናቂዎች ናቸው? ጊዜው ሲደርስ እኮ በምህረት ፍፁማን መሆናችን አይቀርም። ጌታ እየሱስ በምህረቱ ፍፁም ነበር። እሱ እንደ ዘፍጥረቱ ሰው የመጀመርያው አዳም ጅምር መልክና አምሳል አልነበረም ከእ/ር ክብር ጎድለዋልና ሁለተኛውና የመጨረሻው አዳም ግን ያበቃለት እንደ ወረደ ጠፈፍ ያለ ከማይጎድለው የመለኮት ህይወት የተሞላ ነበረ። እ/ር መግለጥ የፈለገው ፍፁሙ መልክና አምሳልም ነው። እንድንመስልለት ከመጀመርያው በልቡ የነበረው መልክና አምሳል ይህ ነበርና። በማስተዋላችን ፈጠን ሆነን በእርሱ እንገኝ ዘንድ ቅዱስ ቃሉ ተነግሮብናል። ወይ በእሳት እንደ ተቀመሙ ሰዎች ደግሞም እንደ በሰሉ ልጆች በመገለጡ እንማራለን ወይ እንደ ዳዊት እንዲህ ማለታችን አይቀርምና።“መዝሙረ ዳዊት 119/71 ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።”

 

አያችሁ አባታችን በምህረት የተሞላ እንደሆነ እኛም ልንሆን የተገባንን ተፅፎልናልና። “(Luke 6:36 [KJV]) Be ye therefore merciful, as your Father also is merciful 37 Judge not, and ye shall not be judged: condemn not, and ye shall not be condemned: forgive, and ye shall be forgiven: አባታችሁ ርኅሩኅ እንደሆነ እናንተም ርኅሩኆች ሁኑ። አትፍረዱ፤ አይፈረድባችሁም፤ አትኰንኑ፤ አትኰነኑም። ይቅር በሉ፤ ይቅር ትባላላችሁ።” ይህ ቃሉ ለራሱ ይናገራል።

ዘካርያስ 6:12 ለእርሱም እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘እነሆ፤ ስሙ ቅርንጫፍ የተባለው ሰው ይህ ነው፤ እርሱም በቦታው ይንሰራፋል፤ የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ ይሠራል። 13የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚሠራው እርሱ ነው፤ ክብርን ይጐናጸፋል፤ በዙፋኑ ተቀምጦ ይገዛል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ስምምነት ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም bible.com/1260/zec.6.13.NASV

(Zech 6:12 [KJV]) And speak unto him, saying, Thus speaketh the LORD of hosts, saying, Behold the man whose name is The BRANCH; and he shall grow up out of his place, and he shall build the temple of the LORD: የቀድሞው ትርጉም ቅርንጫፍ እንደማለት ፈንታ ቁጥቃጦ ብሎ በስተት በመተርጎሙ የእ/ርን ቃል አመሳክረን እውነቱን ለማየት ያስቸግራል ቢሆንም አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጽሐፍ ቅዱስ፥ ቅርንጫፍ ብሎ በትክክል ስላረመው እሱን እንጠቀማለን።

“እነሆ፤ ስሙ ቅርንጫፍ የተባለው ሰው ክርስቶስ ነው።” ስሙ ቅርንጫፍ  የተባለው የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ በሰዎች በመስራት ላይ ያለው ክርስቶስ ነው። ይህ ስለ ጌታ እየሱስ የሚናገር ብቻ ሳይሆን ስለ ክርስቶስ አካልም ጭምር የሚናገር ነው። የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ማለት ደግሞ እንዲሁ ነው። አሁን አንዳንዶች እንደ ሚያስቡት ክርስቶስ አንድ ግለሰብ አይደለም። “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/12 አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤ 1Cor 12/12 For as the body is one, and hath many members, and all the members of that one body, being many, are one body: so also is Christ.” ተጨማሪ ማመሳከርያ ጥቅሶች

“ወደ ሮሜ ሰዎች 12/5 እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥”

“1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/13 አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።”

“1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/27 እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ።”

“ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4/4 በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤”

“ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4-12-13 ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።”

ይህ ስለ ጌታ እየሱስ የሚናገር ብቻ ሳይሆን ስለ ክርስቶስ ብዙ አካልም ጭምር የሚናገር ነው ካልን ዘንዳ  ቤተ ክርስቲያንም የምትሰራው በክርስቶስ አካል በሰው ወይም በእ/ር ልጆች ነው። ክህነቱ የሚሰራው በሰዎች ውስጥ አልፎ በክርስቶስ ህይወት በተሞሉ አካላቶቹ ነው። እየሱስና ቤተክርስቲያን አንድ አዲስ ሰው በምድር ላይ ናቸው። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2/14-15 …አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ” ሁሉንም እነዚህን የመሰሉ ትንቢቶችን አመልካቸነታቸው ለጌታ እየሱስ ብለናል ይህም መልካም ነው። ትቢታዊ አመልካችነቱ ዛሬም አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስትያንም ጭምር ነው። ጌታ የጀመረውን ስራ የምታስቀጥለው አካሉነች[የጀመረው]። የሐዋርያት ሥራ 1/1-2 ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ኢየሱስ …. ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስ-ለ  ጀ-መ-ረ-ው ሁ-ሉ መጀመሪያውን ነገር ጻፍሁ፤

“ኢሳይያስ 4/2 በዚያን ቀን የእግዚአብሔር ዛፍ ቅርንጫፍ ያማረና የከበረ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፈው የእስራኤል ወገን ኵራትና ክብር ይሆናል” እነሆ እዚህ ጋር የእግዚአብሔር ዛፍ ቅርንጫፍ  ይለናል እስቲ በዚህ ምእራፍ እንየው “ኢሳይያስ 11/1 ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፤ ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።” “Isa 11/1 And there shall come forth a rod out of the stem of Jesse, and a Branch shall grow out of his roots:”

በ“ኢሳይያስ 4/2  ላይ የእግዚአብሔር ዛፍ ቅርንጫፍ ብሎ አስነብቦናል እዚህ ደግሞ የእሴይ ግንድና ቅርንጫፍ ይለናል። ምን ማለት ነው?ከእግዚአብሔር የወጣ ቅርንጫፍ ነው ወይስ ከእሴይ የወጣ ቅርንጫፍ? ሁለቱም ነው። ቅርንጫፉ የሚያመለክተው ስጋ መልበሱን ነው። የእግዚአብሔር  ቅርንጫፍ  የሚመሰለው የእ/ር መልክና ክብር ነው። ከእሴይ የወጣው ብትር የሚያመለክተው ለሰው የተሰጠውን ስልጣንና ንጉሳዊነትን ነው።

በመንፈሳዊ መነጽር ስታዩት ጌታ እየሱስ ሰውም መለኮትም ነበረ። እሱ የእግዚአብሔር ሁለቱንም ብትርም ቅርንጫፍም ነበረ። የዳዊትም ቅርንጫፍ ነበረ። ስጋ ስለ መልበሱ ስናወራ “ኤርምያስ 23/5“እነሆ፤ ለዳዊት፣ወይም ከዳዊት የዘር ግንድ ጻድቅ ቅርንጫፍ የማስነሣበት ጊዜ ይመጣል፤እርሱም ፍትሕንና ጽድቅን የሚያደርግ፣ በጥበብ የሚገዛ ንጉሥ ይሆናል” ይላል እግዚአብሔር።”

የመለኮት የእግዚአብሔር ተፈጥሮ ከሰው ዘር ጋር የተቀላቀለውና የተዋሃደው ያ ነው። ጌታ እየሱስ ያ ነበር። የመለኮት የእግዚአብሔር ተፈጥሮ የተዋሃደበት ሰብአዊ የእ/ርን መቅደስ የሚሰራው እርሱ ነው። መለኮትነትን እና ሰብአዊነትን ይጠይቃልና።

“ዮሐንስ 15/1 “እውነተኛው የወይን ተክል እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው። 2እርሱም በእኔ ያለውን፣ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን የበለጠ እንዲያፈራ ይገርዘዋል።”

 

መቸም ጌታ እየሱስ ሙሉ መለኮትና ሙሉ ሰው ነው ሲባል ብዙ ግዜ ሰምተናል። ቆላስያስ ሲነግረን በዚህ የባርያን መልክ ይዞ የመለኮትነት ክብሩን አፍስሶ እራሱን ባዶ አድርጎ በሰው ደረጃ ወርዶ እየሱስ ተብሎ በምድር ላይ በተከሰተው ሌላ ሚስጥር በክብር ይዞ ሲገለጥ ይህም የመለኮት ሙላት ራስነት ሁሉ በእርሱ ተሞልተዋል እናንተም በሱፉፁማን ናችሁ ሲለን ፍጥረት ሁሉ በአድናቆት ክው ቢል ምን ይደንቃል? እርሱ ሁሉን ነውና መጽሐፍት ሁሉ ወደሱ ይናገራሉ ይጠቁማሉና ። ሰው ሲባል ሊከብደን አይገባም በአላማ ስለ ፍቅር ተሰውተዋልና መስዋእቱን ልናከብር ይገባለ “ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2/7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥” “Pilippians2/7. JMT, but to the contrary, He empties Himself (removed the contents of Himself; made Himself empty), receiving (or: taking) a slave’s form (external shape; outward mold), coming to be (birthing Himself) within humanity’s (mankind’s; men’s) likeness”

ጌታ እየሱስ ሙሉ መለኮት ነው ሲባልም እውነት ነው። “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2/9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤ Col 2/9 For in him dwelleth all the fulness of the Godhead bodily.”

“(Col 2:9 [NET])For in him all the fullness of deity lives in bodily form,”

“(Col 2:9 [HCSB])For the entire fullness of God’s nature dwells bodily in Christ,”

“(Col 2:9 [ESV2011])For in him the whole fullness of deity dwells bodily,”

“(Col 2:9 [YLT])because in him doth tabernacle all the fulness of the Godhead bodily,”

“(Col 2:9 [Weymouth])For it is in Christ that the fulness of God’s nature dwells embodied, and in Him you are made complete,”

“(Col 2:9, JMT)9.  because within Him all the fullness of the Deity (the Godship and feminine aspect of the Divine Nature) is bodily settling down and taking up permanent residence (is continuously dwelling bodily),

እኛ  ዳግም ከተወለድንበት ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ መለኮታዊ ና ሰብዓዊ ጥምር መሆኑን ተነግሮናል። እሱ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ነበር። ቆላስይስ ሲነግረን በእርሱ ላይ በዚህ ሰው ላይ ማለትም በኢየሱስ ላይ የእግዚአብሔር: የመለኮት ሙላት  ራስ ሁሉ በኢየሱስ ውስጥ በአካል የተቀመጠ መሆኑን ይነግረናል። ከዚያም ኢሳይያስ 9: 6 ትንሹን ሕፃን ኃያል አምላክ መሆኑን ይነግረናል። ትንሹ ሕፃን ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ የፈጠረው ኃያል አምላክ በውስጡ የያዘ ዋክብትን ወደ ሕልውና ያመጣውን ና የሚያስተዳድራቸውን ሃይል የተሸከመ ነው፡ይለናል። እንዲሁም ያ በሰው ውስጥ መንፈስ የፈጠረው ፈጣሪ ይህ ትንሽ ሕፃን ኃያል አምላክ ነው ይለናል። ይህ ትንሽ ሕፃን የተሸከመው ከአጽናፈ ዓለሙ ፈጣሪ ያነሰ ሳይሆን ሙልአቱን ምንም ሳይጎድል መለኮትን ይዟል። በዚህ ሁለቱንም ማንነት ሰውነትና መለኮታዊነት አብረው በተዋሃደ፤ በተዋደደ ፤ በተለወሰ፤ በተቀላቀለ የሁለቱም ቅርንጫፍ ነው። የጌታ እግዚአብሔርን መቅደስ የሚገነባው እሱ ነው።

የቀደሙት አባቶች ከቃሉ የገባቸውን ያህል ለእኛ ኢየሱስ መለኮታዊ አካል እንደ ነበረ  አስተምረውናል።ነገሩ በሱ አያበቃም የተሰወረብን እውነት ግን አለ። እኛን ግን ተመሳሳይ ናችሁ ብሎ ሊያስተምረን የደፈረ አልተገኘምና አልቀጠልንበትም። የፃድቃን ክብር እ/ር ሆኖ ሳለ ክብራቸው በውስንንነት ተዘረፉ። በሃጥያት ምክንያት የጎደለብን ምን ነበር አዎን የእ/ር ክብር ክርስቶስ ነበር እሰይ ክብራችን ተመለሰ።የእ/ር ልጆች በመንፈሳዊ ከፍታ እንደ ንስር መኖር ሲኖርብን እንደ ዶሮ ጫጩቶች አስበን ሁላችንም ባልተገባ ክብር እንደ ዶሮ ወረድን ተመላለስን። አሁን ግን እምቢ ያለ ንስር ከዶሮ ተራ ወደ ንስር ከፍታ የሚወጣበት ዘመንን እ/ር እያመጣ ነው። የንስር ፃድቃኖች በኛ ውስጥ ባለው ህይወታችን በሆነው ጌታ ደስ ይበለን። እኛ በክርስቶስ ሆነን ከመለኮትነት ጋር የተዋሃድን የተለወሰ የሰው ዘር ኦ ከዛም በላይ የህያው እ/ር ልጆች በእ/ር ልጅነት ክብር መመላለስ የተጠበቀልን ነን። መጽሐፍም “እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና”  ብሎ ይነግረናል። ይህ የገባው ብጹእ(ደስተኛ) ነው እላለሁ። እስቲ አስቡት ይህን እውነት ለእኛ በመጋረጃ በማይከደን ማስተዋል በሙልአት ብናስተውለው ኖሮ የክርስቶስ አካል ምን ማድረግ እንደ ምትችል መገመት ትችላለህ? እኛ የክርስቶስ መንፈሳዊ አካል ከክፋዩ የተገኘን ከአጥንት አጥንቱ ነን፥ ከሥጋም ሥጋው ነን፤ እኛ ከክርስቶስ ተገኝተናልና።

ክርስቶስ መሲሁ የህይወታችን እስትንፋስ እንደሆነ በአዲስ ኪዳን ብቻ ሳይሆን ነብያት እንድንነቃ ተንብየውልን ነበረ። ሰቆቃው ኤርምያስ 4/20 ሬስ። ስለ እርሱ፦ በአሕዛብ መካከል በጥላው በሕይወት እንኖራለን ያልነው በእግዚአብሔር- የተቀባ(ክርስቶስ) የሕይወታችን-እስትንፋስ፥ በጕድጓዳቸው ተያዘ።Lam 4/20 The breath of our nostrilsthe anointed (Christ )-of the Lord, was taken in their pits, of whom we said, Under his shadow we shall live among the heathen አስተዋላችሁን የተቀባው(ክርስቶስ) የሕይወታችን-እስትንፋስ ነው!

እኛ ሁላችን በዚህ ምድር መንፈሳዊ የክርስቶስ አካልን በመገንባትና እንዲሁም በምድር ላይ ክርስቶስን በመግለጥ ላይ ያለን የክርስቶስ አካሎች ብዙ ስንሆን ደግሞም አንድ አካል ነን። አንድን ሰው ስታዩ መላ አካሉን አጠቃላችሁ እከሌ ብላችሁ ትጠሩታላችሁ እንጂ ለብቻው ጭንቅላት፤ ራስ (ክርስቶስ እየሱስ)ወይም ለብቻው አንዱን ብልት ነጥላችሁ አትጠሩትም ወይም እጅ፤ አይን፤ ጆሮ እያላችኁ አትለዩትም የክርስቶስ አካሎች ብዙ ስንሆን ደግሞም አንድ አካል ነን፤ ክርስቶስ! “በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤”

የዮሐንስ ወንጌል 17/20-21 ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።

22-23 እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።

እኛ የእርሱን ምስል የያዝን ና እንዲሁም የእርሱ ስልጣን የተሰጠን በምድር ላይ በእርሱ ስም የምንገልጥ፡ ስሙ ማለትም በርሱ ተፈጥሮና ባህርይ  በክርስቶስ የምንገለጥ መንፈሳዊ ገዦዎች መንግሥቱን ለማስፋፋት ያለውን ሥልጣን የሚገልጥብን አካሉ ነን።

 

አዳም በመጀመሪያ ሥልጣን ሁሉ እንደ ተሰጠው እናውቃለን። ተገቢ ካህን ማለት ምስሉ እና ክብር መሸከሙ ነውና መለኮታዊ ክብሩም ሥልጣን እና ከሃላፊነት ጋር አብሮ የመጣ ነው። በዮሐንስ 15 ላይ ቅርንጫፍ  የነበረው ግንድ ሆኖ ተገኘ እርሱ ሁሉን ነውና  “እኔ እውነተኛ የወይን ግንድ ነኝ ገበሬውም አባቴ ነው.” ቅርንጫፍ የነበረው ግንድ ሆነ።

ዮሐንስ 15: 1-2 “እውነተኛው የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው። እርሱም በእኔ ያለውን፣ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን የበለጠ እንዲያፈራ ይገርዘዋል። ‘

 

የወይን ግንዱ እና የቅርንጫፍ ንጥረ ነገር እና ውስጡ ያለው ህይወት አንድ ነው። እግዚአብሔር እኛን በምድር ላይ ሲያየን ጠቅላላ ሰውን ሁሉ ማለትም ጠቅላላ አካሉን የወይን ግንዱ ሕይወትና ተፈጥሮ ጋር ተጣብቀንና ተዋህደን ነው የሚያየን። ከእርሱ የተለየ አድርጎ እራሱን የሚያይ ሰው በሉቃስ 15 ላይ አባቱ ያለው ነገር ሁሉ የእርሱ ሆኖ ሳለ ባለማስተዋሉ በቤት ውስጥ እያለ የጠፋውን ትልቁን ልጅ ይመስላል። ስለዚህ እውነት የሆነውን ሁሉ በማሰብ ሊድን ይችላል።

ዮሐንስ 15:4-5 ‘በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ካልሆነ በቀር ብቻውን ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፤ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ልታፈሩ አትችሉም። “እኔ የወይን ተክል ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ማንም በእኔ ቢኖር እኔም በእርሱ ብኖር፣ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል፤ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና። ‘

በዮሐንስ 15 ውስጥ እነዚህን ጥቅሶች ስናነብ ሊቀርልን የሚገባው መረዳት ቁልፉ እውነተኛ ማንነታችንን መረዳት ነው። በእርሱ ውስጥ ማደርና መኖር በእውነተኛ ተፈጥሯችን መኖር ነውና እውነት ላይ ትኩረት ማድረግ ለእ/ር ልጆች አይነተኛ ነገር ነው። አንተ/ቺ በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር የተለየ/ች ሰዎች ብቻ ሰብዓዊ ፍጡራን እንዳይደለህ/ሽ ጥበብ ልትነግርህ ይገባል። ጥበብ ግን በልጆችዋ ፀደቀች! ለአንተ/ቺ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን/ሽን ና በምስሉ የፈጠረን በምድር ላይ በክርስቶስ ክብር ለመመላለስ እስከ ዘላለም የተሰጠህ ብቸኛው የተወደድክ መሆንክን/ሽን ልናስተውል ይገባናል። እኛ የእ/ር ልጆች ነን!በእኛ ውስጥ ባለው የእ/ር ክብር በቀር ያለ ክርስቶስ እኛ በምድር ላይ ምንም ማድረግ አንችልም። ጌታ ኢየሱስ እንኳን “እኔ በገዛ ራሴ ምንም ማድረግ አልችልም ይህ ሥራ በኔ የሚያደገው በእኔ ውስጥ እየሰራው አባቴ ነው” አለ። ኢሳ9/6 ህፃኑን የዘልአለም አባት ነው። ይለዋል። ህፃኑ ህፃን ነው ? ወይስ የዘልአለም አባት? ትንሹን ሕፃን ኃያል አምላክ መሆኑን ይነግረናል። ትንሹ ሕፃን ህፃን ነው ? ወይስ የዘልአለም ኃያል አምላክ?

‘ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል። ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል። ‘ኢሳይያስ 9:6-7 አዎን ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤ ህፃኑ በቤትሊሄም በበረት ቃልስጋ ሆኖ ተወለደ ወንድ ልጅ ተሰጠን ግን ሲሰጠን በጫንቃው ላይ አለቅነት ይዞ ተሰጥቶናል ስሙም፣ ወይም ተፎጥሮውና ባህርዩም ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የሌለው ነው።

ዮሐንስ 15:6 ‘በእኔ የማይኖር ተጥሎ እንደሚደርቅ ቅርንጫፍ ነው፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተለቅመው ወደ እሳት ይጣላሉ፤ ይቃጠላሉም።

በፊት በፊት አንደ አንድ ወጣት ክርስቲያን ይህ አባባል የሚያወራ ያለው ፍሬ ያላፈራ ሰው ለዘላለም በመከራ ሊሰቃይ በዘላለማዊነት በሚነድ የገሃነም እሳት የሚጣል ይመስለኝ ነበር። ብዙ ስጋዊ አስተማሪዎችም ይህ ጥቅስ  የዘልኧለም እሳት ቅጣት ህንደሆነ አስተምረውናል። ሰዎች እንዲህ ያለ ውሸት ሲያስተምሩ ስለኖሩ ሁሉንም የምናይበት በነሱ መነፀር ነበር። ጋቭሮቮች አሉ ፋረሶችን የሚሸውዱት አረንጋዴ መነጽር በማድረግ የከረመ ድርቆሽ ይሰጥዋቸዋል ለምለም ሳር ነው ብለውም ሳያመነቱ ግጥም አድርገው ይበሉታል። እኛም ለዘመናት በክርስቶስ ያለንን ክብር ባለማወቃችን ከህይወት ዛፍ ሳይሆን መልካሙንና ክፉውን ከሚያፈራው የእውቀት ዛፍ ስንበላ ኖረናል።

ወደ እሳቱ ፍቺ እንመለስና  አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነው። የእ/ር እሳት የለውጥ ሃይል ነው። ሁሉም እሳቶች አንድ አይነት አይደሉም። ጌታ ለሙሴ በሚነደው ቁጥቃጦ ሲገለጥ ቁጥቃጦው አላሰቃየውም አላጠፋውም አሁን በዚህ ዘመን ሽሮና ዶሮ ወጥ ተከሽኖ ከሚንከተከትበት እሳት ጋርም አንድ አይነት አልነበረም። የእ/ር እሳት የተለየ ነው እንደ እ/ር የፈቃዱ ምክር አላማው ስራውም ይለያያል።

በአረጀው ሰማይ መረዳት እንደ ተነገረን አይደለም እርሱ ማንንም በዘልአለም እሳት አያሠቃይም። ይህ ሁሉ ማለት ግን ስጋዊ አስተሳሰብህን/ሽን ና ሃይማኖታዊ ከፋፋይ ሃሳቦችን ደግሞም የ/ርን ቃል በልጆቹ እንዳይሰራ ከንቱ የሚያስቀሩትን ወግና ባህል ከፍ ያለውን የሰው እውቀትን ሁሉ ወደጎን ካላሽቀንጠርክ/ሽ እሳቱን በተለየ ባህርዩ ትለማመደዋለህ/ሽ። ያም በዘላለም ስቃይ ቅጣት መልክ ማለት ሳይሆን ፍርዱ ከሆነ የሚያርም ፍርድ ነው እሳቱም ከሆነ የሚያነፃ የሚያነጥር ነው። የእ/ር እሳት በተፈጥሮህ ውስጥ ከእርሱ ያልሆነውን ተፈጥሮ ሁሉ ይበላዋል ማለት ነው። ጌታ እየሱስ ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማል ብሎናልና።

‘ ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና። “ጨው መልካም ነው፤ ነገር ግን ጨው ጨውነቱን ቢያጣ እንዴት መልሳችሁ ጣዕም እንዲኖረው ታደርጉታላችሁ? ጨው በውስጣችሁ ይኑራችሁ፤ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።”’ ማርቆስ 9:49-50

ጌታ ሁለት ትምህርት ቤቶች ለልጆቹ አሉት፡ የመጀመርያው በመንፈሱ ለሚመሩና ለፍቅሩ በጎህሊና ምላሽን ለሚሰጡና ለሚታዛዙ ከልጅነት የሚጠበቀውን ባህሪ ለማሳየት ለሚተጉ ልጆቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የልጅነት ክብር ፍሬዎችን ይለማመዳሉ። ፍቅሩን፡ ምህረቱን፡ ቸርነቱን፡ ፀጋውን፡ ሰላሙን፡ በጎነቱን፡ ጥበቡን፡ ምክሩን፡ ትህትናውን፡ከውቂያኖስ ይልቅ ማስተዋሉን፡ሃይሉን፡ምሪቱን፡ወዘተ… ሁለተኛው ትምህርት ቤት ደግሞ ፍቅሩን እባቡ አፈራቸውን[ስጋቸውን]እየላሰ እንዲነቃ ለሚወዱ በእባቡ ባህሪም ሆነው ፍቅሩን ለሚያሰቃዩ ልጆቹ በመገለጥ ካልተማሩ መንፈስ ቅዱስ ወደ ተግባር ትቤት ያስገባቸዋል። ያስጨነከኝ ለመልካም ሆነልኝ እስኪሉ ድረስ እሳቱ መጠኑን ጨምሮ ይታረማሉ ዘንድ ይለማመዱታል። አንድ ተክእሎ ያለው ወርቅ አንጣሪ እሳት ከወርቅ ላይ አፈሩንና ዚንኩን ማለትም መራራውን ንጥረ ነገር ከወርቁ ፈጽሞ እንደሚያራግፍ እንደሚለየው የእ/ር ባህርይ የሚመስለው ወርቁ እስኪቀር ድረስ በእሳቱ ያሳልፋቸዋል። አንድ ተክእሎ ያለው ወርቅ አንጣሪ አንዴ የሚፈለገው ነገር አለ። ወርቁ በእሳት ሲከተው በኧላማ ነው እንጂ ወርቅ የማሰቃየት አባዜ የለበትም። ባለተክእሎ ወርቅ አንጣሪ ለዘልአለምም በእሳት ወርቁን የሚተውበት ምክንያት የለውም በቅድምያ ወርቁ የእሳት ልጅ ወይም ውጤት ስለሆነ የሚፀዳውም በእሳት ብቻ እንደሆነ ያውቃልና።

እሳቱውጥ ሲከተው ባለወርቁ ወርቁለሚፈልገወ ክብር መድረሱን የሚያቀው በእሳቱ ወደሚቀልጠው ወርቅ ፊት ለፊት አጎንብሶ ያያል ወርቁ ላይ የነበረው አፈርና ዚንክ በእሳቱ ገለል ብሎ ፊቱን መልኩን አንፀባርቆ ካሳየው በቃ አሁን መልኬን በሱውስጥ ካታየበት ዘንዳ የክብር እቃ ሆነዋል ብሎ ከእሳቱለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ያወጣዋል፡አባትም እንዲሁነው የሚፈልገውን መልኩን በእኛ ካየ ቡሃላ እሳቱ አላማውን ጨርሰዋል ብሎ ከዛ ያወጣናል። መጽሓፍ የማይጣፋ እሳት ሲል የማይጠፋው የፈለገ ብትንከባለል መሎከትን በአንተ ሳይሰራ አይጠፋም ለማለት እደሆነ የታወቀ ይሁን።

 

የእኛ ሰብዓዊ ሕይወት ውስጥ ገኖ ያለው የሐሰት ስሜት ከእግዚአብሔር ተለይቶ የሚኖር ሰው ነህ የሚልህን/ሽን የእረኛው ሳይሆን የሌላውን ድምጽ ነውና ይህን ከለየነውና ከካድነው ከከለከልነው በክርስቶስ ውስጥ ያለን እውነተኛ ሕይወት እውስጣችን እናገኘዋለን። ይህ ከውስጣችን ያለው የእ/ር ህይወት መንገዱ ጠባብ ቢሆንም የሚያገኝዋትም ጥቂቶች ቢሆኑም የእ/ር ምህረትና ፀጋ ድጋፍ ከዚህ የህይወት ወሃ በደስታና በማስተዋል ልንቀዳና ልንጠጣ ለፍጥረትም ልናካፍል እንችላለን። አንዱን ቅዱስ የእ/ር መንፈስ ጠጥተማልና በዚህ መንፈስ ከመመራት ውጪ ደግሞ ሌላ ልጅነት የለምና። ‘እግዚአብሔር ግን ይህን በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ ገልጦልናል። መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል። በውስጡ ካለው ከራሱ መንፈስ በስተቀር ከሰው መካከል የአንድን ሰው ሐሳብ የሚያውቅ ማን አለ? እንደዚሁም ከእግዚአብሔር መንፈስ በስተቀር፣ የእግዚአብሔርን ሐሳብ የሚያውቅ ማንም የለም። ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ፣ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንምና፤ ይህም እግዚአብሔር በነጻ የሰጠንን እናውቅ ዘንድ ነው። ‘1 ቆሮንቶስ 2:10-12 የእኛን ሰብዓዊ ሕይወት የሐሰት ስሜት ከከለከልን ዘንዳ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ነን ከእግዚአብሔር የተለየን አይደለንም። እኛ የእውነተኛው ግንድ ቅርንጫፍ ነን። ይህን ካወቅን ማንነታችን አወቅን ማለት ነው። ከኛ ተሙዋጦ መጥፋት ያለበት የስጋዊ አስተሳሰባችን ሁሉ ነው። ለመንፈሳዊው ሰው ሁሉ ነገር መንፈሳዊ ነውና። የሁሉ ፍቺ ደጎሞ ሁሉ ነው። ስጋዊ አእምሮ ማለት ሞት ነውና። እኛ ግን በመንፈስ ምስክርነት ላይ እንቆማለን የጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈሳዊ አእምሮ መንፈስ ቅዱስን ያደምጥ እንደ ነበረ እኛም እጣ ክፍላችን እሱ ነውና። አሜን!

 

ለማጠቃለል, ከላይ እንደተነጋገርነው “ሶስተኛው ቤተመቅደስ” ብሎ ነገር የለም “የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ” እኛ ልጆቹ ነን ደግሞም በምህረቱ ባለጠጋ የሆነው አባት ከምህረት ድህነት አውጥቶ ወደ ባህርዩ ወደ ምህረት ባለጠግነት የብስለት ከፍታ እያመጣን ነው ይንንም በአይናችን ፊት በመንፈሱ እየሰራን እያስተዋልነው ነው። እንደሱ ምህረትን እንድናደርግ ተጠርተናልና። (“ምህረትን እወዳለሁ ….ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ ማቴ 9/13” ፤ የማቴዎስ ወንጌል 5: 7፡ ሮሜ 12 8) ይህን ምህረት ለፍጥረት የምናገለግለው ከኛ ውስጥ ከሚገኘው የምህረት መቀመጫ ላይ ነው። መዝሙር 99: 1 እንደሚነግረን እግዚአብሔር ይነግሣል “በኪሩቤል ላይም ተቀምጦ ይገዛል.” “እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።”

ኪሩቤል ከምህረቱ መቀመጫ ዙፋኑ ክፍል አንዱ ነው። ምክንያቱም ሁሉም ከአንድ የወርቅ ክፍል የተሰራ ነው። ከሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት የእግዚአብሔር የምህረቱ ዙፋን በእኛ ውስጥ መሆኑ ማስተዋል በረከት ነው። በሃይል ቀኝ ከክርስቶስ ጋር ተቀምጠናል። በጥላው ከሙሴ ጋር እንዳደረገው እርሱ ከቤተመቅደስ ውስጥ ለእኛ ይናገረናል።  እኛ ቤተመቅደሱ ስለሆንን እርሱ በእኛ ውስጥ ይናገራል ይናገረናል። አሁን ለሰዎች ሁሉ ምህረትን በኛ ሆኖ እየሰጠ ነው። እሱ እንደመረጠው በሌሎች መንገዶች እንደሚፈወሰው የታወቀ ነው። ለሰው ዘር ያለው ፍቅርና የአዲሱ ቃል ኪዳን ሚስጥር ድንቅ ነው የአዲሱ ፍጥረት ውብ ገጽታውም መልካም ነው።

‘ለእነርሱም እግዚአብሔር የዚህ ምስጢር ክብር ባለጠግነት በአሕዛብ መካከል ምን ያህል እንደሆነ ለማሳወቅ መረጠ፤ እርሱም የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ውስጥ ያለው ክርስቶስ ነው። ‘ቈላስይስ 1:27 Colssians1/27.  To whom God wills (purposed; intends) to make known by intimate experience, what [are] the riches of the glory of this Secret (or: the wealth which has it source in this sacred mystery’s manifestation which calls forth praise) within the multitudes (among the nations; in the Gentiles; among the swarms of ethnic groups), which is (exists being) Christ within you folks, the expectation of the glory (or: Christ, which continuously exists within you [is] the hope of the manifestation which calls forth praise)JMT

ጌታ ሲናገር “መጽሐፍት ሁሉ ስለ እኔ ይናገራሉ” በየትኛውም ቦታ በ እግዚአብሔር ቃል ውስጥ ወደ የትም ብትሄዱ የሱስ ክርስቶስ መገለጥ ሆኖ ታገኙታላችሁ።  ዮሐንስ ራዕይ እራሱ ተብሎ መሰየም የነበረበት የየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው። Rev 1/1 The Revelation of Jesus Christ….. [Revelation ]602 apokalupsis ap-ok-al’-oop-sis from 601; disclosure:–appearing, coming, lighten, manifestation, be revealed, revelation. see GREEK for 601 ይህ ክርስቶስ ተከድኖ ያለው በልጆቹ ውስጥ ነው። l ልክ ማእድ የያዘ መሶብ አክንባሎውን[ክዳኑን] ብድግ ብታደርጉት የተከደነው ማእድ ሁሉወደ እይታ እደሚመጣ ሁሉ ክርስቶስም ከተሸፈነበት መቅደሱ ቀስ በቀስ እየተገለጠ ነው። ራዕዩ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንደሆነ በመንፈሳዊ ክብሩ የሚያስተምር መጽሐፍ ነው። በሁሉም መንፈሳዊ ክቡራዊነቱ ይገልጠው፤ በሙላትነቱ ይገልጣል፤ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ውስጥ በመንፈስ ቅኔ ወርቅና ሰም ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስን ታገኛላችሁ እርሱ ራሱ የእግዚአብሄር ክብር መገለጥ ነውና። የራዕይን መልእክት የሚያነብ ልብ በሚያነበብበት ጊዜ በእያንዳንዱ ገጽ ፊቱን ያያል በእያንዳንዳቸው መስመር  ከክርስቶስ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ  በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ካላየን የሚታያየው ሁሉ ከንቱ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደዚህ መጽሐፍ በመቅረብ  በክርስቶስ የክብር ባህር መዋኘት እንችላለን። የእግዚአብሄር ክብር የክርስቶስ መልክ ነው። “ሁሉ ሃጥያትን ሰረተዋል የእ/ር ክብር ጎድላቸዋል” በሃጥያት ምንያት የጎደለብን ብር አልነበረም የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ነው። ሃጥያት የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ልንረዳው ይገባል በግሪኩ HARMATIA ሲሆን ይህ እስፖርታዊ ቋንቋ ነው፤ ትርጉሙም ምልክሩን መሳት ነው። MISSING THE MARK በአንድ ቀስተኛ ቀስቶ የቀስቱን ፍላጻውን ካሽቀነጠረ ኢላማውን ወይም አላማውን ከሳተ ውድዱርን የሚያየው ህዝብ ሃማሪቲያ HARMATIA ብሎ በታላቅ ድምጽ ይጮካል። እኛም ኢላማችን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ስለሳትን ሃማሪቲያ HARMATIA ሆነብን አሁን ግን እ/ር ይመስገን በሃማሪቲያ HARMATIA ያጣነው የጎደለብን የእግዚአብሄር ክብር ክርስቶስ ተመለስን። የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነው። የሐዋርያት ሥራ 7/55 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ክ-ብ-ር ኢ-የ-ሱ-ስ-ን-ም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፦

ይህ ክርስቶስ አሁን በእኛ ውስጥ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ‘ለእነርሱም እግዚአብሔር የዚህ ምስጢር ክብር ባለጠግነት በአሕዛብ መካከል ምን ያህል እንደሆነ ለማሳወቅ መረጠ፤ እርሱም የክብር ተስፋ የሆነው

በ-እ-ና-ን-ተ  ው-ስ-ጥ  ያ-ለ-ው ክ-ር-ስ-ቶ-ስ  ነ-ው። ‘ቈላስይስ 1:27

Colssians1/27.  To whom God wills (purposed; intends) to make known by intimate experience, what [are] the riches of the glory of this Secret (or: the wealth which has it source in this sacred mystery’s manifestation which calls forth praise) within the multitudes (among the nations; in the Gentiles; among the swarms of ethnic groups), which is (exists being) Christ within you folks, the expectation of the glory (or: Christ, which continuously exists within you [is] the hope of the manifestation which calls forth praise),

Brother Binyam T. Alemayehu http://wongelradio.org/

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal