ከውይይት የተጠቀሰ፤ Berhanu Gezu አንተ የባህርዩ ልጅ አይደለኩም ስትል እራስህን ታርቃለሕ የጉዲፈቻ adoption as sons የምትለዋን አንድዋን ቃል ብዙዎች ይዘው ፍቺው ሳይገባቸው ተሰናክለዋል በእብራዊያን ባህል የጉዲፈቻ ፍቺውን ከስር አብራራለሁ። በቅድሚያ ግን ቃሉ “ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች” 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት1፡4 ናችሁ ይልሃል። ይህ ከአንተ ሃሳብ ጋር አይላተምም? ማስተዋል ያለብን የሰማዩ አባታችን መለኮታዊ ተፈጥሮና ባህርዩ ምንድን ነው? በባህርዩ ስጋ ሳይሆን መንፈስ ነው። የዮሐንስ ወንጌል 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው። እሺ ከእግዚአብሔር(ከመንፈስ ባህርይ) ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ(ባህርይ) ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም። ካለ የተወለድከው ከመለኮት ባህርይ ነው የባህርዩ ልጅ ነሕ ። አንደኛው ከምድራዊ DNA ባህርይ ተካፍለህ በስጋ አባትህ ከሆኑት ከአቶ ገዙ ከሥጋ ባህርይ የተወለደህ በመሆንህ የሥጋ ባህርይ አለህ፥ ከምድራዊ አባትህ ዲ.ኔ.ኤ. ዲኦክሲራይቦኑክሊክ አሲድ ፣ ራሱን በራሱ የሚያባዛ ባህርይ ንጥረ ነገር ሳይቀይር በዛ ዘር ውስጥ የህይወት ተቀጽላ ሆነህ ባህርዩን ተካፍለህ ፣ ይህ በሁሉም የምድራዊ የሕይወት ፍጥረታት ውስጥ እንደ ክሮሞሶም ዋና አካል ይገኛል ፡፡ የጄኔቲክ ወይም ዘረመል ባህርይ መረጃ ተሸካሚ ነው ከዚህ ባህርይ ተካፍለሃል፡፡ በአንጻሩ ልክ እንደዚያ ከመንፈስም ባህርይ ማለትም ከመንፈሳዊው የሰማይ አባትህ የመናፍስት አባት እግዚ አብሔር የተወለድክ የባህርዩ ክብር ክፋይ የሆንክ መንፈስ ነህ። የዮሐንስ ወንጌል 3፡6 ከአንተ ከወንድም ብርሃኑ እና ከኢየሱስ የእውነት ቃል የማነው የሚታመነው? እኔ ከራሴ ይልቅ የሱ ቃል አምናለሁ። እሱ እንዲህ ብለዋል። “ከሥጋ/፟ባህርይ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም/፟ባህርይ የተወለደ መንፈስ ነው።” መቼም ኢየሱስ ቀጥፈዋል ብለህ እርሱን እንደማትሞግተው ነው ማለትም አይ አይደለም “ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ሳይሆን ዘራፍ ስጋ ነው።” እንደማትል የታወቀ ነው። የሰማዩ አባታችን የሚባለው ስለወለደ እንጂ ሌላ አይደለም። እናስተውል ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ቃል ማንነቱ ነው ከቃል ወለደህ ሲልክ ከማንነቱ ከባህርዩ ወልዶካል። ይህ ቃል ትዝ ይልካል? በእውነት ቃል አስቦ ወለደን/ እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን ወዘተ….። በዚህም የሰማዩ አባትህ የመለኮት ባህርይ ተካፍለህ የአባትህ ባህርይ ይዘካል። ልክ የስጋ አባትህ ከሆኑት ከሚጠፋ ዘር ከተካፈልክበት ከምድራዊ አባትህ ከአቶ ገዙ ከሥጋ ባህርይ እንደያዝክ ። እንዲሁ በእኩሌታው ከመንፈስም ከባህርዩ ተወልደካል። ሁለተኛው ውልደትህ በመንፈስ ዳግመኛ የተወለድከው ከሚጠፋ ዘር ከጋሽ ገዙ አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ከባህርዩ ከማንነቱ ነው እንጂ ። ቃልም እግዚአብሔር ነበረና።አንደምናስተውለው አሁን ጻድቅ አባት ልጆቹን እያሰለጠነን ነው። በቀጥታ ከአባት ዘንድ ለልጆች ይህ የመታዘዝ obedience ጊዜ ሥልጠና የተወሰነ ተግሣጽን discipline ያካትታል ። ዕብ. 12፡7 እንደምናውቀው ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል(ያለማቃራጥ እያሳዳዱ መቅጣት chastening of the Lord )ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። እንደምናስተውለው በአድንድ ሰው ህይወት ውስጥ ተግሣጽ ልጅ የመሆኑ ዋና ምልክቶች አንዱ ነው ፡፡ ይህ የሥልጠና ጊዜ ገና ሙሉ ለሙሉ ያልበሰለ ልጅ not yet fully mature Son ምልክት ነው ፣ ገላ: 4/1 እንደሚነግረን ልጆች ሳይቀሩ በስልጠና ዘመናቸው እንደ ባሪያው ተመሳሳይ ናቸው ፡፡ ለዚህም ነው ቃሉ ሲነግረን ፤ ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም።የባህርይ ልጆች አይደለንም የሚለው የስህተት መረዳት የተጸነሰው ጉደፈቻ በምትለው ቃል ላይ ተመርኩዞ ነው። ብዙ ግዜ በግልጽ ማስተወስ ካለብን ሃሳብ አንዱ ጳውሎስ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።ያለው ሃሳብ ነው። በእብራዊያን ባህል [GREEK፡ huiothesia፡ the placing as a fully mature son እንደ ሙሉ ብሱል ልጅ ማስቀመጥ] ማንም ልጅ በዚያ ዘመን እስከ 12 አመት በናቱ ጉያ ያድግ ነበር ከ12 አመቱ በፊት ማንም ልጅ አባቱ ግብርና ይሁን ንግድ የሂድ ወደ ስራው ገና ስላልደረሰ በአባቱ ስራ መሳተፍ አይፈቀድለትም ነበር። ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ 12 አመት ከሞላው ቡሃላ በአባት ስራ መግባት የጀመረው። በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? ወይም “ለምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ስራ ላይ መገኘት እንደሚገባኝ አላወቃችሁምን?” How is it that ye sought me? wist ye not that I must be about my Father’s business? [የገዛ ልጁን ሙሉ ለሙሉ የበሰለ ልጅ አድርጎ አባት የሚዋጅበት ወይም የሚቀበልበት ግዜ 12 እድሜው ላይ ነው] “የራስ ልጆች እንደ ጉዲፈቻ adoption as sons” ( ገላ 4:5 ፣ ሮሜ 8:15 ) ይህ ልጅ ብስለት ያለውን ነጥብ ላይ ሲደርስ የሚካሄድ ስርዐት formal ceremony ነው። በወንድማችን ጳውሎስ ዘመን አባት “የራስ ልጆችን እንደ ጉዲፈቻ adoption as sons” የሚያውጅበት ስራት ነው። ልጁ ቃ ብሎ የበሰለ እና ወራሽ ሆኖ የደረሰበት እድሜው ላይ በአባቱ ሙሉ በሙሉ እምነት ሊጣልበት የሚችል ሲሆን በድረሱን ለማብሰር የሚደረግ መደበኛ ሥነ-ስርዓት ነበር ፡፡ ከዛም በጠቅላላው አባትን ወክሎ እንደራሴ ሆኖ ይሾምና የቤተሰብ ንብረት ላይ የውክልና ስልጣን power of attorney መሰጠቱን የሚበሰርበት ነበር ፣ ስለሆነም ፊርማውና የማህተም ቀለበቱ እንደ አባቱ ክብር ልክ በጥብቅ ተቀባይነት የሚያገኝበት የቤተሰብ ስልጣን ሹመት ማብሰርያ ግዜ ነበር ፡፡በሥልጠና ጊዜችን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት “የራስን ልጆች እንደ ጉዲፈቻ adoption as sons” የምንጠባበቀበት ጊዜን ብቻ አይደለም ፡፡ በእግዚአብሄር መንፈስ መሪነት እንደሰጠን መጠን መንፈሳዊ ሥልጣናችንን ተጠቅመን የአባታችንን መንገዶች ለመማር ከሥልጠናችን ብዙ ብዙ የምንማርበት አለ። በመንፈስ ምስክርነት ላይ ቆመን፣ እንደ መንፈስ መሪት ሁሉን መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ አለብን። ወደ ክርስቶስ ቁመት እንድንመጣ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን እንደነበር መርሳት የለብንም ፡፡ ( ገላትያ 3 24 )በዮሐንስ 3፡3 ውስጥ ጌታ ከኒቆዲሞስ ጋር ባደረገው ንግግር እውነቱን ለመረዳት አቅም ላለው ሰው እውነቱን ሲገልጥ ካስተዋለ ይህን ማታለያ ውሸት መፍረሱ አይቀርም፡፡ “ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ[ anothen an’-o-then ከላይ] ካልተወለደ በቀር ይህ ቃል born again ዳግመኛ ካልተወለደ የሚለው ነው born from above ከላይ ካልተወለደ ተብሎ መተርጎም ነበረበት። “ከላይ መወለድ አለብዎት You must be born from above.”ይህ መነሻችን ከእናታችን ማኅፀን ተፈጥሮአዊ ልደት ቀን የወጣንበት ቅጽበት አለመሆኑን ያሳያል ፡፡ በዮሐ 3፡3 መሠረት እውነተኛ አመጣጣችን ከመንፈሳዊው ዓለም ከላይ from above ነው ይህም ማለት መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ከሌለው ከመንፈሳዊው ዓለም ከላይ from the realm of spirit ነው። አዎ በአባታችን ክብር ከምንጭቻችን ዘንድ መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ ብሎ ነገር የለም በመንፈሳዊ ልኬቶች። yes there is neither beginning nor end in the spiritual dimensions.የልጅነት Sonship መልክት መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ ተፈጠርን ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነን ተወዋህዳናልና ከክርስቶስ ጋር ከብረን የሁሉ ነገር ወራሾች እንደሆንን መረዳታችን ብቻ አይደለም። we are heirs of all things ye we are co-heirs with Christ ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡17ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን ። እሱ ከቦታ በላይ ነው ፡፡ እሱ እየሰራ ያለው ከልደት እስከ ጉልምስና ድረስ የሚሰጥ የሥልጠና ጊዜ ነው። የልጆችነት ማረጋገጫ በመንፈስ መመራት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡14 በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። የተገኘንበት መንፈስ አንድ ነው መገለጡ ግ ን ብዙ ነው እ/ር ግ ን አንድ ነው አባት አንድ ነው። ይህም አንዱ መንፈስ በብዙ ክብር ተገልጦ ታይተዋል። ለምሳሌ እግዚአብሔር መንፈስ አንድ ቢሆንም ለማስተዋል ያህል ስያሜውና አንዳንድ ባህሪያቱን በመጽሃፍ በጥልቀት እንመልከታቸው ብንል እርሱ “የእግዚአብሔር መንፈስ The Spirit of God” “የክርስቶስ መንፈስ The Spirit of Christ” “የጉዲፈቻ መንፈስ The Spirit of Adoption “ “የቅድስና መንፈስ The Spirit of Holiness”, “የእውነት መንፈስ The Spirit of Truth”, “የጤናማ አእምሮ መንፈስ The Spirit of a Sound Mind”, “የነጻነት[የአርነት] መንፈስ The Spirit of Liberty”, ” “የሚያቃጥል መንፈስ The Spirit of Burning”, “የአብ[አባት] መንፈስ The Spirit of the Father” “ወልድ[የልጁ] መንፈስ The Spirit of the Son”, “የ ቃል ኪዳኑ[የተስፋው] መንፈስ The Spirit of Promise” “የየዋህነት መንፈስ The Spirit of Meekness” “የመረዳት[የማስተዋል] መንፈስ The Spirit of Understanding” ” የትንቢት መንፈስ The Spirit of Prophecy “” የክብር መንፈስ The Spirit of Glory “” የምክር መንፈስ The Spirit of Counsel “” የጸጋው መንፈስ The Spirit of Grace “” የጌታ መንፈስ The Spirit of the Lord “ወንድም ቢኒ