ከውይይት የተጠቀሰ። Temesgen Atanaw። የተወደድክ ወንድማችን የጠቀስከው ቃል ነፃ አይልም። ለመሆኑ የእምነትን መጠን ያካፈለህ እግዚአብሔር ነው ወይስ ከሱፐር ማርኬት ነው የሸመትከው እምነት በባህርዩ ከእግዚአብሔር ድምፅ ወይም ቃል የሚገኝ ነው እሱም እግዚአብሔር ባለመታዘዝ እራሱ የዘጋውን ልብ ከከፈተው ነው ለቃሉ እምነት ለሞትክበት መንፈሳዊ ህይወት ህያው የምትሆነው። በበደልህና በሀጥያትህ ሙት ከነበርክ ለማመን ከመንፈሳዊ ሙታን መጀመሪያ የእግዚአብሔር ትንሳኤ ሀይል በመንፈስ ካላነሳህ ሙታን ፈቃድ የላቸውም። ፍጥረት በፈቃዱ አልወደቀም በፈቃዱም አይድንም ከመንፈሳዊ ሞት የሚያድን እግዚአብሔር ብቻ ነው። ምሳሌ20: 24 የሰው አካሄዱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው እንግዲያስ ሰው መንገዱን እንዴት ያስተውላል? ወንድማችን አስተውል። ሮሜ ፰ ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ #እግዚአብሔር#ስላስገዛው ነው እንጂ #በራሱ#ፈቃድ#ፈቅዶ#አይደለም፤ እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን ለእግዚአብሔር ባለመታዘዝ ሚስጥር ዘግቶታልና።አሁን ተስፋው ፍጥረት ራሱ ከጥፋት ባርነት ነፃ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው። ለዚህም ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።ከሰው ነፃ ፈቃድ የተነሳ እ/ር ሁሉን ማዳን አይችልም የሚለው ሃሳብ ከእ/ር አቅም ጋር ሲነፃፀር ኢምንት ነው የሚጋጭም ነው። እ/ር ለሰው ፈቃድ ጌታዋ መሆኑን በየዘመናቱ የነገስታትን የህዝብን ልብ እንደ ወንዝ ወዳሻው ሲመራው ሃይሉን አሳይተዋል። በነፈርሆን ልብ ላይ ፡ በነሊድያ ልብ ላይ፤ በናቡክደኖፆር ልብ ላይ በሌሎችም የሰረው መንፈሳዊ ትያትር ልኡል ወይም ፈጽሞ የበላይ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ነው።መጽሐፍ ቅዱስን በፊት ካስተማሩን ተቃራኒውን እንደ ሚናገር ሳውቅ እኔም ደንግጫለሁ። ቃሉን እንደ ልበ ሰፊዎቹ የቤርያ ሰዎች መመርመር አለብን። ከእ/ር የሆነ የእ/ርን ቃል ይሰማልና። ትንቢተ ኤርምያስ 10/23 አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም። መቼም የእ/ር ቃል ከመጣ መጣ ነው። ዳዊት ቃል ከመጣለት ቡሃላ ወዶ አይደለም “ከአስተማሪዎቼ ይልቅ አስተዋይ አደረከኝ” ለመታበይ ሳይሆን የሰውና የእ/ር ሃሳብ ሰማይ ከምድር ርቆ በማግኘቱ ነው ።በቀድሞ መረዳት በገባቸው አቅም ለደከሙልን አስተማሪዎች ጌታ ይባርካቸው ሆኖም ስለ ሰው ነፃ ፈቃድ ሃያልነት ፈቃዱ ለደህንነቱ እንቅፋት እንደሆነ በዚህም ከእ/ር ምህረትን ሳያገኝ ለዘልአለም በሲኦል በስቃይ እንደ ሚቀቀል ሲሰበክብን መኖሩ አይካድም እውነቱ ግን ሰው በጊዚያዊ ባለው በምድራዊ ኑሮው በጥቃቅን ነገሮች ላይ እ/ር ፈቅዶ ባስቀመጠው ሁኔታ ዛቢያ ተጽኖ ስር የፈቃዱን ውስን ምላሽ ብሎም ውስን ስልጣን አለው እንጂ በእ/ር የዘልአለም እቅድ ላይ ግን የሰው ፈቃዱ የበላይ አይደለም። እ/ር እኮ እ/ር ነው።“ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2/13 ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። በጎ የተባለው ያሰበው የፈቃዱም ምስጥር ደግሞ ነግሮናል እ/ር አሰበ ማለት ደግም ሆነ ማለት ነው። “ኤፌ1/9 በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤10 በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።”ይህን እንመልከት “ወደ ሮሜ ሰዎች 9/16 እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። እንግዲህ ምሕረት ለወደደ willeth(ለፈቀደ) ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚ ምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። but of God that sheweth mercy.” እንዴ ምንድ ነው ነገሩ እ/ር ከፈቃዳቸው ውጪ ሰዎችን ሊያድን ይችላል? ሊነሳብን ይችላል። መልሱ አይደለም ነው። እንደዛ ማድረግ አያስፈልገውም። ሰው ሁሉ እ/ር እራሱን ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ይሆናልና። መንፈሳዊ እውርነቱ ሲበራ ወይም የዶንቆሮው ጆሮ ሲከፈት ለሙታንም ህይወትን ሲሰጠው ለከንቱነት የተገዛው ተፈጥራዊው ማንነት ፋንታ መንፈሳዊ አእምሮ ሲሰጠው ሲመለስለት ሁሉ የሰማይ አምላክን ያመሰግናል። ሓዋርያው ጳውሎስ ከሃጥያተኞች ሁሉ ዋንኛ የምሆን እኔን የማረው አቅሙን ለማሳየት ምሳሌውን ለማሳየት ነው አላለንምን? ጌታ ፈቃዱን ሳይጠይቅ በታቅ ብርሃን፡ ጳውሎስ ላይ አልወደቀብትምን ታድያ ምንም እንካ ሳኦል[ጳውሎስ] ከሃጥያተኞች ሁሉ ዋንኛ ቢሆንም ጌታን ተቀበል ብሎ ፈቃዱን ጠየቀውን? ትእይንቱን እናስተውል እ/ር እራሱን ሲገልጥለት ሃጥያተኛው ሳኦል[ጳውሎስ] መቶ በመቶ ፈቃደኛ ሆኖ እያለቀሰ “ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ!!!” በቃ ፍጥረትም እዲሁ ነው እ/ር እራሱን ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ይሆናል። ቢኒ።