የዘልአለም ፍርድ፡ Eternal Judgment ወይም ፍፃሜ አልባ ቅጣት Endless punishment ብሎ ነገር መፅሐፍ ቅዱስ አያስተምርም። የፍርድን ተፈጥሮ ከማስተዋላችን በፊት ዘመን እና ዘልአለም የሚሉትን ሁለት ቁልፍ ቃላቶች ልዩነታቸውንና ተናጋሪው መንፈስ የሆነው እ/ር ከተናገራቸው አካያ ማየቱ እጅግ ጠቃሚ ነው። “የዘልአለም ፍርድ“ ቅጣት እውነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ከሚጠቀሱት ቃላቶች ዋንኛው “ዘልአለም” የሚለው ቃል የእንግሊዝኛውም የአመርኛውም ላይ ከተፈጠረው የትርጉም ስተት የተገኘ ጽንሰ ሃሳብ ነው። ”መጽሐፍትን እና የእግዚአብሄርን ሐይል ካወቅን አንስትም“ በሚለው ፁሁፍ ላይ እንደገለጽኩት የትርጉም ስራዎችን እንደ ፍጽም ስራ እንዳንደገፍባቸው ታሪካዊ አመጣጣቸውን በማስተዋል መቃኘታችን ለዚህና ለሌሎ ች ሃሳቦች እንደ መንደርደርያ እንዲጠቅመን፡ነው። BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS,…..። ክፍል 7 በወንድም ቢኒ፤
ክፍል 7 በወንድም ቢኒ፤ በአዲስ ኪዳን ”ዘልአለም Eteernal, Everlasting” የሚለው ቃል ከዋናው የግሪኩ ቅጂ ላይ “aionions” ከሚለው ቃል የተረጎመ ነው የቃሉ ስር ወይም፡ ንብረትነቱ “EION” ነው። ትርጉሙም “ዘመን age” ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ናቸው ማለት አይደለም ። aion(the noun form) ሰዋሶው ወይም ነባር ስም ሲሆን aionions (the adjective form ቅጽል ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሶው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንት ሰዋሰው ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት፦ እለታዊ, አመት ፦አመታዊ እንደሚባለው መለት ነው። Greek word “aion” (Strongs #165) or its adjective form “aionios” (#166).
በመረዳት ብርሃን ማስተዋል ያለብን ዘመን ማለት ዘልአለም ማለት አይደለም። ብዙ ጊዜና ብዙ ወቅቶች አሉ። ነገር ግን አንድ ዘልአለም ብቻ አለ። ዘልአለም ጅማሬ የለው ፍፃሜም ቢሆን የለውም። ነገር ግን ጊዜ ዘመን ወቅቶች ሁሉም ጅማሬ አላቸው ፍፃሜም አላቸው። ጊዜ ሲያበቃ ዘልአለም ይጀምራል የሚለው አባባል ፈጽሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም ዘልአለም ጅማሬ የለውም የሚያበቃም አይደለም። ዘልአለም ጊዜ ሲመጣ የሚጀምር አይደለም። ዘመናት በዘልአለም ውስጥ የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ልክ ሴኮንድ በደቂቃ ውስጥ ቦታ እንዳለው ደቂቃም በሰአት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው ሰአትም በአመታት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው። አመታት እና ዘመናት ያልቃሉ በዘልአለም ውስጥም የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ጊዜ እናስተውል ዘንድ በነዚህ ቃላቶች መካከል ያለው ልዩ ነት ግልጽ እይታ ሊኖረን ወሳኝ ነው። ዘመን የሚመደበው በጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘልአለም ግን ጊዜ አልባ ነው። በመጽሐፍ ስለ ዘመን የተናገሩትንና ሰለ ዘልአለም የተናገሩትን ለይተን ማስተዋሉ የእ/ርን ጠቅላላ ምክር እናስተውል ዘንድ እጅግ ይጠቅመናል።
በጣም የሚያሳዝነው አብዛኛዎቹ የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች ብዙ የሚመሰገኑበት ቢኖርም ዘመንን በተመለከተ ሲተረጉሙ ግድ የለሽ ሆነው ዘልአለም እያሉ በመተርጎማቸው በእ/ር ህዝብ ላይ ለዘመናት ትልቅ ግራ መጋባትን አስከትለዋል። ይህም ብዙ ትውልዶችን ለአያሌ ዘመናት የተዛባ መረዳት ውስጥ ቆልፎ አስቀምጠዋቸዋል። ለመጥቀስ ያህል የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች KJV ላይ እዲሁም በዚህ መጽሐፍ ተጽኖ ስር የተተረጎሙ ሁሉ ላይ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ስለሚሳደብ ሰው የተናገረውን ቃል እንዲህ ያስቀምጡታል። እግዚያብሄር ያሳያችሁ አንዱ ቃል ወደ ስንት ተበታትኖ እንደ ተተረጎመ age {2 ጊዜ beginning of the World {2} ጊዜ, for ever and ever,(8) course{1}ጊዜ World {32} ጊዜ eternal {42}ጊዜ, world began{1}ጊዜ forever{27}, for evermore{2}, እነዚህ ሁሉ ዘመን ወይም እንደ አገባቡ ከዘመን ዘመን፤ ለዘመናት፤ ለዘመኑ፤ ወዛተ ተብሎ በቀላሉ በዚህ መልክ መተርጎም ነበረበት። ….. ‘ሰው አንድ ጊዜ ሊሞት ከዚያም በኋላ በፍርድ ፊት ሊቆም ተወስኖበታል። ‘ዕብራውያን 9:27 ይሄ ማለት በፊት እንደምንረዳው በአካል መሞት አለብን ማለት አይደለም። ጳውሎስ ሲነግረን ‘እነሆ፤ አንድ ምስጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም[አካላዊ ሞት]፤ ነገር ግን ሁላችንም እንለወጣለን፤ ‘1 ቆሮንቶስ 15:51 ሰው ሁሉ ወደ ሞት ግዛት ሲወለዱ ሞትን ቀምሰዋል ሁሉ በአዳም ሞቱ እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ መጣ። በክርስቶስ ህያው ካልሆነ በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁንም ተፈርዶበታል በኩነኔ እየኖረ ነው። ‘ እውነት ክርስቶስ ነው ለምን እውነት እላችኋለሁ፤ ብሎ በራሱ ማለ? “እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ አሁንም መጥቶአል፤” አሁንም መጥቶአል? ከሞት ግዛት ወደ ሕይወት ግዛት ተሻገረዋል?
“እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም[aionios የዘመኑ(የዘልአለም ህይወት የተወጋው በጊዜ ውስጥ ስለሆነ የዘመኑ የእ/ር ህይወት ተባለ)] ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ አሁንም መጥቶአል፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ። ‘
በወንድም ቢኒ፤5Demis Nida, Hailegiorgis Tefera and 3 others1 Comment4 SharesLikeCommentShare
Comments
- Hailegiorgis Tefera …እልልልልልልል…2
