የንስሐ ጸሎት


Binyam TA is with Pawlos Alula and 45 others.

March 18 at 4:43 PM ·

#የንስሐ #ጸሎት: “ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን በምዘጋበት ጊዜ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣ በማዝበት ጊዜ፣ ወይም በሕዝቤ ላይ ቸነፈር በምሰድበት ጊዜ፣ በስሜ የተጠራው ሕዝቤ ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ፣ ፊቴን ቢፈልግና ከክፉ መንገዱ ቢመለስ፣ ከሰማይ እሰማዋለሁ፤ ኀጢአቱን ይቅር እላለሁ፤ ምድሩንም እፈውሳለሁ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 7፡14”
“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰባብሮናል እርሱም ይጠግነናል እርሱ አቊስሎናል፤ እርሱም ይፈውሰናል፡፡ትንቢተ ሆሴዕ 6፡1
“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔ በቀር አምላክ የለም። አንተ ባታውቀኝም እንኳ፣ እኔ አበረታሃለሁ። ይኸውም ሰዎች ከፀሓይ መውጫ፣ እስከ መጥለቂያው፣ ከእኔ በቀር ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም።እኔ ብርሃንን ሠራሁ፤ ጨለማንም ፈጠርሁ፤ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም[ra` rah፣ evil] እፈጥራለሁ አበለጽጋለሁ፤ አደኸያለሁ፤ ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ “እናንት ሰማያት፣ ጽድቅን ከላይ አዝንቡ፤ ደመናትም ወደ ታች አንጠብጥቡ፤ምድር ትከፈት፤ ድነት ይብቀል፤ ጽድቅም አብሮት ይደግ፤ እኔ እግዚአብሔር ፈጥሬዋለሁ። “ከዐፈር ሸክላዎች መካከል፣ ከሠሪው ጋር ክርክር ለሚገጥም ወዮለት፤ ጭቃ፣ ሸክላ ሠሪውን፣ ‘ምን እየሠራህ ነው?’ ይለዋልን?የምትሠራውስ ሥራ፣ ‘እጅ የለህም’ ይልሃልን? ትንቢተ ኢሳይያስ 45፡5-8”
“በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ፣ አብረው መጓዝ ይችላሉን? አንበሳ የሚበላውን ሳያገኝ፣ በጫካ ውስጥ ይጮኻልን? ምንም ነገርስ ሳይዝ፣ በዋሻው ውስጥ ያገሣልን? ወጥመድ ሳይዘረጋ፣ ወፍ በምድር ላይ ይጠመዳልን? የሚይዘው ነገር ሳይኖርስ፣ ወጥመዱ ከምድር ይፈነጠራልን? የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ ሰዎች አይደነግጡምን? ክፉ [ra` rah፣ evil] በከተማ ላይ ቢደርስ፣ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን? በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምስጢሩን ለአገልጋዮቹ ለነቢያት ሳይገልጥ፣ ምንም ነገር አያደርግም። አንበሳ አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው? ትንቢተ አሞጽ 3፡6” “የዮሐንስ ራእይ 19፡10 የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነው።”
እግዚአብሔር የሰው ልጆችን የሚመቱ ቸነፈሮችን መቅሰፍቶችን በሚሰድበት ግዜ ለማስቆም መፍትሄው ንስሐ መሆኑን መጻሕፍ ቅዱስ ግልፅ አድርጎታል ።
#የንስሐ #ጸሎት: በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ እኛ ሁላችንም በፊትህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እና በደሙ ስር እንቀርባለን መንፈሳዊው የመናፍስት አባት በሰማያት የምትኖር ጻድቅ አባታችን ሆይ አንተ ትክክል ጽድቅህም ለዘላለም ነውና ስለ ሁሉ እናመሰግንሃለን። ጻድቅ አባት ሆይ ቅዱስ ስምህንም ከፍፍ እናደርጋለን። በምድር ላይ ልትፈርድ መጥተሃልና ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት እየፈረድክ ነውና ስለ ጻድቅ፤ እውነትና ቅን ፍርዶችህ እናመሰግንሃለን ፡፡ ፍርድህን በከፊል ወደ ምድር በዚህ መልኩ አምጥከልና የዓለም ሕዝቦች በዚህም ጽድቅን ይማራሉ ልባቸውም አንተን ይማጸን ዘንድ ያዘምማል። በሰማይም በምድርም የሁሉም ነገሮች ወራሽ የሆንክ የነገስታቶች ንጉስ የጌቶች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አንተ ብቻ ለሆንከው በፊትህ እራሳችንን ትሁታን እናደርጋለን ፡፡
አቤቱ ፣ ጌታ ሆይ ፣ ለሚወዱህ እና ትእዛዛትህን ለሚጠብቁ ቃል ኪዳንህን እና ፍቅርህን የሚጠብቅ ምህረትን ይማትነፍግ ታላቅ እና አስፈሪ አምላክ ሆይ ፣ አንተን መፍራት ከብዝዎች ተሰውረዋል፤ ኃጢአት ሠርተናል ፣ ዓመፅም አደረግን ፣ ደግሞም ከትእዛዛትህ እና ከፍርድህ ፈቀቅ ብለናል። ደግሞም እኛ አገልጋዮችህ ቃልህን በአጽናኦት አልሰማንም አለቆቻችንም አባቶቻችንም የአገሩም ሕዝብ ሁሉ አንተን ከመፍራት ይልቅ ዝንጉነት በርትቶባቸዋል።

አቤቱ እፍረት ሲያንስብን ነው። አንተ ብቻ የፈጠርከውን መንገድህን ትተን በመንታ መንገድ በመንታ ምላስ ፈቃድህን ጥሰናል ፡፡ ሽማግሌዎቻችን ሳይቀሩ ቀለዋል። ሁሉ አንተን መፍራት ዘንግተዋል በአንድነትም አምጽዋል አፍረትም የለም። ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ ከደቂቅ እስከ ሊቁ ምንጩ ተበርዘዋል ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውኃ ያመነጫል። በለስ ወይራን ወይን በለስን ልታፈራ ትችላለችን? ከጨው ውኃም ጣፋጭ ውኃ አይወጣምና ከህይወት ውሃ ምንጫችን ብቻ ጠትተን እንድንፈወስ ማረን።
ስለዚህም ምክኛት በአንተ ላይ በስውርና በግልጥ ህዝብህ ዓምፀናል እንዲሁም ቃልህን አልታዘዝንም ወንድም ወንዱሙን ይዘረጥጣል ታናሽ ታላቁን ያንጋጥትጣል ፍርድ ተዛብተዋል ዘረኝነት መራራ ስር ሰደዋል ገንዘብ አንተን ተክቶ በሰዎች ልብ የክፋት ሁሉ ደም ስር አብቅልውዋል ስንቱን ዘርዝረን ንስሃ እንግባ በፊትህ ሁሉ እርቃኑን የተገለጠ ነውና አባት ሆይ ማረን። እንዲሁም በቃልህ በፊታችን ባስቀመጥሃቸው ትምህርቶች ውስጥ ስላልሄድን አንተ ብቻ ርህራሄና ይቅርታን የመስጠት መብትና በጎ ፈቃድ እንዳለህ ልጆችህ ጠንቅቀን እናውቃለን ስለብዝዎችም በፊትህ እራሳችንን እናዋርዳለን።

ጽዋው ስለሞላ ከረጅሙ ትግስትህ ቡሃላ ጥፋትንና መቅሠፍት አከማችተህ በስጋ ልለባሽ ላይ የመከራ ስጋትን አመጣህብን ፤ ስላደረግኸው ነገር ሁሉ ጻድቅ ነህ ፤ ነገር ግን ቃልህን አልሰማንም። ሰዎች የሠሩትን ክፋት እንዲያዩና ከእኛ ጋር ንስሐ እንዲገቡ ልባችንን አዙር የሰዎችህን ዓይኖች ክፈት። በሕጎችህ እና በተፈጥሮህ መሠረት ወደ አዲስ አቅጣጫ እንሂድ ከስጋ ደካም ወደ መንፈስ ብርታት ዘውር አድርገን፡፡ ከእንግዲህ በዙሪያችን ላሉት ሁሉ ነቀፋ አይሁንብን ፡፡

አቤቱ ፥ እንደ ጻድቅ ሥራህ ሁሉ እንዲሁ ወሰን እንደሌለው እንደ ምህረትህ ባለጠግነት ብዛት ቁጣህ ከሕዝብህ ይራቅ። የሰማይ አባት ሆይ ፣ የልጆችህ የአገልጋዮችህን ጸሎቶች እና ልመናቸውን አዳምጥ ፣ እናም ፊትህ በፊታችን ያብራ ፣ በሙሴ እና በኢየሱስ ፊት ላይ እንዳበራ እንደ ገና ጸጋህ በፊትችን ላይ ወገግ ብሎ ያብራ ፡፡ ጆሮችህ እና ልብህ ወደ እኛ ያዙሩ እኛ በፊትህ የምናቀርበው ጸሎታችንን የምናቀርበው በእኛ ምክንያት አይደለም ፣ ነገር ግን በክርስቶስ ካለን የልጅነት ክብር ስጦታ ከታላቅ ርህራሄህ የተነሳ ነው።

ጸሎታችንን ስለሰማሃን እና ለእኛ ላሳየከው ታላቅ ፍቅርህ ተባረክ። አንተ ታላቅ ነህ ማንንም ግን አትንቅም መልስ ስለሰጠህን እናመሰግናለን ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እና ተፈጥሮ ፀልየናል። አሜን!!! “በእግዚአብሔር የተሰጡ ተስፋዎች ሁሉ፣ “እግዚአብሔር ታማኝ እንደሆነ ሁሉ፣ ለእናንተ የምንናገረው ቃላችን፣ “አዎን” እና “አይደለም” ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም እኔም ሆንሁ ሲላስና ጢሞቴዎስ፣ እኛ የሰበክንላችሁ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ “አዎን” እና “አይደለም” አልነበረም፤ ነገር ግን በእርሱ ዘወትር፣ “አዎን” ነው። አዎን” የሚሆኑት በእርሱ ነውና፤ እኛም በእርሱ አማካይነት ለእግዚአብሔር ክብር፣ “አሜን” የምንለው በዚህ ምክንያት ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡18-20” ወንድም ቢኒ።22You, Bele Melaku, Demis Nida and 19 others1 Comment7 Shares

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal