
Binyam TA
ከውይይት የተጠቀሰ፤ Tëmïñã Bœrñ Ãgåíñ ክፍል ሁለት፤ ሰላም ወንድማችን፤ እኔ ብዙም መከራከር አይመቸኝም የተቆረስልህን የህይወት እንጀራ ክርስቶስን ተካፍሎ መብላት እንጂ፤ ስለዚህ ያለኝን ህይወትን ከመከፋፈል አንጻር ነው የምጽፈው። “ከጥንት ጀምሮ የተናገረው ማን እንደሆነ ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት በቂ ማስረጃ ነው” ላልከው ማጥናት አንዱ ክፍል ነው ሆኖም እውነቱ ምንም ብንተጋና ብናጠና መንፈሳዊ ነገር የእውነት መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ እስካልመራህ ድረስ በትምህርት ብቻ ጥሩ ባለአይምሮ የሸመደደ ቲዮሌጅያን ይወጣህ ይሆናል እንጂ ምንም ብንወለድም በመንፈስ ምሪት እየታገዝን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እናድግ ዘንድ በመንፈስ ካልተመራን ልጅነት ሊያገኝ የተገባው መንፈሳዊ የእድገት ምሪት ጋር እንተላለፋለን። ካለ እ/ር መንፈስ ምሪት ልጅነት የለምና። “በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። መንፈሳዊውን ነገር ባለ አእምሮ ሆነን ሳይሆን መንፈሳዊያን ሆነን እንድናየው በጌታ ፍቅር እጠይቃለሁ የክርስቶስ አእምሮ ከተፈጥራዊው አእምሮ ይበልጣልና መንፈሳዊ ነገር ለፍጥረታዊው ሰው የተከለከለ የተከደነ መሆኑንም አንዘንጋና። We all knows we are established by revelation not by education alone! The Holy Spirit will lead and teach us ALL things (John 14:26and His Word is spiritual and much higher than the natural, letter word. The Living Word, Jesus, said, ‘My words are spirit and they are life John 6: 63 to be carnally minded is death or alienated from the truth; but to be spiritually minded is to be one with life and peace. carnal mind person still think heaven is a piece of real estate “out there” in space somewhere, rather than within his own thinking (within his heart and mind – i.e. – a state of being), it’s clear his road to enlightenment has reached an impasse which requires a total paradigm shift in his thinking.
አንተ ስትናገር “ምን አልባት ሌላ አካል አለ ማለት ሞኝነት ወይንም ለአዕምሮ የማይመች ስለሆነ አልተቀበልከውም።” ብለከኛል ሌላ አካል የሚለውን ከየት እንዳመጣከው አላውቅም። ስለ መንፈሳዊው ነገር አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለና። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡4 እግዚአብሔር አንድ አምላክ ነው ወይስ ሁለት ወይስ ስላሴ[ሶስት] ወይስ ሁለት አካል? እ/ር አንድ ነው! ወደ ዘመናይ ክርስትና ስትመጣ አ2 እና 3 ያደርጉታል እንጂ ከጥንትም አንድ ነው። ፡ኦሪት ዘዳግም 6፡4 እስራኤል ሆይ፥ #ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር #አንድ እግዚአብሔር ነው” ከመስማት ይጀምራል። “መንፈስ አንድ ነው፤1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡4”
በአመክንዮ(Logic) ከሆነ መንፈሳዊው ነገር ከምክንያት በላይ ግዙፍ ነው የሆነ ቦታላይ ይሰወራል። ሌላ አካል አልክ? እሺ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በብፅዕት ድንግል ማርያም ማህፀን #የተረገዘው( CONCEIVED by the Holy Spirit.) በመንፈስ ቅዱስ መፅለል ነበር። እንደ ምናስተውለው መንፈስ ቅዱስ ለእርግዝናዋ ምክንያት ነው። እየሱስም ተወለደ ያስረገዛት መንፈስ ቅዱስ ቢሆንም የመንፈስ ቅዱስ ልጅ ግን አልተባለም አልነበረምም ነገር ግን የአባት(አብ) ልጅ ነው።”the Son of the FATHER” (II John 2:3 ያስረገዛት መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው እንጂ ከ2ቱ አካል አንዱ ወይም ከ3ቱ ስላሴዋች አንዱ አይደለም ቢሆን ኖሮ እርሱ ባስረገዘ ሌላ አባት ባልተባለ። እንደ የስላሴ አፈ ታሪክ ቲፎዞዋች አባባል መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ስብእና ለብቻው ያለው ቢሆን ኖሮ ወይም ከ3ቱ ስላሴዋች አንዱ ቢሆን ኖሮ መንፈስ ቅዱስ አባቱ በተባለ ነበር እንጂ ሌላ ጣልቃ የገባ መለኮት አብ የተባለ በጉልበት አባቱ ባልሆነ።
Even any simple minded person can understand that whoever conceives a child in a mother’s womb is the biological F-A-T-H-E-R OF THAT CHILD when it is born, NOT SOME OTHER PERSON or member of Trinity. የማይታየው አብ በብሉይ ኪዳንም ቢሆን አንድም ቦታ እንዳልተገለጠ እናስተውል። በብሉይም ሆነ በአዲስ ያህዌም ሆነ ኢየሱሱ የአብ ብቸኛው የመጨረጫው ልናየው የምንችልበት የመገለጥ መንገድ እንደሆነ ፍንትው ብሎ ልናየው ይገባል። የአብ ባህርይ አይታይም። አብ ድምፁ ከቶ አይሰማም፥ መልኩም አይታይም፤ የአብ ድምፁ የሚሰማው፥ መልኩም የሚታየው በቡሉይ በያህዌ አዶናይ ወዘተ.. ሲሆን በአዲስ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው[በአካሉ በክርስቶስም አክልበት]፤ ኢየሱስ በድፍረት መጽሃፍት ሁሉ ስለኔ ተጽፈዋል ሲል ምን ማለት ነው? መቼም ከሱ ይልቅ እውነት ለአሳር ነውና። ከአብርሃም በፊት እኔ ነኝ ምን ማለት ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትናም ዛሬም ነገም ህያው ነው ማለት ምን ማለት ነው? ወዘተ … መቼም እውነት ኢየሱስ ነው አይደል? ይህን እውነት አስተውል። በቡልይ ኪዳን[ከኦሪት ዘፍጥረ እስከ ትንቢተ ሚልክያስ] “(የአብን …#ድምፁንም #ከቶ #አልሰማችሁም፥ #መልኩንም #አላያችሁም፤ ዮሐንስ 5:37)” አገኘከው? Did You observe it Bro.? ተጨማሪ በመጀመሪያው ቃል ከነበረው ኢየሱስ ምን እንዳለ እናስተውል፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡18 “#መቼም #ቢሆን #[አብን፤ መንፈስን]እግዚአብሔርን #ያየው #አንድ ስንኳ #የለም፤” ።ማለትም በቡልይ ኪዳን[ከኦሪት ዘፍጥረ እስከ ትንቢተ ሚልክያስ] አብ አልታየም። በመረዳት እየተነጠክ ነው? ፡) ቃሉም እግዚአብሔር አብ በማንኛውም ጊዜ ለማንም ሰው በቀጥታ አልተናገረም (ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፥ መልኩንም አላያችሁም፤ ዮሐንስ 5:37), እነ ሙሴ፤ አብርሃም ወዘተ የተገለጠላቸው የማይታየው የአብ መገለጥ ያህዌ ነው። የአባትነት ክብር ከያህዌ/ኢየሱስ ልጁ ዘንድ ትእዛዝ አይወስድም እውነት ነው። ኢየሱስ በአጭሩ የአብ ፍጹም ፈቃድ መገለጥ ነውና የፈቃድ ልዮነት የለም፤ የአብ[የመንፈስ] ቃል፤ የአብ[የመንፈስ] ሃሳብ፤ የአብ ጥበብ፤ የአብ ሃይል፤ የአብ ክብር ክርስቶስ መሆኑ ግልጽ ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ መንፈስ የሆነው የመናፍስት አባት የአብ ሁለንተና ለፍጥረታዊው አእምሮ ይታይ ዘንድ የመንፈስ ወይም የማይታየው ሃይል ሙሉ ክብር መገለጥ ነውና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡24 የአብ ኃይልና የአብ ጥበብ ክርስቶስ ነው። የአብን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ? ምን ማለቱ ነው? መጻሕፍት ስለማን ይናገራሉ *መጻሕፍትንና [የዮሐንስ ወንጌል 5፡39 በመጻሕፍት … ስለ እኔ(ኢየሱስ ክርስቶስ ) የሚመሰክሩ ናቸው። *የአብን ኃይል[የአብ ኃይል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው] አታውቁምና ትስታላችሁ።የማቴዎስ ወንጌል 22፡29
አንተ እንዳልከው [ከቃል ወደ መንፈስነት የቀየረው።] ብለካል እውነቱ ቃል ወደ መንፈስነት አልተቀየረም ቃል መንፈስ ነውን። “ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።የዮሐንስ ወንጌል 6፡63” እንዳንረሳ ሕይወትን የሚሰጥ #መንፈስ ክርስቶስ እራሱ መሆኑንን። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡45 ሌላው ያነሳከው ሃሳብ [መጽሐፍ ሲናገር “ቃል ሥጋ ለበሰ” አይልም፤ “ቃል ሥጋ ሆነ”] የሚል ነው ለበሰ የሚለው ላይ ለምን እንዳተኮርክ ባላውቅም እውነት ነው ቃልም ስጋ ሆነ ስጋ ሆኖ ግን በዛው አልቀረም አንዘንጋ ይህ መንፈሳዊ ነገር ነው። ስጋ ሲሆን የመጨረሻው አዳም ሆነ ይህ ቃል ሥጋ ቢሆንም ሕይወትን የሚሰጥ #መንፈስ ሆነዋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡45 ለመሆኑ በስጋ እዚህ እየታየ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው ሲል ምን ማለቱ ነው?። የሚኖረው በሰማይ[በመንፈሳዊው ግዛት] ነው? እንካን እሱ እኔ እና አንተ በዚህ መንፈሳዊ በር በዙፋኑ ፊት ነቀፋ-አልባ ሆነን መግባት መውጣት መሰማራት እንዲሆንልን በጌታ ተደርገናል። የዮሐንስ ወንጌል 10፡9
እውነቱ የማቴዎስ ወንጌል 11፡27 ከአብ[ከመንፈስ] በቀር ወልድን ማን እንደሆነ የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን[መንፈስን] የሚያውቅ የለም። ወልድም ሊገለጥለት ለፈቀደው ይህን ያስተውል ዘንድ መንፈሱ ለነቃው በሰማያት ያለው አባት[መንፈስ] እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ[ደስተኛ] ነህ ልንለው እንችላለን። ለባለአእምሮው ደግሞ እንዲህ ነው “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡14 ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።” በመንፈስ ካለማወቅ ካለ መቀበል የለም። ይህን እንዳንረሳ አብ በራሱ ተገልጦ አያውቅም። የአብ[የማይታይ] እንዲገባን የመታየቱ መገለጦች እዚህ መልክ እናስቀምጣውና በአሮጌው ኪዳን ብዙ ቢሆንም ከብዙ በጥቂቱ አዶናይ: ጌታ እግዚአብሔር Adonai: Lord God፤ በያህዌ Yōd, Hē, Vav, Yahweh: God፤ አዶናይ፤ ኤልሻዳይ ሁሉን ቻይ አምላክ El Shaddai: God Almigh[The all sufficient God of the Mighty #Breasted One] ። ኤል ሮይ: የሚያየኝ አምላክ፤ ያህዌ: እግዚአብሔር ያዘጋጀል Yahweh Yireh: God Provides፤ ወዘተ….. “(የአብን …#ድምፁንም #ከቶ #አልሰማችሁም፥ #መልኩንም #አላያችሁም፤ ዮሐንስ 5:37)”
ክርስቶስ ልጆች እንዴት ለእ/ር ለመንፈሳዊ አባታችን ህያዋን እንድንሆን እያሰለጠነን እንደሆነ አንዘንጋ። በበሰሉት መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን ነገር ግን የዚችን ዓለም ጥበብ አይደለም ተብሎ እንደተጻፈ እንደ መንፈሳዊያን እንነጋገርና ለመሆኑ እርሱ እንደተመላለሰ እኛም እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና የክርስቶስ አእምሮ መያዝ በጥቂቱም ቢሆን ምን ማለት ነው? ከስጋዊ አእምሮ ወደ መንፈሳዊ አእምሮ ሽግግር ነው። ለውጡ ለአንዱ አለም ሞቶ ለሌላኛው ከፍ ላለው መንፈሳዊ ግዛት ህያው መሆን ነው። ለእ/ር ከሞተው የአዳም ንቃተ ህሊና ለእ/ር ህያው ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ንቃተ ህሊና መነሳት መነጠቅ ነው። ጌታ እየሱስ በስጋ በምድር እያለ የሰው ልጅ የሚኖረው በሰማይ[መመንፈስ ግዛት] ነው ይላቸው ነበር። የክርስቶስ ንቃተ ህሊና የሚያድረው በሰማይ[በመንፈስ ግዛት] ነው። ሃሌሉያ! የዮሐንስ ወንጌል 3:13 ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። ልጅነት እንዲህ ነው ሁለት እግሩ በምድር ቆሞ የሰው ልጅ በመንፈስ አሁን ተነጥቆ የሚኖረው በሰማይ[ the One continuously being (constantly existing) within the heaven] ነው ብሎ እርፍ! “And no one has ascended (stepped up) into the heaven, except the One descending (stepping down) from out of the midst of the heaven: the Son of Mankind (the Son of the human; Humanity’s Son; the Son of man) – the One continuously being (constantly existing) within the heaven . John 3:13
ጌታ እየሱስ እውነት ከሆነ ወሸታም ማነው? ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3/18 …በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥ የሞተው ስጋው እንጂ መንፈስ አይሞትምና በመንፈሱ አልሞተም። በመንፈስ ህያው እስከሆነ ድረስ ስጋውን ማስነሳት ችለዋል። በመንፈስ ህያው እስከሆነ ድረስ ሥጋው በተስፋ አድራል፤ ነፍሱንምን በሲኦል አልተዋትም፥ ቅዱስህንም በስጋው መበስበስን ያይ ዘንድ አልሰጠውም ። በመንፈስ ህያው የሆነው በአብ ክብሩ በስጋ ውስጥ ሆኖ እንደ ተናገረ አደረገው ‘…….እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ” ለመሆኑ እየሱስ ክርስቶስ ስጋ ውስጥ ያለው በውስጡ የሚኖረው ማነው? “በእኔ የሚኖረው አብ ነው!”
ኢየሱስ ያህዌ ነው! እየሱስ ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው!
ጌታ እየሱስ በምን ስልጣን ነበር የተራራው ስብከት ተብሎ በሚታወቀው በማቲዮስ 5-7 ትምህርቱላይ የፍቺውን ትክክለኛ ትርጉም ሲያርም የነበረው?
ሐዋርያው ጳውሎስ ሲነግረን ስለዚህ በፊት ክርስቶስን በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም፡ ከዚህ ቡሃላ መንፈስ ሆነዋልና። ብሎ ናል ።“ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/45” “ ጌታ ግን መንፈስ ነው[ Now the Lord is that Spirit:]፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3/17” [2Cor 3/17 Now the Lord is that Spirit: and where the Spirit of the Lord is, there is liberty.]
እየሱስ ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው! ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በስጋ የመጣው ወደ መንፈስ ሊመራን ነው። በመጀመሪያው ቃል እንደ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር እንደነበረ። ቃልም ሥጋ ሆኖ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ እንደመጣ የማያምን ሁሉ ሃሰተኛ መንፈስ ነው የክርስቶስ ተቃዋሚውም መንፈስ ነው፤ ። ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ነው።
“1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4/2 የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥3 ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።”
*እየሱስ ፈጣሪም ነው ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰውም ያህዌ እሱ ነው! ይህንን እውነት ለማስተዋል በቀደሙት ክፍሎች በብዙ አይተነዋል እንዲሁም እያንዳንዱን መጽሐፍት ብትመረምሩ ጌታን በዛ ውስጥ ታገኙታላችሁ። የእብራይስጥ ቋንቋ እራሱ ይህንን እውነት ያረጋግጠዋል። አንድ የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋ ማንም መረዳቱ የተሰጠውና ቃሉን የሚያጠና ሊቅ ሁሉ ሊያውቀው የተገባ ነው። “የእብራይስጥ ቋንቋ በአብዛኛው የአንድ ቃል ፍቺ ሃብታም ከመሆኑ የተነሳ ከአንድ በላይ ደራርቦ ሃሳብን ሊያሳይ ይችላል። የእብራይስጥ ቋንቋ ቃላት ስእላዊ ገላጭ ያለውና የድምጽ ገላጭም አጣምሮ የያዘ ሊሆንም ይችላል፡፡
ለምሳሌ ሁሉም ፈደሎች ቁጥርም ናቸው ቃላትም ናቸው። ለምሳሌ “alef” የመጀመርያው ፊደል ነው ያው ፊደል የመጀመርያው ቁጥር አንድ ማለትም ነው። “alef” የሚለው ያው ቃል በሬ ማለት ሲሆን ስእላዊ ገላጩም ጥንካሬን፤ ብርታትን [ymbolizes, strength] የሚያመለክት ነው። ሁለተኛው “beth” ቁጥር ሁለት ነው። “beth” የሚለው ቃል እራሱ ቤት ፤ቤተ ሰዎችና ፤ቤተሰቦችን [house or household] ያካተተ ፍቺ አለው።
በእብራይስጥ ቋንቋ ህግ ማለት Torah ነው። በእብራይስጥና ቋንቋ ቶራ[ Torah] ሲፃፍ tav-vav-resh-hey ሆኖ ይፃፋል። ይህ ከተያያዛበት ለየብቻው ቃሉ ሲተረጎም Tav ማለት ምልክት ወይም መስቀል ማለት “a mark or sign” [of the cross] ሲሆን። በዋናው በመጀመርያው ጥናታዊ ያልተበረዘ በእብራይስጥ ቋንቋ “መስቀል” ተብሎ ነበር የተፃፈው። በዘመናይ በእብራይስጥና ቋንቋ ተለይቶ ይገኛን። ይህም የሆነው በባቢሎን 70 አመት ምርኮ ጊዜ የባህል ወረራ ስለደረሰ ከአረሚክ ቋንቋ ጋር ተዳቅሎ ተበረዘ።
ሁለተኛው “vav” የሚለው በግልጽ ትርጉሙ እንደ አገባቡ የተሰቀለው፤በሚስማር
፤የተጠረቀመው፤የተቸከለው “a nail or peg.” ሲሆን ሶስተኛው “resh” የሚለው በግልጽ መሪ ወይም ራስ “a head, or leader.” ማለት ነው። በመጨረሻም “hey” በቃሉ መጨረሻ ሲቀመት ትርጉሙ ከሱ ወይ ከዛ የወጣ የተገኘ ማለት ነው። “what comes from.”
በእብራይስጥና ቋንቋ ህግ ማለትም Torah ከሚለው ቃል ፍቺ እምናስተውለው በመስቀል ላይ ከተሰቀለው መሪ ወይም ራስ የተገኘ “what – comes – from – the – Leader- nailed- to- the – Cross” ማለት ነው ። በሌላ አነጋገር እየሱስ ህግን የሰጠውና በመስቀል ላይ የተሰቀለው መሪ ወይም ራስ እሱ መሆኑን በዚህ ታላቅ ሚስጥር ውስጥ የእ/ር ድንቅ ስራ ይስተዋላል።
ጌታ እየሱስ ከስጋ ወደ መንፈስ ሊመራን ነው የመጣው። “2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡16 … ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።” አዎን ቃል ስጋ ሆኖ 33 ½ አመት በስጋ ውስጥ ተዎስኖ በሚመስልም ህይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነበረ:: “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡45 …ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።” ደግሞም ከሰማያት ሁሉ በላይ አልፎ ሁሉን ሞልቶታል በስጋ ተወስኖ ሁሉ መሙላት አይችልም ወደ መንፈስ ክብሩ ተመልሶ እንጂ። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡10 ይህ የወረደው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው። ሰላም ሁኑልኝ ። ወንድም ቢኒ።3You, Mulugeta Shiferaw and Demeke Abebayehu1 Comment3 SharesWowCommentShare