
(1) Binyam TA – ጥያቄና/መልስ፤ ሰይጣን ይታረቃልን?፡ Melaku Mulu እና Terefe Bekele…
Binyam TA
February 19 at 1:45 AM · checkmarkcaution-solid
ጥያቄና/መልስ፤ ሰይጣን ይታረቃልን?፡ Melaku Mulu እና Terefe Bekele ሰላም ወንድሞች፤ ለጥቅማችን መልሱን በቀጥታ ከማካፋሌ በፊት የገባኝን ስለመንፈሳዊ ነገር ባስቀድም መልካም ነገር ይቀርላችሃል ብየ አሰብኩ። ከብዙ ወገኖቼ ጋር ውይይት ጀምሬ ሞከደኛ ከሆኑ ጥቂት ወገኖች በቀር መንፈሳዊውን ነገር በሙላት መወያየት ብዙውን ግዜ ከተወሰነ ርቀት በላይ መሄድ ለብዙዎች ጭንቅ ስለሆነ ከብዝዎች ጋር መወያየት አልተቻለም። ለመንፈሳዊ ሰው ሁሉም ነገር መንፈሳዊ ነው ለተፈጥራዊው ሰው ሁሉም ነገር ተፈጥራዊ ነው ሆኖም ብዙ ወገኖችን በክርስቶስ ገና ሕፃናት እንደመሆናቸው እንደ ተፈጥራዊያን እንጂ እንደ መንፈሳውያን መንፈሳዊውን ነገር መወያየት አልተቻለም መንፈሳዊውን ነገር ተፈጥራዊ አድርጎ ለማየት እንደጉጉት ወፍ አይናቸው ትልቅ ነውና። በኛ ዘመንም ከክርስቶስ አእምሮ ጋር ያለው መላተም አሁንም በግልጽ እየተለማመድነው ነው። ስለመንፈሳዊው እውነታ ሲነገር እንደ ወንድማችን ኒቆዲሞስ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ማለት አልቆመም። ትላንትም ዛሬም ነገም ያው የሆነው ክርስቶስ ዛሬም መልሱ ያው ነው እርሱ አይለወጥምና። “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን? እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም። ስለ ምድራዊ(ተፈጥራዊው) ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ(መንፈሳዊው) ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?”
ለጥቅማችን ላክልበትና በቅድሚያ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአገልግሎቱ ሁሉ መንፈሳዊውን በተፈጥራዊ ቋንቋ በምሳሌ ማስተማሩ ማወቅ በራሱ በረከት ነው። “የማቴዎስ ወንጌል13/34-35 ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤በነቢዩም፦ #በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ #ሰወረውንም #እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።” ይህንንም በነብዩ ዳዊት ላይ ሆኖ መንፈስ በመዝሙር 77/2 ላይ አስቀድሞ ተናግሮት ነበረ በኢሳያስም እዲሁ። እንደ ምናስተውለው ትንቢቱ ፍፃሜ ያገኘው ጌታ ያለ ምሳሌ ስላስተማረ ነው።
በዚህም መሰረት ጌታ ከ 41 በላይ ምሳሌዎችን ተናግረዋል የዘልአለም ስቃይ ሰባኪዎች ግን ነጥለው እውነተኛ ታሪክ ነው የሚሉት የሃብታሙ ሰውና አልአዛር ምሳሌን ነው።
ጌታ ከተናገራቸው ምሳሌዎች ለማስታወስ ያህል። ከእንቅብ በታች ያለ መብራት፤ የሰናፍጭ ቅንጣት፤ ልባምና ሰነፍ አናፂዎች፤ በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ እራፊ፤ በአረጀ አቅማዳ ላይ አዲስ ወይን፤ ዘሪና የመሬት አይነቶች፤ የተሸሸገ እርሾ ፤ በባህር ላይ የተጣለ መረብ፤ የጠፋ በግ፤ምህረት የማያደርግ ባርያ፤ አስሩ ቆነጃጅት፤ በጎችና ፍየሎች፤ ደጉ ሳምራዊ፤ የጠፋ ድሪም፤ ወዘተ…… ዶክትሪናቸውን ለማጽደቅ ሁሉም የዘልአለም ስቃይ ሰባኪዎች ነጥለው መንፈታዊውን ወደተፈጥራዊነት የሚከረብቱና እውነተኛ ታሪክ ነው ብለው የሙጭኝ የሚሉት መካከል የሃብታሙ ሰውና አልአዛርን ምሳሌን ነው ወዘተ… ይህ ምንኛ ተፈጥራዊው አእምሮ የክርስቶስ ተቃዋሚ መሆኑን ያሳየናል።
እውነታው ግን ጌታ ከ 41 በላይ ምሳሌዎችን ተናግረዋል አንዳቸውም በእውን የተፈፅሙ የተከሰቱ ታሪኮች አልነበሩም። ተምሳሌትን ምሳሌነቱን ትተን ወደ እውነተኛ ታሪክ ስንከረብተው ወይም ስንገለብጠው ተምሳሌነቱ ይጠፋል።ሁላችንም እንደምናውቀው ምሳሌ ወይም ተምሳሌት የሚነገረው በጥሬው ካለው ትርጉሙ ውጪ ሌላ ነገርን የሚወክል ቃል ወይም ሃረግ ነው። ለምሳሌ አንበሳ የጀግና ምሳሌ ነው፤ በግ/እርግብ የየዋህነት የንጽህና ምሳሌ ነው። እባብ የተንኮለኛና የመርዛማ፤ የአሾክሻኪ ባህርይ ምሳሌ ነው። በተፃራሪው ታሪክ ማለት ደግሞ ባለፉት ዘመናት እውን የነበሩ ክስተቶች ትውፊት፤ የሚዘገብ ክንዋኔ፤ ለምሳሌ ቀድሞ የነበረ ወግ፤ ጀብድ፤ ጀግንነት፤ የሃገር ኩራት፤ ወዘተ….ማንኛውም የሚያኮራ ይሁን አሳፋሪ ክስተት ሁሉ በዘመኑ ባለ ትውልድ እንደ “ነበረ” የሚታሰብና የሚነገር የሚዘገብ የአላፊ ጊዜ “ክስተት” ታሪክ ይባላል። ጌታ እየሱስ በየትኛውም ቦታ ለፈሪሳውያን ይሁን ለህዝቡ ሲያስተምር ያለ ምሳሌ ሲያስተምር አታዩም። ምሳሌዎቹ ግን ብዙ ገፅታ ሊያሳዩ ይችላሉ። መሃከሉ መንፈሳዊ እውነታውን የሚያሳይ ሲሆን በተመሳሳይ ግዜ የአላፊ ግዜ ፤ የወቅቱ ሁኔታ ፤ ደግሞም የወደፊቱን የሚያመለክቱ ትንቢታዊ ሊሆኑ ይችላሉ።
እ/ር መንፈሳዊውን እውነት ያስረዳን ዘንድ በዘይቤ metaphor ወይም ዘይቤያዊ አነጋገር፣ ተለዋጭ ተተኪ ቃል፣ ስእላዊ ምትከ ገላጭ ተጠቅሞ እንደሚናገር እናውቃለን(በዘይቤ metaphor ፡ቃል ወይም ሐረግ ቃል በቃል ተፈጻሚ በማይሆንበት ለአንድ ነገር ወይም እርምጃ ላይ የተተገበረበት የንግግር ዘይቤ። a figure of speech in which a word or phrase is applied to an object or action to which it is not literally applicable.) አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከጥንት በነበረ እንቈቅልሽ እናገራለሁ መዝሙረ ዳዊት 78፡2 የማቴዎስ ወንጌል 13፡34-35 ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።” “የዮሐንስ ራእይ 1፡1 ኢየሱስም መልአኩን ልኮ ለአገልጋዩ ለዮሐንስ በምልክት signified ገለጠለት (signified ፡ signified ከሴማ (ምልክት ፣ እርግጠኛው ያልሆነ አቅርቦት); ለማመልከት: – ምልክት ማድረግ። from sema (a mark; of uncertain derivation); to indicate:–signify. KJV: he sent and #signified it by his angel unto his servant John”
ይህን ካስተዋልን መንፈሳዊ እይታ እንዳለው ታውቀዋለህ ያንን አንተና ጌታ ጨርሱት ለውይይት እንዲመቸን ወደ ተፈጥራዊው እይታ ወርደንም ቢሆን እንየውና የሰይጣን አገልጋዮቹ የጽድቅ አገልጋዮች መሆናቸውን እንደ ነገረን አንርሳ። በመጀመሪያ ሰይጣን እና አገልጋዮቹ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም… 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡14-15 ይህ እንግዲህ እያየነው ያለ የወቅቱ የነጣቂዎቹ የባቢሎን ነገስታት ትንንሽ የየራሳቸውን መንግስት መስርተው የእ/ርን ህዝብ በባቢሎን ምርከኛ አድርገ የሚበዘብዙበት ትእይንት አንዱ ገጽታው ነው መንፈሳዊ አመልካች ፍቺው ከአንድ በላይ ሊሆን እንደሚችል አውቃለሁ።
ያ አንዱ ገጽታ ነው የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል ብቻ ሳይሆን ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ ለእርሱ እንደተፈጠሩ አንርሳ። እናስተውል በዛ አላበቃም ሲተነትን በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ #በምድር ወይም #በሰማያት ያሉትን #ሁሉ ለራሱ #እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። የክርስቶስ አእምሮ በማስተዋሉ ፈጣን ለማመን ያልዘገየ ነው። እ/ር አለ ማለት ሆነ ማለት እንደሆነ በአገራችን በአበው አባባል የተበላ እቁብ ነው እንደማለት ነው። እዮብ ቀድሞን አሳብቡ ይከለከል ዘንድ እንደማይቻል በማወቅ ሳይቀድመን አልቀረም ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ስለነበረ በማስተዋል ቢባረክ አይደንቀኝም ለዚህም ይመስለኛል ሰውንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ነው አለው ያለን። “ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። መጽሐፈ ኢዮብ 42፡2”
በምንም መልኩ ፍችውን ወይም ትርጉሙን እንረዳው ያነሳከው ሃሳብ ጋር ለመወያየት ያክል በሰማይ እንደሚኖሩ መገንዘብ አለብን ኤፌ. 6፡ 11፡12 ዲያቢሎስ…… ከፍ ባለው መንፈሳዊ ክፋት ላይ “#የዲያብሎስን የተንኰል ሥራ መቋቋም ትችሉ ዘንድ….ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከሥልጣናትና ከኀይላት እንዲሁም #በሰማያዊ ስፍራ #ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው። the #devil….against spiritual wickedness in #high [GREEK፤ epouranios ፤ celestals፣ #heaven]] እና ምድር (ራዕ. 12፡9) የአንድ ጊዜ ክስተት አይደለም) ፡፡ በነገራችን ላይ በአንድ ሰማይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ሰማዮች ወይም ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርስዋም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ነው ብሎ ቃሉ እንደነገረን አንርሳ ያ ሁሉን ፍጥረት ያጠቃልላል ሰይጣንን ጨምሮ። ኦሪት ዘዳግም 10፡14 ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለ ሥልጣናት፣ #ሁሉም ነገር #በእርሱና #ለእርሱ #ተፈጥሮአል።ቆላስይስ ሰዎች 1፡15-16 የ #ሁሉም ነገር ትርጉም ሁሉም ነው። (ሰማያ አንድ ብቻ አይደለም ሰማያት ይለናልና። … እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ።…..)መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 8፡27 እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም። መዝሙረ ዳዊት 115፡16 የሰማያት ሰማይ ለእግዚአብሔር ነው። መዝሙረ ዳዊት 89፡11 ሰማያት የአንተ ናቸው። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል። ማስተዋል ያለብን በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ ሰይጣንና ጭፍሮቹ ለእርሱ እንደተፈጠሩ አንርሳ። እናስተውል በዛ አላበቃም ሲተነትን በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ #በምድር ወይም #በሰማያት ያሉትን #ሁሉ ለራሱ #እንዲያስታርቅ ሲፈቅድ እናንተ ከሌላ ብሄርተኞች ናችሁና አትታረቁም አላለም እንደሰው በምህረቱ ድሃ ወይም ንፉግ አይደለም በምህረቱ ባለጠጋ ነው።
ሌላው ማስታወስ ካለብን አንዱ። “ስለዚህ እግዚአብሔር እጅግ ከፍ አደረገው፤ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው፤ ይኸውም በሰማይና those in HEAVEN በምድር those in EARTH፣ ከምድርም በታች those UNDER THE EARTH፣ ጒልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው confess that Jesus Christ IS LORD ።”(ቆላ. 2 9-11)። አንድ ነገር ያወቅነው በሰማይና those in HEAVEN በምድር those in EARTH፣ ከምድርም በታች those UNDER THE EARTH እነዚ የሚታዩና የማታዩ ፍጥረታቱ ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ መለኮት መበየኑን እናውቃለን። ሆኖም
[5] “#ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ ሥር እስከሚያደርግ ድረስ እርሱ [ጌታ ኢየሱስ] ይገዛል For He [Lord Jesus] must reign till He has put ALL ENEMIES (ሰይጣን ጠላት ነው (ጠላት ዲያብሎስ ነው ማቴ. 13፡39 Satan is an enemy]) ከእግሮቹ በታች … እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆናል (እነሆ ሁሉንም የእግዚአብሔር ፍጥረታት የሚያካትት ነው]” (1 ኛ ቆሮ. 15፡25 እና 28)፡፡
ከዚያም ግዛትን፣ ሥልጣንና ኀይልን ሁሉ ከደመሰሰ በኋላ መንግሥትን ለእግዚአብሔር አብ ሲያስረክብ፣ ያን ጊዜ ፍጻሜ ይሆናል። 25ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ ሥር እስከሚያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና። 26የሚደመሰሰውም የመጨረሻው ጠላት ሞት ነው፤ 27“ሁሉን ነገር ከእግሩ ሥር አስገዝቶለታል” ተብሎአልና፤ ነገር ግን፣ ሁሉን ነገር አስገዛለት ሲል፣ ሁሉ ነገር በክርስቶስ ሥር እንዲገዛ ያደረገውን እግዚአብሔርን እንደማይጨምር ግልጽ ነው። 28ሁሉ ከተገዛለት በኋላ እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ እንዲሆን ወልድ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ለእርሱ ይገዛል።
ስለዚህ ጠላቶቹ ሁሉ እነ አጅሬን ጨምሮ ማወቅ ያለብን የእ/ር ታላቅ አሰራር ያካትታቸዋል “ጌታ ጌታየን ሁሉን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው” ማለትም ከእግሩ ስር የሚያመለክተው ሁሉን ከስልጣኑ ስር እስኪ ያደርግለት ድረስ ማለት ነው የሁሉ ትርጉም ደግሞ ሁሉ ነው።
በጎ የተባለው ያሰበው የፈቃዱም ምስጥር ደግሞ ነግሮናል እ/ር አሰበ፤ተለመ፤አቀደ፤ነደፈ፤አጀንዳ ያዘ፤ቀንም ቀጠረ ማለት ያለጠርጣራው ቶማስ ባህርይ ስሳያዩ የሚያምኑ ብፁአን(ደስተኛች) ናቸው ሆነ ማለት መሆኑን ያስተውላሉና። “ኤፌ1/9 በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤10 በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።” ከመጠቅለል ማን ያስቆመዋል ቲዮሌጅያን የስነ፟መለኮት ቡዱኖች? አይመስልም አለ ወዳጆ አርበኛው።
በነገራችን ላይ “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/3 ….በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ። 1Cor 12/3 ….that no man can say that Jesus is the Lord, but by the Holy Ghost” እናስተውል በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቆናል አሁን ጠላቶቹ የሆኑት አድስዋቸው ከክርስቶስ ስልጣን ስር ሲጠቀለሉ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ሆነው ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ ለበጉ ክብርን ተንበርክከው ይሰጣሉ። “የዮሐንስ ራእይ 5/13 በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ። Rev 5/13 And every creature which is in heaven, and on the earth, and under the earth, and such as are in the sea, and all that are in them, heard I saying, Blessing, and honour, and glory, and power, be unto him that sitteth upon the throne, and unto the Lamb for ever and ever.” ሞት በህይወት ይዋጣል፤ ጨለማ ብርሃን እሳቱ ነው በብርሃን ይበላል፤ጥላቻ በፍቅር ይዋጣል ወዘተ… እንግዲህ የመጨረሻው ጠላይ ሞት ከነ መውጊያው ከሃጥያት ጭምር ሲደመሰስ እ/ርም እራሱን ለፍጡራኑ ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ሆኖ እያለቀሰ በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ። እንዳለን አንርሳ በመንፈስ ቅዱስም ሆነው እየሱስ ጌታ ነው! በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን! ይላሉ። ወንድም ቢኒ። አሜን!!!5You, Hailegiorgis Tefera, Bele Melaku and 2 others4 Comments4 SharesWowCommentShare
Comments
- Binyam TA የውይይቱ ሊንክ፤ https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=2766723686746905&id=100002279031400Edit or delete this
- Mulugeta Shiferaw በልክ በተሰራ ቀጸላ ሰው ሰውነቱን አይሸፍንም ። የጸጋው ቃል በተውሶ መነጽር የሚታይ ከሆነ አንዱ ጎልቶ ሌላው አንሶ ይነበባል ።
አጋንንትም እግዚአብሔርን ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል…
(ያዕቆብ 2 : 19)
አጋንንት በስራቸው ጌታን ይክዱታል !
ለብዙዎች ጥያቄ የዚህ ክህደት መጨረሻው ተገልጿል ።
በሚመጡት ዘመናት ( አዮንስ ) የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ በሰማይና በምድር ያሉት በክርስቶስ ይጠቀለላሉ።
በሚመጡት ዘመናት (አዮንስ) ! ይህ ትልቅ መልክት ሆኖ ለልባችን የቀረ እውነት ክርስቶስ ሁሉን በሁሉ መሆኑ ነው ። በዚህ ዘመን ( አዮን ) የተከፈለ የሚመስለው …. : የክርስቶስ ማዳን በሚመጡ ዘመናት ( አዮንስ ) በሰማይና በምድር ያለውን በመጠቅለል የተጻፈው ይፈጸማል !!
ቤኒ ጌታ ይባርክህ !2Delete or hide this- Binyam TA Mulugeta Shiferaw. ሙሌ የእግዚአብሔር ሰው ብሩክ ነህ።እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው አውሪያዊ ባህርይ ሁሉ ተንኮለኛ more subtle ሲያደርገው በአላማ ነው። ሁሉን በአላማ ፈጠርክ አደል ቃሉ የሚለው። ሁሉ ግዛቱ ነው ማን ይመስለዋል።2Edit or delete this
- Melaku Mulu *የእ/ር ባለጠግነትና ጥበብ እዉቀቱም እንዴት ጥልቅ ነዉ ፡፡ፍርዱ የማይመረመር ለመንገዱም ፍለጋ የለዉም* ሮሜ 11:33; Many thanks bro.for your explanation.2Delete or hide this