የፍጥረት ናፍቆት የእግ/ርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃል የሚለው ሀሳብ ላይ!! ፍጥረት ማነው? ፍጥረት አንበሳና በሬ፣ ሳር ዛፍ ነው? ወይስ የሰው ልጅ?


Binyam TA

December 7, 2019 ·

ከውይይት የተጠቀሰ፤ Demis Nida #ጥያቄ፤ የፍጥረት ናፍቆት የእግ/ርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃል የሚለው ሀሳብ ላይ!! ፍጥረት ማነው?
ፍጥረት አንበሳና በሬ፣ ሳር ዛፍ ነው? ወይስ የሰው ልጅ????

#መልስ፤ ሰላም፤ ፍጥረት? ጌታችን ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም #ለፍጥረት #ሁሉ ስበኩ ሲል #ፍጥረትን ወክሎ የተነገረላቸውና ወንጌሉ የሚሰበኩት ለሰዎች ወይስ ለሬና ፤ዶሮ፤ አወራሪስ፤ ፈረስ ወዘተ… ? የእ/ርን ቃል የእ/ር ቃል ይፈታዋል። በቅድሚያ ግን ብዙም ሳንደክም አውዱን በማንበብ መልሱን እራሱ ይሰጠናል። አስተውሉት መጀመርያ፤ ፍጥረት ሁሉ የሚጠባበቀው የመጀመሪያውን የመንፈስ ፍሬ በኩራት ያገኙትን የእግዚአብሔርን ልጆች በሙላት ክብር[ማለትም በእየሱሱ ክርስቶስ ሙሉ ክብር] መገለጥን በናፍቆት ይጠባበቃል ለምን? ፍጥረት ራሱ ከንቱነት እና ከመበስበስ ባርነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነጻ ወጥቶ የእግዚአብሔር ልጅነት ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ የከበረው ነጻነት እንዲደርስ እያማጠ ነው። ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ ይኸውም በራሱ ምርጫ ፈቅዶ ሳይሆን፣ በተስፋ እ/ር ስላስገዛው እንደምናውቀው ይህ መገዛት ምንም እግዚአብሔር እራሱ ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ የአመጻ ሚስጢር ቢዘጋውም። ሮሜ ሰዎች 11፡32 አሁን ግን ፍጥረት ራሱ ከንቱነት ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ የእግዚአብሔር ልጅነት ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ የከበረው ነጻነት እንዲደርስ የመጀመሪያውን የመንፈስ ፍሬ በኩራት ያገኙትን የእግዚአብሔር ልጆች ራስ ወደ ሆነው ክርስቶስ አድገው በእግዚአብሔር ክብር ክርስቶስ ይገለጡ ዘንድ አያቃሰት ይጠባበቃል ያለው።ሮሜ 8፡19፡23 “የማርቆስ ወንጌል 16፡15 እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም #ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።” በተፈጥራዊው አእምሮ ካየነው በሬና ፤ዶሮ፤ አወራሪስ፤ ፈረስ ወዘተ… ፍጥረት እንስሣ ናቸው ብለን እንደመድማለን፤ መጀመርያ ነገር እንስሣት ፈቃድ የላቸውም እንሣዎች አይደሉም በራሳቸው ምርጫ ሳይፈቅዱ ለከንቱነት እ/ር ያስገዛቸው ሰዎች እንጂ። ወይም በምህታት ተአምርም ከእንስሣነት በክርስቶስ ወዳለው ልጅነት ይቀየራሉ እያለን ሳይሆን የመንፈስ በኩራት ያልተቀበሉት ፍጥረታቱ ሁሉ ናቸው ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥተው የእግዚአብሔር ልጅነት ክብር መድረስ የሚናፍቁት በሬና ፤ዶሮ፤ አወራሪስ፤ ፈረስ ወዘተ… ወደ ልጅነት ክብር አይቀየሩም እነሱ ለመጀመርያው አዳም ስልጣን ሲሰጠው ኦሪት ዘፍጥረት 1 ላይ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። ተብሎ ኦሪት ዘፍጥረት 3 ላይ በአዳም መተላለፍ ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን ብሎ ምድርና በውስጥዋ ከእርሱ የተነሳ ተረግመዋል በክርስቶስ የመጨረሻው አዳም እርግማኑ ሲነሳ እንስሦችም አብረው በቀጥታ ከእርግማን ነጻ ይሆናሉና።

ሌላው ማስተዋል ያለብን ይህ መንፈሳዊ መልእክት ነው እንጂን ተፍጥራዊ አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር #ፍጥረት መጀመሪያ ነው። እንዲሁ ማንም በክርስቶስ ቢሆን ደግሞ አዲስ #ፍጥረት ነው “አሜን የሆነው [ኢየሱስ] የታመነና እውነተኛ [ኢየሱስ] የእግዚአብሔር #ፍጥረት መጀመሪያ the beginning of the #creation of God (ራዕ 3፡ 14). ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤ ቆላስይስ ሰዎች 1፡15-16 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ #ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”
ጌታ ኢየሱስ እንደምሳሌ ፍጹም ሰው ሆኖ የተጠናቀቀው ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ነው። እርሱ የአብ ፍጹም አምሳል ነው ፡፡ የሚቀጥለው የእግዚአብሔር ታዳጊ ልጆች በኩሩን ወንድማቸውን ያን መልክ ይመስሉ ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እየተለወትጡ ነው።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡18 ልጆች በክብር ሲገለጡ እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደተናገረው፥ ነገር ሁሉ የሚታደስበት ዘመን የሐዋርያት ሥራ 3፡21 በክርስቶስ አካል በልጆች ፍጥረትን ሁሉ ወደ ልጅነት ክብር ያመጥታል። በዚህም በክርስቶስ [ራስና አካል፤ አካል ብዙ ብልቶች ቢኖሩትም አንድ አካል ነው፤ ነገር ግን ብልቶች ብዙ ቢሆኑም አካል አንድ ነው። ክርስቶስም እንደዚሁ ነው።] ያቀደውንም የፈቃዱን ምስጢር እንደ በጎ ሐሳቡ እንድናውቅ እንዳደረገን። በዘመን ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ያለው ሐሳቡ በሰማይም በምድርም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ስልጣን ሥር ሁሉን ይጠቀልለዋል። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡9 ወንድም ቢኒ። የጥያቄው ሊንክ
https://www.facebook.com/demis.nida.7/posts/807615616334289?notif_id=1575701914007502&notif_t=feedback_reaction_generic_tagged

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal