በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ላይ። ይድረስ ለኢትዮጵያችን መሪዎች፡ ምክር ለምድራችን የተከበራቹሁ መሪዎች ይሁን።


በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ላይ። ይድረስ ለኢትዮጵያችን መሪዎች፡ ምክር ለምድራችን የተከበራቹሁ መሪዎች ይሁን። ህዳር 4 – 2012 ዓ/ም “በእስራኤል ያሉ መሪዎች ሲመሩ፣ሕዝቡም በፈቃዱ ራሱን ሲያስገዛ፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ። መጽሐፈ መሣፍንት 5፡2 መሪው መሪ ነውና ከፊት ይቅደም።
የምንኖርበት ወቅት ዓመፃን የወደደ ነፍሱን የጠላ የበዛበት በዚህም ምክንያትም ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር የቀዘቀዘበት በመሆኑ ከመቼውም ግዜ ይልቅ ሕግን እና ሥርዓትን መጠበቅ ባስፈለገው ማህበረሰብ ውስጥ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ የህግ አስፈጻሚ ሃይሎች ከምንግዜው በላይ ህጉን ለማስጠበቅ ህጎቹን ለማስከበር በሙሉ ሃይላቸው መረባረብ ያለባቸው ዘመን ላይ ነን፡፡ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ግዛቶች በዚህ ዘመን በነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታላቅ ሁከት የስጋት ድባብ የሰፈፈበት ግዜ ነው። እልቂት ድንገት የሚስተናገድበት አጋጣሚ ብዙ ሆነዋል። ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና የማቴዎስ 26፡52 ሰይፋቸውን ያነሱ ሁሉ ከመጥፋታቸው በፊት ሰይፉን ወደ ስፍራው ለመመለስ የሚያስገድድ የህግ አስፈጻሚ የበላይነት ስምሪት ወሳኝ ትግበራ ብቸኛው መፍትሄ ነው። እንደሚታወቀው ትንሽ በማይባሉ ክልሎች በሰላም ወጥቶ መግባት አስተማማኝ አይደለም ይህ እንደ ሰደድ እሳት ምድሪቱን ከመብላቱ በፊት እረኛው ተመቶ በጎቹ እንዳይበተኑ እረኛው ይንቃ። ህዝብ በአገሩ መሪ ላይ ያለው እምነት ተሸርሽሮ ማለቅ የለበትም ይህ ሌላን ነገ ሊያገነፍል ይችላልና።
“ ደም ምድሪቱን ስለሚያረክሳት፣ ደም ለፈሰሰባትም ምድር ስርየት ሊደረግላት የሚችለው በሌላ ሳይሆን በዚያው ደሙን ባፈሰሰው ሰው ደም ብቻ በመሆኑ፣ የምትኖሩባትን ምድር በደም አታርከሷት” ኦሪት ዘኍልቍ 35፡33
አንድ ሀገር ሕግን እና ሥርዓትን እንዴት መጠበቅ እንዳለባት ግልጽ ነው። አብዛኛው ሰፊው የኅብረተሰብ ክፍል ሕግን እና ሥርዓትን ተከትሎ የሚኖር ነው። ሰአቱ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገትጥ ሕግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች ያላቸውን ኃይሎች ተባብረው ሃይል የመጠቀም ገደብ በመጠን ጨምረው ና አስተካክለው በሃይል ሕጎችን ማስከበር ሕግን እና ሥርዓትን ማስጠበቅ ተገቢ የእርምጃ ጊዜው በደጅ ነው። ድንጋጌና ህግ ለዓመጸኞችና ህግን ለሚተላለፉ ሁሉ ሕግ እንደ ተሰራ እንጂ ለጻድቅ እንዳልተሰራ ግልጽ ነው ጻድቅ ለህግ በመሸነፍ ህግን አሸንፎታልና።
የህግ አስፈጻሚ ኃይሎች ሰላምን ማደስ፤ ስርቆት፣ የቤተክርስቲያን ማቃጠል ፣አስገድዶ ማተብን ማስበጠስና ከክርስትና ወደ እስልምና እምነት ማስቀየር፤ ተቃማትን ማቃጠል፤ ሁከት እና የአድማ ብጥብጥ እና በወንጀል በተንሰራባቸው ብሎም በሚሽሎከሎኩ የጎበዝ አለቆችና የመንጋ መሪዎች በተንሰራፉበት የአገሪቱ ክፍሉች ሁሉ ከሰው ፊት ሳያዳሉ ሕግ የሚተተላለፉትን ተመጣጣኝ ቅጣቶችን ለአመጻቸው ልክ አራሚ ምላሽ በመስጠት በፍጥነት ህግን ማስፈጸም እና አገሪትዋን ማዳን ስራ ሊሰሩ ይገባል፡፡ የሕግ የበላይነትንም እኪመለስ የአብዛኛው የታወኩ ክልል ህዝቦች ልዩ ልዩ ተቃማት በጽኑ እጅ መመራት አለባቸው ፡፡
ወደ ሮሜ ሰዎች 7፡1 ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን?
ሰራዊት ለጦርነት ቀን ቢዘጋጅም ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። በታሪክ እግዚአብሔር ሲፈርድ የአሕዛብን ምክር ያጠፋል የአሕዛብንም አሳብ ወደሃላው መልሰዋል። አያቴ የምትመስለው ምሳሌ ነበራት ። “እግዚአብሔር ሲጣላ አይማታም በብትር ምክር እያሳሳተ ያደርጋል ድንብርብር።” ትል ነበር። እግዚአብሔር ሲፈርድ የመሪዎችን እና የሕዝብን ምክር ይሰውራል። እግዚአብሔር ምክር ያጫጫብሽ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ! ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኚ፣ እርሱም ከአንቺ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጊው ይገኝልሻል፤ ብትተይው ግን፣ ይተውሻል። እግዚአብሔር የሚያስፈራ አምላክ ነው የአንድን ህዝብ መካሮችን እንደ ዘረፋ በግዞት ይወስዳቸዋል ይበትናቸዋልም የቀሩትንም ፈራጆችን ያሳብዳል ብዙዎችንም ማስተዋላቸውን ይመታል በፍርድም ደጋግመው ይስታሉ። ከእግዚአብሔር ዘንድ ምክር የበዛለት ህዝብ ግን እየበረታ ትሄዳል። ድልም ተዘልሎ የተቀመጠው ብዙ ምክር ባለበት ዘንድ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው። መልካም ምክር ከሌለ ታላቅ ሕዝብ እንካን ይወድቃል፤ አንድ አገር ዘመኑን የሚያውቁ መካሮች በብዛት ካሉት ግን ደኅንነት ይሆናል።አንድ ህዝብ የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች እ/ር ሲሰጥ ለአንድ አገር መልካም ይሆናል። ምክር ከሌለ ግን የታሰበው ሳይሳካ ይቀራል፤ መካሮች በበዙበት ዘንድ ግን ሞገስ በህዝብ ላይ ይጸናል። ይህ አዲስ አሰራር አይደለም በዘመናይ አገሮችም በጥንት አገዛዞችም ስራ ላይ የዋለ አካሄድ ነው።

ኢዮሳፍጥ ህዝብ ህግ የሚያስተምረው አጥቶ መረን በወጣ ጊዜ #እግዚአብሔር እራሱ #በተለያየ #መከራ #ያስጨንቃቸው #ስለ #ነበር#አንዱ #መንግሥት #በሌላው #መንግሥት፣ #አንዱም #ከተማ #በሌላው #ከተማ #ይደመሰስ ነበር። ኢዮሳፍጥም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ወታደር አኖረ ህግ እሚያስተምሩም አሰማራ። እግዚአብሔርም ከኢዮሳፍጥ ጋር ነበረ፥ እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸና፤ ይሁዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢዮሳፍጥ አመጣ፤ እጅግም ብዙ ብልጥግናና ክብር ሆነለት። ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ ከፍ ከፍ አለ፤ የኮረብታውን መስገጃዎችና የማምለኪያ ዐፀዱንም ከይሁዳ አስወገደ። በነገሠም በሦስተኛው ዓመት በይሁዳ ከተሞች ህግን ለህዝቡ ሁሉ ያስተምሩ ዘንድ መሳፍንቱን፥ ቤንኃይልን፥ አብድያስን፥ ዘካርያስን፥ ናትናኤልን፥ ሚክያስን፥ ሰደደ። ከእነርሱም ጋር ሌዋውያንን ሸማያን፥ ነታንያን፥ ዝባድያን፥ አሣሄልን፥ ሰሚራሞትን፥ ዮናትንን፥ አዶንያስን፥ ጦብያን፥ ጦባዶንያን ሰደደ፤ ከእነርሱም ጋር ካህናቱን ኤሊሳማንና ኢዮራምን ሰደደ።እነርሱም በወታደር ታጅበው የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ ያስተምሩ ነበር፤ ወደ ይሁዳም ከተሞች ሁሉ ሄደው ሕዝቡን ያስተምሩ ነበር። ይህ ህግን የማስተማር የማስከበር ተግባራዊ ስራ ተከትሎ በይሁዳም ዙሪያ በነበሩ መንግሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ድንጋጤ ሆነ፥ ከኢዮሳፍጥም ጋር አልተዋጉም። ከሚቃወሙት ዘንድ ሳይቀር ሞገስን አገኘ ከፍልስጥኤማውያን ለኢዮሳፍጥ እጅ መንሻና የብር ግብር ያመጡ ነበር፤ ኢዮሳፍጥም እየበረታና እጅግም እየከበረ ሄደ በይሁዳም ግንቦችንና የጎተራ ከተሞችን ሠራ። በይሁዳም ከተሞች ብዙ ሥራ ሠራ፥ በኢየሩሳሌምም ጽኑዓን ኃያላን ሰልፈኞች ነበሩት።

አሁን የኢትዮጵያ መሪ ሊያደርጉ የሚገባው ይህን ነው። ሳያቅማማ የአስቸካይ ግዜ አዋጅ በምድሪቱ ላይ ያውጁ። እ/ር በባህሪው ፍቅር ቢሆንም የሚባላ እሳትም ፈራጅም ነውና። እንደ ኢዮሳፍጥ አቅም ባጡና ሁከት በነገሰባቸው ክልሎች ሁሉ በተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ውስጥ ወታደር ያሰማራ ህግ እና ስራትን እንደገና ያስፍር። አሁን ችግሩ በአለም አህጉራት ሁሉ ያለው ስርአት በአጠቃላይ ለፍጥረት እረፍትን በፍፁም አያመጣም የፍጥረት እረፍት ክርስቶስ ብቻ ነው። ይህም ስራት ለዚህኛው ዘመን የተመደበ የእግዚአብሔርን ሥርዓት መሆኑ ግልጽ ነው።ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡1-5 በአለም ያሉ የስልጣን ሽግግሮች ሁሉ ከአዳም ወደ አዳም ወይም ከፈርኦን ወደ ሌላ ፈርኦን መሆናቸው ግልጽ ነው ከአዳም ወደ ክርስቶስ የሚሆንበት ዘመን ግን ለተቀጠረለት ዘመን ነው። ዲሞክራሲ ጭምብል ነው። Democracy (Greek: δημοκρατία dēmokratía, literally “rule of the people”) ያስቃል ብዙሃኑ ህዝቦች መቼም አገር መርተውም ገዝተው አያውቁም አንደራሴ ተብለው የተቀመጡት ሹሞኞች እንጂ ሆኖም ይህ ስርአት ከአለም ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ በቅዱሳን አገዛዝ እ/ር እስኪ ተካው ድረስ ለአሁን መቀጠሉ አይቀርም እዚጋ ነው ብዙ ሰው የተላለፈው ለዚህም የሰው ስርአት ቢሆን ጌታ ጌታው እንደሆነ የታወቀ መሆን አለበት። ለወደደው በጽድቅ የሚመሩ መሪዎችን ሊሰጥ ይችላል። ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡1 ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።
2 ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።
3 ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤
4 ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። 5 ስለዚህ ስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።
ንጉሥ አሳ ልክ አሁን ኢትዮጵያ ያጋጠማት መከራ አይነት የመጣ መሪ ነበር በአገሩ ላይ ያደረገው ተሐድሶ እርስ በእርሳቸው በሚተላለቁ አመጸኛ ከተሞች ላይ ወታደራዊ ስራትን ዘርግቶ ህግን አንደገና ዘረጋ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ
15፥16-19 ተጓ ምብ – 1ነገ 15፥13-16
1የእግዚአብሔር መንፈስ በዖዴድ ልጅ በአዛርያስ ላይ መጣ። 2እርሱም አሳን ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፤ አሳ፣ እናንተም ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ፣ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤ ብትተውት ግን፣ ይተዋችኋል። 3እስራኤል ያለ እውነተኛ አምላክ፣ ያለ አስተማሪ ካህንና ያለ ሕግ ብዙ ዘመን አሳልፈዋል። 4በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው። 5በዚያን ዘመን በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ #ታላቅ #ሁከት ስለ ነበር፣ #በሰላም ወጥቶ መግባት #አስተማማኝ #አልነበረም። 6#እግዚአብሔር #በተለያየ #መከራ #ያስጨንቃቸው #ስለ #ነበር፣ #አንዱ #መንግሥት #በሌላው #መንግሥት፣ #አንዱም #ከተማ #በሌላው #ከተማ #ይደመሰስ ነበር። 7እናንተ ግን የድካማችሁን ዋጋ ስለምታገኙ በርቱ፤ እጃችሁም አይላላ።”

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 17
1ልጁ ኢዮሣፍጥ በእርሱ ፈንታ ነገሠ፤ በእስራኤል ላይ በረታ። 2እርሱም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ወታደር አኖረ፤ እንዲሁም በይሁዳ ምድርና አባቱ አሳ በያዛቸው በኤፍሬም መንደሮች ዘበኞች አስቀመጠ።
3በለጋነት ዕድሜው አባቱ ዳዊት በሄደበት መንገድ ስለሄደ፣ እግዚአብሔር ከኢዮሣፍጥ ጋር ነበር፤ የበኣልንም አማልክት አልጠየቀም፤ 4ነገር ግን ከእስራኤል ድርጊት ይልቅ፣ የአባቱን ፈለገ፤ ትእዛዛቱንም ተከተለ።
5 እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤ መላው ይሁዳም ስጦታ አመጣለት፤ ከዚህ የተነሣም ታላቅ ብልጽግናና ክብር አገኘ። 6ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ የጸና ነበር፤ እንደዚሁም ማምለኪያ ኰረብታዎችንና የአሼራ ዐምዶችን ከይሁዳ አስወገደ።
7በነገሠ በሦስተኛው ዓመት በይሁዳ ከተሞች ያስተምሩ ዘንድ ሹማምቱን ማለትም ቤን ኀይልን፣ አብድያስን፣ ዘካርያስን፣ ናትናኤልንና ሚካያን ላካቸው። 8ከእነዚህም ጋር ጥቂት ሌዋውያን ነበሩ፤ ስማቸውም፦ ሸማያ፣ ነታንያ፣ ዝባድያ፣ አሣሄል፣ ሰሚራሞት፣ ዮናትን፣ አዶንያስ፣ ጦብያና ጦባዶንያ ነበር። ካህናቱ ደግሞ ኢሊሳማና ኢዮራም ነበሩ። 9እነርሱም የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በመሄድ በይሁዳ ሁሉ ላለው ሕዝብ አስተማሩ፤ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በመዘዋ ወርም ሕዝቡን አስተማሩ።
10በይሁዳ ዙሪያ ባሉ ነገሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርሀት ስለወደቀባቸው ኢዮሣፍጥን አልተዋጉትም። 11ከፍልስጥኤማውያንም አንዳንዶቹ እጅ መንሻ አመጡለት፤ ጥሬ ብርም ገበሩለት፤ ዐረቦችም ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በግና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየል መንጋ አመጡለት።
12ኢዮሣፍጥም እያየለ ሄደ፤ በይሁዳም ምሽጎችና የዕቃ ማከማቻ ከተሞች ሠራ። 13በይሁዳም ከተሞች እጅግ ብዙ ስንቅና ትጥቅ ነበረው። ደግሞም በቂ ልምድ ያላቸውን ተዋጊዎች በኢየሩሳሌም አስቀመጠ። 14እነርሱም በየቤተ ሰቦቻቸው ሲመዘገቡ እንደሚከተለው ነው፤ ከይሁዳ የየሻለቃው አዛዦች፣ አዛዡ ዓድና ከሦስት መቶ ሺ ተዋጊዎች ጋር፤ 15ከእርሱ ቀጥሎም አዛዡ የሆሐናን ከሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ጋር፤ 16ከዚያ ቀጥሎም ለእግዚአብሔር አገልግሎት በፈቃደኝነት ራሱን የሰጠው የዝክሪ ልጅ ዓማስያ ከሁለት መቶ ሺህ ተዋጊዎች ጋር፤ 17ከብንያምም ጀግናው ወታደር ኤሊዳሄ ቀስትና ጋሻ ከያዙ ከሁለት መቶ ሺ ሰዎች ጋር፤ 18ቀጥሎም ዮዛባት ለጦርነት ዝግጁ ከሆኑ ከአንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ጋር፤ 19እነዚህ እንግዲህ በመላው ይሁዳ በተመሸጉት ከተሞች ካስቀመጣቸው ሌላ፣ ንጉሡን ያገለግሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡1 ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።
2 ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።
3 ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤
4 ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። 5 ስለዚህ ስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው። ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal