
ከጥያቄና/መልስ። Mak ሰው መንፈስ ነውን? መልስ ከቢኒ። ሰላም ለአንተ ይሁን በክርስቶስ ወንድሜ። ብዙ ግዜ ከወገኖች ጋር ተነጋግረንበታል ። እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥የዮሐንስ ወንጌል 4/24 ጥያቄው ልጆቹ እሱን ይመስላሉ ወይስ ሌላ? የሰው እውነተኛ ምንጩ መንፈስ የሆነው እ/ር ነው ከምንጩ ባገኘው ማንነት መንፈሳዊ ፍጡር ነው፡ ሰው መንፈስ ብቻ ነው ማለት ሳይሆን ነፍስ ያለው ስጋ ለባሽ መሆኑም መዘንጋት የለበትም የለብንም። በዚህ ተፈጥራዊ ግዛት የሰው ሁለንተናው መንፈስ፤ ነፍስንም ሥጋንም የያዘ ማንነት አለውና። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡23 የሰላምም አምላክ ራሱ #ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ #መንፈሳችሁም #ነፍሳችሁም #ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ። ሰው ያተገኘው የፈጠረውም መንፈስ ነው ምንጩ እ/ር እራሱ ነው። ያለ እ/ር መንፈስ በአጭር ቋንቋ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ የሰው ድንካኑም ማለትም ማደርያ ስጋውም ወደ አፈር ይመለሳል።
እ/ር መንፈስ ሆኖ ሳለ ነፍስ እንዳለው በመጽሐፍ አስተውላችሃል ኦሪት ዘሌዋውያን 26፡11 ማደሪያዬንም በእናንተ መካከል አደርጋለሁ ነፍሴም አትጸየፋችሁም።
ኦሪት ዘሌዋውያን 26፡30 የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ የፀሐይ ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ #ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2:35 የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም #በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።
ትንቢተ ኢሳይያስ 42፡1 እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ #ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል። ትንቢተ ኤርምያስ 5፡9 በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር #ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?
የማቴዎስ ወንጌል 12፡18 እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ #ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።
መጽሐፈ ምሳሌ 6፡16 እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም #ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች
17 ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
18 ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
19 በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
ኮንኮርዳንስ ብታዩ እ/ር #ነፍስ እንዳለው ታስተውላላችሁ እ/ር መንፈስ እንደሆነ ስንቶቻችሁ ታስተውላላችሁ?እ/ር ሰው እንዳልሆነስ ታውቃላችሁ ። እ/ር መንፈስ እንደሆነ ነፍስ እንዳለው ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ?መንፈስ ነፍስ እንዳለው ታስተውላላችሁ? ። ከኔ ጋር ናችሁ ?1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች2፥6 በበሰሉት መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፥ ነገር ግን የዚችን ዓለም ጥበብ አይደለም የሚሻሩትንም የዚችን ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም፤ we speak wisdom among them that are perfect
መንፈስ፤ ስንቶቻችሁ እ/ር አይምሮ እንዳለው ታስተውላላችሁ ፈቃድ እንዳለውስ ሰሜት እንዳለውስ GOD gets angry እ/ር ይናደዳል ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡30 ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።Eph 4፡30 And grieve not the holy Spirit of God, whereby ye are sealed unto the day of redemption.
እ/ር ይስቃል። የሃጢያተኛው ቀኑ እንደደረሰ አይተዋልና እ/ር በሰማይ #ይስቃል “መዝሙረ ዳዊት 2/4 በሰማይ የሚኖር #እርሱ #ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።”
እ/ር #ደስ ይሰኛል መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3፡10 ሰሎሞንም ይህን ነገር ስለ ለመነ፥ ነገሩ #እግዚአብሔርን #ደስ #አሰኘው። እግዚአብሔርም አለው፦ ፍርድን ትለይ ዘንድ ለራስህ ማስተዋልን ለመንህ እንጂ ለራስህ ብዙ ዘመናትን ባለጠግነትንም የጠላቶችህንም ነፍስ ሳትለምን ይህን ነገር ለምነሃልና እነሆ፥
የመንፈስ ፍሬ ምን እደሆኑ ታውቃላችሁ የእ/ር ስሜት ናቸው። ወንድም እህቴ በሚሰማኝ ነገር ሳይሆን የምመላለሰው በእምነት ብቻ ነው ትል ይሆናል። ዜና አለኝ ላንተ በሚሰማኝ እመለለሳለሁ ። መጽሓፍ በሚሰማህ እንዳት መላለስ በእምነት ብቻ እንጂ እንደ ማይል ታውቃለህ?መጽሃፉ ላይ የለም መጽሃፉ የሚነግረን በእምነት መየትን ነው። በእምነት መየትን እንጂ በሚሰማኝ እንዳልሆነ ነው።
ብራዘር የእ/ር ሰላም ፊሊንግ ወይም የሚሰማህ ነገር ነው፤ The joy of the Lord is a filing የእ/ር ደስታ የሚሰማን ነገር ነው። የእ/ር ትእግስ የሚሰማህ ነገር ነው። በዛ በሚሰማኝ ሰላም፣ ደስታ፣ ትእግስ፣ እምነት፣ እመለለሳለሁ። በዛ ህያው የእ/ር መልካምነት የእ/ር አባቴና አምላኬ ንቃተ ህሊና በሂወቴ ባለ በዛ እምላለሳለሁ። የመንፈስ ፍሬዎች ከእ/ር imoton ስሜቶች ጋር የተያያዙ ናቸው።
እ/ር መንፈስ ነው ሆኖም minde will imotion disier አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ አለው። እ/ር መንፈስ ነው ሆኖም ነፍስ አለው። ከማይጠፋው ዘር ከእ/ር የተወለደው አዲሱ ሰው መንፈሳችሁ ነፍስ አለው። አሮ ጌው ስጋዊው ሰው ነፍስ እንዳለው ታውቃላችሁ ?the mind of the flsh ስጋዊ አይምሮ ፣ መጽሓፍ the will of the flsh የስጋ ፈቃድ ፣ምኞት አትፈጽሙለት ።
የስጋ ሰራ ምን እደሆኑ ታውቃላችሁ ?የስጋ ስሜት መገለጥ ፍሬዎች ናቸው።
የመንፈስም የስጋም minde will imotion disier የመንፈስ አይምሮ፣ የስጋ አይምሮ አለ፣ የመንፈስ ፈቃድም የስጋም ፈቃድ አለ፣ የመንፈስ ስሜት አለ የስጋ ስሜትም አለ፣ የመንፈስ ምኞት አለ የስጋ ምኞት አለ። እያንዳዳቸው የነፍስ ክፍል ናቸው (አሮ ጌው ስጋዊው ሰው ነፍስ አለው አዲሱ ሰው መንፈሳችሁ ነፍስ አለው።)
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡17 ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው። 1Cor 6፡17 But he that is joined unto the Lord is one spirit.
ወደ ጌታ ህብረት ስንመጣ አንድ መንፈስ ስሆን ወደ እ/ር የነፍሱ ፈቃድም እዋሃዳለሁ ማለት ነው። አሁን የእ/ር minde will imotion disier አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ በመንፈሴ አለ ማለት ነው። በተመሳሳይ ጊዜ አሮ ጌው ስጋዊው ሰው ነፍስ አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ አሉ። ስንቶቻቹ እነዚህ ሁለቱ በውስጣችሁ ሲፈራረቁ አይታችሃል? እውነት ነው አሁን ችግሩን ለየነው A double minded (GR- soo-khos ነፍስ፣ ሶል) man is unstable in all his ways ሁለት አሳብ (አይምሮ ነፍስ) ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል።
አሁን ችግሩ ታየ !ሁለት ነፍስ ወይም አሳብ አይምሮ የሚዋልለውን ሰው ኧስተዋልነው እንደ ፔንዱለም ወዲህ ደዲያ ይወዛወዛል የቱን እንደ ሚጨብጥ ሚስጥር ሆኖበታል።
የትኛውን እንደሚታዘዝ ግራ ይገባዋል ዛሬ ለመንፈሳዊው ሰው ነገ ለስጋዊው ሰው ያድራል በሁለተ መካከል እተፈራረቀከ እተንገላታ ይታዘዛል እንደውሃም ይዋልላል ። ሮቤል እንደውሃ ይዋልላንና መሪነት አይገባውም” ጎራውን ያለየ ጠንካራ አቃም ከሌለው መሪነት?
አስተውሉ፡ ነፍስ ነጠላ ነው። በሌላ አነጋገር አንድ የነፍስ ክፍል ነው ያለን። ምሳሌ እንስጥ ከተባለ ስለ አገራችን የስልጣን ወንበር እንይ አንድ ፓርቲ አሸንፎ የሚይዘው በትረ መንግስት ነው ያለው በ97 ካያችሁ ኢሃዲግና ቅንጅት ተወዳደሩ ። ሁለቱም ወንበሩን ሊጠቀሙበት ፈለጉ በትረ መንግስቱን ይዞ የስልጣን ወንበር ላይ ሁለቱ ተደራርበው ለመቀመጥ ሲፋለሙ ብራዘር እዛጋ ነው ትልቅ ችግር ፍጭት የመጣው ። አንዱን የነፍስ ፋክሊቲ ወይም ተቋም ለመጠቀም ውጊያ አለ በሌላ አነጋገር የእ/ር መንፈስ ፈቃድ በዛ አይምሮ ሊጠቀምና ሊገለጥ ይችላል የሰጋ ፈቃድ ከበረታ በዛ አይምሮ ሊጠቀምና ሊገለጥ ይችላል።
እኛ ግን ነጠላ አይምሮ ነው ያለን በእ/ር መንፈስ ምስክርነት ላይ ቆመናል። አሜን!
ስለነስፍስ አንድ ነገር በመጽሃፍ ስናስተውል ነፍስ ወስጥ minde will imotion disier አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት ወዘተ ናቸው። ለምሳሌ ከቃሉ ስናስተውል #በነፍስህ #ፈቃድም መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 28፡9 አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ #የነፍስንም #አሳብ ሁሉ ያውቃልና፥ የአባትህን አምላክ እወቅ በፍጹም ልብና #በነፍስህ #ፈቃድም አምልከው ብትፈልገው ታገኘዋለህ ብትተወው ግን ለዘላለም ይጥልሃል። ነፍስ #ትመኛለች desireth መጽሐፈ ምሳሌ 13፡4 የታካች ሰው #ነፍስ #ትመኛለች አንዳችም አታገኝም የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።
በህይወት የመኖራቸው ምስጢር እ/ር መንፈስ እራሱ ነው። ከሱ የራቀ ወይም የወጣ ከባህር የወጣ አሳ ማለት ነው። ከባህር ከወጣ አጨብጭቦ ጸጥ ይላልና። መጽሐፈ ኢዮብ 27፡3 እስትንፋሴ በእኔ ውስጥ፥ #የእግዚአብሔርም #መንፈስ #በአፍንጫዬ ውስጥ ገና #ሳለ። አስተዋልከው? #የእግዚአብሔርም #መንፈስ #በአፍንጫዬ ውስጥ ገና #ሳለ።? መጽሐፈ ኢዮብ 34፡14 እርሱ ልቡን ወደ ራሱ ቢመልስ፥ #መንፈሱንና #እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፥ 15 ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ ሰውም ወደ አፈር ይመለሳል። ምን ምን አለ የሰው ወይስ የራሱን #መንፈሱንና #እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፥? ለፈጣን ጆሮና በማስተዋሉ ለማይዘገይ እውነቱ ይህ ነው። መጽሐፈ ኢዮብ 32፡8 ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጣል። መጽሐፈ ኢዮብ 12፡10 የሕያዋን ሁሉ ነፍስ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናት። መጽሐፈ ኢዮብ 26፡4 ይህንስ ቃል በማን እርዳታ ተናገርህ? የማንስ መንፈስ ከአንተ ዘንድ ወጣ? መጽሐፈ ኢዮብ 32፡18 እኔ ቃል ተሞልቻለሁና፥ በውስጤም ያለ መንፈስ አስገድዶኛልና። ሰቆቃው ኤርምያስ 4፡20 በእግዚአብሔር የተቀባው[መሲሁ፤ ክርስቶስ]፣ የሕይወታችን እስትንፋስ። ምን ምን አለ ማነው የህይወታችን እስትንፋስ? ክርስቶስ! የሕይወታችን እስትንፋስ ነው፤ የዚህ ሃሳብ ማወፈርያ ሃሳብ ይህን አስተውሉ። የሐዋርያት ሥራ 17፡25 እርሱም #ሕይወትንና #እስትንፋስን #ሁሉንም #ለሁሉ #ይሰጣልና አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም። 26-27 ምናልባትም #እየመረመሩ #ያገኙት እንደ ሆነ፥ #እግዚአብሔርን #ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም #ከእያንዳንዳችን #የራቀ #አይደለም። 28 ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ፦ እኛ ደግሞ #ዘመዶቹ[ግሪክ፡ his offspring ዘሮቹ፤ ሃረጉ ነንና፤ ትውልዶቹ፣ ልጆቹ] ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ #በእርሱ #ሕያዋን ነንና #እንንቀሳቀሳለን #እንኖርማለን።
መጽሃፍ ምን ይላል? በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ እግዚአብሔርም ነበረ። በቃል ውስጥ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ሁሉ ብርሃን ነበረች። በቃል ውስጥ የሰው ሁሉ ሕይወት የሰው ሁሉ ብርሃን ታጭቀዋል። ይህ ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም መጣ ስጋ ለብሶ ተገለጠ እንጂ በዓለም ውስጥ ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ የሆነ ነው፥ ዓለሙም ሁሉ ኝ አላወቀውም። የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ #ወገኖቹም[ወገኖቹ ብርሃናቸው የሆነው ሰው ሁሉን ነው እንጂ የጁዲህዝም ቡድንን ብቻ የሚያሳይ አይድደለም] አልተረዱትም።የዮሐንስ ወንጌል 1፡1-9
እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥የዮሐንስ ወንጌል 4/24 ልጆቹም እሱን ይመስላሉ እንጂ ሌላ አይመስሉም። መቼም ነገር ሳይንዛዛ በአጭር ቃል እንቅጩን እንደጌታ የሚያስቀምጠው የለም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ #ከመንፈስም #የተወለደ #መንፈስ ነው። የዮሐንስ ወንጌል 3/6 አለቀ እግዚአብሔር መንፈስ ነው ከመንፈስ እግዚአብሔር የተወለደ መንፈስ ነው! አንዳንዱ ሰው ከመንፈስም የተወለደ ሥጋ ነው ብሎ ገልብጦ ይረዳዋል።
እግዚአብሔር ዘፍጥረት 1 ላይ ሁሉ እንደ #ወገኑ #ዘሩን ያዘጋጅ ይብዛ አላለም? በምድርም ላይ #እንደ #ወገኑ #ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።እግዚአብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን፥ ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውንም ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።እግዚአብሔርም አለ፦ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን #እንደ #ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፤ እንዲሁም ሆነ።
ታዲያ ሰው ጋር ሲደርስ እንደ ወገኑ እንደ እግዚአብሔር የማይዘጋጅበት ምን ምክንያት አለ? እግዚአብሔር ቃል ነው ቃልም መንፈስና ህይወት በውስጡ አለው እንደ ወገኑ ከመንፈስ እግዚአብሔር ዘር የተወለደም መንፈስ ነው! እነርሱ ከእግዚአብሔር ወገን ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወገን ወይም ከወንድ ፈቃድ ወገን አልተወለዱምና ።የዮሐንስ ወንጌል 1/13
መንፈሳዊው የስንዴ ቅንጣት ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ወድቆ ሞተ ህይወት የሚለቀቀው በሞት ውስጥ ነውና ብቻውን አልቀረም፤ ብዙ መንፈሳዊ የስንዴ ዘለላዎችን ተንዠርግጎ ፍሬ አፍርተዋል። እግዚአብሔር ይብዛላችሁ፤ ህይወት ይብዛላችሁ። ወንድም ቢኒ።