
የብርሃናት አባት Father of lights ። በወንድም ቢኒያም አለማየሁ። 5/27/2019 የያዕቆብ መልእክት 1፡17 በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ #ከብርሃናት#አባት ይወርዳሉ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? እግዚአብሔር በራእሱ ቃል በልጁ ወይም በወልድ በኩል ይናገራል! “እርሱ የእግዚአብሔር ቃሉ ነውና” ቃሉ ብቻ ሳይሆን “እግዚአብሔር ቃል ነው” በኢየሱስ ውስጥ ይህ ይህ ነው። Actually if you see (Concordant) literally this verse says, “God was the Word” የዮሐንስ ራእይ 19:13 ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል። ክብሩን አየን? ምን ማለት ነው? የማ ክብር ነው በስጋ ተገልጦ የታየው? “የእግዚአብሔር ቃል ማነው?” ኢየሱስ ክርስቶስ የእ/ር ቃል ነው አብ ሌላ ቃል የለውም ቃሉ እራሱ ነው። በሰው ቃል እንኛገረው ብንል እንካ የመለኮት ሙላት መገለጥ ቃል አቀባይ ሆኖ ሎጎስ – እንደራሴ ተወካይ ሆኖ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ምክንያቱም ማንም ሰው አብን ሰምቶት አይቶት አያውቅም አላየውም ምክንያቱም አብ አንድን ነገር ለሰው ዘር በቃሉ የሚገልጠው የእሱ መልእክተኛ – የእሱ ሎጎስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ የክብሩ ብርሃን መንጸባረቅ ነው [the Light-being, the out-raying or radiance of the divine] Heb 1:3 [AMP] ኢየሱስ የክብሩ ብርሃን መንጸባረቅ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ክብር የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡24 ኢየሱስ እራሱ ነው። እ/ር ሌላ ክብር የለውም ክብሩ ኢየሱስ ነው። የሐዋርያት ሥራ 7፡55 የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየ” ኢየሱስ ታላቅ ብርሃን ነው።የማቴዎስ ወንጌል 4፡14 ኢየሱስ እንደ ፀሐይ ብርሃን ተለወጠ።የማቴዎስ ወንጌል 17፡2 ኢየሱስ የሰው ሁሉ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነው።የዮሐንስ ወንጌል 1፡4 ኢየሱስ እርሱ እውነተኛው ብርሃን ነው።የዮሐንስ ወንጌል 1:8-9 ኢየሱስ የዓለም ብርሃን ነው የዮሐንስ ወንጌል 8፡12 ኢየሱስ ውስጥ እራሳችሁን ማየት ትችላላችሁ 17 ከጌታ ጋር የሚዋሃድ ግን አንድ መንፈስ ነውና። የማቴዎስ ወንጌል 5፡14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡17 ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው። 1Cor 6፡17 But he that is joined unto the Lord is one spirit.
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡16 እርሱ ብቻ የማይሞት[ ኢመዋቲ ፡የማይበሰብስ ህያውነት ያለው፣ immortality] ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን። በነገራችን ላይ ኢየሱስም እንደ አባቱ የማይሞት[ ኢመዋቲ ፡የማይበሰብስ ህያውነት ያለው፣ immortality ክብር አለው። በሥጋ ሞተ እንጂ በመንፈስ ግን ሕያው ነበረ ህያው ስለሆነም በመንፈስ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት[ግሪክ፡መናፍስት] የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናቸውን ወንጌል ሰበከላቸው። እንደ ሰዎች በሥጋ በኖህ ዘመን በውሃ አስጥሞ ፈረድባቸው በኢየሱስ ስብከት ግን በመንፈስ እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ወንጌልን በወኅኒ ለሙታን ደግሞ የምስራቹ የመዳናቸውን ወንጌል ተሰበከላቸው። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:18፟-19 ፡ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡13 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡6
አባት ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ ልጅም ብርሃን ነው። ልዩነታቸው ምንድነው? የብርሃን ክብር ደርጃ አለው ወይስ አንድ ነው? የብርሃን ክብር ሆነ የብርሃኑ ነጸብራቅ ጨረሩ ወደ ነጸብራቅነት ቢፈነጥቅም አንጽብርቆ ከመነጨበት የብርሃኑ ምንጭ ንጥረ ነገሩ የተለየ ወይም ያነሰ የብርሃን ክብር የለውም። ብርሃን በየትኛውም ክበብ ሆነ ግዛት ብርሃን ነው። በተለያየ ክበብ መታየቱ በተለያየ መአዝን ሆነው ለሚያዩት ግን ለእይታቸው ባዩት ብርሃን መጠን ክብሩን ይመዙኑታል በልዩነትም ይናገራሉ። በመሃከላችን መንፍሳዊያን የሚመስሉ ብዙ ባለ አእምሮ ሰዎች እስካሉ ድረስ Let me be perfectly clear not only on the word ኦፍ God but also, logically, before I highlighted Scriptural words on this matter: ኢየሱስ በመለወጥ ተራራ ብርሃን light መሆኑን አስመስክረዋል። የማቴዎስ ወንጌል 17፡2 በፊታቸውም #ተለወጠ[ metamorphoo met-am-or-fo’-o “metamorphose”):–change, transfigure, transform]፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። And then, all of a sudden, He was #transformed (changed in external form and appearance) and His face radiated light, like a lamp, and shone like the sun. His outer garments also turned white – bright as the light! JMT ወደ መለኮታዊ ምንጩ ማስተዋል ለመምጣት ብርሃንን በጥቂቱም ቢሆን በሰው ቃል ልንረዳው ይገባል እንታገዛለንና። የብርሃንን ሙላት ክብር ለመረዳት በመጀመሪያ ብርሃን light እንዴት ከተፈጥራዊው ቁሳዊ አካል [ከማተር matter] ጋር እንደሚገናኝ እንደሚግባባ መረዳት አለብን first let us understand how light interacts with matter. በተፈጥረዊው መረዳት ብርሃን በተፍጥሮው የሞገድ ባህሪያት ያለው ማንም በሙላት ክብሩ ሊያየው የማይችል የኤሌክትሮማግኔቲክ ጨረር electromagnetic radiation እምቅ ክምችት ሃይል ነው። በምሳሌ ለማየት ፀሐይን ማንም በጥሬ አይኑ አግጦ ቢያይ ይታወራል ብርሃኑ ክምችት ክብር ታላቅ ነውና። በፍንጣቄ በነጸብራቅ መልክ ሲገለጥ ግን ለህይወት ይሆናል። በሥርዓተ-ፀሐይ በስርዓቱ መሃል ላይ የምትገኝ ታላቅ የብርሃን ኮከብ ናት። በዲንቶል ሂደቱ አማካኝነት መግነጢሳዊ መስክን የሚያመነጭ ውስጣዊ ማራኪ እንቅስቃሴ ያለው ታላቅ ሞቃታማ ታላቅ ብርሃናማ ፍጹም ፕላዝማ ነው ለማለት ይቻላል። ፀሐይ በምድር አጽናፍ ላይ ላለው ሕይወት ሁሉ ከፍተኛው የኃይል ና የብርህን ምንጭ ነው። ፀሐይ ብራህንና የፀሐይ ጨረር ክብራቸው ልዩነት የለውም ጨረሩ ከፀሐይ ምንጩ ክብር ተገምሶ ያንጸባረቀ አንድ አይነት ክብር ነው። የብርሃን የኤሌክትሮማግኔቲክ ጥምጥሙ ሲፈነጠቅ በጨረር ርዝመት ተመስርቶ በበርካታ ነጸብራቅ መጠን ወደሚታየው እራሱን ወስኖ ሊከሰት ይችላል። ወደ መገለጥ የመጣው የሚታየው ብርሃን ከእምቁ ብራሃን በጨረር መልክ ተገምሶ በሩቅ ሆነ በቅርብ ርቀት መካከል ያለውን የብርሃን ሞገድ ርዝመት በመወከል ሊታይበት በሚችል መጠን ሚዛኑን ጠብቆ ከአንዱ ክብር ግምሶ እራሱን ያሳያል።
የሉቃስ ወንጌል 11፡34 የሰውነትህ መብራት ዓይንህ ናት። ዓይንህ ጤናማ በሆነች ጊዜ ሰውነትህ ሁሉ ደግሞ ብሩህ ይሆናል። ዓይንህ ታማሚ በሆነች ጊዜ ግን ሰውነትህ ደግሞ የጨለመ ይሆናል። የሰውነት መብራት ዓይን ናት። በአይናችን ብርሃን ስናይ የመረዳት ጥልቀቱ የሚወስነው ዓይኖቻችን እነዚህ የብርሃን ጨረራ መሰል ሞገድ ርዝመቶችን እንደ የተለያዩ ህብረ ቀለማት ይተረጉሟቸዋል ግንዚያቢችንም በዛ የተመሰረተ ይሆናል። አንድ የብርሃን ሞገድ ነጸብራቅ ርዝመት ወይም የተወሰነ የሞገድ ርዝመት ብቻ በእይታችን ቀጠና ቢገኝ እና ወደ ዓይናችንን ቢገባ እንደ አንድ ቀለም ይተረጉማቸዋል። በሚታየው ክልል ውስጥ ምንም ረቂቅ የብርሃን ጨረራ ሞገድ ርዝመት ከሌለ ይህን እንደ ጥቁር ጨለማ አይናችን ይተረጉምልናል። አንድ ወፈር ያለ ሞገድ ርዝመት በህልውናው ቢገኝ እኛ ስንረዳው አንዷ የደመቀ ነጭ ቀለም የብርሃን ትርጉም እንዳለን በሰው ቋንቃ እንናገራለን። ሁሉም የብርሃን ክምችት የማየት ችሎታ ቢኖረንና የብርሃን ርዝመት በቱባ መልክ ያለውን ጥምጥም ክምችቱን በሙላቱ በህልውናው ቢከሰት, ዓይኖቻችን ይሄንን እንደ ከባድ ነጭ ብርሃን ይተረጉመውና አይናችን ብርሃን በዝቶበት ይታወራል። በአሳዳጁ ሳኦል ላይ የሆነው ይከው ነው። ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ። ጉዳዩ ባለቀ ጊዜ ሳውልም ከምድር ተነሣ፥ ከብርሃኑ ሃይል የተነሳ አይኖቹም በተከፈቱ ጊዜ ምንም አላየም፤ እጁንም ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ ወሰዱት።
ስጋ ሆነ ካለ በዛ ስጋ ውስጥ ምን ተሞልቶ አደረ? ቃልም ሥጋ ሲሆን፤ ሥጋው ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ ነው። መሎኮት ተሞልቶ ነው። #የመለኮት#ሙላት#ሁሉ ![ግማሹ ሳይሁን #ሁሉ የሁሉ ትርጉም #ሁሉ ነው] ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡9 የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በእርሱ ይኖራልና “In Him dwelleth all the fullness of the Godhead bodily…” Then let me ask you if you can see this: Is the Lord Jesus in the Godhead or is the Godhead in the Lord Jesus? “In Him dwelleth all the fullness of the Godhead bodily! Can you hear that? I can, so I can say amen to that!!! በወንድም ቢኒያም።