
ምስል[አምሳል] ምን ማለት ነው? ወንድም ቢኒ 5/30/2019
‘እርሱ የማይታየው invisible[የዮሐንስ ወንጌል 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥(መንፈስ በባህርዩ አይታይም] አምላክ #አምሳል[ምስል] ነው፤ ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለ ሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። ‘ ቈላስይስ 1:15-16 ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል? ታድያ ሁለት ወይስ ሦስት ፈጣሪ አለ እንዴ? ወይስ ፈጣሪ አንድ ነው? በእርግጥም አንድ ፈጣሪ አለ። ክርስቶስ የአብ[አባት] ምስል ፍጹም መገለጥ ነው። አብ መንፈስ በመሆኑ አይታይም መታየት ይቻል ዘንድ እንዴት እራሱን ገለጠ?። የማይታየው ባህሪ ያለው የአብ ክብር ወደ ሚታየው መተርጎም አለበት ። ኢየሱስ ክርስቶስ ለተፈጥራዊው ሰው አብ እንዲገባው የመጨረሻው የአብ ፍጹም ትርጉም ነው። ክርስቶስ ልዑል፣ ከፍተኛ፣ ከሁሉ በላይ የሆነ[ልእለ ተፈጥሮ] ምስለ ነጸብራቅ ነው። [ለምሳሌ አንድ ሰው ወይም እርሶ ጠዋት ጠዋት መስተዋት ላይ ምስሎን ሲያዩ መስተዋት ላይ ያለው ምስሌ ከኔ ያንሳል እያሉ ይማገታሉን? የብዙ ሰዎች ሙግት ፎብያ ካልሆነ በቀር ከንቱ ሙጉት ነው። ልክ አንዲሁ አብ በመስተዋት ፊት ቢቆም ምስሉ ለኛ ክርስቶስ ሆኖ ተንጸባርቆ ታየን ለራሱ እንደሚታየው ተረዳነው። ልጁ የአባቱ ፍጹም ምስል መልክ መሆኑን ካወቅን እኛ ማንን እንደምንመስል እናውቃለን። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡29 ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
ወይም እርሶ ወይም አንድ ሰው በቲቪ ምስሉ በብርሃን ቀለማት ቀመር እንደሚፈነጥቅ ነው። ይህ ልዩነቱ ህያው ልእለ ተፈጥሮ ምስል መሆኑ እና በዚህ የአብ ምስል በውስጡ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ መኖሩ ነው። ክርስቶስም የአብ የነፍሱ የህይወቱ ክብር ፍጹም ምስልና ለለ ተፈጥሮ የመጨረሻው ፍጹም መለኮይታዊ ትእይንትና ነጸብራቁ የአብ የራሱ ከማይታተው ባህርይ ወደ መታየት የመጣ የአብ ፍጹም መገለጡም ምስሉም ነው። በተፈጥሮ ከዋናው የተወሰደ ተንቀሳቃሽ ምስልን እንኻን ብናይ አንድ የቴሌቪዥን ተንቀሳቃሽ ምስል ወይም ትእይንተ ትርዒት ወይም ፊልም ሲመለከቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ምስሎችንና ፎቶግራፎች አንዳቸው በሌላው ላይ እየተከታተሉ በስርአት እንደተነሱት በመስኮቱ ተንቀሳቃሽ ምስል ሆነው ያያሉ። እነዚህ ስዕሎች ከዋናው አካል ነጸብራቅ ሆነው በተሰጣቸው ስራትና ትዕዛዝ ውስጥ ስራአታቸው ሳይፋለስ ሲታዩ ተንቀሳቅሰው ተንቀሳቃሽ ምስል ሆነው ለእርሶ ይታያሉ። እያንዳንዳቸው ምስሎች ፒክሴልስ pixels ተብለው የሚጠሩ ትናንሽ ውብ ህብረ ቀለም የተነከሩ ነጥቦችን ያቀፉ ብዙሃን ስብስብ ውጤት ናቸው። ፒክስሎች ልክ እንደ ባለ ቀለም የተነጣጠቁ ነቁጣ ነጠብጣቦች ይመስላሉ። ነገር ግን በተናጠል ከርቀት ፒክስሎች ለማየት በጣም ትንሽ ናቸው። አንዱን ነጥሎ ለማየት ያስቸግራል ስለዚህ ይልቁንስ ትርጉም ያለው የተፈለገው ሰው ወይም የማንኛውም ነገር ምስል ለማየት የፒክሰሎች ስብስቦች እንደ ሙሉ ሆነው ሲታዩ ሙሉ ምስል ሆነው ይታዩናል።. ይህን የበለጠ ለማብራራት ልጆች የሚጠቀሙበትን ማጉያ መነጽር በመጠቀም ፎቶግራፍ ወይም በጋዜጣ ውስጥ ቢያዩ ምስል የፒክሰሎች ስብስቦች እንደሆነ ይረዳሉ። ይህ ምስል ከአንድ አውነተኛ ማንነት የተቀረጸ ወይም የተቀዳ የዛ ነገር ፍጹም የምስሉ ነጸብራቅ ነው። የጓኡዙ አለም ምስል ይህን ይመስላል። በያዋን ምድር ምስል ደግሞ ፍጹም ህያው ነው።
እርሱ ገለጠው። ሊታይበት ወደ ሚችለው አወጣው። እርሱ እንዲታወቅ አደረገው።” RHM የተባለው ትርጉም ደግሞ “እርሱ ገለጠው አስተረጎመው” ይላል። እንዲህ ትርጉም ጽህፈት ቤት ሰው የሚሄደው በሚገባው ወይም በተፈለገው ቋንቋ ተተርጉም ነገሩን ለመረዳት ነው። ጌታ እ/ርንም[መንፈስንም] በሚገባን በሰው ቋንቋ ተርጉሞ አሳየን። ሌላ ትርጉም ሙልአት ወዳለው መገለጥ አመጣው ይላል። እንግዲህ እየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ውስጥ የሚኖረው የማይታየው አምላክና አባት ሙሉ መገለጥ ነው። እ/ር በሙልአት እራሱን በልጁ አስቀመጠ ወይም አደረ የማይታይ የዘልአለም ባህርዩን ለሰው ይገልጥ ዘንድ።
Strong’s Concordance Original Word: εἰκών, όνος, ἡ ፍቺ: – ምስል, ሐውልት, ውክልና Definition: an image, statue, representation 1504 eikṓn (ከ 1503 / eíkō , “be like”) -በአግባብነት properly , “መስታወት መሰል ቅርጽ ያለው ውክልና mirror-like representation,” በጣም ቅርብ በሆነ መልኩ (ልክ እንደ “ከፍተኛ-ጥራት” ትይታ[ ትወራ] በጥቅሱ እንደተገለጸው) ማለቱ ነው። referring to what is very close in resemblance (like a “high-definition” projection, as defined by the context . ምስል Image ( 1504 eikṓn ) የምንጩን ፍጹም ነጸብራቅ (በቀጥታ የወከለውን አመልካች) then exactly reflects its source(what it directly corresponds to). ለምሳሌ ያህል፤ ክርስቶስ መንፈስ በመሆኑ የማይታየው ባህሪ ያለው የአብ ልዑል፣ ከፍተኛ፣ ከሁሉ በላይ የሆነ[ልእለ ተፈጥሮ] ምስለ ነጸብራቅ ነው። [ለምሳሌ አንድ ሰው በመስተዋት ፊት ቢቆም ምስሉ ተንጸባርቆ ለራሱ እንደሚታየው ወይም በቲቪ ምስሉ በብርሃን ቀለማት ቀመር እንደሚፈነጥቅ ክርስቶስም የአብ የነፍሱ የህይወቱ ክብር ፍጹም ምስልና ለለ ተፈጥሮ የመጨረሻው ፍጹም ነጸብራቁ ነው] ( 1504 / eikṓn ክርስቶስ የበላይ መግለጸ ምስለ መለኮት ነው። ( ቆላ 1:15 2ቆሮ 4፡4). For example, Christ is the very image supreme expression of the Godhead
HEBREWS 1:3. Who, being a beam (radiance; effulgence; outshining) from the Glory, and an exact impress (as from a stamp or die) of His substructure (the substance standing under as a foundation) and continuously bearing (carrying) the whole (all things; everything; or, as a masc.: all men) by the thing which is spoken belonging to His power (the saying pertaining to His ability; in the spoken word of His power), making a cleansing (purification) of failures (of the misses of the target; pertaining to the sins), seated Himself within the right part of greatness resident within high places. JMT
‘ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ ይኸውም ዘላለማዊ ኀይሉና መለኮትነቱ፣ ከፍጥረቱ በግልጽ ይታያል፤ ስለዚህ ሰዎች ማመካኛ የላቸውም። ‘ ሮሜ 1:20 አስተውሉ የእግዚአብሔር ባሕርይ ይኸውም ዘላለማዊ ኀይሉና መለኮትነቱ፣ የማይታይ ነው ለፍጥረቱ መታየት ፈለገና በመጀመሪያው ቃል የነበረ እግዚአብሔር ወደ ሚታየው እራሱን መግለጥ ፈለገ ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ። እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ እንደሌለ ግልጽ ነው። ፤ የዮሐንስ ወንጌል 1/18 መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ ለሙሴ እንደነገረው ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም ብሎታል እ/ር በክብሩ ቢገለጥ ሰው አይድንም ኦሪት ዘጸአት 33/20 ደግሞም፦ ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም አለ።
ቃል ወይም መንፈስ የሆነው ጌታ ስጋ ሆኖ በልጅነት ክብር ተገለጠ ። ምክንያቱም መንፈስ የሆነውን ጌታ ማንም ሊያየው በማይችል ብርሃን የሚኖሮ ከሆነ እ/ርን ማየት ለስጋ ለባሽ የማይቻል ነው። የስጋዊው አእምሮ መንፈሳዊን አለም ያስተውል ዘንድ ብቃት የለውምና። እ/ር መንፈስ እንደሆነ እንደኛም ተፈጥራዊ አካል እንደሌለው ካስተዋልን ዘንዳ በብሉይ ኪዳን ዘመን እ/ር አንድን ሰው ማናገር ከፈለገ ወይም ሊገለጥለት ከፈለገ እራሱን በሚታይ ነገር በሚዳሰስ ነገር ለምድር ነዋሪዎች ሊረዱት በሚችሉት በቋንቋቸው ማለትም በዚህ በሚገባው ቋንቋ ወይም ነገር እራሱን ይገልጥ ነበር።
መንፈሳዊውን ነገር በተፈጥራዊው ቋንቋ ካልገለጠው በቀር ለማስተዋል አይቻልምና ለዚህም ነው የራእይን መጽሓፍ ጨምሮ መንፈሳዊውን ነገር በሚወክሉ በምልክቶች ለባርያው አሳወቀው። ስለዚህ በብሉይ ወይም በአሮጌው ኪዳን ተፈጥራዊውን ነገር እራሱን ለመግለጥ ይጠቀም፡ነበር ። ይህም ሆኖ መንፈስ የሆነው ጌታ አጠገባቸው በመካከላቸው ሆኖ ሳለ የሚያየው አልነበረም ውጤቱን ግን ያዩ ነበር። ክርስቶስ ግን ሙሉ መገለጡ ነው። ወንድም ቢኒ 5/30/2019