
ከውይይት የተጠቀሰ፤ Binyam TA ሰላም ወንድሜ ብዙነህ፤ ልክ ነህ አንተ ባልከው መአዝንም ማየት ይቻላል። መርሳት የሌለብን በልጅነት ክብር መግዛት በዘመናት የተወሰነ የእ/ር አጀንዳ ነው ልጅነት በአባትነት ይጠቀለላልና። ልጅነት በአባት ከብረዋል ልጅነት ግን አባትነትን አይበልጥም። ልጅነት ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን የአባትነት ክብር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ባስገዛለት በአባት ይጠቀለላል።
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡27 ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን፦ ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው።28 ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል።
ስለ ስም ከአውዱ ሃሳቦች ብቻ እንካ ለማየት ብንሞክር። ከራሱ ስሞች ጋር እያወዳደረ ሳይሆን የሱ ስም #በዚህ#ዘመንም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን #ሊመጣ ባለው #ዘመን ከማንኛውም ስያሜ የተሰጣቸው ሃይላትና ጉልበቶች ሁሉ በዚህ ስም ሃይል እንደ ሂሳብ ስሌት በ0 እንደተባዙ ይቁትጠሩት ሁሉም ጉልበቶች ይርዳሉ ይንበረከካሉ። #አለቅነት፤#ሥልጣናትም፤ #ኃይልም ሁሉ፤ #ከጌትነትም፤ #ሁሉ#በላይና #በዚህ #ዘመንም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን #ሊመጣ ባለው #ዘመን ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ ነው የሰጠው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፥20-21 ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም [age ዘመን aion] ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም [age ዘመን aion] ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፥9 በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም #ይንበረከኩ ዘንድ፥11 መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። ቢኒ።