
እ/ርን ያውቁታል! ታውቁ ዘንድ! ከታናሹ እስከ ታላቁ ሁሉም ያውቁኛል!
በወንድም ቢንያም የተፃፈ። ቁጥር,7/2006 እ.አ.አ.
“ልበ ኑፁሆች ብፁአን ናቸው፥ እግዝያብሄርን ያዩታልና{ያውቁታልና። ማቲ5/8” ያዩታል የሚለው የግሪኩ ቃል ያውቁታል ከሚለው ጋር የአንድ ቃል ስር ናቸው። ማወቅ ደግሞ የመረዳት ወይም የማስተዋል ግዛት ነው። በስጋ አይን ከማየትም ይለያል። “ልበ ኑፁሆች ብፁአን ናቸው፥ እ/ርን ያውቁታል 9:”<blessed are the pure in heart: for they shall see{know} GOD!> {strong’s concordance or vine’s dictionary ,perf. Of 1492} አመሳክር።መፅሀፍ እ/ርን ስለማወቅ ብዙ ፅፎልናል። “የጥበብ መጀመርያ እ/ን መፍራት ነው። ቅዱስንም ማወቅ ማስተዋል ነው። ምሳ9/10} በቀላሉ በፅሀፍ ማስተዋል ማለት ቅዱሱን እርን
ማወቅ ማለት እንደሆነ ያስተምረናል። “መፅሀፍ እ/ርን የሚያውቅ ህዝብ ምስጉን ነው። ”ብሎ ሲያሞካሻቸው በተቃራኒው እ/ርን የማያቁቱን ምናምንቴ ብሎ ይጠራቸዋል። “የኤሊ ልጆች ምናምንቴዎች ነበሩ። እግዚያብሄርንም አያውቁም ነበር።1ኛ ሳሙ2/12 ማስተዋል ያለብን ፍሬ ሀሳብ እ/ርን ማወቅ በራሱ ብርታትን ያበዛል።“ዳን11/32 ነገር ግን አምላካቸውን የሚያቁ ህዝቦች ይበረታሉ።” ይሀውላችሁ ብርታታችን ምን ላይ እንደተመሰረተ እዩ እርሱን በማወቅ ላይ ነው። አላማውን በማወቅ፥ ነገር ሁሉ በቁጥጥር ስሩ እንዳለ ማወቅ፥ በዚህም ምክንያት ምንም ሁኔታዎች አያስፈሩንም። ነገር ግን በነገሮች ሁሉ ላይ የበላይ ሉኡል እንደሆነ እውቅና በመስጠት አይምሮን ሁሉ የሚያልፈው ሰላሙ እውስጣችን ይፀናል። ሀዋርያው በኤፌ1/19“ከሁሉ የሚበልጠውን የሀይሉ ታላቅነት ምን እንደሆነ ታውቁ፤ ዘንድ ነው።” ከማለቱ በፊት የጥበብና የመገለጥ መንፈሱ ደግሜ እላለሁ መንፈሱ የሚመጣው የክብር አባትን በማወቅ ነው። ብሎ ፅፎልናል” የክብር አባት የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የመገለጥና የጥበብ መንፈስ እንዲሰጣችሁ እጠይቃለሁ” ።አስተዋላችሁ የጥበብና የመገለጥ መንፈሱ እሚመጣው ከየት ነው አለ “የክብር አባትን በማወቅ” ሀሌሉያ!
ታውቁ ዘንድ!
ለመሆኑ ታውቁ ዘንድ! ተብሎ የተፃፈልን ምንድ ነው? “ በእ/ር ልጅ ስም ለምታምኑ እናንተ የዘላለም ህይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ ይህን እፅፍላችሀለሁ። 1ኛ ዮሀ5/13 እንዳስተዋልነው “የዘላለም ህይወት እንዳላችሁ” ምን እንል ዘንድ “ታውቁ ዘንድ” ታዲያ ይሄ የዘላለም ህይወት ማለት ምን ማለት ነው? “እውነተኛ አምላክ የሆንከውን አንተንና የላከውን እየሱስን ያውቁ ዘንድ ይህቺ የዘላለም ህይወት ናት። ዮሀ17/3” በእርግጠኝነት የሁሉን የእውቀት ገፅታ ውበት ለማደን በአንዴ የማስተዋልን ቃታ መሳብ እንደማንችል የታወቀ ነው። መንፈሳዊው ነገር ከማስተዋላችን በላይ ግዙፍ ነውና። ደረጃ በደረጃ እንደ አስፈላጊነቱ ግን የታመነው እሱ መንፈስ ቅዱስ ይገልጥልናል ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል። “ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችሀል። ዮሀ16/13” እንደተረዳነው , እውነትን ሁሉ ወደ ማወቅ ሊያመጣን በሚፈቅድ በእርሱ ዘንድ የሚሰራ ልእለ ተፈጥሮ የፀጋው ስራ ነው። ታዲያ የዘላለም ህይወት ማለት እርሱን ማወቅ ማለት ከሆነ ይሄ የዘላለም የእ/ር ህይወት ምንድን ነው? የእ/ር የሁለንተናው ይዞታ እ/ር እራሱ ነው። እ/ር ውስጥ ያለው ሁሉ ነገሩ እና በእ/ር ህይወት ውስጥ እ/ር የሆነውን። ከማስተዋል በላይ የሆነው የሁለንተናው ክብር ተደብቆ ያለው በእ/ር ህይወት ውስጥ ነው። የእ/ር ተፈጥሮ ይዞታው ያለው በእ/ር ህይወት ነው። ጥበቡ እውቀቱ ፈቃዱ ሀይሉ ክብሩ ያለው በእ/ር ህይወት ውስጥ ነው። እያንዳዱ የተሰወረና የተገለጠ የማንነቱ የነፍሱ የመንፈሱ ክብር ነፀብራቅ ያለው በህይወቱ ውስጥ ነው። እያንዳንዱ ነገር ከማይታየው ወደሚታየው ወደ ተግባር ከመገለጡ በፊት ክብሩ ያደረው በእ/ር በህይወቱ ውስጥ ነው። ህያውነቱ ያለው በህይወቱ ውስጥ ነው። እግዝያብሄር ልእለ ተፈጥሮ የሆነ ማንነት የያዘ ነው። ያም ማንነት በህይወቱ ውስጥ ያድራል።
እውነቱ ቢሆን ቅድስናው ቢሆን ብርሀንነቱ ፍቅርነቱ በምህረቱ ባለጠጋ ነቱ ቢሆን ሌሎችም ክብሮቹ እንደ አባይ ፋፋቴ እንደጅረት ዋዋህ እያለ ለፉጥራኑ የሚፈሱት እና ከመልካምነቱ የምያጠግቡት ምንጫቸው ከህይወቱ ዘንድ ነው። መሎከታዊ ችሎታው ሀይሉ ተግባሩ የሚፈነጥቁት ከምንጫቸው ከእ/ር ከህይወቱ ነው። በክብርና በሀይል በግርማ የከበረ አምላክ የሆነበት ምክንያት በክብርና በሀይል በግርማ የከበረ ህይወት ስላለው ነው። እንግዲህ ይሄ ታላቅ የመንፈስ ህይወት ደረጃ በደረጃ ወርሶን የልጁን መልክ ማለትም የክርስቶስ አይምሮ እስክንለብስ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን። 1ኛ ቆሮ3/18 ላይ አስተውል!
“ በአገራችን አባባል ወፍ ቢንጫጫ ባይንጫጫ መንጋቱ አይቀር እንዲሉ ሰው ቢፈቅድ ባይፈቅድ በእ/ር ግዜ ወደ ልጁ ፍጹም መልክ መለወጣችን አይቀሬ ነው። መንፈስ እንደሆነው ጌታ በእ/ር መንፈሳዊ አሰራር ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን። ታዲያ የአምላኩን መልክና ማንነቱን ህብረቱን አምላኩን በሚገባ የሚያውቅ ህዝብ እየበረታ እየበረታ” የሚሄድ ከሆነ እንደ ወንድማችን ጳውሎስ እ/ርን የበለጠ ለማወቅ እንዘረጋለን። “ይህን ሁሉ አግኝቻለሁ ወይም ፍፁም ሆኛለሁ ማለት አይደለም። ነገር ግን ክርስቶስ እየሱስ እኔን የራሱ ያደረገበትን ያን እኔም የራሴ ለማድረግ እጣጣራለሁ። ወንድሞች ሆይ እኔ እንደያዝኩት አድርጌ እራሴን አልቆጥርም ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ። ከሀላየ ያለውን እየረሳሁ ከፊቴ ወዳለው እዘረጋለሁ።…እንግዲህ እኛ ብስለት ያለን ሁላችን ነገሮችን በዚህ ሁኔታ ማየት ይኖርብናል። ፊሊ3//12””
ከታናሹ እስከ ታላቁ ሁሉም ያውቁኛል!
“ከእንግዲህ ማንም ሰው ጎረቤቱን ወይም ወንዱሙን “ጌታን እወቅ” ብሎ አያስተምርም ምክንያቱም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛል።”እብ8/11 ሁላችንም ከታናሹ እስከ ታላቁ ስናውቀው እና ወደ ፍፁም ህብረቱና አንድነት ስንመጣ ያን ጊዜ ህጉ{ቃሉ) በህይወታችን ፍፃሜ አገኘ ይባላል። ህጉምiቃሉ} በውጪ ከተቀመጠበት ትእዛዝነቱ ይቀራል። ህጉ እራሱ የእ/ርን ፈቃድ የሚገልፅ ነው። ይሄም ህጉ ስንበላውና በውስጣችን ሲወሀድ ከማንነታችን ጋር አንድ ሲሆን መንፈስና ህይወት የሆነው ቃል ስጋ ሲሆን ወይም በሌላ አማርኛ ቃሉ ህይወታችን ሲሆን አሊያም ማንነታችን ሲሆን እንደ ጌታ እየሱስ ማሰብና መራመድ እንጀምራለን። እርሱ ለቅፅበትም ህጉ ላይ አመፃን ወይም ሀይለ ኝነትን አላሳየም አባቱ የሚያደርገውን ብቻ ያደርግ ነበርና። ሌላው ለመሳካቱ ታላቁ ሚስጥሩ አባቱ ሲያደርግ ካላየ ምንም አያደርግም ነበር።
የሰው ዘር ሁሉ በዚያ ቦታ ላይ ሲያርፍ ሁሉም ያውቁኛል የሚለው ቃል ሙልአትን ያገኛል። የእያንዳዱ ህይወት በህግና በነብያት በወንጌል በመልክቶች ሁሉ የተፃፈው የእ/ር ቃል በህይወቱ ሲንፀባረቅ ደግሞም ወደ ልጁ ህብረት ከጠራን እ/ር የተካፈልነው መለኮታዊ ባህርዩ ለፍጥረት ሲገለጥ ያን ጊዜ እንደተፃፈልን ሆንን ማለት ነው። ድል ነሺዎች ሁሉ በሙልአት ፀባያችን በፀባዩ እስኪ ወረስ ባህርያችን በባህርዩ እስኪ ወረስ ፈቃዳችን በፈቃዱ እስኪ ወረስ ህይወታችን በህይወቱ እስኪ ወረስ ከክብር ወደ ክብር እየተለወጥን እርሱን እርሱን እስክንመስል ሀይልን በሚሰጠን በእርሱ ልባችንን እንዳሰፋው መጠን በትእዛዙ መንገድ እንሮጣለን።” “ልቤን አስፍተሀልኛልና በትእዛዝህ መንገድ እሮጣለሁ” መዝ 119/32 ተፈፀመ! ሀሌሉያ! አሜን!
እግዝያብሄር ማለት ነው። እ/ርን ያውቁታል! በወንድም ቢንያም
ከወንድም ቢንያም አለማየሁ ስራዎች መሀከል
አቤቱ የሚናገር እግዝያብሄር ቁጥር 1/2003 እትም
እ/ርን ድምፅ መስማት //ጌታ እ/ር በተለያየ ስም እራሱን ለፍጥረት የገለጠበት የአመራር ዘርፍ
እ/ርን መስማት እ/ርን መውደድ ያመጣብናል
እር ሁሉን ነገር የሚያድስበት ዘመን ቁጥር 3/2005 እትም
ጥያቄው የሰው ዘሮች ሁሉ የዘላለም ፍፃሜ ምንድነው?
እ/ርን ያውቁታል! በወንድም ቢንያም
ስማ! የፀጋ ዘመን በቅርቡ ያበቃል ማለትህ ምን ማለትህ ነው?
የሁሉ ነገር መታደስ
ሰው ነፃ ፈቃድ የተነሳ እ/ር ሁሉን ማዳን አይችልም ማለትህ ምን ማለትህ ነው?
ምርጫውው የእ/ር እንጂ የሰው አይደለም!
የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ እግዝያብሄር ቁጥር 4/2005 እትም
ሁሉም ነገር ከእ/ር ነውን? // ስማ የዘላለም ፍርድ ስትል የዘመናት ፍርድ ማለትህ ነውን? // የእ/ርን ፍርድ ሁለት ገፅታዎች
ማወቅ!/ / ስማ የዘላለም ሞት ስትል ምን ማለትህ ነው? ሞት ይሻራልና! // እንደ መፅሀፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞት
ና የእሳት ባህር ፍቺ // ሲኦል በእሳት ባህር ውስጥ ተጥሎ ይደመሰሳልና ዘላለማዊ አይደለም! መፅሀፍትንና
የእ/ርን ሀይል ካወቅን አንስትም! // እ/ር ለኛ ያለው የራሱ ፍቅር!
የዚህ አገልግሎት ውጤቶች በፍቅር ስጦታ ለወገኖች ሁሉ በነፃ የሚታደሉ ናቸው። “በነፃ ያገኛችሁትን በነፃ ስጡ” ተብሎ እንደተፃፈ ቃሉን በዚህ መልኩ ለመፈፀም ለምትፈቅዱ ብሩካን የዚህን የተቀባ ብዕር ኮፒ ቢያንስ ለአምስት ወገኞች አባዝታችሁ እንድታድሉ እናበረታታችሀለን። በክርስቶስ እየሱስ ያለው አይምሮን ሁሉ የሚያልፈው የእ/ር ሰላም እንዲወርስዎ እንፀልያለን። አሜን! ክብር ሁሉ ለቅዱስ ስሙ ይሁን! አሜን!
ማውጫ ፥እ/ር ማለት እግዝያብሄር ማለት ነው። እ/ርን ያውቁታል! በወንድም ቢንያም አለማየሁ ቁጥር,7/2006 እ.አ.አ.