
ከውይይት የተጠቀሰ፣ሰላም ይሁን። ወንድሞች Hassat Engedawork አና Willy Mac ባነስዋቸው ሃሳቦች ወገኖች ብዙ ብላችሁበታል እኔ ከነዚህ ሃሳቦችና ተያያዝ ሃሳቦች ማጠቃለያ ላክልበት ። ሰው መንፈሳዊ ፍጡር ነው የፈጠረውም መንፈስ ነው ምንጩ እ/ር ነው ያለ እ/ር መንፈስ በአጭር ቋንቋ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ የሰው ድንካኑም ወደ አፈር ይመለሳል። መቼም እ/ር አለ ማለት ሆነ ነው አይዋሽምና። ከማይታየው ማንነቱ የሚታየውን ፍጥረትን ሁሉ ፈጠረው ማለት የማይታየው እራሱ እ/ር ነው። የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና ሲል እውነት ነውና። ሁሉ ከእርሱ ወጥተዋል በእርሱ ይኖራል በእርሱ ያበቃል ማለትም እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆል ከዛም የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል። የዮሐንስ ራእይ 10፡7
ስለ መንፈስ ቅዱስ ከተስፋ አንጻርም ብናየው ሆነ እስትንፋሳችን ከመሆኑ አንጻር ብዙ ማየት ይቻላል። “ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ #መንፈሴን በሥጋ ለባሽ #ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ” የሁሉ ትርጉም ሁሉ ነው። ተስፋውን አሁን እያስጨበጠ ነው። መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ እስካለ ድረስ የማይፈስባቸው ካሉ ብረት ለባሾች እንዳይሆኑ እሰጋለሁ የሉም እንጂ። በቅድምያ በብሉይም ሰው መንፈስ እንዳለውና ያለ መንፈስ ቅዱስ ዋጋ እንደሌለው በቃሉ እናስተውል ልዩነቱ የእ/ር መንፈስ በመረጠው ላይ በሃይል መስራቱ ነበር ባልተመረጡት ደግሞ በውስጠ አዋቂነት በህይወት የመኖራቸው ምስጢር እ/ር መንፈስ እራሱ ነው። መጽሐፈ ኢዮብ 27፡3 እስትንፋሴ በእኔ ውስጥ፥ #የእግዚአብሔርም #መንፈስ #በአፍንጫዬ ውስጥ ገና #ሳለ። አስተዋልከው? #የእግዚአብሔርም #መንፈስ #በአፍንጫዬ ውስጥ ገና #ሳለ።? መጽሐፈ ኢዮብ 34፡14 እርሱ ልቡን ወደ ራሱ ቢመልስ፥ #መንፈሱንና #እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፥ 15 ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ ሰውም ወደ አፈር ይመለሳል። ምን ምን አለ የሰው ወይስ የራሱን #መንፈሱንና #እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፥? ለፈጣን ጆሮና በማስተዋሉ ለማይዘገይ እውነቱ ይህ ነው። መጽሐፈ ኢዮብ 32፡8 ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጣል። መጽሐፈ ኢዮብ 12፡10 የሕያዋን ሁሉ ነፍስ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናት። መጽሐፈ ኢዮብ 26፡4 ይህንስ ቃል በማን እርዳታ ተናገርህ? የማንስ መንፈስ ከአንተ ዘንድ ወጣ? መጽሐፈ ኢዮብ 32፡18 እኔ ቃል ተሞልቻለሁና፥ በውስጤም ያለ መንፈስ አስገድዶኛልና። ሰቆቃው ኤርምያስ 4፡20 በእግዚአብሔር የተቀባው[መሲሁ፤ ክርስቶስ]፣ የሕይወታችን እስትንፋስ። ምን ምን አለ ማነው የህይወታችን እስትንፋስ? ክርስቶስ! የሕይወታችን እስትንፋስ ነው፤ የዚህ ሃሳብ ማወፈርያ ሃሳብ ይህን አስተውሉ። የሐዋርያት ሥራ 17፡25 እርሱም #ሕይወትንና #እስትንፋስን #ሁሉንም #ለሁሉ #ይሰጣልና አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም። 26-27 ምናልባትም #እየመረመሩ #ያገኙት እንደ ሆነ፥ #እግዚአብሔርን #ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም #ከእያንዳንዳችን #የራቀ #አይደለም። 28 ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ፦ እኛ ደግሞ #ዘመዶቹ[ግሪክ፡ his offspring ዘሮቹ፤ ሃረጉ ነንና፤ ትውልዶቹ፣ ልጆቹ] ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ #በእርሱ #ሕያዋን ነንና #እንንቀሳቀሳለን #እንኖርማለን።
መጽሃፍ ምን ይላል? በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ እግዚአብሔርም ነበረ። በቃል ውስጥ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ሁሉ ብርሃን ነበረች። በቃል ውስጥ የሰው ሁሉ ሕይወት የሰው ሁሉ ብርሃን ታጭቀዋል። ይህ ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም መጣ ስጋ ለብሶ ተገለጠ እንጂ በዓለም ውስጥ ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ የሆነ ነው፥ ዓለሙም ሁሉ ኝ አላወቀውም። የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ #ወገኖቹም[ወገኖቹ ብርሃናቸው የሆነው ሰው ሁሉን ነው እንጂ የጁዲህዝም ቡድንን ብቻ የሚያሳይ አይድደለም] አልተረዱትም።የዮሐንስ ወንጌል 1፡1-9
ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፦ በአንተ #አሕዛብ #ሁሉ #ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ። እናስተውል ወንጌሉ #የመንፈስን #ተስፋ #በእምነት እንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ #አሕዛብ ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ። እምነትን የሰው ስራ አደረከው። #ማሳመን #የእግዚአብሔር #ሥራ ነው ። “የዮሐንስ ወንጌል 6:29 ኢየሱስ መልሶ። ይህ #የእግዚአብሔር #ሥራ እርሱ በላከው #እንድታምኑ ነው አላቸው።” John 6፡29 Jesus answered and said unto them, This is the #work of #God, that ye #believe on #him whom he hath sent.
#አብ #ካልሳበው ወደ ጌታ እየሱስ አንተን እኔን ጨምሮ ማንም መምጣት አይችልም። “የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 :44 የላከኝ አብ ከሳበው #በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥”
እኛ የዳነው “በእምነታችን በኩል በጸጋ ነው” (ኤፌ 2 8), ነገር ግን ከእግዚአብሄር እስካልተሰጠን ድረስ እምነት የእኛ አይደለም. ሮሜ. 12: 4, “እግዚአብሔር ለእያንዳንዱም የእምነትን መጠና አካፈለው ለገሰው” እግዚአብሔር ለእኛ እምነት ከሰጠን በኋላ የእኛ ይሆናል! በጣም ቆንጆና ቀላል ሆኖ ልንረዳው ከምንችለው በላይ ባለመፃፉ ደስ ይላል።
‘ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ መጀመሪያ በኵራት የሆነው ክርስቶስ፣ ከዚያም በኋላ እርሱ ሲመጣ የክርስቶስ የሆኑት። ‘ 1 ቆሮንቶስ 15:22-23
አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስ ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል አለው። ‘እኔ ግን ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን #ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ[ እጎትታለሁ: በጡንቻ በሃይል to drag , muscular ።” ዮሐንስ12:32 #ሁሉ ወደ ራሱ ጎትቶታል ስቦታል።
አንዳንዶች የተቀላቀለ ጥያቄ ያቀርባሉ ሁሉም ድነትን ተቀብሎ ከሆነ ምስክር መሆንና ወንጌልን መስበክ ለምን አስፈለገ? ይላሉ። በተጨማሪም እ/ር ሁሉን የሚያድን ከሆነና ሲኦልም ሞትም በእሳት ባህር የሚደመስሰው ከሆነ ለምን እናመልከዋለን እንደልባችን አንሆንም የሚሉ መተላለፍን በዋንጫ ለመጨለጥ የሚናፍቁም አሉ። ይህ የሚያሳየው እ/ርን የሚከተሉት ፍርድና ሲኦልን ፈርተው እንጂ ለእ/ር ፍቅር ስላላቸው እንዳልሆነ ከልባቸው የተገለጠው ሰልፍ ያሳያል። በብሉይ ኪዳን የታቦቱ ማደርያ ድንካን በ16 የብር ችካሎች ተወጥሮ የጸና ከመሆኑ የተነሳ የመጣ ነፋስ አይነቀንቀውም ነበር። የአዲስ ኪዳን ማደርያ ድንካኑም የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ ሲለን sixteen characteristics of love እያሳያን ነው። በ16 የፍቅር ፍሬዎች ወይም ችካሎች የጸና ሊሆን ይገባል። An overcomer Son may possibly go through life without demonstrating or manifesting the gifts of the Spirit although this is not likely to be true or to happen but love is absolutely indispensable it’s absolutely necessary for Sons.
1ፍቅር ይታገሣል፥ 2ፍቅር ቸርነትንም ያደርጋል፤ 3ፍቅር አይቀናም፤ 4ፍቅር አይመካም፥ ወይም አይታበይም፤
5ፍቅር የማይገባውን አያደርግም[ጋጠ ወጥ አይደለም]፥ 6ፍቅር የራሱንም አይፈልግም፥ 7ፍቅር አይበሳጭም፥ 8ፍቅር በደልን አይቆጥርም፤ 9ፍቅር ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል 10ፍቅር ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ 12ፍቅር ሁሉን ይታገሣል፥ 13ፍቅር ሁሉን ያምናል፥ 14ፍቅር ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ 15ፍቅር በሁሉ ይጸናል።16ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤
ወደ ተለመደው የደህንነት ጥያቄ ስንመለስ እያንዳንዱ በራሱ ተራ ስለሚድን ማለትም ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ተራውን ስለማናውቅ ወንጌልን እንሰብካለን።ለሁሉም ሰዎች የእግዚአብሔር ፍቅር ይሰበካል ይታወጃል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፤ የእውነትን ቃል በቅንነት ማስተዋልና መለየት፤ እውነትን በፍቅር ማስተማር፤ በክርስቶስ ተቀባይነትን፤ እና ይቅርታን ለማድረስ እንጥራለን! የእግዚአብሄር ትግስት ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ እንደሆነ እናውቃለንና።
አሁንም አስተውል ሃጣያተኛው በራሱ ንስሃ ሊገባ አይችልም እ/ር ካልሰጠው በቀር። ለሕይወት የሚሆን ንስሐን የሚሰጠው እ/ር ብቻ ነው። እንግዲህ ትምክህትህ ከየት ነው የሚመካ በእ/ር ይመካ። “የሐዋርያት ሥራ 11፡18 ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና፦ እንኪያስ እግዚአብሔር #ለአሕዛብ ደግሞ #ለሕይወት የሚሆን #ንስሐን #ሰጣቸው እያሉ #እግዚአብሔርን አከበሩ።”
መዳን በእምነት ነው በእርግጥም እውነት ነው! ጥያቄው የሚዳንበት፡ እምነት መንፈሳዊ ንጥረ ነገሩ ምንጩ ማነው? ነው ጥያቄው። ሰው ሁሉ በአዳም ወገብ ውስጥ ሳለ ከአዳም ጋር ተባብረህ ሃጥያት ሰርተሃል የእ/ር ክብርም ጎድሎሃል። ደግሞም በሃጥያታችሁና በበደላችሁ ሙታን ናችሁ ከተባለ ዘንዳ። ሙታን ፈቃድ አላቸውን? በእነሱ ዘንድ ዕውቀት አለን? “መጽሐፈ መክብብ 9/5 …ሙታን ግን አንዳች አያውቁም!” ወይስ የእምነት ፋብሪካው ሰው ነውን? ከየትስ መጣ ከሰው ውስጥ እንደ ድማሚት የፈነዳ ከእ/ር ያልሆነ በሰው ውስጥ ያለ ከሰው የተዘጋጀ ነውን? ወይስ ምንጩ ከእ/ር ነው? እንደ ሚጥሚጣ የሚያቃጥለው ጥያቄው ያነው።መቸም ይገባችሃል የምናወራው መንፈሳዊነገር ነው። ለመንፈሳው ሰው ሁሉ ነገር መንፈሳዊ ነውና በማስተዋሉም ፈጣን ነውና እቀጥላለሁ እውቀት አስተዋዮች ካልሆነ ለቸልተኞች የተከለከለ ነውና። በቅድሚያ ሙታን እንኴንስ እምነት ሊኖራቸው በቅድሚያ ከሙታን በትንሳኤው ሃይል መነሳት አለባቸው። ከሙታን የሚነሱት በእ/ር ሃይል ብቻ ነው! ከዛም ቅደም ተከተሉ ይቀጥላል። እሱ ብቻውን …ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ ነውና። “ወደ ሮሜ ሰዎች 4/16 …ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ የሚጠራ ።”
ታዲያ በኤፌሶን ያላሉት የምስራቹን ከሰሙ ቡሃላ አምነዋል አሁን በክርስቶስ ኢየሱስም ቁዱሳን ሳይባሉ ገና ሃጥአን ሳሉ መንፈሳዊ ሙታን፡ ሳሉ እምነቱን ኬት አመጡትና አመኑ? በቅድምያ ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጥቶ ከሙታን አስነሳቸው። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2-5 ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን – ሙታን- እንኳ -በሆንን -ጊዜ- ከክርስቶስ -ጋር -ሕይወት -ሰጠን፥ -በጸጋ -ድናችኋልና፥ ”
“ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3/1 … ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ” “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2-12 … ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ” እምነት በተፈጥሮው መንፈሳዊ ነው መንፈስም ነው። እምነት የሚመነጨው ከእ/ር ቃል ነው ቃሉ ደግሞ መንፈስና ህይወት ነው። እምነት በዜግነቱ መንፈሳዊ ነው “2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4/13 ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤” ታድያ የእምነት መንፈስ ካለ መንፈሱን የሚሰጥ ማነው?በእርግጥም መንፈስ የሆነው እ/ር ነው!ዮሃ4/24 “ወደ ገላትያ ሰዎች 3/2 ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ፤ በሕግ ሥራ ወይም ከእምነት ጋር በሆነ መስማት መንፈስን ተቀበላችሁን? 3 እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን? 5 እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ …. ለኤፌ ሰዎች ሲናገር “መንፈስን የሚሰጣችሁ ….ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥” ማስተዋል ያለብን እምነት ከእ/ር ዘንድ የተሰጠ ወይም የታደለ ነው። 1ኛ “….ለቅዱሳን አንዴና ለመጨረሻ ስ-ለ ተ-ሰ-ጠ-ው እ-ም-ነ-ት እንድትጋደሉ ለመምከር እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።”ይሁዳ 1:3 Jude 1/3 the- faith -which -was -once -delivered unto- the- saints። Did you see that Bro. faith was -once #delivered from God unto- the- saints.
አዲሱ መደበኛ ትርጒም እምነት ከራሱ ከእ/ር የተሰጠ ነው! (KJV)Jude 1:3 for the faith which was once delivered (የታደለ፣ ) unto the saints.
(Jude 1:3 [Weymouth]) the subject of our common salvation, I find myself constrained to write and cheer you on to the vigorous defense of the faith #delivered once for all to God’s people.
(Jude 1:3 [YLT]) concerning the common salvation, I had necessity to write to you, exhorting to agonize for the faith once #delivered to the saints,
(Jude 1:3 [Webster]) Beloved, when I gave all diligence to write to you concerning the common salvation, it was needful for me to write to you, and exhort you that ye should earnestly contend for the faith, which was once #delivered to the saints.
2ኛ በሌላ ቃል ደግሞ እንየው ብዙ ማብራራት ቃሉ አያስፈልገውው የቃሉ ስልጣን በራሱ ይናገራልና። “ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3 እግዚአብሔር ለ-እ-ያ-ን-ዳ-ን-ዱ የ-እ-ም-ነ-ት-ን መ-ጠ-ን እ-ን-ዳ-ካ-ፈ-ለ-ው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።” እምነት ከእ/ር የተካፈልነው ነው! ስለዚህ [ግሪክ] ሁሉ ከእርሱ ወጥተዋል በእርሱ ይኖራል በእርሱ ያበቃል። አሜን።
መንፈስ ቅዱስ የእየሱስ ወይም የጳራቂላጦስ ክብር እስከሆነ ድረስ። በመንፈስ ቅዱስ ኅይል ፍጥረት ሁሉ ኢየሱስ ጌታ ነው ብሎ ይድናል። “1ኛ ወደ ቆ ሮንቶስ ሰዎች 12/3 ….በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ። 1Cor 12/3 ….that no man can say that Jesus is the Lord, but by the Holy Ghost” እናስተውል በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቆናል አሁን ጠላቶቹ የሆኑት አድስዋቸው ከክርስቶስ ስልጣን ስር ሲጠቀለሉ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ሆነው ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ ለበጉ ክብርን ተንበርክከው ይሰጣሉ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2/10ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥11መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።
“የዮሐንስ ራእይ 5/13 በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ። Rev 5/13 And every creature which is in heaven, and on the earth, and under the earth, and such as are in the sea, and all that are in them, heard I saying, Blessing, and honour, and glory, and power, be unto him that sitteth upon the throne, and unto the Lamb for ever and ever.”
እንግዲህ የመጨረሻው ጠላይ ሞት ከነ መውጊያው ከሃጥያት ጭምር ሲደመሰስ እ/ርም እራሱን ለፍጡራኑ ሲገልጥለት መቶ በመቶ ፈቃደኛ ሆኖ እያለቀሰ በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በመንፈስ ቅዱስም ሆነው በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ይላሉ።። አሜን!!! ትንቢተ ኢሳይያስ 11፡9 ..።ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና ትንቢተ ዕንባቆም 2፡14 ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለችና። ኤፌሶን1፡9 በክርስቶስ ያቀደውንም የፈቃዱን ምስጢር እንደ በጎ ሐሳቡ እንድናውቅ አደረገ። 10በዘመን ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ያለው ሐሳቡ በሰማይም በምድርም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ሥር ለመጠቅለል ነው።ወንድም ቢኒ።