የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ታሪክ መረዳት። Understanding Bible Translations History


Understanding Bible Translations History የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ታሪክ መረዳት። የእግዚአብሔር አስደናቂ ረቂቅ ስራ በመፅሀፍ ቅዱስ ዋናው ፅሑፎችና የትርጉሞች ታሪካዊ ገፅታ በጠለቀ ጥናት ላማቅረብ ተሞክረዋል።
በዘልማድ ስልሳ ስድስቱ መፅሀፍት በመባል ከሚታወቁት መካከል ከዘፍጥረት እስከ ሚልክያስ የአሮጌው ኪዳን መፅሀፍት በመባል ይታወቃሉ። ከማቲዮስ ወንጌል እስከ የሀንስ ራእይ አዲስ ኪዳን በመባል እንደ ሚታወቁ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነው። ቅዱሳት መፅሀፍት ሁሉ የእ/ር መንፈስ ያለባቸው ናቸው። ለማስተማር ለመገሰፅ ለማቅናት በፅድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ። ይሀውም የእ/ር ሰው ለመልካም ስራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው። 2ኛጢሞ3/1617 መፅሀፍ ቅዱስ የተቀደሰ ወይም የተለየ ማለት ነው። ይሀውም የቅዱሳት መፅሀፍ መዝገብ ነው። ከላይ እንዳስተዋልነው መፅሀፉ የአርጌው {የብሉይ} ኪዳን እና የአዲስ ኪዳን ጥምር ነው። እነዚህ እ/ር እራሱ የመረጣቸውን በመንፈሱ እየነዳ ያፃፋቸው ናቸው።2ኛ ዮሀ1/2021.ተመልከት። “ የአዲስ ኪዳን ፁሁፎች ከአሮጌው ኪዳን ፁሁፎች ውስጥ ከእ/ር ዘንድ በመጣ መጠነ ሰፊ መገለጥ የተመሰረቱ ፅሁፎች ናቸው። አዲስ ኪዳን ለፍጥረት ያለውን መልክት ለመረዳት የፍጥረት ውድቀትና የፍጥረት መታደስን ሁሉን በተገቢው ለማስተዋል ከአሮጌው ኪዳን ምንጩን ማንበብ ተገቢ ነው። አዲስ ኪዳን የተፃፈው በታወቀው የቀድሞው ጊዜ የአውሮጳ ቋንቋ በግሪክ ዘየ ነው። የኣሮጌው ኪዳን የተፃፈው ሴማዊ ቋንቋ በሆነው እብራይስጥና አረሚክ ነው። ከ strongs vine dictionary ከመቅድሙ {መግቢያው} የተጠቀሰ። እንግዲህ እነዚህ ዋና ፁሁፎች ኦርጂናል) አሮጌው ኪዳን ከ1400-400 አመተ ክርስቶስ ልደት በፊት በልዩ ልዩ ቦታዎች አርባ በሚያህሉ ፀሀፊዎች እንደተፃፈ ይታመናል። አዲስ ኪዳን ደግሞ ከ40-96 እንግዲህ እነዚህ ዋና ፁሁፎች ኦርጂናል} አሮጌው ኪዳን ከ1400-400 አመተ ክርስቶስ ልደት
በልዩ ልዩ ቦታዎች አርባ በሚያህሉ ፀሀፊዎች እንደተፃፈ ይታመናል። አዲስ ኪዳን ደግሞ ከ40-96 አመተ ምህረት በስምንት ሰዎች ተፃፈ። እስከ 2000 እኤአ ድረስ በነበረው ጥናት መሰረት መፅሑፉ በሙሉ ወይም በከፊል ከ2100 ቋንቋዎች በላይ ተርጉመዋል። መፅሀፍ ቅዱስ በተለያየ ቋንቋዎች መተርጎማቸው ሰዎች የእ/ርን ቃል በገዛ ቋንቋቸው አንብበው እንዲረዱ ይጠቅማል። በአገራችን የመፅሀፍ ቅዱስ ታሪክ ስንመለከት ዛሬ ላለንበት ደረጃ ኣያሌ የእ/ር አገልጋዮች በመሰጠትና የቻሉቱን ሁሉ መስዋእት በማድረግ ከዛ ተወራርዶ እዚህ ዘመን ደርሰናል። “በእትዮጵያ አምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጡ ተሰአቱ ቅዱሳት ቅዱሳት መፅሀፍትን ወደ ግእዝ እንዲተረጎሙ አደረጉ።
ከእነሱ ዘመን ቀደም ብሎ አንዳንድ መፅሀፍት በነአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሀን {በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጥረት ተተርጉመዋል። ከዚያም ወዲህ አባ ሰላማ መተርጉመ መፅሀፍት {በ14ኛው መቶ ክፍለ
ዘመን} በትርጉም ስራ ብዙ ደክመዋል። በኢትዮጵያ በእንድምታ ትርጋሜ የደከሙ ሊቃውንት ምን ጊዜም ቅዱሳት መፅሀፍትን ወደ አማርኛ ሳይተረጉሙ አልቀሩም። እነ ጴጥሮስ ሄይሊንግ በከፊል ነጠላ ትርጋሜ ሲያዘጋጁም መፅሀፍ ቅዱስን በሙሉና በነጠላ ትርጋሜ ወደ አማርኛ የተረጎመ አብርሀም {አባ ሮሜ} የሚባል መነኩሴ ነበር። ይህ ትርጉም በመፅሀፍ ቅዱስ ማህበር በኩል በ1816 አ.ም. አራቱ ወንጌላት በ1821 አ.ም. ሙሉው መፅሀፍ ቅዱስ ታትሞ ወጣ። የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋ በሚያውቁ አንዳንድ የውጪ አገር ዜጎች {ለምሳሌ ማርቲን ፍላድ} ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባበር ትርጉሙን #ካሻሻሉ ቡሀላ በ1878ኢም እንደገና #ታርሞ ታተመ። ከጣሊያን ወራራ ቡሀላ
የቀድሞው ትርጉም #እንዲታረም ስለታሰበ ብዙ ሊቃውንት ከደከሙበት ቡሀላ 1953 አም አዲሱ ትርጉም ታርሞ ወጣ። ዛሬ በብዙ ሰዎች እጅ የሚገኘው ይሀው ትርጉም ነው። ከዚያም ቡሀላ የኢትዮ መ. ቅ ማህበር ቀለል ባለ አማርኛ በ1980 አም. አዲስ ትርጉም አሳተመ። አለቃ ተወልደ መድህን ገብሩ መፅሀፍ ቅዱስን ወደ ትግርኛ፤ የወለጋው ተወላጅ ኦኔሲሞስ ነሲብም ወደ ኦሮምኛ ተርጉመዋል። ከኢትዮ መ.ቅ. ማህበር የመፅሀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ከገፅ95
የተጠቀሰ። እንዲሁም ቀለል ባለ አማርኛ የህያው ቃል ተተርጉመዋል። በ1993 አ.ም. ቀጥሎም ከአገራችን ትርጉሞች እስካሁን ከተሰሩት ለየት ባለ መልኩ በብዙ ድካምና ጥረት አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነማጥኛው ታትመዋል። ይም ሁሉ የክብር አምላክ እ/ር ይክበር ከላይ ለተሰጣቸ ነገር ለተጉ ወገኖች የሚመሰገን ስራ ነው እንላለን። የጻድቅ ሃብቱ ትጋቱ ነውና።

እንግዲህ ከዚህ እንደ ምንረዳው ከቋንቋ ተለዋዋጭ ባህርይ የተነሳና ትርጉሞቹ ፍፅምናን ይዘው ባለመተርጎማቸው ለእርማት ሲባል የትርጉም ስራዎች በብዙ ጥረትና መስዋእት በየጊዜው ተሻሽለው እንዲተሮጎሙ ግዴታ ሆነዋል። በአንድ ወቅት በህዝቡ ቅቡል የነበሩ ትርጉሞች የተሻለ የቋንቋ መረዳት ያለው ወገንና ትውልድ እ/ር ሲያስነሳ ከዋናው ከእብራይስጡና ከግሪክ ጋር ያለው ቀጥተኛ ሀሳብ እንዲያቀብሉ አድርጎ በመተርጎም ተደራስያኑ የእ/ርን ቃል እውነት ፍቺ እንዲያገኙት ለማድረግ ሲባል የትርጉም ስራዎች ማካየድ ምንኛ አስቸጋሪ እንደሆነ ከአገራችን የትርጉሞች የታሪክ ሂደት ከሞላ ጎደል አስተውለናል።
የምንፈልገው ነጥብ ጋር ለመምጣት የአማርኛ ትርጉም የታሪክ ገፅታ ማየት ብቻ ሳይሆን የአማርኛ ትርጉሞች የተሰሩት የእብራይስጡንና የግሪኩን ዋና ፅሁፎች በመጠቀም ብቻ ሳይሆን የታወቁ የእንግሊዝኛ ትርጉሞችን በመጠቀም ጭምር በመሆኑ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ታሪካዊ ሂደት መዳሰስ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። የተለያዩ ጥንታውያን መጽሃፍትንና እንዲሁም ጸሃፍያን በመመርመርና በማጥናት ለማህበረሰባች በሚገባ መልኩ ቀለል ባለ አማርኛ ያስተውሉ ዘንድ ከብዙ በጥቂቱ ከረጅም ባጭሩ ቀነጫጭበን አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን ለማቅረብ እንጥራለን። {በዚህና በሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች የሰፋ መረዳት ለማግኘት “አቤቱ የሚናገር እ/ር” በወንድም ቢንያም አለማየሁ የተፃፈውን ያንብቡ)።
“ትምህርትና እውቀት እየበዛበት የመጣበት የነበረው ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ቡሀላ ነበር። ብርሀኑ መታየት የጀመረው ግን ከ14ኛው ክፍለ ዘምን ቡሀላ በጆን ዊስሊ ህይወት ነበር። ይህ ሰው የኦክስፎርድ ዩንቨርስቲ ኩራት የነበረ ሰው ነበር። ለቀኑ ከሁሉ የላቀ ሊቅና በእንግሊዝ አገርም ተፅኖን የሚያያመጣ ሰባኪ ወይም ተናጋሪ ነበር። በብዙ ስብከቱና ፁሁፉ ፖፑን ፀረ-ክርስቶስ እያለ በአደባባይ ይቃወማቸው ነበር። የእውነት ቃል ታፍኖ በሀይማኖት ዘዴ በመቸርከሙ እውስጡን አስቆጥቶት ነበርና። ይህም ድፍረቱ የዚያ ዘመን የሃይማኖት መሪዎች እንደሚያደርጉት በእንጨት ላይ ተሰቅሎ እንዲቃጠልላቸው እጅግ ይሹ ነበር። ነገር ግን አንዳንድ የንጉሳዊ ቤተሰቦች ዘንድ እ/ር በአይናቸው ፊት ሞገስን እንዲያገኝ ስላደረገ የቤተ ክርስቲያን ምኞት እንዳይፈፀም እንቅፋት ሆነ። ጆን ዊስሊ ከሚያነሳቸው ነጥቦች መካከል ቤተ ክርስቲያን እውነተኛው የእ/ር ቃል እንዳይሰበክ ለራስዋ የሚመች አድርጋ አፍና ይዛለች የሚል ይገኝበታል። ስለ አንድን ነገር ተገንዝቦ ነበር። የተፃፈውን የእ/ር ቃል ለስጋዊ ፈቃዳቸው ለማስፈፀም ሲሉ ቃሉን ከንቱ ያስቀሩታል።{Great Voices of the reformation,h.e,pg.18 የተወሰደ።) ሰዎች እደ ንፁህ ወርቅ የነጠረ የሆነውን ቃሉን ወስደው በመጠምዘዝ ብረት አልብሰው የሞት የእግር ብረት ያደርጉታል። ከዛም ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው የብዙ ትውልዶችን አመለካከት አጨልሞ ቢይዝም እ/ርን እውነቱን
ገፅ 10 መፅሀፍትንና የእ/ርን ሀይል ካወቅን አንስትም! የእግዚአብሔር አስደናቂ ረቂቅ ስራ በመፅሀፍ ቅዱስ ዋናው ፅሑፎችና የትርጉሞች ታሪካዊ ገፅታ። በወንድም ቢንያም አለማየሁ
ከመግለጥ አላስቆመውም። በዚያ በጨለማው ዘመን ነገሩ በጆንዊስሊ አላበቃም በጆን ሁስ ጊዜ እንዲሁም በማርቲን ሉተር እ/ር ብርሀኑን ለመግለጥ በሀይል ተጠቅሞባዋቸዋል። ትውልዳቸውም ላይ በእውነት አለት ወድቀውበታል።
እ/ ር ዛሬም አገልጋዮችን የእሳት ነበልባል አድርጎ እየሰራ ነው። መዝ104/3። ዊልያም ተንደል {1492-1536} እ/ር ህዝቡን ከጨለማው ዘመን ለማውጣት ከተጠቀመባቸው አንዱ ነበር። ይህ ሰው የእብራይስጥና የክሪክ ቋንቋዎችን በሚገባ ጠንቅቆ አጠና። በዚያን ዘመን የተገኙትን ጥቂት የብራና መፅሀፍትን በማጥናት ብዙ ጊዜ ያጠፋ ነበር። በዚህም ቤተ/ክ የምትጠቀምበት ትምህርት ሁሉ ምንኛ ስህተት እንደሆነ በተገኙት ጥቂት ብራናዎች በሚገባ ተገነዘበ። በዘመኑ በነበረ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ኣዲስ ኪዳንን ተረጎመ። ትርጉሙን ለማሳተምና በተራው የእንግሊዝ ህዝብ እጅ ለማስራጨት ተስፋ አድርጎ ነበርና። ነገር ግን የለንደኑ ቢሾፕ ዘንድ ድጋፍ ስላላገኘ በለስ ሳይቀናው ቀረ። እንዲያውም ለስደትና ለብዙ መሰናክል ምክንያት ሆነበ ። ቤት/ክ መጽሓፍ ቅዱስ በረራው ሰው እጅ ቢገባ ግራ መጋባትንና እውነትን ካወቁም በቤተ/ክ ደንብ ላይም የስራት መፋለስን ብሎም የመመን አመጽን ያመጣል በማለት ተቃውመዋን አወጀች ።
ከዚህ ቡሀላ ነበር ይሄ ሰው ዊትንበርግ ጀርመን በመሰደድ{1483-1546 እኤአ} መፅሀፍ ቅዱስን ወደ ጀርመንኛ የተረጎመውን ማርቲን ሉተርን የተገናኘው። በሉተር እርዳታና ማበረታታት የእንግሊዝኛን ትርጉም ጨርሶ አሳተመና ወደ እንግሊዝ ላከ። ይህም የሀላህላ ሂወቱን አስከፍሎታል። በወቅቱ ወደ እንግሊዝ አልተመለሰም። በትርጉም ስራው የእውነት የብርሀን ፀዳል በመፈንጠቁ ቤተ/ክ እጅግ ተበሳጭታ ነበርና አሳልፎ የሚሰጠውን ጋደኛውን አዘጋጀችለት። ጋደኛውም ለጥቅም ሲል በቅጥፈት የህዝቡን ደስታ በማየት ቤተ/ክ ሃሳብዋን ቀይራ እንደተደሰተች ዋሽቶት ወደ ለንደን ተመልሶ መጣ። ወደ እስር ቤትም አገቡትና ከዚያም octobe 6,1536} ሰምአት ሆነ።
ከዛም በመቀጠል ማይልስ ኮቨርደል ሌላኛው የእውነት ብርሀንን ስላፈነጠቀ ስቃይ የደረሰበት ሰው ነበር። ተንደል ከሞት ቡሀላ ይህ ሰው የሱን ስራ ዋልታ በማድረግ እናም የሉተር የጀርመኑን ትርጉም በመሞርከዝና በመታገዝ የተመሰረተ የመጀመርያውን ሙሉ የእንግሊዝኛ ትርጉም አሳተመ። ንጉስ ሄነሬ ስምንተኛ የተንደልን መፅሀፍ ቅዱስ ትርጉም ክፉኛ የተቃወመው ነበር። ‘ መፅሀፍ ቅዱስ በተራው እንግሊዝኛ ተተርጉሞ በተራው በእንግሊዝ ህዝብ እጅ መግባቱ አላስፈላጊ ነው። በቃሉ ላይ በሚኖራቸው እምነት ወይም ክህደት ምክንያት ለበላይ ባለስልጣናት ለእብሪተኝነት ምክንያት ይሆናል። “ብሎ ያስብ ነበርና። በባህልና በሰዋዊ ወግ እንዲሁም በስልጣን ወንበር ላይ ቁጭ ያሉ የሚቆጣጠሩት መሪ ከቁጥጥራቸው ውጪ እንዳይሆን በመፍራት እ/ርን የሚወግኑ በመምሰል በተቻለ ሴራ ሁሉ በመጠቀም ስራዎችን ሊቀጩ ካልቻሉም ስደትን በማምጣት ባገኙት አጋጣሚ የቅዱሳንን ደም ያፈሱ ነበር። ይህ ሁሉ መከራ በቅዱሳን ላይ እያለፈም የእ/ር ቃል ግን እያሸነፈ ይመጣ ነበር።
በ1537 ጆን ሮጆር የታንደል ተባባሪ የነበረ ማቲዮስ መፅሀፍ ቅዱስ በመባል የሚታወቀውን ትርጉም አሳተመ። ይህ ሰው የኢብራይስጥ መረዳት ስላልነበረው 2/3 ከተንደል ደግሞም 1/3 ከኮቨርዳል ነበር የተጠቀመው። ይህ ሰው በመጨረሻ1555 ላይ ሰምኣት ሆነ። ከሁለት አመት ቡሀላ ቶማስ ካርንመር የተባለ ሊቀ፟-ጳጳስ የክርስቶስ እውነተኛ ትምህርት ላይ አዘንብለሀል ተብሎ በእንጨት ላይ ተቃጥለዋል። በ1560 ጄኔቫ መፅሀፍ ቅዱስ በመባል የሚታወቀውን አንድ የሊቃውንት ቡድን በጄኔቭ ሆነው ሰሩ። ሁለተኛውም እትሙ በ1652 ታተመ። ይህም ነበር የመጀመርያው ከእንግሊዝኛ ትርጉሞች በብራና መልክ ወጥ ፅሁፍ የነበረውን መፅሀፍ ቅዱስ ለአንባብያን እንዲመች ለመጀመርያ ግዜ በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው። ከዚህ ቡሀላ ሲሾፑ መፅሀፍ ቅዱስ የተባለው ትርጉም ነበር በመስመር ላይ የነበረው። በወቅቱም የጄነቫ መፅሀፍ ቅዱስ ታዋቂነቱ ገንኖ ነበር። የእንግሊዝ ቤተ/ክ ባለስልጣናትም ለህዝቡ ለቤተ/ክ አሰራርና ደንብ የሚያስገዛ የትርጉም እትም እንዲታተም አዛለች ብለው አወጁ። ሊቀ ጳጳስ ፓርከር በጠቆሙት መሰረት የቀድሞ እትሞችን መሰረት በማድረግ የቢሾፕ መፅሀፍ ቅዱስ የተባለው ተሰራ። ከኪንግ ጀምስ መፅሀፍ ቅዱስ በፊት የመጨረሻዎቹ እትሞች በመባል የሚታወቁት ሪየምስ አዲስ ኪዳን{1582} እናም ዶይ አሮጌው ኪዳን እትም [1609] ሲሆኑ ሁለቱም የሮማ ካቶሊክ እትሞች ነበሩ። እስከ የቅርብ ጊዜው ሞንሲግኖር ሮናልድና ኤ.ኖስ እነዚህ ሁለቱ እንደ አንድ መፅሀፍ ቅዱስ በሮማ ካቶሊክ ዶይ መፅሀፍ ቅዱስ ተብለው ብቻቸውን ተቀባይነት አግኝተው በካቶሊክ ዘንድ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል።
ይህም የኪንክ ጀምስ መፅሀፍ ቅዱስ ሲሰራ የአዲስ ኪዳኑ ላይ በብዛት ከተጠቀሙበት አንዱ ነው። አሁን እንግዲህ ከትርጉሞች ሁሉ ወደር የሌለው ስራ የተሰራበት የኪንግ ጀምስ መፅሀፍ ቅዱስ ትርጉም የምናስተውልበት ጊዜ ነው። ንጉስ ጀምስ በ1605 በእንግሊዝ አገር የስልጣን ኮርቻ ላይ በተፈናጠጠ ጊዜ እራሱና ህዝቡ በሀይማኖት ቀውስ ላይ በግራ መጋባት ተመትው በባህር ወጀብ ላይ እየተንዋለሉ አገኘው። ቀውሱንም ስርአት ለማስያዝ ተስፋ በማድረግ የቤተ/ክ ሰዎችን ስብሰባን ጠራ። ጠቃሚ አስተያት የተሰጠው በሁሉ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ኣዲስ ትርጉም እንዲሰራ ነበር። ለቤተ/ክ አሰራር እንቅፋት የማይሆን ስራ እንዲሰራ አዘዘ። ይህንን የተቃወሙ ነበሩ የንጉሱ ትዛዝ ነውና ስራ ተጀመረ። ለትርጉም ስራውም አርባ ሰባት ካህናትና ሊቃውንት ተመረጡ ። ቡዱኖችም ለስድስት ተከፍለው ተመደቡ። እያንዳዱ በየግላቸው ከሰሩ ቡሀላ ከዛ የቀሩት ቡድኖች እስከ ሚስማሙ ድረስ ስራውን ይሰሩ ነበር።
ከሰው ልጅ የብስለት እርከን ውስንነት የተነሳ የሰው ስራ ነውና ለማረም እንዲመች አንዱ ክፍል ሲያልቅ ለሌላኛው ለትችት ወይም ለነቀፌታ ይቀርባል። በመጨረሻም ሁለት ቡዱኖች የሁሉን ከሰሙ ቡሀላ ሁሉን እንዲስማማ ይሰሩት ነበር። ይህ መጽሐፍ ሲሰራ የቢሾፕ መፅሀፍ ቅዱስ ትርጉም እንዲጠቀሙ ተገደው ነበር። ምክንያቱም የአሮጌው ኪዳን ሲተረጉሙ የጥንታዊ እብራይስጥ ቅጂዎች ነበራቸው። ነገር ግን እስከ 1628 እ.አ.አ. ድረስ በግሪክ ቋንቋ በእጅ የተፃፉት የብራና መጣጥፍ በሙልአት ወደ እንግሊዝ ገና አልገቡም ነበር። ስለዚህ የኪንግ ጀምስ መፅሀፍ ቅዱስ ተርጋሚዎች ትልቁን ሀላፊነቱን ሲወጡ ፍፅምና በሌላቸው የቀድሞ ትርጉሞች በብዛት ተጠቅመዋል።
በዚህም ምክንያት ነበር በ1760 ዎቹ ሰዎስት ሺህ ህዳግ መግለጫዎች ወደ ትርጉሙ የተጨመሩት ። አሁንም እንካን በትርጉሙ ላይ ላሉት ስተቶች ቃል በቃል ከዋናው እንዳለው ቢታረም መፅሀፉን እሱ ነው ብለን አንለየውም። አርባ ሰባቱ ሊቆች ለአስር አመታት አስገራሚና አስደቃቂን ስራ ሰርተዋል። በውበቱ በዘየው እስከዛሬ ከተሰሩ ትርጉሞች እንደሱ አልተሰራምና። በሰው እስከ ተተረጎሙ ድረስ አንዳንድ ጥቃቅን የሆኑ ግድፈቶች ወይም ወሳኛ ስተቶች አይገኙም ማለት ግን ሞኝነት ነው። `የተጠቀው ተፈፀመ። ለዚህም ነው መፅሀፍ የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል ብልህ ግን አካየዱን ይመለከታል : ምሳሌ 14/15″ የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል። የሚለው። ብዙ ክርስቲያኖች ከማየት የወደቁበት ችግር ማንኛውም የአማርኛም ይሁኑ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ወይም መነሳሳት በቀጥታ የተፃፉ ያለመሆናቸውን ነው። የዋናው የእብራስጥና የግሪኩ መጣጥፎች ብቻ በነብያትና በሀዋርያት በመንፈስ ቅዱስ እየተነዱ የተፃፉት እንጂ ትርጉም ትርጉም ነው። እንግዲህ ኦርጅናሉ ወይም ዋናው ፅሁፎች አሮጌው ኪዳን በእብራይስጥ አዲሱ ኪዳን በግሪክ ከተፃፈ ዘንዳ ከ2100 ቋንቋዎች በላይ በአብዛኛው የእብራይስጥና የክሪክ ቋንቋ በሰለጠኑ ሊቃውንት የተተረጎሙ አስደናቂ ስራዎች እንደሆኑ ነገር ግን ፍፁም እንዳልሆኑ በማስተዋል መጠቀሙ ይረዳናል። ልባም የሆነና እራሱን የእ/ር ቃል ተማሪ አድርጎ የሚቆጥር
ማድረግ ያለበትን ማወቅ አለበት። ጥሩ የሆኑ መፅሀፍት ለምሳሌ {yaung’s or strong’s concordance} በመግዛት ወይም ቤተ መፅህፍት በመሄድ ወይም ኦንላይን ላይ በማሰስ እንዴት እንደ ሚጠቀም ማወቅ ከዛም መጠቀም መጀመር አለበት። እንዲሁም ጥሩ የግሪክና የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላትን ኦንላይን ላይ በማሰስ ወይም በመግዛት ለምሳሌ {Emphatic Diaglott or strongs VINES dictionary} የቃላቶችን ፍቺ በራሱ መገንዘብ መጀመር አለበት። ከዛም ስለ ብዙ ነገር እኔም ብሆን ሊላ ስጋ ለባሽ ስለሚለው ነገር በእርሱ አይደገፍም። ተፈፀመ!
መፅሀፍትንና የእ/ርን ሀይል ካወቅን አንስትም! የእግዚአብሔር አስደናቂ ረቂቅ ስራ በመፅሀፍ ቅዱስ ዋናው ፅሑፎችና የትርጉሞች ታሪካዊ ገፅታ ። በወንድም ቢኒያም አለማየሁ ቁጥር 5/2005 G.C.[ Gregorian calendar በግሪጎሪያን ቀን መቁጠሪያ] U.S.A

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal