
Discussion Quotes፡ Binyam TA አባት የሲኦል ጌታ መሆኑን በተግባር አሳይተዋል። በኖህ ዘመን የነበሩት የማይታዘዙት እ/ር 120 አመት የታገሳቸው እና የፈረደባቸው ፍጻሚያቸውን በቃሉ ስታስተውለው ወደ ሴኦል እራሱ ከቶ እራሱ አወጣቸው ። ጌታ እየሱስ ከሞቱና ከትንሳኤው ቡሃላ በኖህ ዘመን አልታዘዝ ያሉት አመጸኞች በእስራት ለነበሩትን ነፍሳትን (spirits መናፍስትን) ሰበከላቸው። ለነሱም የማስታረቁን ቃል ይዞላቸው ወረደ። የሚያሳየንም ክርስቶስ ለሃጢያታቸው መሞቱን ብቻ ሳይሆን መነሳቱም ለመጽደቃቸው መሆኑን ነው።
ይህንን ቃል Weymouth’s translation. ከተባለውን ትርጉም እናስተውል 1Pe 3:18 Christ also once for all died for sins, the innocent One for the guilty many, in order to bring us to God. He was put to death in the flesh, but made alive in the spirit, in which He also went and proclaimed His Message to the spirits that were in prison, 1Pe 3:20 who in ancient times had been disobedient, while God’s longsuffering was patiently waiting in the days of Noah during the building of the Ark, in which a few persons–eight in number–were brought safely through the water.”
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3 ፡18 ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥ 19 በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት(spirits መናፍስትን) ሰበከላቸው፤ 20 ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።
የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።” እነዚህ ለየት የሚያደርጋቸው ( spirit መንፈሳቸው) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር እንደ መመለስ ፈንታ እ/ር አሰራቸው። ጌታም ሄዶ በኖህ ዘመን የእግዚአብሔር ትዕግሥት 120 አመታት ያስጨረሱትን በኖኅ ዘመን አልታዘዙም ለሚላቸው ወንጌልን ሰበከላቸው። ለምን ወንጌሉን መስበክ አስፈለገው?
እዛው ወረድ ብሎ በ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡6 መልሱን ይነግረናል።
በነገራችን ላይ መጽሐፍ ቅዱስ በብራና መልክ የተዘጋጀ ወጥ ፅሑፍ ነበረ። ለአንባቢያን እንዲመች በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው በ1560 ጄኔቫ መጽሃፍ ቅዱስ በመባል የሚታወቀው አንድ የሊቃውንት ቡድን በጄነቭ ሆነው ሰሩ። ሁለተኛው እትሙም በ1652 ታተመ ይህ ነበር የመጀመርያው የእንግሊዝኛ ትርጉም በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው ።
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡6 ስናስብ የተያያዘ ጽሁፍ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ቃሉን አስተውሉ!“እንደ ሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና።”
የሃዋሪያው መልእክት ግልጽ ነው። ስጋቸው በተመለከተ ሙታን ናቸው። ህያዋን ሆነው ያሉት በመንፈስ እንደሆነና ታስረውም እንዳሉ ወንጌሉ ተሰበከላቸው። መገንዘብ ያለብን በሲኦል የዘላለም ስቃይ ይጠብቅሃል ተብለው አይደለም የተሰበከላቸው። ነገር ግን ወንጌል “የምስራች መልካም ዜና የእ/ር ኁይል ለማዳን ነው” የተሰበከላቸው።በስጋቸው ሳሉ ሃጢያታቸው የከፋ ስለ ነበር እ/ር ጎርፍ ልኮ በውሃ በማስጠም በጎርፉ ጠራርጎ ወደ ሲኦል ወሰዳቸው በዚያም ለዘላለም ሳይሆን ያሰራቸው ለሁለት ሺ ሶስት መቶ ሃምሳ ዘመናት ታሰሩ። “እንደ ሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው የሚለን ያንን ነው ። በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ በሲኦልም ላይ ስልጣን ያለው ጌታ ሄዶ ወንጌልን ሊሰብክ ሄደ እንጂ ለቫኬሽን አልሄደም ወንጌሉም የእ/ር ታላቅ ስራ ፍርዱ የዘላለም ሳይሆ በዘመናት ወስጥ የተወሰነ እንደሆነ እናስተውላለን ። በዚህም በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ሆኑ። ማንም ሲናገር እንደእ/ር ቃል ይናገር። አሜን!
ኢሳ 29/9 ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩት ጽድቅን ይማራሉና:> በአለም ያሉ ሁሉ ጽድቅ ተምረው ታይቶ ይታወቃልን ስለዚህ ይህ ገና የሚፈጸም ትንቢት ነው።> when thy judgments are in the earth , the inhabitants of the WORLD will learn righteousness .[uprightness & right standing with GOD.] Isaiah 26/9 አስተዋላቹሁን ፍርዱ በአለም ሲገለጥ ምንን ይማራሉ ይላል? ጽድቅን! እንግዲያውስ ፍርዱ Correctional judgement የሚያርም ፍርድ ነው። ሃሌሉያ!
Ps 130፡4 But there is forgiveness with thee, that thou mayest be feared ትፈራ ዘንድ በአንተ ዘንድ
ይቅርታ አለ። አሜን። BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING, WRITINGS