በጌታ ጸጋና እውቀት ራስ ወደ ሆነው ክርስቶስ ማደግ። ወንድም ቢኒ።


በጌታ ጸጋና እውቀት ራስ ወደ ሆነው ክርስቶስ ማደግ። ወንድም ቢኒ።

«2 ጴጥ3/18 ነገር ግን በጌታችንና በመድሃኒታችን በእየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤አሜን።»

«በጌታችንና በመድሃኒታችን በእየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ» የሚገርም ቃል ነው። ለአማኞች ሁሉ የማያቃርጥ ተግዳሮት ቢኖርብን በጌታችን ጸጋና እውቀት ለማደግት ያለው ሂደት ነው። ማደጋቹ በነገር ሁሉ ይደግ ይገለጥ #ራስ #ወደ #ሆነው #ክርስቶስ #እደጉ፤ ስለማደግ  የእ/ ቃል ብዙ ያስተምረናል። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:15 ነገር ግን #እውነትን #በፍቅር እየያዝን #በነገር #ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን #ወደ #ክርስቶስ #እንደግ፤” ከእነዚህ አንዱና  ዋንኛው አስፈላጊ ነገር በአማኞች ህይወት ውስጥ ልናድግብት ያለ ከመንፈሳችን ውስጥ በሚወጣው  ህይወት መኖር መለማመድ ነው፡ ከአይምሮ ብቻ ሳይሆን ከዚያም ባሻገር  የክብር ተስፋ ካለው በውስጣችን ካደረው ከክርስቶስ ህይወት መቅዳት ይበዛልን ዘንድ በዚህም እርሱ እውቅትና መረዳታችን ይሆንልናል።

ይህ በኛ አውን ይሆን ዘንድ የስጋዊው ሰው ሃሳብ  መፍረስና  አይምሮን ደግሞ መማረክን  ሁለቱን ያጣመረ ተግባርን ያዛል። ‹2ኛ፣ ቆሮ 10/5 የሰውንም ሃሳብ በእግዚያብሄርም እውቃት ላይ የሚነሳውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳላን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን።> ብዙ ግዜ ይህን ሃሳብ ከውጪ ላሉት እንጠቀምበታለን ተቀዳሚ መልክቱ ግን በእኛ ውስጥ ስጋ በመንፈስ መንፈስም በስጋ ላይ በለው የእሽቅድድም ትእይንት የሚያመለክት ነው። ለምን ስጋዊው አስተሳሰብ መፍረስ አይምሮ ደግሞ ይታዘዝ ዘንድ መማረክ አስፈለገው? ምክንያቱም <ስለስጋ ማሰብ ሞት ነውና ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ህይወትና ሰላም ነው።ሮሜ 8/6  <For to be carnally minded is death; but to be spiritually minded is life and peace.> ስጋዊ አይምሮ መያዝ ሞት ነው። በቀላሉ የሞት ፍቺው ነው። ጌታ ደግሞ ሞትን ሊደመሥሥ ምጥተዋልና። ምንፈሳዊ አይምሮን መያዝ በአንጻሩ ህይወትና ሰላም ነው። የክርስቶስ አይምሮ ህይውትና ሰላም ነውና።

  እኛ ደግሞ የክርስቶስ አይምሮ አለን፡ <But we have the mind of Christ.1Cor 2/16የእ/ ልጅነታችን ከምልክቱ አንዱ በዚህ አይምሮ ለመጠቀም ማደጋ መቻላችን ነው። ያም ማለት የክርስቶስ አይምሮ በመንፈስ የሚመራ እንደሆነ እናስተውላለንና እኛም እንደዚሁ ይጠበቅብናል፡፡ <ማቲ3/16 የእ/ መንፈስ ወረደብት> ከዛም  ማቲ4/1 መንፈስም ይፈተን ዘንድ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው> ክዛም በመንፈስ ሃይል ተምለሰ፡ አገልግሎቱም የጌታ መንፈስ በኔ ላይ ነው ብሎ ከጀመረ ቡሃላ መንፈስ ከሆነው አባቱ ዮሃ4/24 ለመሳካቱ ሚስጥር የሆነው ከአባቱ የሚሰማውን የሚያየውን ብቻ ያደርግ ስለነበር ነው። የራሱን ፈቃድ አንዳች እንኻን አያደርግም ነበር።

አባቱ ሲያደርግ ካላየም ዝም ይል ነበር አንጂ የራሱን ፈቃድ አላደረገም።  < በእግዚያብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእ/ ልጆች ናቸው ሮሜ8/14> ልጅነትና መንፈስ ቅዱስ የተያያዙ ናቸው። በእ/ መንፈስ ከመመራት ውጪ የእ/ ልጅነት የለም፡   

መንፍሳዊ እድገት የአይምሮ ጅምናስቲክ ውጤት አይደለምና፡  መመራታችን በበዛልን ልክ እድገታችንም ተገቢው ህይደትና ውጤታማም እድገት ይታይበታል። ጌታ<በማቲዮ 6/27 ከእናተ በመጨነቅ (በማሰብ) መቁመቱ ላይ አንዳች መጨመር አይችልም> ብልዋል በተፈጥራዊው ሰው አስቦ ቁመቱ ካላደገ ያም ማለት የምድሩን ካልቻለ ማለት ነው በመንፍሳዊው ላይማ አይታሰብም።< ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው።ዮሃ3/6> ጳውሎስ ይህን ቀጽሎ ሲያስረዳን < በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ ገላ5/25  በዚህ በመንፈስ መኖርና መመላለስ ውስጥ ብዙ የምንማረው የምናውቀው አለ። ስለ መመላልስ፤ ስለመስማት፤ ስለመናግር፤ በእውነት በመንፈስ ያለው የየእለት ህይወት እውን ከሆነልን የከበረ ነገር ነው።

 <በሮሜ8/5 እንደ ሰጋ ፈቃድ የሚኖሩ የስጋን ነገር ያስባሉና እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉእንደ ምናስተውለው ሁለት አይነት ሰዎች ሃሳባቸው የተቀመጠብትን ናያለን፡ እነዛ ባልተቀደሰ የስጋ ፍላጎት ላይ ሃሳባቸውን ያስቀመጡና የስጋን ምኞቱን የሚፍጽሙ ደግሞም በተቀደሰው የመንፈስ ፈቃድና ፍላጎት የሚኖሩ ሃሳባቸው የተያዘው በመንፈስ ነገር ላይ እንደሆነ እናስተውላለን። በስጋ ግዛት የሚኖሩ ባልተቀደሰው የስጋ ፍላጎት ቁጥጥር ስር ናቸው። በአንጻሩም በመንፈስ ገዛት የሚኖሩ በተቀደሰው በመንፈስ የሚመሩም እንዲሁ ናቸው።

ለመሆኑ በመንፈሳችን ውስጥ  ምን ስላለ ነው / ደጋግሞ ለዚህ የውስጥ ህይወት ህያው እንድንሆን ደጋግሞ በተለያየ መልኩ የሚናገረንና የሚያስተምረን/ በህይወታችን ምንን ስላስቀምጠ ነው? አዎን መንፈሳዊ ሃብት ወይም መዝገብ ስላስቀመጠ ነው። ይህም ሁብት ወይም መዝገብ ክርስቶስ ነው። ‹ በትንቢተ ኢሳ45/3 በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ / እኔ እንደ ሆንኩ እንድታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መምዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሃብት እሰጥሃለሁ› ጌታ ነው የሚናገረው ስውር መዝገብ እሰጥሃለሁ የተደበቀችን ሃብት እሰጥሃለሁ፡ ለምን? በስምህ የምጠራህ / እንደሆንኩ ታውቅ ዘንድ። ምንድን ናቸው እነዚህ በትንቢት የተነገሩ መዝገብና ስውር ሃብቶች?

በቆላ2/2-3 ልባቸው እንዲጸናና በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደ ሚገኝ ወደ መረዳት ባለጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእ/ርንም ሚስጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ። የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና። አሁን አወቅን / ሃብት መዝገብ እያል ግድ የሚለው የእ/ ጥበብና እውቀትን ነው፡ እነዚህም በየሱስ ክርስቶስ ተሰውረው ተቀምጠዋል በቆላ1/27 ቀደም ብሎ የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናተ ውስጥ ነው ብሎ ላዘመናት ተሰውሮ የየተደበቀውን ሚስጢር ገልጦላቸዋል። አስተዋልን/ በእኛ ያስቀመጠው ነገር አለ ክርስቶስ በእሱ ውስጥ ደግሞ ሃብትና መዝገቡ ታጭቆ አለ ውደ ብስለት ግዛት ማደጋችን ይህን ሃብት መጠቀም ያስችለናል።

ምሳሌ2/3 ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት ለማስተዋልም ድምጽህን ብታነሳ እርስዋንም እንደ ብር ብትፈልጋት እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት የዚያን ጊዜ /ርን መፍራት ታውቃለህ የአምላክህንም እውቀት ታገኛለህ» ሃብቶች ምን እደሆኑ አስተዋልን እውቀት፤ ማስተዋል፤ የአምላክህን እውቀት ሃሌሉያ ታገኛለህ! ይሄ ሃብት ነው በክርስቶ ተሰውሮ ያለው እለት እለትም ከዚህ በውጣችን ካለው የክብሩ ሃብት እንደ በሰሉ ልጆች መጠቀም እንችል ዘንድ / ያሳድገናል።1ኛ፣ቆሮ3/7  እንግዲህ የሚያሳድግ / ነው እንጂ የሚተክል ቢሆን የሚያጠትጣ ቢሆን አንዳች አይደለም።እንግዲህ የክርስቶስ አይምሮ ካለን ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ያደምጥ እንደ ነበር ማድመጥ አለብን።‹  ቆላ2/18 አካል ሁሉ በጅማትና በማሰርያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠምም እግዚያብሄር በሚሰጠው ማደግ ያድጋልየሚያሳድገን መንፈሳዊ ምግብ የምናገኘው በዚሁ መልክ ነው፡  በእ/ መንፈስ የሚመሩ እነሱ የእ/ ልጆች ናቸውና ልጅነታችን የተመረኮዘውም በዚህ የምንፈሱ ህይወት በመጠቅምና ለማደግም መልሱ ያለው በውስጣችን ካለው መጣመር ነው። መታዘዝ ከመስዋእት ይበልጣል!

 መንፈስ ለቤተ/ የሚናገረውን ከሰማን ለዘመናችንና ለትውልዳችን ድል ነሺዎች ነን። “እ/ር ግን እውቀትና ጥበብን ይሰጣል” ጥበብን ለጠቢባን እውቀትን ላስተዋዮች” ዳንኤል ላይ። ለገዛ ዘመናችንም ልንጠቀምበት የተገባውን ምክርና ጥበብ ማስተዋልም የአምላካችንም እውቀት ቢሆን ከኛ አይሰወርም ከእርሱ የተነሳ እናድጋልን   ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ከእ/ አፍ ተዘጋጅት በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂየበላ ያድጋልና መንፈሳዊ እንጀራና ውሃ የሁነውን እለት እለት እንመገብ።  በማስተዋላችንም ፈጣኖች አንሆናለን። ሃሌሉያ! ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውሃ ነው አይምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል። ምሳ»20/5  ብርታታቸው ከእ/ የሆነና አማካሪያቸውም በምክሩ ድንቅና ግሩም የሆነው / የሆነ ምንኛ ብጹአን ወይም ደስተኞች ናቸውአሜን! ወንድም ቢኒ። Posted on April 1, 2011 ።

 

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal