#በክርስቶስ #ኢየሱስ #ባለው #የሕይወት #መንፈስ #ሕግ በአይምሮ የመታደስ ሂደት


#በክርስቶስ #ኢየሱስ #ባለው #የሕይወት #መንፈስ #ሕግ በአይምሮ የመታደስ ሂደት)ወንድም ቢኒ።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:16 እንዲያስተምረው የጌታን ልብ[#አይምሮ #mind] ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ[#አይምሮ #mind]  አለን።1Cor 2:16 For who hath known the mind of the Lord, that he may instruct him? But #we #have #the #mind #of #Christ.

 

እ/ር የመለኮት መንፈሳዊ የህይወት ህግ ያለው ነው። ይህ #ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ይለያል። መንፈሳዊ የህይወት ህግ የሚሰራው በመንፈሳዊ ህግ ነው ይህ ህግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነጣ ያወጣን ነው።  “ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡2 #በክርስቶስ #ኢየሱስ #ያለው #የሕይወት #መንፈስ #ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና።Rom 8፡2 For the law of the Spirit of life in Christ Jesus hath made me free from the law of sin and death” እ/ር በሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ምን አለ? አዎ አርነት አውጥቶናልና ሁለት ህጎች እናያለን 1ኛ, የሕይወት መንፈስ ሕግ 2ኛ, ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ችግሩ ከጥያትና ከሞት ነፃ የሚያወጣን የሕይወት መንፈስ ነው ነፃ የሚያወጣን ተብለን ነው የተነገረን እኛም ተቀብልነው። ሁሉም የራሱ ድርሻ ቢኖራቸውም በዚህ ነጥብ ላይ ስናተኩር ግን እውነቱ #የሕይወት #መንፈስ ብቻ ሳይሆን #የሕይወት #መንፈስ #ሕጉ ነው ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት  የሚያወጣው። የሕይወት መንፈስ በኔ ላይ ነው ይሄ ሃይል ይሄ ቅባት አለኝ በእኔ ያለው የእ/ር ህይወት ነፃ ያወጣኛል እንላለን ያ በራሱ መልካም ቢሆንም በሙላት “እውነት የሆነውን አስቡ” እንደ ተባልን እውነቱ ግን የሕይወት መንፈስ ሳይሆን ነፃ የሚያወጣን የሕይወት መንፈስ ህጉ ነው ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት የሚያወጣን። አንዱ ህግ በሌላው ላይ የበላይ ዘር ወይም ስልጣን አለው ብቻ ሳይሆን የበላይ ስልጣን ነው። አንድ ወንድም ታልቅ የእ/ር ሰው እንዳስቀመጡት፤ “ህግ ስንል ምን ማለታችን ነው? ምሳሌ መጠቀም እንችላለን ። The low of gravity ሲባል ሰምታችሃል፣ የመሬት ስበት ህግ ለምን ህግ ሆነ ለምን ሰበት ብቻ አልሆነም?ለምን  ህግ ሆነ ህግስ ሰንል ምንድን ነው? ህግ ሲባል ማንኛውም በተፈጥሮ ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ በተመሳሳይ ሁኔታ የሚከሰት ነው። ምንም ብታባብሉት ስራውን በተመሳሳይ ሁኔታ ከመከሰት አያቆምም።

እህን ብእር ብጥለው ህግ ስለሆነ ይወድቃል ስበት ያስገድደዋልና ነገ ብሞክር ህጉ ይስበዋል። ወደላይ አይመለሰም ስለዚህ ሀግ ይሰራል ማለት ነው። ሁሉም ህግ ይሰራል ይሰመርበት እንድታስተውሉ ህግ ይሰራል። አንዳንዴ የሚሰራ ሌላ ግዜ የማይሰራ ህግ አይደለም። ሁሉም ህግ ይሰራል ህግ የለማቃረጥ የሚሰራ ነውና። ማድረግ ያለብህ ህጉን በተግባር ላይ ማዋል ነው ህጉም ይሰራልሃል። ከህጉ ጋር በስምምነት መጠቀም ነው። ህጉን ግን ሃይለኝነት ብታሳየው ህጉ በልዩ መንገድ ይገጥምሃል

 

 

እ/ር ፍቅር ነው። የእርሱ እውነተኛ ፍቅሩ ፍቅር ነው ፣እ/ር መንፈስ ነው ስለዚህ ፍቅር መንፈስ ነው። እ/ር የፍቅር ተቃራኒ አይደለም እ/ር ፍቅር ነው!አለቀ መርሳት የሌለብን ግን ያ የፍቅር ማንነቱ አቋሙን አያስቀይረውም እ/ር የሚባላ እሳት መሆኑ ነው። “ዕብራውያን 12፡29አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።Heb 12;29 For our God is a consuming fire ”

አስተዋላቹ እ/ር ፍቅር ነው። እ/ር የባላ እሳት መሆኑ ነው። ለእ/ር ፍቅር እንዳላችሁ ዝምድና አይነት ፍቅሩን ትለማመዱት አላችሁ ለፍቅሩ በቅንነት ምላሽ ብንሰጥ በረከቱን፡ሰላሙን፤ ደስታውን ፤መዋጀቱን፣ ቸርነቱን፣የዋህነቱን በጎነቱን ምሪቱን ጥበቃውን ሞጎስን ወዘተ ተጠቃሚዎች እንሆናለን። ፍቅሩን (አቢዩዝ)ብናሰቃየው ግን ወደያው ፍቅር በሌላ መንገድ ትለማመዱታላችህ፡ በእሳትነቱ አሁንም መርሳት የሌለብን ፍቅር መሆኑን ነው። ወደ “ዕብራውያን 12፡29አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።Heb 12;29 For our God is a consuming fire ” የእ/ር ቁጣ ወይም መአት ለማረም ፣ለማትራት ለማጽዳት ለማንጻት ለማቅናት ወደ ጽድቅ ለመለስ ለመግራት ፣የልብን ሸለፈት ለመግፈፍ ይገለጣል። አባት ያለምክንያት ለማረም ካልሆነ በቀር ልምጭ አያነሳም። ምን እያልን ነው እ/ር የሚሰራው በመንፈሳው ልእለ ተፈጥሮ ህጉነው የሚሰራው እጉን በስራ ላይ ብታውሉት ይሰራል ህጉን ብትጥስ ህጉበስራቱን አያቆምም ። ህግን የምታሸንፉት ለህግ በመገዛት ነው። ለናተ አግዞ ይሰራል በማይተዘዙ የልጆች አመጽ ሲሰራ ህጉ በተቃራኒው ይሰራል ትፋቱ ሲያልቅ ግን ህጉእነሱን በመቃወም ቢሰራም ለነሱጥቅም እ/ር አሁንም እየሰራ እንደነበር ታስተላላችሁ ለእ/ር መንፈስ በመገለጥ እቢ ካልክ በተግባር ትምህርት ቤት ያስገባሃል።

 

“የያዕቆብ መልእክት 1፡7-8 ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው።

Jas 1፡7 For let not that man think that he shall receive any thing of the Lord.8 A double minded man is unstable in all his ways.”   በአይምሮ መታደስ የሚመጣው ለውጥ፣ መሰረታዊ ስለሆኑ የእዚአብሄር መንገዱን አሰራሮችን እናያለን። ለውጥ አለ ያለውጥ የሚመታው በአይምሮ መታደስ ነው፤ ይህም አንዱ መለኮታዊ የእ/ር መንፈሳዊ ህግ ነው። ስንቶቻቹ እ/ር በባሪያዎቹ መንገዱን ሁሌ እንደሚገልጥ ታስተውላላችሁ?።

“መዝሙረ ዳዊት 103፡7 ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ ለእስራኤል ልጆችም አደራረጉን።Ps 103፡7 He made known his ways unto Moses, his acts unto the children of Israel.” ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል

A double minded (GR- soo-khos ነፍስ)man is unstable in all his ways ሁለት አሳብ (አይምሮ ነፍስ) ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል

ስንቶቻችሁ ሁለት አይምሮ ነፍስ ያለው ግለሰብ አይታችሃል? አንድ አይምሮ ነፍስ ሳለን እንዴት ሁለት ይለናል። እ/ር መንፈስ ሆኖ ሳለ ነፍስ እንዳለው በጽሃፍ አስተውላችሃል

ኦሪት ዘሌዋውያን 26፡11 ማደሪያዬንም በእናንተ መካከል አደርጋለሁ ነፍሴም አትጸየፋችሁም።Lev 26
11 And I will set my tabernacle among you: and my soul shall not abhor you.

ኦሪት ዘሌዋውያን 26፡30 የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ የፀሐይ ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።Lev 26፡30 And I will destroy your high places, and cut down your images, and cast your carcases upon the carcases of your idols, and my soul shall abhor you.

መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2:35 የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።1Sam 2:35 And I will raise me up a faithful priest, that shall do according to that which is in mine heart and in my mind: and I will build him a sure house; and he shall walk before mine anointed for ever.

 

ትንቢተ ኢሳይያስ 42፡1 እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።Isa 42፡1 Behold my servant, whom I uphold; mine elect, in whom my soul delighteth; I have put my spirit upon him: he shall bring forth judgment to the Gentiles.

ትንቢተ ኤርምያስ 5፡9 በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?

የማቴዎስ ወንጌል 12፡18 እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።

Matt 12፡18 Behold my servant, whom I have chosen; my beloved, in whom my soul is well pleased: I will put my spirit upon him, and he shall shew judgment to the Gentiles.

መጽሐፈ ምሳሌ 6፡16 እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለችProv 6፡16 These six things doth the Lord hate: yea, seven are an abomination unto him:

17 ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
18 ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
19 በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።

ኮንኮርዳንስ ብታዩ እ/ር ነፍስ እንዳለው ታስተውላላእሁ እ/ር መንፈስ እንደሆነ ስቶቻችሁ ታስተውላላችሁ?እ/ር ሰው እንዳልሆነ ታውቃላችሁ ። እ/ር መንፈስ እንደሆነ ነፍስ እንዳለው ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ?መንፈስ ነፍስ እንዳለው ታስተውላላችሁ ። ከኔ ጋር ናችሁ ?1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች2፥6 በበሰሉት መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፥ ነገር ግን የዚችን ዓለም ጥበብ አይደለም የሚሻሩትንም የዚችን ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም፤we speak wisdom among them that are perfect

አንድ ነገር በመጽሃፍ ስናስተውል ነፍስ ሶል minde will imotion disier አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ ክፍል እደሆነ እናውቃለን

በነፍስህ ፈቃድም መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 28፡9 አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና፥ የአባትህን አምላክ እወቅ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው ብትፈልገው ታገኘዋለህ ብትተወው ግን ለዘላለም ይጥልሃል።And thou, Solomon my son, know thou the God of thy father, and serve him with a perfect heart and with a willing mind: for the Lord searcheth all hearts, and understandeth all the imaginations of the thoughts: if thou seek him, he will be found of thee; but if thou forsake him, he will cast thee off for ever.

*የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና፥ የአባትህን አምላክ እወቅ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው ብትፈልገው ታገኘዋለህ ብትተወው ግን ለዘላለም ይጥልሃል።

ነፍስ ትመኛለች desireth መጽሐፈ ምሳሌ 13፡4 የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች አንዳችም አታገኝም የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።Prov 13፡4 The soul of the sluggard desireth, and hath nothing: but the soul of the diligent shall be made fat.

 

ስንቶቻችሁ እ/ር አይምሮ እንዳለው ታስተውላላችሁ ፈቃድ እንዳለውስ ሰሜት እንዳለውስ GOD gets angry እ/ር ይናደዳል

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡30 ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።Eph 4፡30 And grieve not the holy Spirit of God, whereby ye are sealed unto the day of redemption.

God ላፍስ ፣ እ/ር ይስቃል የሃቴተኛው ቀኑእንደደረሰ አትዋልና እ/ር በሰማይ ይስቃል

እ/ር ደስ ይሰኛል  መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3፡10 ሰሎሞንም ይህን ነገር ስለ ለመነ፥ ነገሩ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው። እግዚአብሔርም አለው፦ ፍርድን ትለይ ዘንድ ለራስህ ማስተዋልን ለመንህ እንጂ ለራስህ ብዙ ዘመናትን ባለጠግነትንም የጠላቶችህንም ነፍስ ሳትለምን ይህን ነገር ለምነሃልና እነሆ፥

የመንፈስ ፍሬ ምን እደሆኑ ታውቃላችሁ የእ/ር ስሜት ናቸው ወንድም በሚሰማኝ ነገር ሳይሆን የምመላለሰው በእምነት ነው ዜና አለኝ ላንተ በሚሰማኝ እመለለሳለሁ ። መጽሓፍ በሚሰማእ እንዳት መላለስ  በእምነት እንጂ እንደማይል?መጽሃፉ ላይ የለም መጽሃፉ የሚነግረን በእምነት መየትን ነው። በእምነት መየትን እንጂ በሚሰማኝ እንዳልሆነ ነው።

ብራዘር የእ/ር ሰላም ፊሊንግ ወይም ፈሚሰማህ ነገር ነው፤ The joy of the Lord is a filing የ/ር ደስታ የሚሰማን ነገር ነው። የእ/ር ትእግስ የሚሰማህ ነገር ነው። በዛ በሚሰማኝ ሰላም፣ ደስታ፣ ትእግስ፣ እምነት፣ እመለለሳለሁ። በዛ ህያው የእ/ር መልካምነት የእ/ር አባቴና አምላኬ ንቃተ ህሊና በሂወቴ ባለ በዛ እምላለሳለሁ። የመንፈስ ፍሬዎች ከእር imoton ጋር የተያያዙ ናቸው።

እ/ር መንፈስ ነው ሆኖም minde will imotion disier አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ አለው። እ/ር መንፈስ ነው ሆኖም ነፍስ አለው። ከማይጠፋው ዘር ከእ/ር የተወለደው አዲሱ ሰው መንፈሳችሁ ነፍስ አለው። አሮ ጌው ስጋዊው ሰው  ነፍስ እንዳለው ታውቃላችሁ ?the mind of the flsh ስጋዊ አይምሮ ፣ መጽሓፍ the will of the flsh የስጋ ፈቃድ ፣ምኞት አትፈጽሙለት ።

የስጋ ሰራ ምን እደሆኑ ታውቃላችሁ ?የስጋ ስሜት መገለጥ ፍሬዎች ናቸው።

የመንፈስም የስጋም minde will imotion disier የመንፈስ አይምሮ፣ የስጋ አይምሮ አለ፣ የመንፈስ ፈቃድም የስጋም ፈቃድ አለ፣ የመንፈስ ስሜት አለ የስጋ ስሜትም አለ፣  የመንፈስ ምኞት አለ የስጋ ምኞት አለ። እያንዳዳቸው የነፍስ ክፍል ናቸው (አሮ ጌው ስጋዊው ሰው  ነፍስ አለው አዲሱ ሰው መንፈሳችሁ ነፍስ አለው።)

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡17 ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው። 1Cor 6፡17 But he that is joined unto the Lord is one spirit.

ወደ ጌታ ህብረት ስንመጣ አንድ መንፈስ ስሆን ወደ እ/ር የነፍሱ ፈቃድም እዋሃዳለሁ። አሁን የእ/ር minde will imotion disier አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ በመንፈሴ አለ ማለት ነው። በተመሳሳይ ጊዜ አሮ ጌው ስጋዊው ሰው  ነፍስ አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ አሉ። ስንቶቻቹ እነዚህ ሁለቱ በውስጣችሁ ሲፈራረቁ አይታችሃል። እውነት ነው አሁን ችግሩን አይደንትፋይ (ለየነው)አደረግነው A double minded (GR- soo-khos ነፍስ፣ ሶል) man is unstable in all his ways ሁለት አሳብ (አይምሮ ነፍስ) ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል።

አሁን ችግሩ ታየ !ሁለት ነፍስ ወይም አሳብ አይምሮ የሚዋልለውን ሰው ኧስተዋልነው እንደ ቴንዱለም ወዲህ ደዲያ ይወዛወዛል የቱን እንደሚጨብጥ ሚስጥር ሆኖበታል።

የትኛውን እንደሚታዘዝ ግራ ይገባዋል ዛሬ ለመንፈሳዊው ሰው ነገ ለስጋዊው ሰው ያድራል በሁለተ መካከል እተፈራረቀከ እተንገላታ ይታዘዛል እንደውሃም ይዋልላል ።

ሮቤል እንደውሃ ይዋልላንና መሪነት አይገባውም ጎራውን ያለየ ጠንካራ አቃም ከሌለው መሪነት?

አስተውሉ፡ ነፍስ ነጠላ ነው። በሌላ አነጋገር አንድ የነፍስ ክፍል ነው ያለን። ምሳሌ እንስጥ ከተባለ ስለአገራችን የስልጣን ወንበር እንይ አንድ ፓርቲ አሸንፎ የሚይዘው በትረ መንግስት ነው ያለው በ97 ካያችሁ ኢሃዲግና ቅንጂት ተወዳደሩ ። ሁለቱም ለጠቀምበት ፈለጉ በትረ መንግስቱን ይዞ የስልጣን ወንበር ላይ ሁለቱ ተደራርበው መቀመጥ ሲፋለሙ ብራዘር እዛጋ ነው ትልቅ ችግር ፍጭት ያለው ። አንዱን የነፍስ ፋክሊቲ ለመጠቀም ውጊያ አለ በሌላ አነጋገር የእ/ር በንፈመስ ፈቃድ በዛ አይምሮ ሊጠቀምና ሊገለጥ ይችላል የሰጋ ፈቃድ ከበረታ በዛ አይምሮ ሊጠቀምና ሊገለጥ ይችላል።

እኛ ግን ነጠላ አይምሮ ነው ያለን በእ/ር መንፈስ ምስክርነት ላይ ቆመናል።

ወደ ሮሜ ሰዎች 12 Rom 12
1 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። 1 I beseech you therefore, brethren, by the mercies of God, that ye present your bodies a living sacrifice, holy, acceptable unto God, which is your reasonable service.
2 የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። 2 And be not conformed to this world: but be ye transformed by the renewing of your mind, that ye may prove what is that good, and acceptable, and perfect, will of God.

 

የእግዚአብሔር የነፍሱ ፍጹም ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ mind መታደስ ተለወጡ   የቃሉ ምንጭ ከጥንት GR-metamorphoo ከሚለው የመጣ ሲሆን EN- Metamorphosis የሚለው ትርጉም ያዘለ ነው ጌታ ማርቆስ 9:2-3 transfigured ብሎ የተተረጎመው ነው ቃሉ በግሪክ አንድ ነው

2 ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ልብሱም አንጸባረቀ፤ 2 And after six days Jesus taketh with him Peter, and James, and John, and leadeth them up into an high mountain apart by themselves: and he was transfigured before them.
3 አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ። 3 And his raiment became shining, exceeding white as snow; so as no fuller on earth can white them.

ለዚህ Metamorphosis በተፈጥሮ the most clasick example in nature is የቢራቢሮ ለውጥ ነው ከኧባ ጨጋሬ በምድር ላይ ተስቦ ከሚሄድ ወደ ሚበር ፍጥረት የመቀየርዋ ሂደት  ነው የተጠቀመበት from catrepiler to buterfly Metamorphosis እደሆነ 7ኛ ከፍል ተምረናል። cocoon እጭ ውስጥ ኧባ ጨጋሬ አካሉን ይከትና ጭንቅላቱ ወደ ውጪ ያስቀራል ጭንቅላቱ ይወድቅና (ስጋዊ አይምሮ ማጣት አለብን) የቀረ አካሉ ሲወጣ በተአምር በሚመስል ቢራቢሮ ሆኖ ይወጣል።

ያለውጥ transformion ከኧባ ጨጋሬ በምድር ላይ ተስቦ ከሚሄድ ወደ ሚበር ፍጥረት የመቀየርዋ ሂደት የሚገርም ነው። ከአንድ ፎርም ወደ ሌላ ፎርም ያለ ለውጥ ነው። እየተለወጥን ነው እንዴት በአይምሮ መታደስ be ye transformed by the renewing of your mind

Transformed መለወጥ ወይም Metamorphosis አለ የሚመጣውም በአንድ መንገድ ነው renewing of your mind በአእምሮ መታደስ ተለወጡ

በአእምሮ መታደስ ከሌለ ለውጥ የለም Metamorphosis ከ mind ጋር አገናኝዋቸው እ/ር አእምሮ ላይ ካልሰራ ለውጥ የለም transformion፣ Metamorphosis የለም

የክርስቶስ አእምሮ መንፈስ ቅዱስን ያደምጥ እደነበረ የክርስቶስ አእምሮ ያለንም በእርሱ ዘንድ የነበረ ሃሳብ በእኛ ይሁን።

Renovatio መታደስ renewing ቤት ስታድሱ ምን ታደርጋላችሁ ?መጀመርያ የምታደርጉት ብዙ እቃ ታስወጣላችሁ እቃው ይወጣል ጥግ የሚዘው ይይዛል ብል የበላው ግድግዳ ካለ ይተረተርና እንደአዲስ ይጠገናል በፊና ታሳምሩታላችሁ በቀለም ይቀለማል ። ጣራው መታደስ ካስፈለገው ገንጥላችሁ ይታደሳል ። ያ ነው የማደስ ሂደት ማለት የመተካት ህግ። be ye transformed by the renewing of your mind በአይምሮ እድሳት ላይ አንዱን መርሳት አዲሱን ማስታወስ ሂደት ነው።the prosese is  forgeting and remembering እንደምታውቁት አንድን ነገር ስትረሱት ታጡት አላችሁ አንድን ነገር ስታስታውሱት ቦታ ታስይዝታላችሁ። አሮጌውን አስተሳሰብ ወይም መራጃ በማስወገድ በኧዲሱ የመተካት ህግ ነው። አሮጌውን ሃሳብን በሃሳብ የመሻር ስልጣንን መለማመድ ያለተቀደሰውን በተቀደሰው በእ/ር ቃል መተካት

 

መጽሐፈ ምሳሌ 16፡32 ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ ይበልጣል።

Prov 16፡32 He that is slow to anger is better than the mighty; and he that ruleth his spirit than he that taketh a city.

እኛ ግን ነጠላ አይምሮ ነው ያለን በእ/ር መንፈስ ምስክርነት ላይ ቆመናል። እኛ ግን ነጠላ አይምሮ ነው ያለን በክርስቶስ ምስክርነት ላይ ቆመናል። አሜን!

አንዳንዴ በአይምሮ እድሳት ላይ አንዱን መርሳት አዲሱን ማስታወስ ሂደት እሱ ብቻ ላይሆን ይችላል ከአይምሮ ዳር ባለ እድሳት በተለይ ማለት ነው።

ትንሹ ለጅ ቢላ ቢያነሳ ምን ታደርጋላችሁ ወይኔ ብላችሁ ወ ይ ዘላችሁ ቢላውን ትነጥቁታላችሁ ወይም

ጥበብን ትጠርዋታላችሁ የሚወደውን አሻንጉሊት ታነሱና ታሳይታላችሁ ሃሳቡ በዛ ሲያዝ ቢላውን ታስለቁቅታላችሁ  በአይምሮ እድሳት ላይ አንዱን በማስተዋወቅና በማስረሳት አዲሱ በተካት ሂደት ተጠቀማችሁ። ይህን አሮጌውን በአዲስ የመተካት ሂደት ነው ጌታ አይምራችን ለማደስ የሚጠቀምበት ሂደት።

*አሁን የእ/ር እያደረገ ያለው የአሮ ጌውን ስጋዊው ሰውአይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ እያስወገደ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ የአዲሱ ሰው  ላይ የነፍሱ ክብር ማለትም  አይምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት፣ ምኞት፣ወዘተ እንዲወርሰን  በዚህም የልጁ ህይወት በእኛ ያለመከልከል ይገለጥ ዘንድ እየሰራ ነው ። እርም ክብሩ ይሰፋል።

የጌታ የመሳካቱ ትልቅ ሚስጢር የአባቱ ፈቃድ ብቻ ማድረጉ ነው እኔ ከአባቴ የመየውንና የምሰማው ሁል ጊዜ አደረጋለሁ። ያ ነው የክርስቶስ አይምሮ።

 

ኦሪት ዘፍጥረት 3፡1 እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። Gen 3፡1 Now the serpent was more subtil than any beast of the field which the Lord God had made. And he said unto the woman, Yea, hath God said, Ye shall not eat of every tree of the garden?

ሴቲቱንም፦ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ጥያቄው በመንፈስ ስልጣን ላይ ጥያቄ እንዲፈጥር ያነጣጠረ ነበር ወደ አዲስ ኪዳን ስትመጡ ግን የክርስቶስ አእምሮ የሰይጣንን ሃሳብ ሁሉንም ድል ነሳቸው። እኛ የተሸውደው የመጀርያው አዳም አእምሮ ዘር ሳይሆን ያለን የማይሸወደው የክርስቶስ አእምሮ ነው ያለን! 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:16 እንዲያስተምረው የጌታን ልብ[#አይምሮ #mind] ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ[#አይምሮ #mind]  አለን።1Cor 2:16 For who hath known the mind of the Lord, that he may instruct him? But #we #have #the #mind #of #Christ.

#በክርስቶስ #ኢየሱስ #ባለው #የሕይወት #መንፈስ #ሕግ በአይምሮ የመታደስ ሂደት)ወንድም ቢኒ። ይህ ጥሁፍ ከተለያዩ 2007_2018 ባለው ግዜ የተቀነጫጨበ ነው።

 

 

 

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal