
የእግዚአብሔር ሉአላዊነትና የሰው ነጻ ፈቃድ ላይ እንዴት ሚዛኑን የጠበቀ አመለካከት ሊኖረን እንደሚገባ ! ወንድም ቢኒ።
መቼም ሚዛኑን የጠበቀ አመለካከት የጌታ እየሱስ ክርስቶስን ያህል ምድር አስተናግዳ አታውቅም። መቼም ነገር ሁሉ ሚዛኑን የጠበቀ ሲሆን ውበት እንዳለው የታወቀ ነው። እ/ር ነገርን ሁሉ ሚዛኑም እንዳይፋለስ በልክ ፈጥሮታል አዞም አጽንቶታል።
“ትንቢተ ኤርምያስ 5፡22 በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር እንዳያልፍ አሸዋን በዘላለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፍበትም።
KJV Jer 5፡22 Fear ye not me? saith the Lord: will ye not tremble at my presence, which have placed the sand for the bound of the sea by a perpetual decree, that it cannot pass it: and though the waves thereof toss themselves, yet can they not prevail; though they roar, yet can they not pass over it?” አስተውሉ ሰው ባህርን በኮንክሪት ታላቅ ግድብ ሰርቶ ውሃ ሊያስቆም ይጥራል እ/ር ደግሞ ታላቁን ባህር ምንም በማይመስል በደቃቅ አሸዋ ልክህ ከዚህ አይለፍ ይለዋል። ጥበቡ ረቂቅ ነው።
ደግሞም ለነፋስም እንኳን ሚዛን አድርጎለታል።
“መጽሐፈ ኢዮብ 28፡25 ለነፋስ ሚዛንን ባደረገለት ጊዜ፥ ውኆችንም በስፍር በሰፈረ ጊዜ፥ KJV Job 28፡25 To make the weight for the winds; and he weigheth the waters by measure.”
“ትንቢተ ኢሳይያስ 40;12 ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛንኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው?
KJV Isa 40;12 Who hath measured the waters in the hollow of his hand, and meted out heaven with the span, and comprehended the dust of the earth in a measure, and weighed the mountains in scales, and the hills in a balance?” እ/ር ፈጣሪ ስራዎቹ ሁሉ ሚዛናቸው የተጠበቀ እደሆነ ከቃሉ እናስተውላለን።
መቼም ሰውን የእ/ር ጸጋ ካልረዳው በሚዛን ይበድላል። “መዝሙረ ዳዊት 62;9 ነገር ግን የሰው ልጆች ከንቱ ናቸው፥ የሰው ልጆችም ሐሰተኞች ናቸው በሚዛንም ይበድላሉ፥ እነርሱስ በፍጹም ከንቱ ናቸው።
KJV Ps 62;9 Surely men of low degree are vanity, and men of high degree are a lie: to be laid in the balance, they are altogether lighter than vanity.” ጌታ እ/ር በአመለካከታችን ሆነ በተግባራችን በእውነት ላይ የተመረኮዘ ሚዛኑን የጠበቀ ማንነት እዲኖረን ይፈላጋል። በአንድ ጉዳይ ላይ ነገሩን ወደዛ ለጥጠን ጸንፈኛ (extremist) አመለካከት እንድንይዝ አይፈልግም።
ኦሪት ዘሌዋውያን 19 Lev 19
35 በፍርድ፥ በመለካትም፥ በመመዘንም፥ በመስፈርም ዓመፃ አታድርጉ። 35 Ye shall do no unrighteousness in judgment, in meteyard, in weight, or in measure.
36 የእውነትም ሚዛን፥ የእውነትም መመዘኛ፥ የእውነትም የኢፍ መስፈሪያ፥ የእውነትም የኢን መስፈሪያ ይሁንላችሁ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ ነኝ። 36 Just balances, just weights, a just ephah, and a just hin, shall ye have: I am the Lord your God, which brought you out of the land of Egypt.
37 ሥርዓቴን ሁሉ ፍርዴንም ሁሉ ጠብቁ አድርጉም እኔ እግዚአብሔር ነኝ። 37 Therefore shall ye observe all my statutes, and all my judgments, and do them: I am the Lord.
ያውላችሁ እንግዲህ በፍርድ፥የእውነት ሚዛን፥ በአመለካትም፥ የእውነት ሚዛን፥ በመመዘንም፥ የእውነት ሚዛን፥ በመስፈርም የእውነት ሚዛን፥ ዓመፃ አታድርጉ የእውነትም መመዘኛ ይሁንላችሁ። ይለናል መቼም ምላሻችን አሜን በነገር ሁሉ የእውነት ሚዛን ይሁንልን ነው ብየ አስባለሁ።
“መጽሐፈ ምሳሌ 11;1 አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው እውነተኛ ሚዛን ግን ደስ ያሰኘዋል።
KJV Prov 11;1 A false balance is abomination to the Lord: but a just weight is his delight.”
“መጽሐፈ ምሳሌ 16;11 እውነተኛ ሚዛንና መመዘኛ የእግዚአብሔር ናቸው የከረጢት መመዘኛዎች ሁሉ የእርሱ ሥራ ናቸው።
KJV Prov 16;11 A just weight and balance are the Lord’s: all the weights of the bag are his work.”
በአመለካትም፥ የእውነት ሚዛን፥ ስለመያዝ ካስተዋልን ዘንዳ ስለ የእግዚአብሔር ሉአላዊነትና (God’s sovereignty) የሰው ፈቃድ በተመለከተ በእ/ር ቃል ውስጥ እንዳለው ሚዛኑን የጠበቀ እይታ ሊኖረን ይገባል። የእግዚአብሔር ሉአላዊነት በሰው ፈቃድ ላይ የበላይ ነው ብለው በሚያምኑትና ሰው ነጻ ፈቃድ (free will) ያለው ነው ብለው በሚያምኑ መካከል የከረመበት መፋጠጥ አለ። ሰው ነጻ ፈቃድ አለው የሚሉት በትክክል የሰውን ሃላፊነት ካጎሉ ቡሃላ ሰው በእ/ር ፊት ተጠያቂ ነው ይሉና የእ/ርን ሊረዳ ተዘጋጅቶ የሚጠብቅ ነገር ግን በጨረሻም በእውነተኛው ሃያሉ ሰው ነጻ ፈቃድ የተነሳ ሃይል አልባ በማድረግ ከገዛ ከፈጠራቸው ሰዎች እግዚአብሔር የሚያህል የሃይል ሁሉ ምንጭ ተጎጂ ያደርጉታል።
በሌላው ገጽ የእግዚአብሔር ሉአላዊነት የሚያምኑት የሚያተኩሩት የእግዚአብሔር ሉአላዊ እንደሆነና በፍጡራኑ ሁሉ ላይ ሃይል እንዳለው ይህም አመለካከት ሃጢያታቸውን ለማጽደቅ ሃላፊነታቸውን ሁሉ በእ/ር ላይ በመጣል ለድርጊታቸው ሽፋን ይሰጣሉ። በሌላ መንገድ ይህ አመለካከት እ/ር ነው ሁሉን የሚያደርገው በማለት ምን እዳያደርጉ ሽባ ያደርጋቸዋል። ለጽድቅ ህያዋን እንደሆኑና በእነሱ ያለው የእ/ር ዘር ሃጥያት መስራት እንደማይችል እስከመዘንጋት ያደርሳቸዋል።
Son’s of God let us have balanced perspective on God’s sovereignty & man’s free will, ሁለቱም ወገኖች ሃሳባቸው የሚደግፋላቸውን የጥቅስን ክፍል በማድመቅ ሁለቱም እውነትን ያሳያሉ ይዘዋልም። ችግሩ ብዝዎች ብዙ እውነት በአንድ በኩል ይዘዋል በሌላ በኩል ያለውን ሚዛኑን እዳይጠብቅ ያደርገዋል። መፍቲሄው ማመን የሚገባው እግዚአብሔር ሉአላዊ ነው ሰው ደግሞ በምድር ላይ ስልጣን ተሰጥቶታል ነው። እነዚህ ሁለቱ ጎን ለጎን የሚሄዱ ናቸው። ሉአላዊ መሆኑ ዝም ብሎ ሃይሉን ይገልጣል ማለት አይደለም በአላማው ወይም በሆነ ምንያት ከሰው ነጸ ፈቃድ መስማማት ውጪ ሃይሉን ሊገልጥ አልፈቀደምና። በሌላው ገጽ የሰው ስልጣን ከነጻ ፈቃድ ጋር አንድ አይደለም ምንም እንኳን ብዙዎቹ እይታቸውን ለማረጋገጥ በመሞከር ለሰው የተሰጠውን ስልጣን በመጥቀስ ሁለቱን ሃሳቦች ግራ ቢያጋባቸውም የእግዚአብሔር ሉአላዊነትና (God’s sovereignty) ብቻ ነው እውነተኛ ነጻ ፈቃድ ያለው Only sovereignty has free will. ። የሰው ስልጣን ውስን ነው። Man’s authority is limited by situations when’s the situation change man understand they are not sovereignty with free will.
Posted on January 18, 2012 By Brother Binyam T. Alemayehu
በአመለካከትም፥ የእውነት ሚዛን፥ ይኑረን ዘንድ ተስፋ በማድረግ የዚህ ትምህርት አላማም ሰዎችን ሚዛኑን ወደ ጠበቀ የቀረበ መረዳት በዚህ ጉዳይ ላይ ለማስጨበጥና የእግዚአብሔር ሉአላዊነትና (God’s sovereignty) የሰው ስልጣን man’s authority በተመሳሳይ ሰአት አብረው እንዴት እንደሚሰሩ ፍንጩን እንድናየው ነው። መቼም ለፈጣን ጆሮ ግማሽ ቃል ይበቃዋል እንደ ሚባለው አባባል ነውና። ይህ በሌላ መልኩ በአመለካትም፥ የእውነት ሚዛን፥ ልኩን ሲይዝ በሁለቱ መካከል የከረመውን መፋጠጥ ሊረዳ ይችላል። ይህም እ/ር እንዴት በምድር ላይም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ያሰበውን አላማውን ግቡን እንደሚመታ የጠራ አመለካከትን ሊሰጥ ይችላል። ከአላማው አንጻር ስለ በጎ ፈቃዱ እግዚአብሔር በሉአላዊነቱ (God’s sovereignty) በሰው ውስጥ መፍቀድንም ማድረግንም ሊሰራ ብቃቱ አለውና።
“ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡13 ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።
KJV Phil 2፡13 For it is God which worketh in you both to will and to do of his good pleasure.”
በዚህም የእግዚአብሔር ሉአላዊነትና (God’s sovereignty) የሰው ስልጣን man’s authority በተመሳሳይ ሰአት አብረው እንዴት እንደሚሰሩ ሚዛኑን የጠበቀ እይታ ሊኖረን የተገባ ነው። በነገራችን ላይ የእ/ር ፈቃድ ቢሆንብን ተጠቃሚዎቹ እኛው ሰዎች ነን። የእ/ር ፈቃድ ወደ ልጅነት ሳበን የጎደለንን የእ/ር ክብር ክርስቶስ ተመለሰልን ተስፋችንን አስጨበጠን። የእ/ር ፈቃድ በጸጋው የማይንከባከባቹሁ ቦታ አይወስዳችሁምና ብርቱ ክንዱም የማይደግፋችሁ ቦታም አይወስዳችሁም፡ ፍላጋ የሌለው ባለጠግነቱም የማያቀርብላቹሁ ቦታም አይወስዳችሁም፡ ሃይሉ የማያበረታቹሁ ቦታም አይወስዳችሁም። የእ/ር ፈቃድ የእ/ር መንፈስ በእናተ ውስጥ የማይሰራበት ቦታ የማይመራቹ ቦታ አይወስዳችሁም፡ ልጅነት ከእ/ር መንፈስ መመራት ውጪ የለምና። የእ/ር ጥበብ የማያስተምራቹሁ ቦታም አይወስዳችሁም፡ ሰራዊቱን ቀዳሚ ሆኖ የማይጠብቃቸው ቦታም አይወስዳቸውም፡ የእ/ር እጅ የማይሞርዳቹሁ ቦታም አይወስዳቹሁም። የማይቀምማቹ እሳት ውስጥ አይከታችሁም። የእ/ር ፈቃድ በፍቅሩ የማያረሰርሳቹሁ ቦታም አይወስዳቹሁም፡ ምህረቱ በህይወት አኑሮ የማያጸናቹሁ ቦታም አይወስዳቹሁም፡ ፍርሃትን አጥፍቶ አይምሮን ሁሉ የሚያልፈው ሰላሙን የማይሞላችሁ ቦታም አይወስዳቹሁም፡ ሉአላዊነቱና ወሰን የሌለው ስልጣኑ የማይገዛቹ ቦታም አይወስዳቹሁም። የእ/ር ፈቃድ በማጽናናቱ እንባቹሁን የማያብስበት ቦታም አይወስዳቹሁም፡ የህይወት እንጀራ ቃሉን የማይመግባቹሁ ቦታም አይወስዳቹሁም፡ ተአምራቱም ለናተ የማይሰራበት ቦታ አይወስዳቹሁም፡ በአንድ ጊዜ በሁሉ ስፍራ በሚገኝ ማንነቱ የማያገኛቹ ቦታም አይወስዳቹሁም። የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ የሆነውን ጌታ በተግባራዊ ሂደቱ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እማንለውጥበት ቦታ አይወስዳቹሁም። አሜን! የእ/ር ፈቃድ ይሁንብን:: አሜን! ወንድም ቢኒ።
Posted on January 18, 2012 By Brother Binyam T. Alemayehu