ከጥያቄና/መልስ የተወሰደ። ሰላም ወንድማችን። ድንገት ጥያቄህን ሳየው ጥቂት ልበልህ ብየ ነው። ልጅነትን ለማሳየት ጽድቅን ሁሉ መፈጸም አለበ። መጀመርያ ለምን ልጆች ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና ተባልን። ጸሎት ምን ጋር ቢያገናኘን ነው?። ይህ ቢጋባህ አንተም ትለማመደው ነበር በክርስቶስ ኢየሱስ ላይም ጥያቄ አይጭርብህም ነበር ለምን እንደ ሚጸልይ ይበራልሃልና። Bro. One thing we already know – the spirit realm of the unseen is the realm of all power የማይታየው መንፈሳዊው ግዛት የኃይል ሁሉ ምንጭ ነው። ጸሎት ስታረግ በአጭሩ ከሃይል ምንጭህ ከመንፈሳዊ አባትህ ዘንድ መገናኘት ነው። የመኪናህ ባትሪ ቢደክም ወይም ቢሞት ሪቻርጅ ለምን ይሆናል ከሃይል ጋር ስለተገናኘ ነው ልጆችም እንዲሁ ናቸው። ለጸሎት ቀመር ወይም ፎርሙል አየለውም ስራውን ግን ይሰራል የአባት ፈቃድ ታስተውላለህ። ባትጸልይም ፈቃዱ ይፈጸማል። “ጸሎት ባህርን ከፈለዋል፤ የሰማይትን ሰራዊት ስራት ደፍረዋል በገባዖን ላይ ፀሐይን አስቁመዋል፥ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃን፤ ጸሎት የሰማይን ኤለመንት ለ3 አመታት ዘግተዋል። አለትን ወደ ፏፏቴዎች ቀይርዋል። መካኖች ማህጸናቸውን ከፍተውበታል። መንግሥታትን ላይ ድል ተቀናጁበት፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል ጨበጡበ ። የእሳት ነበልባልን ሃይል አመከኑበ ። ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉበ ። ሙታን ወህይወት ተመለሱበት ። የሃያላንን ቀስት ሰበሩበት፤ የአንበሶችን አፍ ለጎሙበት፥ የእሳትን ኃይል አኮላሹበት፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡበት፥ በጸሎት ከስጋ ድካማቸው ወደ መንፈስ ብርታት ዘወር አሉበት፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። በአሕዛብ ላይ በቀልን፥ በሰዎችም መካከል ቅጣትን አደርጉ። ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት፥ አለቆቻቸውንም በእግር ብረት አሰሩ። የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ። ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ክብር ናት። ሃሌ ሉያ።አንተም ወንድሜ የልብህን መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ብትጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። የሁሉም መልስ ከላይ ታስተውላለ ። መጽሐፈ ምሳሌ 2/3 ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት፥ ለማስተዋልም ድምፅህን ብታነሣ፥[ብትጸልይ]
4 እርስዋንም እንደ ብር ብትፈላልጋት፥ እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፤
5 የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ።
“የዮሐንስ ወንጌል 1/1 ….. ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
የዮሐንስ ወንጌል 1/14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥” በስጋ እንደመጣ ካላመንክ ተሸዋውድውካል። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4/3 ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2/6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ …..7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥
‘እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ …. ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤ ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ። ‘ፊልጵስዩስ 2:6-8 አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ከደቀ መዛምርቱ አንዱ ጠርጣራው ቶማስ እያማረረ ጌታን ጠየቀ “ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም መንገዱንስ እንዴት እናውቃለን” እኔ ነኝ መንገዱ፤ እየሱስም ደገመ፤ እኔ ነኝ እውነቱ፤ እየሱስ ሰለሰ እኔ ነኝ ህይወቱ፤ ማርታ በሃዘን በተሞላ አነጋገር”በመጨረሻው ቀን በትንሳኤ እንዲነሳ አውቃለሁ አለችው” እየሱስም መለሰ “ትንሳኤ እኔ ነኝ፤ ህይወት እኔ ነኝ” ;;
መጽሃፍት ትመረምራላችሁ መጽሓፍት ሁሉ ግን ስለኔ ይናገራሉ ህይወት እንዲሆንላችሁ ግን ወደኔ ልትመጡ አትወዱም። ምን ምን? መጽሓፍት ሁሉ ግን ስለኔ ይናገራሉ ? ሁሉ ስለኔ የሁሉ ትርጉም ሁሉ ነው። “እኔ ነኝ” “I am” መጨረሻ የለውም የወይኑ ግንዱ እኔ ነኝ፤ በሩእኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ የአለም ብርሃን እኔ ነኝ ፤ አልፋ እኔ ነኝ ፤ ኦሜጋ እኔ ነኝ ፤ የመጀመርያው እኔ ነኝ፤ የመጨረሻው እኔ ነኝ፤ የምዋጀው እኔ ነኝ ፤ ብርታትህ እኔ ነኝ ፤ የሚኖረው እኔ ነኝ ፤ ሞቶ የነበረው እኔ ነኝ ፤ ትንሳኤው እኔ ነኝ ፤ የዘጋሁትን ማንም የማይከፍተው የከፈትኩትን ማንም የማይዘጋው እኔ ነኝ ፤ የዳዊት ስርና እኔ ነኝ ፤ የንጋት ኮከብ እኔ ነኝ፤ ስሙም ድንቅ መካር እኔ ነኝ ፥ ኃያል አምላክ እኔ ነኝ ፥ የዘላለም አባት እኔ ነኝ ፥ የሰላም አለቃ እኔ ነኝ “ያለውና የሚኖረው እኔ ነኝ:
እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ… እኔ እኔ ነኝ በላቸው” [I AM that I AM, tell the pepople that I AM hath sent you] እነሆ ለስነቱ መጨረሻ የለውም ። “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2/9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤የዮሐንስ ራእይ 1/8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።” አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ ያለኝ እኔ እኔ፤ የታመነውና እውነተኛው ምስክር እኔ ነኝ፥።የዮሐንስ ራእይ 4/10-11 ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም[ለደስታህ ተፈጥረውማልና for thy pleasure they are and were created.] ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ። ወንድም ቢኒ።