እግዚአብሔር ለምን በተቃራኒ ኀይላት ልጆችን ያሰለጥናል? 06/07/2017 በወንድም ቢኒ። በጌታ ፍቅር ሰላም ይሁን።
መጽሐፈ መክብብ 7/10 ከዚህ ዘመን ይልቅ ያለፈው ዘመን ለምን ተሻለ? ብለህ አትናገር፤ የዚህን ነገር በጥበብ አትጠይቅምና።
ከአዳም ወደ ክርስቶስ ወዳለው የንቃተ ህሊና ጉዞ ሰው ሁሉ በእሳት ሊቀመም የግድ ነው። የጌታ እየሱስ ክርስቶስ ትግስት ይገርማል። ለ3 አመት ከ½ አገልግሎት የ30 አመት ስልጠና መውሰዱ የሚገርም ነው። በዚህ ዘመን ለ30 አመት አገልግሎት በ3 አመት ዝግጅት ሰው ለአገልግሎት ይሮጣል። ጌታ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ የልጅነት ምሳሌ ህይወቱን ስታዩ በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ። በሰዎች ዘንድ ናዝሬት መልካም ነገር የማይገኝበት አቧራማ መንደር የከንቱነት ሰፈር ነው። እ/ር ታላቅን ስራ ይሰራ የነበረው በታላቂትዋ እዮርሳሌም የወቅቱ ታላላቅ ቲዮሎጅያን የህግ ዶ/ሮች ባሉባት የሰለሞን ባለግርማ ውብ ቤተ መቅደስ አልነበረም ታላቁን መፃኢ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ የጀመረው በብዙዎች ከንቱ በተባለ የእዮርሳሌም ተቃራኒ ቦታ መልካም በማይመስል በናዝሬት ነበር። ስንቶቻቹሁ እ/ር ናዝሬት በሚመስል ሁኔታ የታላቁን ወንድማችንና ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ቀመር በናንተ ላይ ደግሞት አይታችሃል? የመናፍስት አባት እ/ር ዛሬም ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል ወራሹ የተስፋው ዘር ክርስቶስ በእኛ ተወልደዋል ሊገለጥ የግድ ነው ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ በእኛ ውስጥ ይህ የሃይል ትግል ስጋ በመንፈስ ላይ መንፈስ በስጋ ላይ ይታያል። ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት።አባራት ይላል ከስጋ የተወለደው ማንነት አይወርስምና ሊባረር የግድ ነው። በእሳት የመቀመም ሂደቱ ቀጥለዋል እሳቱም ከወርቁ ላይ አፈሩንና ዚንኩን እየፈለቀቀ እያስወገደው ነው።እ/ር መንፈስ ነው። እ/ር እሳት ነው። እ/ር የሚባላ እሳት ነው። ፍቅር መንፈስ እሳትም ነው በማንነቱ ይወርሳል ይቀምማል። የእ/ር የራሱ የማድረግ ቅናት ይህን ያደርጋል። “…ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥ ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው።መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 8/6
ወደ ዕብራውያን 5፡8 ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ወደ ሮሜ ሰዎች 8/17 ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
ወደ ዕብራውያን 2/18 እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4/1-2 ክርስቶስም በሥጋ ስለ እኛ መከራን ስለተቀበለ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፥ እናንተ ደግሞ ያን አሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት፥ በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአልና።
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10/13 ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።
ወደ ዕብራውያን 12/5-6 እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር፦ ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል።
7 ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?
8 ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።
9 ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
10 እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።
11 ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል።
12 ስለዚህ የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጉልበቶች አቅኑ፤
13 ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ።
14 ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።
የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው? ከሚገልጥልን በቀር ማስተዋል አይቻልም መንፈሳዊው ነገር ከሰው ማስተዋል በላይ ግዙፉ ነውና። ቢሞከርም ከውቂያኖስ ይልቅ ጠሊቅ ከሆነው ምክሩ በማንኪያ ጨልፈን እደመረዳት ያህል ነው። ስለ ተቃራኒ ኀይላት ስናስብ መገንዘብ ያለብን ከሚቋቋመን ተቃራኒ ነገር የምንማረው ነገር አለ። ለዚያም ነው እ/ር ተቃራኒ ሃይላትን የፈጠረው። በትንቢተ ኢሳይያስ 45፡7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አዎን ሁሉን መፍጠሩን እ/ር ሃላፊነቱን ወስደዋል:: እራስ በራሳቸው የሚቃረኑትም ጭምር ማለት ነው። ለማሰብ ያህል መራራና ጣፋጭ፤ ሃዘንና ደስታ፤ ድሃና ባለጠጋ፤ ጨለማና ብርሃን፤ መልካምና ክፉ፤ ህግና ጸጋ፤ ተፈጥራዊ ነገሮች ና መንፈሳዊ ነገሮች፤ ሞትና ህይወት፤ እስራትና ነጻነት፤ ለምን ብሎ እ/ር እንደዚህ በጥብቅ የሚቃረኑ ሃይላትን ፈጠረ?
አዎን ማየት ያለብን እ/ር መንገዱን ሊያስተምረን ተቃራኒ ሃይሎችን መፍጠር ነበረበት። መልካምን እንዴት እንረዳው ነበረ ክፉ ባይኖር ኖሮ? የእ/ርን ረቂቅ ጥበቡን በመጠኑም ቢሆን ልንገነዘበው ይገባል። ፉጡራኑን ወደ ብስለት ለማምጣት በምን እደሚያሳልፈን ስናስተውል ይደንቃል:: ተፈጥሮውና ባህርዩ በሰው ውስጥ ይገለጥ ዘንድ የሚጠቀመው ተቃራኒ ሃይላትን ነው:: “መዝሙረ ዳዊት 119፡71 ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።” መጽሐፈ ኢዮብ 36፡15 …. በመከራም ጆሮአቸውን ይገልጣል። Job 36፡15 He… openeth their ears in oppression.
አንድ ሰው በእብራዊን ቋንቋ የጌታን ድምጽ ሰማሁ ካለ ፈጽሞ ሰምቶ ፈጽሞ መታዘዙን የሚያሳይ ነው። ሰምቶ ካልታዘዘም ፈጽሞ አልሰማም። በመገለጥ እንዲሰማም በሌላ ሂደት ያልፋል። “በመከራ ጆራቸውን ይከፍታል። እዮብ36፡15 በእብራይስጥ መከራ የሚለው ውጥረት ይለዋል። አንዳንድ ጊዜ ለምን ይሄ ሁሉ ውጥረት በመንገዳችን እንደ ሚያልፍ እንደነቃለን። እንደ ዛም ሆኖ ነገር ሁሉ ተያይዘው ለበጎ እንዲደረግ እንረዳለን። በብዙ መከራ ማለፋችንም ለብዙ አላማ እንደሆነ እናውቃለን። ከዛ ውስጥ አንዱ ጆራችን እዲከፈት ነው። ጳውሎስ የደቀ መዛምርቱን ልብ በማበረታታትና በእምነታቸወ ጸንተው እንዲሩ በመምከር “ወደ እ/ር መንግስት ለመግባት በብዙመከራ (ግሪክ፦ pressure, እደአገባቡ ቃሉ ሲተረጎም ውጥረት ግፊት መገፋፋት ተጽኧኖ የሚያመጣ ውጥረት )ማለፍ አለብን “” ሐዋ14፡22 ይህም ውጥረት ከአሮጌው አውጥቶ ወደ አዲሱ ተጭኖ ያስገባናል። እ/ር አምላክ ጥበበኛ ነው። አንዱን ውጥረት ከአንድ ነገር ለማውጣትና በተመሳሳይ ሰአትም የስጋን ፈቃድ ሰብሮ የመንፈስን ድምጽ ወደ መስማት ግዛት ያመጣናል።”
በአሮጌው ሰማይ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች እግዚአብሔር በሚሰጠን አገልግሎት እንዲሰሩ የሰጠን መሳሪያዎች ነበሩ። እያንዳንዳችን የተለየ ጥሪ ስላለን, ለእያንዳንዱ ለእሱ ወይም ለሳ ተስማሚ የሆኑ መንፈሳዊ መሳሪያዎች እንደየሰው ይለያያሉ። ነገር ግን መሳሪያ መሣሪያ ነው, ምንም ያህል ጥሩ መሣሪያ ቢሆንም ለራሱ ክብር መስጠት አይገባም። በእርግጥም መንፈሳዊ መሳሪያዎች በሰዎች ያለአግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።
ለዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ምሳሌ ሊሆነን የሚችለው ሙሴ ነው። ሙሴን ዓለቱን ለሁለተኛ ጊዜ በዘኍልቍ ላይ ሲመታው ይታያል. በዘኍልቍ 20: 8-11 . እሱ ጌታ እንዳዘዘው ዓለቱን በቃል መናገር የነበረበት ቢሆንም እሱ ግን አልታዘዘም በህዝቡ ተጽኖ ተናዶ አለቱን በብትር ዠለጠው። ይሁን እንጂ ሕዝቡ እንዲጠጣ ውኃ ከዓለት ውስጥ ፈልቀዋል። ጌታ ለሙሴ የተሰጠውን መንፈሳዊ ሥልጣንና ስጦታ ስለሚያከብር “ስኬታማ” ቢሆንም, ይህ ክስተት ሙሴን ወደ ተስፋዪቱ ምድር እንዳይገባ አደረገው ። የሚገርመው ሙሴ ያልበራለት ክርስቶስ በዚያ መኖሩን በሙልአት አለማስተዋሉ ነው። በዱላ የመታው አለት ክርስቶስን ነበርና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10/4 ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ። 1Cor 10/4 And did all drink the same spiritual drink: for they drank of that spiritual Rock that followed them: and that Rock was Christ. መርሳት የሌለብን በቀደሙት ላይ የሆነው ሁሉ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 15/4 በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና።
ጌታ ኢየሱስ በማቴዎስ ምዕራፍ 7 /22 ውስጥ በዚያች ዘመን ብዙዎች እንዲህ ይላሉ ” በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን ? በስምህስ ብዙ ድንቅ ነገሮች አላደረግንምን ?” እነዚህ ሰዎች ግን ህገ-ወጥነት በግሪክ anomia ህግ አልብነትን ስለ ሚለማመዱ lawlessness ለተስፋዪቱ ምድር ብቁ እንዳልሆኑ ይነገራቸዋል። ኢየሱስም አለ “እናንተ ዓመፀኞች, ከእኔ ራቁ” ዓመፀኞች የሚለው የተተረጎመው( ኧኖሚያ፡ ህግ አልብነትን ነው).
በአሮጌው ሰማይ ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ የመንፈስ ፍሬ ሳይኖራቸው የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች ሲጠቀሙ ቃሉ ዓመፀኞች ወይም ኧኖሚያ፡ ህግ አልብነትን እየተለማመዱ ነው ይላል። እግዚአብሄር በስጦታው ባይፀፀትም ህገ ወጥ ና ዓመፀኞች ይላቸዋል። ያም ማለት ስጦታቸውን እንደያዙ ወደ አለመታዘዝ በመዞር ለመንፈስ ቅዱስ ከመገዛት ይልቅ ወደ ሌላ ያዘነብላሉና ማለት ነው። በጴንጤቆስጤ ዘመን እንደ ንጉሥ ሳኦልን በቅን ልቦና ተነሳስተው ትንቢት የተናገሩ ብዙ ሰዎችን ታይተዋል ( 1 ኛ ሳሙ 10 10 ) ግን ኧኖሚያ ሁሉም ባይባሉም አብዛኛዎቹ፡ ህግ አልብነትን ያዘለ ልብ ያላቸው ናቸው። እ/ር የሳኦልን ሳይሆን ዳዊትን እንዴት እንዳሰለጠነው ሳስብ ብዙ ጊዜ እንደልቤ የሆነውን የእሰይን ልጅ አገጀሁት በቅዱስ ቅባቴም ቀባሁት እንዳለ ሁሉ በክርስቶስ ባለ ህወታችንም አባት በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ብሎ እስኪመሰክርልን ድረስ እንዲያሰለጥነን ዘወትር እጸልያለሁ። አሰራሩ ልዩ ልዩ ቢሆንም ውቴቱ ግን ወጤታማ አባት በፍርዱስቶ አያውቅም። ሳኦልን ና ዳዊት ሁለቱም ነቢያት ናቸው, ነገር ግን የህይወታቸው እጣ ፈንታ በተለያዩ መንገዶች ላይ አብቅተዋል።
በዚህ ውስጥ ያለው ትምህርት በየትኛውም ሰማይ እንሁን በሕይወታችን ውስጥ ትኩረታችንን መሆን ያለበት ክርስቶስ ነው። የመንፈስ ፍሬዎችን ለማፍራት እንድንችል ኢየሱስን በመምሰል ፍርያችን ይበዛል አባትም በዚህ ይከብራል። ከዚያም እግዚአብሔር የመንፈስ ስጦታን ቢሰጠን, ያንን ስጦታ እንደ ቅዱስ ፈቃድ እንጠቀምበታለን እንጂ የልቡ ሸለፈት እንዳልተገረዘ ሰው መንፈሳዊ ስልጣናችን አናሰቃየውም። ከግላዊ ትንሽ መንግሥት ግንባታ ወይም ሀብትን ለማግኝት ከመጠቀም እንቆጠባለን አላማችን እ/ርን ወይም ህይወትን መግለጥ ብቻ ይሆናል። ልጅነት ብዙ ከእ/ር ዘንድ የግል ስልጠና እንደሚያስፈልገው አስተውላለሁ። (በተቃራኒው) የፋሲካ አገልግሎት በቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ውስጥ ጥቂት ዓመታት ብቻ እንደሚጠይቅ እንዲያውም የጴንጤኮስታል አገልግሎት በአጠቃላይ ያን ያህል ስልጠና አያስፈልግም። ልጅነት ግን ብዙ ከእ/ር ዘንድ የግል ስልጠና እንደ ሚያስፈልገው የታወቀ ነው።
እስቲ ለትምህርታችን ዮሴፍን እንመልከት የስሙትርጉም “ፍሬያማው ልጅ” ( ዘፍ 49/22 ) እንመልከተው . ወንድማችን በ 17 ዓመቱ, ሁለት ሕልሞችን ያያል ያስተውላልም። ሁለት ሕልሞች በላይ ላያቸው ላይ እንደሚገዛ የሚያመለከቱ ነበሩ። ይህንን ራዕይ ለመላው ቤተሰቡ ማካፈሉ ከፊል ሞኝነት ነበረ ። አልያም ስለ ትኩስ ሃይሉና ወጣትነቱ ምናልባትም የጉርምስና እብሪተኝነትም ውጤትም ሊሆን ይችላል። ዮሴፍ የመንፈስ ፍሬን ለማሳየት ተጨማሪ ሥልጠና እንደ ሚያስፈልገው ግልጽ ነው። በመሆኑም ጌታ አምላክ ስህተቱን ተጠቅሞ ወንድሞቹን በቅናት እሳት አቀጣጥሎ ስለነበር ወደ ግብፅ ሸጡት። እዚያም እግዚአብሔር የዮሴፍን የተግባር ትምህርት ቤት አስጀመረውና ሥልጠናውን ሊጀምሩ የሚችሉ ክፉ ሰዎችን የማያምኑትን በላዩ እንዲሰለጥኑበት ፈቀደ። እንደ የመጀመሪያ ደረጃ ት / ቤት ሰልጣኝ አድርጎ ተጠቀመባቸው።
ምናልባት ዮሴፍ ዛሬ እንዳለነው ልጆች እንደ እኛ ነበር ብየ አስባለሁ። ምክንያቱም በዚህም ዘመን ሰብዓዊው ተፈጥሮ ከቀድመው ዘመን እምብዛም ምንም ለውጥ አላሳየምና። በዛም ዘመን ዮሴፍ ጳጢፋራ በእግዚብሔር ልጅነት ያለውን መልካም ሕይወት እንዳይደሰት የከለከለ ጠላቱ አድርጎ በማሰብ ዮሴፍ መንፈሳዊ ሥልጣኑን ሊጠቀምበት ይሞክራዋል ብዬ አስባለሁ። ዮሴፍ የእስረኛነቱን ቅጣት በፍጥነት እንዲያቋርጥ በመንፈሳዊ ትእዛዞች ሊወጣ እንደ ሚሞክር ማሰብ እችላለሁ። እንዲሁ ሳስበው በእስር ቤት ዮሴፍ በእምነት ኮንፌሽን ለመዳን ሊፎክርና ምናልባትም ተጨማሪ የገንዘብ ጉቦ ለመስጠት በመጠየቅ ዮሴፍ ለማምለጥ የሞከረ ይመስለኛል።
በመጀመሪያ አሰራሩ ይለያይ እንጂ የእግዚአብሔር ልጆች ለእንደዚህ አይነት ጥብቅ ስልጠና እንደተጠበቁ ለዮሴፍ ግልጽ የነበረ አይመስለኝም። የእግዚአብሄር ልጅነት ማለት እኮ በአፋቸው የብርና የወርቅ ማንኪያዎች እየበሉ ማደግ ማለት አይደለም። በተደላደለ ኑሮ አልተወለዱም። በእርግጠኝነት ልጆች በእግዚአብሔር ካልተማሩና ካልሰለጠኑ በአብዛኛው የእነሱ ጥሪ ምናልባት በፋሲካ ወይም በጴንጤቆስጤ ግዛት የተገደበ ሊሆን ይችላል ብዮ አስባለሁ በዳስ በዓልን የተመሰለውን ወይም የተወከለውን የልጅነት አገልግሎት አይጨምርምና። ጌታ እየሱስ እራሱ በናዝሬት ማለትም በከንቱነት ስፍራ ምንም መልካም ነገር በማይገኝበት በአባራማ ናዝሬት መንደር በአምላክ መልክ ሲኖር ሳለ እራሱን ባዶ አድርጎ ቃል ስጋ ሆኖ እነ ዮሴፍን ጋር አናፂ ሆኖ ባርጩማ ወንበር ሲሰራ እነሱን እያገዘ እየታዘዛቸው በዛ ያሳለፈውን ከህያዋን ምድር ማን አስተውሎ ይሆን? ጌታ እየሱስ ምንም እንካ ልጅ ቢሆን ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ከተማረ ወንድሞቼ ብሎ ሊጠራቸው የማያፍርባቸውስ ቢሆኑስ በመከራውም በክብሩም ሊመስሉት የግድ እንደሆነ ግልጽ አይደል። ልጅነት አባትን ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር ያደርጋልና ደግሞም ከአባት የሚሰማውን ብቻ ይናገራል። ያ ማንነት ከእ/ር ለመበዝበዝ ግን ከአባት መማርና አካይድንም ከሱጋር ማድረግ ወሳኝ ነው። ልጅነት ከአባት ካላየ ካልሰማ ዝም ይላል ዝም ሲልም እንካ ጥበብ ይሆንለታለና ለጌታ እየሱስ የተሳካ መንፈሳዊ ትእይንት አካሄድና ክስተት ሚስጥሩ እሱ ነበርና። ልጅነት አባትን ዘወትር ደስ የሚያሰኘውን ማድረግ ከሆነ ወደዛ ብስለት አባት እስኪ ያመጣን ድረስ ምነው አሁን ዘወትር ማለት ባንደፍርም አብዛኛውን ጊዜ አባትን ደስ የሚያሰኘውን ብቻ እናደርጋለን ለማለት በቻልን። የዮሐንስ ወንጌል 8/29 የላከኝም ከእኔ ጋር ነው፤ እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና አብ ብቻዬን አይተወኝም አላቸው። ወደ ዕብራውያን 5/8 ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤
ዮሴፍ ለመዳን የተቀጠረለት ጊዜ ነበረው ያንን እውነት ግን ገና አልተገነዘበም ነበር። ምክንያቱም እንዲህ ዓይነቱ መገለጥ ቢኖረው ኖሮ ከእምነት ውነታው ጋር ሊጣረስ ይችል ነበር። የእብራዊያን 11 የእምነት ግዙፋን ልጆች እግዚአብሄርን ያለ እምነት አላስደሰቱትምና ከአዳም 7ኛ የሆነው ሄኖክ ሞትን ሳያይ ከመወሰዱ በፊት በእምነት እግዚአብሄርን ማስደሰቱ ተነግሮናል። ከእ/ር ጋር አረማመዱን ያደረገው በእምነት ነበር። እኛ አሁን በራሳችን ሳይሆን በእግዚአብሔር ልጅ እምነት እንኖራለንና Not my own faith but by the faith of the Son of God! Gal 2/20 I am crucified with Christ: nevertheless I live; yet not I, but Christ liveth in me: and the life which I now live in the flesh I live by the faith of the Son of God. እርሱ የእምነታችን ደራሲ ነው። ‘እግዚአብሔር እንኪያስ ከሚታገሣቸውም በምርጦቹ ዘንድ የሰው ልጅ ወደ መቅደሱ በሚመጣበት ጊዜ በዚህ የሸክላ መዝገብ በምድርህ/ሽ ላይ እምነትን ያገኝ ይሆንን?” ‘ሉቃስ 18:7-8
ዮሴፍ ለመዳን የተቀጠረለት ጊዜ ያለማወቁ በጥርጣሬ በተስፋ እ/ርን እንዲጠብቅ ከሚያረጉት አንዱ ነው የሆነበት። ተስፋ የሰጠው ግን ተስፋን የሚያስጨብጥ ነውና እግዚአብሔር ይመስገን። እሱ ከእብራውያን 11 የእግዚአብሔር የእምነት ግዙፎች አንዱ ነው። ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ እንደ ተመሰከረለት, መከራ ዋና አሰልጣኙ ሆኖ እ/ር ተጠቅሞቦታል። ዳዊት ያስጨነከን ለመልካም ሆነልኝ ሲል ዮሴፍ የተሰራ ማንነቱ ጋር ሲደርስ እንዲህ ለማለት አቅሙ ነበረው ” እናንተ ለክፉ አደረጋችሁት, ነገር ግን እግዚአብሔር ለመልካም እንዲሆን አድርጎታል ” ( ዘፍ 50 20 ).
ወደ ዕብራውያን 11/5 ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፤ ‘ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ፤ ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ እምነት ነው። ‘ገላትያ 2:20
ከመንፈስ ፍሬዎች አንዱ ትዕግስት ዋንኛው ነው ትግስት በልምድ ታልፎ ይመጣል እንጂ ዝምብሎ አይፈራም( ገላ 5 22 ). ያም ማለት ፍሬው ደርሶ ከመበላቱ በፊት በጣም ቆምጣና መራራ ነው። ትዕግስት ሊበስል ጊዜ ይጠይቃል ለማደግ ለማፍራት ጊዜ ይወስዳል። የጊዜው ርቀት በረጅም መስመር መካከል ያለው ሁለት ነጥቦች ስለሚሆን የጊዜ ንጥረ ነገሮች ወደ ብስለት ሊያመጡን ያለው ጊዜ የዋዛ አይደለም። ለጊዜው አጭር መስመርን መመልከት እንጂ አሻግረን የማየት ብቃታችን የብስለታችን ደረጃ ይወስነዋል። ለአጭር ጊዜ በመኖራችን ምክንያት ያም ማለት ለረጅም ዕድሜ ስላልኖርን ብድራታችንን ትኩር ብለን ለማየት ብዙውን ጊዜ ይከብደናል።
ዮሴፍ በ 18 ዓመቱ ወደ ግብፅ ገብቷል, ሲል የያሽር[ ጥንታው መጽሐፍ ያስተምራል (The book of Jasher 1840 Translated into English from the Hebrew) በመጽሓፍ ቅዱስ ስለዚህ መጽሓፍ በሁለት ስፍራ ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? እያለ ስለመጽሐፉ እውነታ ይመሰክርለታል። ለምሳሌ መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 10/13 ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም። መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 1/18 የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ፥ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፎአል።
ዮሴፍ ጥሪው ተፈፀሞ የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆኑ በፊት 12 ዓመታት ሊፈጅበት ችላል። አስራ ሁለት ዓመታት ለሌሎቹ አጭር ጊዜ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በራሳችን ላይ ቢደርስብን ለረጅም ጊዜ ልምድ ሲኖረን ነገሩ ይለያል። ስለ ሙሴ የአርባ ዓመት የሥልጠና ዘመን ምን ማለት እንችላለን? ከነብሰ-ገዳይነት ቀይሮት በምድር ላይ ከነበሩ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ልበ ትሁት ነበረ እስኪባል ድረስ ክርስቶስ በሂዎቱ ታየበት ። ይህም የሆነው ብድራቱን ትኩር ብሎ በእምነት በመንፈስ ዘመናትን አሻግር ክርስቶስን ሲያየው በልቡ ትሁትና የዋህ የተባለ ቀሊል ቀንበር ብቻ ተሸክሞ አየውና ከግብጽ የነገስታት ክብር ይልቅ ክርስቶስንና ያለውን መምሰል መረጠ። ንጉስሽ የዋህ ሆኖ በአህያይቱ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል። አስቡት እስኪ የሰማይና የምድር ንጉስ የዋህ ሆኖ? ይህን ሲያስተውል ነፍስም አልቀረለትም ስለ እሱ ትንቢት ከመናገር በቀር። እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ እንዳቀደ ሁሉን ነገር የሚያድስበት ዘመን አለ ያ ከመሆኑ በፊት ግን እንደኔ ያለ ትሁት ልብ ያለው ነብይ ይነሳል። የሚገርመው ሙሴ በምድር ላይ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ትሁት ልብ ነበረው ብሎ ስለራሱ በፔንታቶክ መጽሐፍት የፃፈው እራሱ ስለራሱ ነበር። የሐዋርያት ሥራ 3/21 እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና።22 ሙሴም ለአባቶች፦ ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል፤ በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት።23 ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች አለ።
ያቆብንም ቢሆን ጌታ መጣና ስምህ ማነው? በመጽሐፍ ስም የሚያመለክተው ተፈጥሮንና ባህርይን ነው። ስምህ ማነው? ሲለው ያቆብ ስልችቶታል ማሰናከሉ ለመለወጥ ዝግጁ ስለነበር ሌባውን ና አሰናካዩ ነኝ፤ ያቆብ ነኝ!አለ የያቆብን ማንነት ጨርሶ እስራኤልን ከውስጡ አወጣ። ስምኦንንም ቢሆን ሸምበቆውን ለመጥማጣ ማንነቱን፤ ተሰባሪውን ባህርይ፤ የተደገፉትን መልሶ እጅ ከሚሰነጥቅ ማንነት ቀይሮ ጴጥሮስ አለት የሆነ ማንነት አመጣበት። የጤርሰሱ ሳኦልንም በአንድ ድምጽ ለዘመናት የደረጀ ባህርዩን አስጥሎ
ጳውሎስን ከውስጡ አወጣ ሐዋርያት ሥራ 26/14 ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ። ጌታን ሲመጣ መጣ ነው።ጌታን ተቀበል የለ በቃ ጌታ ሲመጣ ሲገለጥ ማንም ሰው ነፃ ፈቃድ ብሎ ነገር የለውም የእ/ርን ክብር ያየ ሁሉ ሙሉ በሙሉ ፈቃደኛ ሆኖ መልሱ ይህ ነው ።ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ? ! የሐዋርያት ሥራ 9/6 እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ፦ ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ? አለው። ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል አለው።
ዛሬ በዓለም ውስጥ ብዙ ያልተቀመሙ ነቢያት አሉ በእሳቱ ያልተቀመሙ ነቢያት ብቻ አይደሉም ነብይነት ታፔላ ወይም ቦሎ በለጠፈ ዓይደለም። በስራና በቃል የበረታህ ከሆንክ ስያሜን እራሱ ተግባሩ ያመጣዋልና። በተመሳሳይም ጳውሎስ በኤፌሶን ምዕራፍ 4 ቁጥር 11 ውስጥ የጠቀሰቸውን ዐምስቱ አገልግሎት በትመለከተም እያንዳንዱ ከቆምጣጣ ፍሬ ደረጃ ሌሎች ሊበሉ ከሚችሉት ጣፋጭ መንፈሳዊ ፍራፍሬዎችን እንዲያዘጋጁ በገበሬው ኩትካቶ ማጥራት መገረዝ ሊያልፉ ወሳኝ ነው። ሓዋርያው ሲናገር የበረሀ ከነበረ ወይራ ሲል እኮ ሁለቱም ወይራ ናቸው ልዩነታቸው የበረሃ ያልሆነው እኮ በገበሬው በደህና የታረመ የተኮተኮተ cultivated የሆነ ስለሆነ ነው። የcultivated ትርጉሙ እራሱ refined and well educated. “he was a remarkably cultivated and educated man” cultured, educated, well read, civilized, enlightened, discerning, discriminating, refined, polished; More
ወደ ሮሜ ሰዎች 11/24 አንተ በፍጥረቱ የበረሀ ከነበረ ወይራ ተቆርጠህ እንደ ፍጥረትህ ሳትሆን በመልካም ወይራ ከገባህ፥ ይልቁንስ እነዚያ በፍጥረታቸው ያሉት ቅርንጫፎች በራሳቸው ወይራ እንዴት አይገቡም?
የዮሴፍ ዕድሜው 30 ዓመት ሲሆን ሌላ ሰው ሆኖ ነበር። በ 17 ዓመቱ ከነበው ማንነት ተለውጠዋል። የእስር ቤት ህይወት አብዛኛውን ሰው መራራ የሚያደርግ ነው። ዮሴፍን ግን ጣፋጭ አድርጎታል. በፍቅርና በትእግስት የሚሰራ የእ/ር እምነት በውስጡ ህያው ነበረ። መልካም ምኞትና አዎንታዊ አስተሳሰብ ቢሆን ኖሮ በዮሴፍ ወስጥ ያለው ከጥቂት ድክመቶች በኋላ የመረረ ስብእና ይኖረው ነበር። የሸጡትን ወንድሞችንም ልበቀል ባለ ነበር። ነገር ግን እውነተኛ እምነት ሁልጊዜ ጥሩ ጣዕም ይኖረዋል ያፈራልም ትእግስት የበሰለ እምነት ማስረጃ ነው አባቶች በእ/ር አባት ፊት የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። እንዳትሸወዱ እምነት መንፈሳዊነው ወደ ልጅነት መረዳት መምጣት ከሰው የሆኑ ነገሮችን እንጂ ከእ/ር የሆነውን መጣል አይደለም። ከአንድ የመረዳት ሰማይ ከፍ ወዳለ የመረዳት ሰማይ በመንፈስ እስከ እ/ር ህሊና በክርስቶስ መወሰድ ነው። እ/ርም በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ብሎ ይመሰካራል። ልጄ በልቤም በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል ብሎ በደስታ የመንፈስ ምስክርነት ይገለጣል፤ በሌላ አማርኛ ከእ/ር አፍ ተዘጋጅቶ በሚወጣ ቃል ሁሉ በመጣ እምነት ልጆች ሃሴት ያደርጋሉ። የእግዚአብሔር ጽድቅ እኮ ከእምነት ወደ እምነት from faith to faith, from out of faith, into faith በእርሱ በጌታ ያለማቃረጥ የሚገለጥ ነው! ።ወደ ሮሜ ሰዎች 1/17 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።Rom 1/17 For therein is the righteousness of God revealed from faith to faith: as it is written, The just shall live by faith.kjv
Rom 1/17. For in It God’s justice (righteousness; qualities and characteristics of the Way pointed out; victory of the righteous cause; way of righting wrong; righteous act) is continuously (progressively) being unveiled (revealed), from out of faith, into faith, according as it has been written, GMT
ይሄ ለምሳሌ ያህል ነው እንጂ ይህን የሚረጋግጡ ብዙ ነጥቦችም አሉ። እናተም የምትገነዘቡትም ብዙ ይኖራል። በእግዚአብሄር አሰራር ውስጥ የሚጠቀምባችውን ተቃራኒ ሃይላት ካላስተዋልን ለመማር እንቸገራለን። እራሳችንን በፊቱ ዝቅ አድርገን ለመንገዶቹ የነቃ ህሊና ይኑረን። ወደ መለኩና አምሳሉ ሊያመጣን ሊሞርደን ተቃራኒ ሃይላት እደሚጠቀም መገንዘባችን ውስጥ ሃይል አለው። ምን አይነት ታላቅና በጥበብ ሁሉ የተሞላ አምላክና አባት ነው ያለን? ጌታ በማርቆስ ወንጌል 9፡49 ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ ሲል እውነቱን ነገሮናል እውነት የሆነውን አስቡ ተብለናልና እውነት የሆነውን እናስብ። ወደ ዕብራውያን 5፡8 ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ እኛ ከሱ አንበልጥምና መታዘዝን እንማር ዘንድ በሚያሳልፈን መንገድ ሁሉ ፈቃድህ ይሁን እንጂ ፈቃዳችን አይሁን ማለት እንችል ዘንድ የእ/ር ጸጋ ይርዳን። በጌታ ፍቅር ሰላም ይሁን።አሜን!
BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING, AND BEYOND