For e-v-e-r-y o-n-e shall be salted with fire


ጥያቄና/መልስ። Afework Kara You pick up the answer Yes/ No, “For e-v-e-r-y o-n-e shall be salted with fire,” First of all you didn’t ask direct question don’t expect direct answer it’s maybe simple NOT direct, b/c you are really way off the base to the true meaning of hell, traditionally religions see it as a spiritual realm of evil and suffering place, Don’t miss understood the fact that Lord told them many things unto them in p-a-r-a-b-l-e-s to give them understanding, Simply Hell and Gangnam is a symbol of judgment. And God’s judgments are Correctional judgment by Nature Isa 26/9 …. for when thy judgments are in the earth, the inhabitants of the world will learn righteousness. የማቴዎስ ወንጌል 13/34-35 ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።
KJV
Matt 13/34 All these things spake Jesus unto the multitude in parables; and without a parable spake he not unto them:
35 That it might be fulfilled which was spoken by the prophet, saying, I will open my mouth in parables; I will utter things which have been kept secret from the foundation of the world. በእብራይስጥ ትክክለኛው ገሃነም Gehenna [የሄኖም ሸለቆ Ge-Hinnom “valley of Hinnom”]የአሮጌው ኪዳኑ “hell” ወይም ገሃነመ እሳት ስያሜ ምንጭ የመጣበት በእዮርሳሌም፡ በስተደቡብ ይገኝ ከነበረ “የሄኖም ሸለቆ” ከተባለው ነው። በእንግሊዝኛው “Hell” በአማርኛ “ገሃነም” “ሲኦል” ተብሎ የተተረጎመው ነው። ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮ ይለማመዱ የነበሩ ነገስታት በነበሩት በአክአዝና በምናሴ ዘመነ መንግስት ሞሎክ ለተባለ ለአሞናውያን ጣኦት ሰዎች በጭካኔ ወንድ ልጁን እና ሴት ልጁን መስዋእት አድርገው በዚህ ሸለቆ ያቀርቡበት ነበር። ይደረግ የነበረው ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮም የተነሳ ኢዮስያስ ይህን ሸለቆ ርኩስ ሆኖ እንዲቆጠር አደረገ። ይህም ስፍራ ለዘመናት የከተማው ቆሻሻ መጣያ ና ማቃጠያ ቦታ ሆነ ቡሃላም የፍርድ ቅጣት ተምሳሌት ሆኖ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ተጠቅሞበታል። ከዚህ ሸለቆ አጠገብም ከፍ ባለው አቀበት ወይም ከፍታ ላይ ነበር እዮርሳሌም የተገነባችው።
መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 23/10 ማንም ሰው ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት እንዳያሳልፍ በሄኖም ልጆች ሸለቆ የነበረውን ቶፌትን ርኩስ አደረገው።[የቀድሞው ትርጉም]
‘በሄኖም ሸለቆ የነበረውን ቶፌት የተባለውን ማምለኪያ አረከሰ፤ ይኸውም ማንም ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ እንዳያቀርብበት ነው። ‘2 ነገሥት 23:10[መደበኛው ትርጉም]
2Kgs 23/10 And he defiled Topheth, which is in the valley of the children of Hinnom, that no man might make his son or his daughter to pass through the fire to Molech.[KJV]
ኤርምያስ 7:30-32/ የይሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉን ነገር ሠርተዋል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ርኵሰታቸውን አኑረዋል። 31 እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያለችውን የቶፌትን መስገጃዎች ሠርተዋል።32 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ስፍራ ከማጣት የተነሣ በቶፌት ይቀበራሉና የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።[የቀድሞው ትርጉም]
‘እኔ ያላዘዝኋቸውን፣ ከቶም ያላሰብሁትን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት አቃጥለው ለመሠዋት በሄኖም ልጅ ሸለቆ የቶፌትን መስገጃ ኰረብቶች ሠሩ። ስለዚህ አስተውሉ፤ ይላል እግዚአብሔር ፤ ስፍራ እስከማይገኝ ድረስ ሙታንን በቶፌት ስለሚቀ ብሩ፣ የዕርድ ሸለቆ እንጂ ከእንግዲህ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል። ‘ ኤርምያስ 7:31-32 [መደበኛው ትርጉም]
30 For the children of Judah have done evil in my sight, saith the Lord: they have set their abominations in the house which is called by my name, to pollute it.
Jer 7/31 And they have built the high places of Tophet, which is in the valley of the son of Hinnom, to burn their sons and their daughters in the fire; which I commanded them not, neither came it into my heart.
32 Therefore, behold, the days come, saith the Lord, that it shall no more be called Tophet, nor the valley of the son of Hinnom, but the valley of slaughter: for they shall bury in Tophet, till there be no place.[KJV]

እግዚአብሔር በነብይ ኤርምያስ የእ/ርን ቁጣ በትንቢት ተናገረ ፍርድ በእዮርሳሌም ሲመጣ “የዕርድ ሸለቆ” ተብሎ እንደ ሚጠራ ተነበየ።
ትንቢተ ኤርምያስ 19/6 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡[የቀድሞው ትርጉም]
Jer 19/6 Therefore, behold, the days come, saith the Lord, that this place shall no more be called Tophet, nor The valley of the son of Hinnom, but The valley of slaughter.
እ/ር በትንቢት ሲናገር ፍርድ በእዮርሳሌም ሲመጣ “የሸክላ ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፤ ይህን ሕዝብና ይህቺን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤” ብለዋል ብለህ ንገራቸው አለው።
‘“ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፤ እንዲህም ትላቸዋለህ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሸክላ ሠሪው ገንቦ እንደ ተሰበረና ሊጠገን እንደማይቻል፣ ይህን ሕዝብና ይህቺን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤ የቀብር ቦታ ከመታጣቱ የተነሣ ሙታናቸውን በቶፌት ይቀብራሉ። ‘ኤርምያስ 19:10-11
ከዛም እዮርሳሌም ትንሽ ቆይታ በባቢሎናውያን ሰራዊት ጠፋች። ከአንድ ክፍለ ዘመን ቡሃላ በነህምያ ዘመን ድጋሚ ተሰራች። ላለፉት 2000 ሺ አመታት በተደጋጋሚ ጠፍታ ነበር። የደገመች ተሰራች። ከተማዋም አሁን ቆማለች። የኤርምያስ ትንቢት የመጀመርያው የፍርድ ገጽታ ነው የተፈፀመው። የዚህ ትንቢት ሙሉ ጥፋት የሚያካትተው ቅሪት አለው።
ጌታ እየሱስም ከገሃነም ጋር ተያይዞ የተነገረውን ትንቢት በእዮርሳሌም ላይ የተነገረውን ጭምርና በተምሳሌነትም ደጋግሞ ተናገረው። በገሃነም ምሳሌም 11 ግዜ ተጠቅሞበታል። ( በማቴ 5:22 , 29 , 30 ; 10:28 ; 18: 9 , 23:15 , 33 ; ማርቆስ 9 43 , 45 , 47 ; ሉቃስ 12 5 ያንብቡ ።)

‘ “እናንተ እባቦች፤ የእፉኝት ልጆች! ከገሃነም ፍርድ እንዴት ልታመልጡ ትችላላችሁ? ስለዚህ ነቢያትን፣ ጠቢባንንና መምህራንን እልክላችኋለሁ፤ ከነዚህም አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹንም በምኵራቦቻችሁ ትገርፏቸዋላችሁ፤ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዷቸዋላችሁ። ስለዚህ፣ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው ንጹሕ ደም ሁሉ እናንተ ተጠያቂዎች ናችሁ። እውነት እላችኋለሁ፤ ላለፈው ነገር ሁሉ ይህ ትውልድ ይጠየቅበታል። ‘ማቴዎስ 23:33-36
ቡሃላ ወረድ ብሎ በእዮርሳሌም ላይ የፍርድ ቃሉን ሲናገር እናያለን።
‘ “አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ አንቺ ኢየሩሳሌም! ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ! እናንተ ግን ፈቃደኛ አልሆናችሁም፤ እነሆ፤ ቤታችሁ ወና ሆኖ ይቀርላችኋል! እላችኋለሁና፤ ‘በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው’ እስከምትሉ ድረስ ዳግመኛ አታዩኝም።”’ማቴዎስ 23:37-39
ኤርሚያስ የእዮርሳሌምን ጥፋት ከገሃነም ሸለቆ ላይ እንደተሰበረው የሸክላ ገንቦ እንደምትሰባበር ከፍርድ ጋር ካያያዘው ቡሃል ገሃነም የእ/ር ቃል የሚቃወሙት ላይ የመለኮት ፍርድ ተምሳሌት ሆነ ። ጌታም እዮርሳሌም እንደምትጠፋ ደግሞ ተነበየ።
ስለዚህ፣ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው ንጹሕ ደም ሁሉ እናንተ ተጠያቂዎች ናችሁ። እውነት እላችኋለሁ፤ ላለፈው ነገር ሁሉ ይህ ትውልድ[genea, “ዘር race, ዝርያ offspring”] ይጠየቅበታል። ‘ማቴዎስ 23:34-36
ጌታ እየሱስ አማኞች እየሩሳሌም በውጭ ጦር ስትከበብ ከከተማዋ ፈትለክ ብለው እንዲያመልጡ አስጠነቀቃቸው። እነሱም ከ 66-67A.D. ገደማ ተበተኑ። በ70AD ላይ ታይተስ የተባለ የሮማ ጀነራል እዮርሳሌምን አጠፋት። አሁንም የትንቢቱ ሙልአት ገና በመሆኑ አማኞች የእየሱስን ቃል ሊያስቡበት ይገባል። አማኞች እየሩሳሌም በውጭ ጦር ስትከበብ ከከተማዋ ፈትለክ ብለው ሊያመልጡ ይገባል እ/ር ያድነናል ብለው መቀመጥ የለባቸውም ይህ ትንቢት ከላይዋ ነው እና። የነብዩ ኤርሚያስ ትንቢት ግልጽ ነው ዳግም ልትስራ እስከማትችል በገሃነም ሸለቆ ላይ እንደሰበረው የሸክላ ገንቦ እንደምትሰባበር ተናግረዋልና አማኞች የወረራ ምልክት ካዩ ሊዘናጉ አይገባም። ምናልባትም ከተማይቱ መርገሙየሚሰበርላት “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” ብላ ክርስቶስን ከተቀበለች ብቻ ነው።
ስለዚህ ጌታ ጋሃነም የሚለውን የእብራይስጥ ቃል ተጠቅሞ ለግሪኮችና ለሮማዊያን ዝምድና የሌለው ቃል ቢሆንም ለ11 ግዜ በእርሱ ቃል የማይታመኑትን እነሱም እያስጠነቀቀ ካላመኑ የኤርሚያስ ትንቢት እንደ ሚፈፀምባቸው እየነገራቸው ነበረ። እነሱም በግላቸው በጅምላ ፍርዱ ላይ ተካተው ሊገኙ እንደሚችሉ ኤርሚያስ እንደ ተነበየው “የእርድ ሸለቆ” እንደ ሚሆን አስጠነቀቃቸው።
ሌላው ጌታ ከተናገራቸው የገሃናም ተምሳሌት ፍርድ መካከል ሊታዩ የሚገባቸው አንዱ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤” የሚለው ቃል ነው።
‘ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጒለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤ ‘ማርቆስ 9:47-48

ጌታ የጠቀሰውና የተነተነው የነብዩ ኢሳያስን ትንቢት ነበር። ‘“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”’ኢሳይያስ 66:24
ኢሳያስ እየተናገረ የነበረው ስለ አሮጌዋ እዮርሳሌምና ስለ አዲስትዋ እዮርሳሌም ነበር።
‘“ወዳጆቿ የሆናችሁ ሁሉ፣ ከኢየሩሳሌም ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ስለ እርሷም ሐሤት አድርጉ፤ ለእርሷ ያለቀሳችሁ ሁሉ፣ ከእርሷ ጋር እጅግ ደስ ይበላችሁ። ‘ኢሳይያስ 66:10
‘“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ የእናንተና የዘራችሁ ስም እንደዚሁ ጸንቶ ይኖራል” ይላል እግዚአብሔር ፤ ‘ኢሳይያስ 66:22
ስለዚህም ነበር ጌታ ገሃናምን የተጠቀመው ይደረግ የነበረው ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮም ርኩሰት በዛ ዘመን ቆሞ ነበርና በዚያ ዘመንም ይህም ስፍራ ለዘመናት የከተማው ቆሻሻ መጣያ ና ማቃጠያ ቦታ ሆነ ቡሃላም ብዙ የሞቱ እንስሶች እና የሰዎች አካል ሳይቀር ይጣልበት ነበርና የበሰበሰም የበዛበት ያለማቋረጥ በትላትሎችም የተሞላ ነበረ። ጠረኑን ለመቋቋም ሲባል ቆሻሻውንም ለማቃጠል ሁልጌዜ የማይጠፋ ፍምና እሳት ይታይበት ነበረ። በዚህም የፍርድ ቅጣት ስፍራ ምሳሌ ሆኖ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና” የሚለውን ተጠቅሞበታል።
‘ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጒለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤ ‘ማርቆስ 9:47-48
ሌላው ሲኦል የሚለው ቃል በመጀመርያ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ የሚገኘው ፔንታቱክ [ባለ አምስት ቅጽ መጽሓፍት(ማለት ነው)] ተብለው በሚታወቁት አምስቱ የሙሴ ጹሁፎች መካከል በኦሪት ዘኍልቍ 16/30 ሲሆን ከዛ ቡሃላ በብዙ ቦታ ላይ ተጽፈዋል። ይህም አንድ የእብራይስጥ ቃል እናም ሰዎስት የግሪክ ቃል በእንግሊዝኛው “Hell” በአማርኛ “ሲኦል” በማለት የተተረጎመው ነው። በአብዛኛው በብሉይ ወይም በአሮጌው ኪዳን በሁሉም የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ሁሉ “SHEOL” የሚለው ቃል ተጠቅመውበታል ትርጉሙም ድርብ ሳይሆን ነጠላ የሆነ “የሙታን ቦታ” “the place of the dead.” ማለት ነው። ሌላው ትርጉሙ የሙታን መቃብር grave, ጉድጋድ pit የሙታን ግዛት the realm of the dead።
ኦሪት ዘኍልቍ 16/30 እግዚአብሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እንደ ናቁ ታውቃላችሁ። Num 16/30 But if the Lord make a new thing, and the earth open her mouth, and swallow them up, with all that appertain unto them, and they go down quick into the pit[ sh’owl sheh-ole’] then ye shall understand that these men have provoked the Lord.

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal