
እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ አጽናኙ ነው። Binyam TA Afework Kara universalism ? ወንድሜ አፈወርቅ እንግሊዝኛ ስለሆነ ባእድ አይምሰልህ ይህ እቅድ የአባታችንና አምልካችን ሃሳብ ነው። እ/ር አሰበ ተናገረ ማለት ደግሞ ሆነ ማለት እንደሆነ የታወቀ ይሁን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1/9 በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤
10በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። እ/ር እሳት ነው። ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማል። አጉራ ዘለል ሆኖ የልጁን መልክ መምሰል የለም ተሰርቶ ያበቃ መልክ የለም ገና ሁላችንም ያንን መልክ እስክንመስል ከክብር ወደ ክብር እየተቀየርን ነው። ነገሩ በቃሉ ማየት ይቻላል በክርስቶስ አእምሮ ካየነው የጥበብና የመገለጥ መንፈሱ በእኛው አድረዋልና። በተፈጥሮ አእምሮ ካየነው ግን ነገሩ “ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?” መሆኑ አይቀርም። እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ ነው። በሌላ አነጋገር እራሱ መንፈስ ቅዱስ ነው። የግሪኩ ቃል ፍቺ ይህን ያረጋግጥልናል። በእርግጥ አማርኛችን ጨምሮ ብዙ ትርጉሞች እውነቱን እንዳናይ የራሳቸው የከለላ ድርሻ አበርክተዋል።
እውነት ወይም ምስክርነት የሚፀናው ወይም የሚመሰረተው በሁለት ወይም በሰዎስት ነውና ተጨማሪ የእ/ር ቃል ያስፈልገናል። የዮሐንስ ወንጌል 8:17
ጌታ ምን እንዳለ አስተውሉ። ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። መጣ እሺ ከዛስ በኋላስ መንፈስ ስለሆነ ምን አለ? ዓለም አያየኝም፤እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ በዚያን ግዜ ምን ይከሰታ? ማወቅ ይከሰታል። ‘እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።’ ሃይሉ ያለው ማወቁ ላይ ነው ዓለም አያየኝም፤እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤’ ቅኔውን ሲፈታው ስለራሱ እንጂ ስሌላ እያወራ እንዳልሆነ አስተዋላችሁ? ።
የዮሐንስ ወንጌል 14/18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። 19ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ። 20እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።
“I will NOT leave you abandoned[comfortless], or send you off as orphaned ones. I am repeatedly (habitually) and progressively coming toward you [in the form of the comforter and spirit of truth] men. (Jn 14:18
ጌታችን ምን እንዳለ በግማሽ ሳይሆ በሙሉ ትኩራታቹሁ አሁን አስተውሉ። መንፈስ ማን እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሆነ ግልጽ ያደርግልናል። የስላሴ 3ኛ አካል ነው ?ጌታ እራሱ ይናገር።
20እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን[አጽናኙ በሚመጣበት ቀን] ታውቃላችሁ።
“IN THAT DAY [the day when the comforter comes] you shall know that I am in My Father, and you in Me, and I IN YOU” (Jn 14:20
“John 14/28 Ye have heard how I said unto you, I am going, and I AM COMING TO YOU” የዮሐንስ ወንጌል 14/28 እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ።
አስተዋላችሁ ጌታ ምን አለ ? I am going, and I AM COMING TO YOU! እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ!
አሁን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ ተብሎ መጠራቱን በእ/ር ቃል እናረጋግጥ። nother Comforter[ጳራቂላጦስ] ሌላ አጽናኝ[ጳራቂላጦስ] ይሰጣችኋል ያለው ጳራቂላጦሱ ማን እንደሆነ እናያለን።
የዮሐንስ ወንጌል 14/15-16 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ[ pray] ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] ይሰጣችኋል፤
John 14/15 If ye love me, keep my commandments.16 And I will pray the Father, and he shall give you another Comforter[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.], that he may abide with you for ever;
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2
1 ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
1John 2/1 My little children, these things write I unto you, that ye sin not. And if any man sin, we have an advocate[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] with the Father, Jesus Christ the righteous: ያውላቹ እንግዲህ ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ጳራቂላጦስ አጽናኙ እራሱ ነው። በተረፈ በጌታ ፍቅር ሰላም ለአንተ ይሁን። የመለካከት ልዩነት በሃዋርያትም ዘመን ንርበረ ሁሉም የእ/ር ልጆች ናቸው። በመጨረሻ ደስ የሚለው እ/ር የሚያመጣን ቦታ አለ እሱም ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ስራውን እየሰራ ነው ለክርስቶስ መንፈሳዊ አካል ሕንጻ ፍጹማን ያደርገናል። ክብር ለቅዱስ ስሙ ይሁን።