
አጥፊው የወደቀ መላክ አይደለም ከ-፟መ፟-ጀ-መ-ሪ-ያ-ም በእ/ር አጥፊ ሆኖ የተፈጠረ ነው። ከ-፟መ፟-ጀ-መ-ሪ-ያ-ም ነፍሰ ገዳይ ነበረ። እባቡ ከ-፟መ፟-ጀ-መ-ሪ-ያ-ም እግዚአብሔር አምላክ ሲፈጥረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ሆኖ ነበር።
‘“……..የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ጥፋት እንዲያደርስም የፈጠርሁ እኔ ነኝ አጥፊውንም የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ‘ኢሳይያስ 54:16 አዲሱ መደበኛ ትርጉም Isa 5416 Behold, …….I have created the waster to destroy.
የዮሐንስ ወንጌል 8/44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።
ኦሪት ዘፍጥረት 3/1 እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ።
የዮሐንስ ራእይ 20/2 የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው
በትንቢተ ኢሳይያስ 45፡7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አዎን ሁሉን መፍጠሩን እ/ር ሃላፊነቱን ወስደዋል:: ኦሪት ዘጸአት 4/11 እግዚአብሔርም፦ የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው? ዲዳስ ደንቆሮስ የሚያይስ ዕውርስ ያደረገ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?እርስ በራሳቸው የሚቃረኑትም ጭምር ማለት ነው። ለማሰብ ያህል መራራና ጣፋጭ፤ ሃዘንና ደስታ፤ ድሃና ባለጠጋ፤ ጨለማና ብርሃን፤ መልካምና ክፉ፤ ህግና ጸጋ፤ ተፈጥራዊ ነገሮች ና መንፈሳዊ ነገሮች፤ ሞትና ህይወት፤ እስራትና ነጻነት፤ ለምን ብሎ እ/ር እንደዚህ በጥብቅ የሚቃረኑ ሃይላትን በአላማ ፈጠረ። ወንድም ቢኒ።