የአካል መነጠቅ(rapture) ውሸት ነው!


የአካል መነጠቅ(rapture) ውሸት ነው!
የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሚነጠቁት ሀጥአን ወይስ ፃድቃን?
July 25, 2011 Brother Binyam T. Alemayehu
 
የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ ክፍል አንድ።
ፁሁፉን አንድ ወንድም ጅማሪውን ባስቀመጡት መግቢያ ልጀምረው።
“አብዛኛው ሰው ዘመናዩ ከመከራው በፊት መነጠቅ(rapture) የሚለው ንድፈ ሃሳብከ 200 መቶ ያነሰ እድሜ እንዳለው አይገነዘብም። የዚህ ጽንሰ ሃሳብ የጀመረው በ1812 በስፓኒሽ ቋንቋ የካቶሊክ እምነት ተከታይ የነበረ ሰው manuel de lacunza ydiaz የተባለ በ2 መጽሐፍት እትም 900 ገጽ ስራው “ዘካሚንግ ኦፍ መሳያ ኢን ግሎሪ ኤንድ ማጂስቲ “በሚለው ተጀመረ ። ቡሃላም በሬቨረንድ edward irving በ1827 ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ ታተመ።” የተጠቀሰ።
 
ይህ ሃሳብ ያስከተለውን የአመለካከት መዘዝ ወደፊት እንነካካዋለን። በእ/ር ቃልም እሳት እናሳልፈውና አንጥረነው በዚህጉዳይ የነጠረውን እውነት ጌታ እንደ ረዳንንመጠን እንይዛለን። ስለ መነጠቅ ከብዙ ወገኖቼ ጋር በጸጋ ለመጠቃቀም በመነጠቅ ሃሳብ ላይ ከዚህ ቀደም ተነጋግሬ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይም ከጥቂቶች በቀርፈጽሞ ከእ/ር ቃል ጋር የማይጠጋጋ ከአራምባና ቆቦ ይልቅ መራራቅ እንዳለው አስተውያለሁ። በዛሬው ጥናታችን እንድናየው የምፈልገው አማኞች ሁሉ ይነጠቁና የማያምኑት መከራውን ሊፋለሙ በዚህ ይቀራሉ የሚለውን አመለካከት ነው።
 
እነዚህ የተለመዱ አመለካከቶች ከተደገፉባቸው ቃላት መካከል በማቴ 24፡39-41 የሚገኘው ነው። “39 የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። 40 በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤ 41 ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች።” በዚህ ቃል ላይ የተለመደው አመለካከት አማኞቹ እንደሚወሰዱ እና የማያምኑት እንደሚቀሩ ነው። ጌታ ግን ይህን እያስተማረ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ይህን እንድናስተውል ከላይ በቁጥር 37-38 ያለውን እናስተውል። “37 የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። 38 በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥” በቁጥር 37 የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ እንደ ሚሆን ይነግሮናል። በኖህ ዘመን እንደ ነበረ ከሆነ በኖህ ዘመን ምን ይመስል ነበር የሚለው ጥያቂያችን ነው። ዘፍጥረት7፡13-23 ይገልጽልናል።
 
“13 በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ፥ የኖኅ ልጆችም ሴም ካም ያፌትና የኖኅ ሚስት ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከርሱ ጋርገቡ። 14 እነርሱ፥ አራዊትም ሁሉ በየወገናቸው፥ እንስሳትም ሁሉ በየወገናቸው፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱተንቀሳቃሾችም ሁሉ በየወገናቸው፥ ወፎችም ሁሉ በየወገናቸው፥ የሚበሩ ወፎችም ሁሉ፥ 15 ሥጋ ያላቸው ሕያዋን ሁሉ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ኖኅ ወደመርከብ ውስጥ ገቡ። 16 ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ገቡ እግዚአብሔርም በስተኋላው ዘጋበት። 17 የጥፋትም ውኃበምድር ላይ አርባ ቀን ነበረ ውኃውም በዛመርከቢቱንም አነሣ፥ ከምድርም ወደ ላይከፍ ከፍ አለች። 18 ውኃውም አሸነፈ፥በምድር ላይም እጅግ በዛ መርከቢቱምበውኃ ላይ ሄደች። 19 ውኃውም በምድርላይ እጅግ በጣም አሸነፈ ከሰማይም በታችያሉ ታላላቆች ተራሮች ሁሉ ተሸፈኑ። 20ውኃው ወደ ላይ አሥራ አምስት ክንድ ከፍከፍ አለ ተራሮችም ተሸፈኑ። 21 በምድርላይ ሥጋ ያለው የሚንቀሳቀሰው ሁሉ፥ወፉም፥ እንስሳውም፥ አራዊቱም፥ በምድርላይ የሚርመሰመሰው ተንቀሳቃሹም ሁሉ፥ሰውም ሁሉ ጠፋ። 22 በየብስ የነበረውበአፍንጫው የሕይወት ነፍስ እስትንፋስያለው ሁሉ ሞተ። 23 በምድር ላይየነበረውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳድረስ፥ እስከ ሚርመሰመሰውም ሁሉድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍ ድረስ ተደመሰሰከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውትበመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ።”
 
ከቃሉ እንዳስተዋልነው ጻድቁ ኖህና ቤተሰቡ ነበሩ በምድር የቀሩት ተጠርገው የተወሰዱት ሃጥአን ነበሩ። እ/ር የሃጢያት ጽዋቸው ስለ ሞላ በውሃ አስጥሞ በመግደል ከምድር የወሰደው ሃጥአኑን ነው እንጂ የነጠቀው ጻድቃኑን አልነበረም። በቀደመው ኪዳን መጽሐፍትም ሃጣንን እ/ር በፍርድ ሲነሳ ረጅምን እድሜ ሳይጠግቡ ከምድር እንደ ሚነጥቃቸው የሚያሳዩ ብዙ የእ/ር ቃላት አሉ። ለምሳሌ
 
መጽሐፈ ምሳሌ 2/22 ኃጥኣን ግን ከምድር ይጠፋሉ፥ ዓመፀኞችም ከእርስዋ ይነጠቃሉ።
 
መዝሙረ ዳዊት 50/22 እግዚአብሔርንየምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ አለዚያግን ይነጥቃል የሚያድንም የለም።
 
የሰው ልጅ መምጣት እንደዚህ እንደ ኖህ ዘመን ከሆነ በዚያን ቀን የሚሆነው ብዙዎች እደሚያስቡት ሳይሆን ተቃራኒው ነው የሚከሰተው። ያም አማኞች ወደ ሰማያት ይነጠቃሉ ከዚያም ነጭ ቢጃማ ለብሰው ዘምባባ እያውለበለቡ ምንም ሳይሰሩ ለዘላለም ሊኖሩ እንደሚያስቡት ሳይሆን በኖህ ዘመን እንዳደረገው የማያምኑትን በፍርድ ከምድር እንደሚነጥቅ የሚናገር ሃሳብ ነው። ጌታ እየሱስ ይህንን ሃሳብ የሚመስል በዚህ ምእራፍ ላይ ብቻ አይደለም ያስተማረው
 
“የማቴዎስ ወንጌል 13:24-30 ሌላምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች። 25 ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ። 26 ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ። 27 የባለቤቱም ባሮች ቀርበው። ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት። 28 እርሱም፦ ጠላት ይህን አደረገ አላቸው። ባሮቹም። እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት። 29 እርሱ ግን፦ እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም። 30 ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን።እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።31 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህምአለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤”
 
ከዚህ ቃሉ እንደ ምናስተውለው አማኞች(ስንዴዎች) ከማያምኑት(እንክርዳዶች) ጋር አብረው እንዲያድጉ የመከሩ ጌታ ፈቅደዋል። በጨረሻው የመከር ጊዜ ሲደርስ አጫጆችን ያዘዘው አስቀድማቹሁ እናስተውል አስቀድማችሁ የማያምኑትን(እንክርዳዶችን) ልቀሙ በእሳት ለማቃጠልም በየኖደው እሰሩ ነው ያለው እንጂ ስንዴዎችን አስቀድሙ አይደለም። ይሄም ሌላ ግልጽ ተቃራኒ ምሳሌ ጡንቻ ያወጣውን ገናና የመነጠቅ አስተምህሮትን ሚዛን እንዳይደፋ ያቀለዋል። ነገሩ ማንም ሲናገር እንደ እ/ር ቃል ይናገር ነውና እውነትን ለመናገር መፍራት የለብንም።
 
ሌላው ይህን እውነት የሚያጸናው ጌታ በሚቀጥሉት ቁጥሮች ይህንኑ መሚከተለው መልኩ ስለ ምሳሌው ፍቺ ገለጻ መስጠቱ ነው።
 
“36 በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤትገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው። የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት 37 እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤ 38 መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤ 39 እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት(መልእክተኛች) ናቸው። 40 እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል። 41 የሰው ልጅ መላእክቱን( መልእክተኛች) ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥ 42 ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። 43 በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥትእንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለውይስማ። ”
 
የምሳሌው ገለጻው በአብዛኛው ያተኮረው ለእንክዳዶቹ ምን እንደ ሚደርስባቸው ነው። ተለቅመው ወደ እሳት ባህሩ የተላኩት እነሱ ናቸው። እሳቱን በምንም መልኩ ተረዱት ቅደም ተከተሉ ግን ያ ነው። “ እ/ር የሁሉ ፈጣሪና ዳኛ” በሚለው መልክት የእሳት ባህሩ ፍቺ “a lake of divine purification የመለኮት የማጣሪያ ባህር” እደሆነ ፍርድ የሚለው ሃሳብ እንደ ተጠበቀ ሆኖ አይተነው ነበረ ። ከጌታም ምሳሌዎች አንድ ነገር ግልጽ ነው ከምድር የሚወሰዱት አማኞች ሳይሆኑ የማያምኑት ናቸው።
 
“የሉቃስ ወንጌል 17፡34 እላችኋለሁ፥በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል። 35 ሁለት ሴቶች በአንድ ወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች ሁለተኛይቱም ትቀራለች። 36 ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል።”
 
እንግዲህ እንደ እነዚህ ያሉ ቃላቶች ፍቻቸው በፊልም እንደ ተሰራው ሳይሆን ከላይ በቃሉ የእውነት ብርሃን እንዳስተዋልነው በመጨረሻው “እንደ ኖህ ዘመን ይሆናል” እንዳለው ነው። ቀሪው በተሰሎንቄ ያለውን ሃሳብ ጨምሮ ጌታ ቢፈቅድ በሚቀጥለው ጊዜ እናየዋለን። የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ 1
 
ጌታ ይብዛላችሁ አሜን! ክፍል 2 እና 3 ይቀጥላል። ከዚህ ያንቡቡ http://wongelradio.org/%E1%8B%A8%E1%8A%96%E1%8A%85-%E1%8B%98%E1%88%98%E1%8A%95-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B0-%E1%8A%90%E1%89%A0%E1%88%A8-%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%88%8D-2/
 
BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING, WRITINGS, ማደግ
  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal