ጥያቄ ከወንድም ደምስ:  ኢሳይያስ 4:1ን ልታብራራ ትችላለህ?


ጥያቄ ከወንድም ደምስ:  ኢሳይያስ 4:1ን ልታብራራ ትችላለህ?

ክፍል አንድ፦ መልሱ ሁለት ገጽታን ያዘለ ነው የመጀመርያው ታሪክዊ እውን እንድምታ ተፈፃሚነት ያገኘው ሲሆን ሁለተኛው መንፈሳዊ ፍቺው ከአዳም ወደ ክርስቶስ ተፈጥሮ ወዳለው ሽግግር መንፈሳዊ ጉዞውን ገፀ ባህሪ የሚነካካ ነው።

ትንቢተ ኢሳይያስ 4:1 በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች፦ የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ መሰደባችንንም አርቅ ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።

1ኛ፣ የታሪክዊ እንድምታ መልስ-  የመጀመሪያዎቹን  የትንቢተ ኢሳይያስ  ሶስት  ምዕራፎች ስታነቡ ስለ ሁለቱ የደቡባዊ ነገዶች በተመለከተ እግዚአብሔር አባትና አምላክ ስለሚሰጠው ማስጠንቀቂያ ታገኛላችሁ በግልጽ ታስተውላላችሁ።  የአይሁድና የቢንያም የደቡባዊ ነገዶች በእንቢተኝነት ውስጥ ሲፋንኑ ይስተዋላል። በአብዛኛው ለህዝቡ ኃጢአተኛነት ሲበዛ የእግዚአብሔር ትንቢታው ፍርድ ሲመጣ በመጀመሪያ ተፈጥራዊ የትንቢቱ የመፈፀም አቅም ሲኖረው ቅደም ተከተል ሊኖረው ይችላል እንጂ የመጨረሻ  መንፈሳዊ እርከን ላይ የሚፈፀም ጉልበት ይዞ ሊነገርም ይችላል።

የዚህ ቃል ጉልበት ሁኔታው ሁለት ገጽታን ያዘለ ነው የመጀመርያው ታሪክዊ እውን እንድምታ ተፈፃሚነት ያገኘው ሲሆን ሁለተኛው መንፈሳዊ ፍቺ ያቀፈ ነው።

እስራኤል በመባል የሚታወቁት ከ12ቱ ነገዶች አሥሩ ሰሜናዊ ነገዶች በ 721[BC] ከክርስቶስ ልደት በፊት በእግዚአብሔር ያህዌ ላይ በማመፃቸው በእ/ር በራሱ ፍርድ በአሦራዊያን በምርኮ ተወስደዋል።  የደቡብ ነገዶች በመባል የሚታወቁት ሁለቱ ውህድ ይሁዳ ነገዶች ። የሰሜናዊያን ነገዶች ዘመዶቻቸው በግዞት ሲወሰዱ በማየት ትምህርት ማግኘት ነበረባቸው ነገር ግን ማስተዋሉ አልተሰጣቸውም ነበር።

በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ትንቢታዊው ፍርድ ሰደድ ቀጠለና ሁለተኛው ተፈጥራዊ የትንቢታዊ መፈፀም ቅደም ተከተሉን ጠብቆ በ 606[BC] ከክርስቶስ ልደት በፊት በአሶራውያን አሥሩ ሰሜናዊ ጎሳዎች በተማረኩ  ከ115 ዓመታት በኋላ  በባቢሎናውያን በተካሄደው ወረራ በግዞት እንደሚወሰዱ ተንብዮ እንደነበረው ተፈፀመ።  “በኢሳያስ ምዕራፍ 39 /5 ኢሳይያስም ሕዝቅያስን፦ የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። 6 እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ 7 ከአንተም ከሚወጡት ከምትወልዳቸው ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ አለው። 8 ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፦ የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው አለው። ደግሞም፦ በዘመኔ ሰላምና እውነት ይሁን አለ።”

በትንቢቱ እንዳስተዋልነው ከተማረኩ ቡሃላ በባቢሎን ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች[ወንድነታቸው የተሰለቡ፤ የተቆረጡ] ይሆናሉ አለው። አሁን ሰባት ሴቶች አንድን ወንድ የሚይዙበትን “ያ ቀን” የሚለው ጥቅስ በኢሳይያስ 4: 1 ን ምክንያቱ በባቢሎናን ምርኮኞች ውስጥ አብዛኞቹ ሰዎች ሲገደሉ እንደነ ነብዩ ዳንኤል እና ጓደኞቹ  ያሉ ብዙ ተያዙ።

በእነዚህ አስፈሪ የእ/ር ፍርዶች ብዙዎች ተገድለዋል ብዝዎችም ተይዘው በመማረክ ምክንያት በእነዚያ ቀናት ለባልነት የሚሆኑ የወንዶች እጥረት ተከስቶ ስለ ነበረ ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ለማግባትና በስሙ ለመጠራት ይጋደሉ ነበር። ሴቶቹ ለማግባት ሲሉ በተፈጥሮ ሴትን መንከባከብ የሰውዬው ሃላፊነት የሆነውን ሁሉ ሳይቀር ለራሳቸው ሃላፊነቱን ይወስዱለታል። ሁሉዋም ሴት የራሷን ምግብ እና ልብስ ትገዛለች ወጪዋን እራስዋ ትችላለች ይህ ሁሉ የሚጋደሉበት ምክንያት ያለመውለድ ነቀፌታ እንዲነሳላቸው ነበር። ምንያቱም ታስታውሱ እንደሆነ ፤ እያንዳንዳ የአይሁድ ሴት “የሴቲቱን ዘር” መሲህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በማእፀንዋ ለመሸከም ፈልጎትዋ ታላቅ ነበርና (ዘፍጥረት 3 15)። ይቀጥላል….. 2 ወንድም ቢኒ

ክፍል ሁለት

2ኛ። መንፈሳዊ ፍቺው ከአዳም ወደ ክርስቶስ ተፈጥሮ ወዳለው ሽግግር መንፈሳዊ ጉዞውን ገፀ ባህሪ የሚነካካ ነው ብለናል።

ትንቢተ ኢሳይያስ 4/1 በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች፦ የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ መሰደባችንንም አርቅ ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።

ይህ ስለ ሰባት ሴቶች ይናገራል። ሰባቱ ሴቶች ደግሞ የክርስቶስ አካል የሆኑት ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ናቸው! “የዮሐንስ ራእይ 1/4-5 ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥”

በዛን ቀን አንዱን ሰውን ይይዛሉ እሱም ክርስቶስ ነው። ግን ችግሩ አሁንም የመጀመሪያ ባላቸውን አልቀበሩም። አሁንም የቀድሞ አሮጌው ሰው አዳማቸውን[ባላቸውን] የሙጭኝ ብለ እንደያዙ ናቸውና ይህ ደግሞ መንፈሳዊ ዝሙት ነው። በዚህ ታላቅ የጌታ ቀን ወደ ክርስቶስ እየመጡ ጌታ ሆይ በስምህ[በተፈጥሮህ፤ በባህርይህ፤] እንጠራ ነቀፋችንን ለማስወገድ እንሻለንና ይሉታል። ነገር ግን አሁንም የራሳችንን ዳቦ[ስጋዊ አስተሳሰብ] መብላት እና [ክርስቶስን ሳይሆን]የራሳችንን ልብስ አሮጌውን ሰው እንለብሳለን። በሌላ አባባል ‘ጌታ ሆይ፡ በስምህ[በተፈጥሮህ፤ በባህርይህ፤]  ለመጠራት እንፈልጋለን ነገር ግን ስምህን[ተፈጥሮህን፤ ባህርይህን፤]  መሆን አንፈልግም !  በስድስቱ የስሜቶቻችን ህዋሳት መመላለስ እንዲሁም የነፍስ ሀሳባችንን (carnal (soulish thoughts) መመገብ እንችል ዘንድ ግን እንወዳለን። በሃይማኖታዊ እምነታችን መቀጠል፤ ትምህርቶቻችንን እና መንገዳችንን ጠብቀን መኖር እንፈልጋለን፡ እንዲሁም በዘየ በራሳችን ጽድቅ ውስጥ ለመኖር እንፈልጋለን። የልባችንን ጣኦቶችና የሥጋችንን ምኞቶች (የራስ ምኞት ፤ የመጀመሪያዋ ባል – አደም) ፍላጎታችንን ለማርካት የእራሳችን ነገር መሄዳችንን እንቀጥላለን። ነገር ግን ጌታ ሆይ፡ ከስምህ ጋር የሚመጡት በረከቶችን ደግሞ እንፈልጋለን። ጌታ ሆይ፡ በሁለት መንገዶች በእርግጥ መኖር እንፈልጋለን! “እያሉት ነው። ይቀጥላል….. 3 ወንድም ቢኒ

ክፍል 3

እምናወራው ያለው ስለ መንፈሳዊ ነገር እደሆነ እንደ ተሰመረበት ይሁንና መንፈሳዊውን ጋብቻ በምሳሌ የሚያስስረዱ ሁለት አይነት የጋብቻ ግንኝነቶች እንዳሉ ሳይወሳ መታለፍ የሌለበት ነው።

በገላቲያ4: 22/31-22 አንዱ ከባሪያይቱ አንዱም ከጨዋይቱ የሆኑ ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደ ነበሩት ተጽፎአልና።

23 ነገር ግን የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዶአል፥ የጨዋይቱ ግን በተስፋው ቃል ተወልዶአል።

24 ይህም ነገር ምሳሌ ነው፤ እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና። ከደብረ ሲና የሆነችው አንዲቱ ለባርነት ልጆችን ትወልዳለች፥ እርስዋም አጋር ናት።

25 ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና።

26 ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት።

27 አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።

28 እኛም፥ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን።

29 ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው።

30 ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት።

31 ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም።”

 

ሐዋሪያው ስለ ሁለት ኪዳኖች በሁለቱ ሚስቶች እንደ ሚመሰሉ ነግሮናል ማለትም አጋርና ሳራ ባሪያይቱና (bondwoman) ነጻ ያልሆነችው ሴትና ጨዋይቱ (freewoman) ነጻይቱ ሴት ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሁለት የተለያዩ የጋብቻ አይነቶች ነበሩ። ሰውየው ባሪያይቱን ካገባ ያላቸው ግንኝነት የጌታና የባሪያ ነው። እዲህ አይነትዋ ሚስትም ያላት መብት ውስን ሲሆን በቤተሰብ ውሳኔ ውስጥ ምንም ድምጽ የላትም። ባልዋ እድሉን ሊያቀርብ ይችላል ነገር ግን እደዛ እዳያደርግ የተወሰነ ነበረ።

ይህ የአጋር አይነት የጋብቻ ግኑነት ነው። እስራኤል ከእ/ር ጋራ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ በጋብቻ በተሳሰሩ ጊዜ ያለውንም ያሳያል። ይሄ የአሮጌው ኪዳን ጋብቻ ነው። በዘፅአት 19/5 እስራኤል ለባልዋ ለመታዘዝ መማል ነበረባት። እስራኤልም የእ/ር አገልጋይ ሚስቱ ሆነች። ይሄ መጥፎ አይደለም በዛው አንጻርም እ/ር ከህዝቡጋር ሙሉ ለሙሉ የሚፈልገው ጋብቻ አይደለም። የተሻለ ህብረትን ይሻልና ለዚህም ነበር በአጀንዳው ውስጥ እስራኤልን ሊፈታት እቅዱን ያስቀመጠው።

“ትንቢተ ኤርምያስ 3፡8 ከዳተኛይቱም እስራኤል ስላመነዘረች ስለዚህ ፈትቻታለሁ የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን እንዳልፈራች እርስዋም ደግሞ ሄዳ እንደ ጋለሞተች አየሁ።

Jer 3፡8 And I saw, when for all the causes whereby backsliding Israel committed adultery I had put her away, and given her a bill of divorce; yet her treacherous sister Judah feared not, but went and played the harlot also.” ከዛም በተሻለ ነገር ላይ የተመሰረተውን አዲሱን ኪዳን አደረገ።

አዲሱ ኪዳን የተመሰለው በነጻይቱ ሴት በሳራ ነው። በአዲሱ ኪዳን የተመሰረተው ጋብቻ መታዘዝ በሚለው ሃሳብ ላይ የተመሰረተ አይዳለም። ሁለት የተጋቡ ወንድና ሴት ከተስማሙ እዲታዘዙ መናገር የሚያስፈልግ አይደለም። አንዳቸው አንዳቸው አንድን ነገር እንዲያርጉ በስልጠን የሚያዙበት ምክንያት የለም ስምምነቱ አለና ። የቤተሰብ ስልጣን የሚገለጠው የስምምነት እጥረት በመካከላቸው ካለ ነው።

በዚህ ምንያት እ/ር ድል ነሺ ካልሆኑበቀር ለማግባት ሃሳቡም የለውም። ድል ነሺነው ከእ/ር ጋር ወይም ከጌታ እየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚስማማው። ድል ነሺ የጌታን አይምሮ ያውቃል አሊያም እንዲያውቀው ይሻል። የእ/ርን ፈቃድ ሲያገኘውም ከፈቃዱ ጋር ተስማምቶ እራሱን ያገኘዋል። አልያም ከፈቃዱ ጋር ፍጹም አንድ እስኪ ሆን መረዳትን ለመቀበል እስከ መጨረሻው ይሻል። በመንፈሳዊ እድገት የመማር ሂደት ወስጥ በእርግጥም ድል ነሺው የእ/ርን ሃሳብ ቶሎ ላያስተውል ይችላል:: እንደ እ/ር አገልጋይ እ/ርን ይታዘዛል። ሙሉ ግንዛቤን ገና ስላላገኘ ፈቃዱን በማድረግ ብቻ ገና አልረካም የእ/ርን አይምሮ እስኪ ያገኘውና ገብቶት በሙሉ ስምምነት እራሱን እስኪ ያገኘው ወደ ፊት ይዘረጋል።

 

ከእ/ር ጋር አለመስማማት ምክንያቱ የመረዳት እጥረት ነው። መላው አለምን እ/ር እንደሚያየው ብናየው እ/ር የሚያደርገውን ሁሉ ለምን እደሚያደረገው ያለመስማማት ባልኖረ ነበር። ችግሩ አለም ሁሉ መለኮት ከሚያየው አካያ አናየውም። ይህ አብ አንድን ሰው ወደ ጌታ እንደ ሳበው በጌታ እንደሆነ የሚገኝ ለውጥ አይደለም። በመንፈስ ሲሞላም በነገር ሁሉ ከእ/ር ፈቃድ ጋር ሙሉ ለሙሉ መስማማቱ ወድያው አይመጣም። ከእ/ር ጋር አብሮ መጔዝን ይጠይቃል አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ የእ/ርን ባህርይ አይበዘብዝም አብሮ ጊዜ ማሳለፍን ይጠይቃል ደቀ መዛሙርቱ ሰዎች ከንግግራቸው የተነሳ ከእየሱስ ጋር እደነበሩ ያወቁት ለሰዎስት አመት ተኩል አብረው በመውጣት በመግባት ባህርዩን በከፊል ስለ ተካፈሉ ነው።

ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal