
ጥያቄና/መልስ በክርስቶስ ኢየሱስ “ውስጥ” ተፈጠረናል ወይ? ወንድም ቢኒ
ክፍል 1 እሺ ተባረክ ብራዘር ሃሳብህ፡ገብቶኞል አማርኛችን ላይ የትርጉም ስተት እንዳለ አትዘንጋ ካልሆነ የከበረውን ነገር አታገኘውም ከአማርኛው ትርጉም በቀር ሁሉም ትርጉሞች በትክክል ተርጉሞውታል። የአማርኛ ትርጉም መልካም ነው ሆኖም በማይጠቅም ትህትናን በሚመስል ከንቱ መንፈስ ስር ብዙ ቃላቶችን ሲተሮጎሙ ወርደው ተተርጉሞዋቸል። ትንሽዋን ቃል ለምሳሌ እንይ፡ “ጠይቅ” ካለ ኢትዮጵያዊ ትህትና ነው ብሎ የሚያስበውን [የልመና መንፈስ የሰለጠነበት አገር ስለሆነ] “ለምን” ብሎ ይተረጉሞዋል። እንደ ዲቃላ፡ ልጅ አባቱን የግዴታ መለመን አለበት እንዴ? ዳዲ: አባ አባ ብሎ መጠየቅ ድፍረት ነውን? ወንድሜ በእ/ር ልጆች መካከል የመረዳት ልዩ ነት አዲስ አይደለም በነ ሃዋርያው ጳውሎስ ዘመንም ነበረ[….. በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ….የሐዋርያት ሥራ 15/2] ዶክትሪንን ከመቃወም መንፈስ ሳይሆን እውነትን ከማወቅና ያወቅነው እውነት ከአእምሮ በላይ ቢሆንም አርነት እደሚሆነን በማወቅ ልናየው ይገባል።
ብራዘር መቆፈር አለብን ብዙ ሰው እየታገለ ያለው ከትርጉም ጋር መሆኑን ረስቶ ጌታ የሰጠው ክብሩ ተበዝብዘዋል። የንስር ተፈጥሮ ያለውን ዶሮ ነህ ብትለው የመብረር ጊዜው ሲመጣ በማንነቱ የስበትን ህግ በመነሳት ህግ ይሽረዋል። አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበለናል እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበልንም። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ማንነት ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ የታወቀ ነው ።አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ[እግዚአብሔር ] እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።
ይህን የክርስቶስ ማንነት Identity የራሳቸው ማንነት Identity አርገው ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን የሰጣቸው፤ እራሱ እ/ር ነው። የልጁን መልክ እንድንመስል አስቀድሞ የወሰነው እራሱ እንጂ እኛ አይደለንም እሱ ወሰነ ማለት ሆነ ማለት ነው ማምለጫ የለም። እንደ አገራችን አባባል ወፍ ተንጫጫ አልተንጫጫ መንጋቱ አይቀርም። የእ/ር ቃል አንድ ይበቃል።
አይንህ የከበረውን እውነት ሁሉ እንድታይ በትርጉም ብቻ አትደገፍ ትርጉሞች በመንፈስ ቅዱስ ተነሳስተው አልተፃፉም ተተርጉሞው ሊሆን ይችላል። ነገሩ ሰው ወደ ቡላድ ድንጋይ እጁን ይዘረጋል፥ ተራራውንም ከመሠረቱ ይገለብጣል።ዓይኑም ዕንቍን ሁሉ ታያለች።
ሰው ወደ ቡላድ ድንጋይ እጁን ይዘረጋል፥ ተራራውንም ከመሠረቱ ይገለብጣል። 10 ከድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያ ይወቅራል፤ ዓይኑም ዕንቍን ሁሉ ታያለች።መጽሐፈ ኢዮብ 28:9-10
ክፍል 2
1ኛ, ሐዋ 10~41 (አመሳክረው)
*በእድሚያ በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን በክርስቶስ ኢየሱስም ላሉት ምእመናን ሁሉ ነው የፃፈው። እነሱም በኤፌሶን ለሚኖሩት አይሁዶችና ግሪኮች[አሕዛብ] ሁሉ ያካትታል። እያለ ያለው ለአብርሃም አስቀድሞ እንደተነገረው በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ያለበትን ምክንያት ማስተዋል አለብን። ይህ ተስፋ ለኛ ብቻ ነበረ ብሎ አልተናገረምና። ጳውሎስ ህግን ጠንቅቆ የተማረ ነበር እንጂ ከእውቀት ነፃ የሆነ ሚስኪን አልነበረም። መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ እንደ ሰበከ ያውቃል ። እንካንስ አህዛብ አይሁድም በክርስቶስ ባለ እምነት ባቻ እንደሚጸድቁ መርዶውን አርድታቸዋል በዚህም ትምክታቸው ፈረሰ።
“በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ” መጀመርያ ማስታወስ ያለብን እነዚህ ሰዎች አስቀድመው በክርስቶስ ተስፋ ያደረጉበት ምክንያቱ በሙሴ የስጋ ዘመን በኦሪት ዘጸአት ላይ መመረጣቸው እንጂ በየትም የእግዚአብኤር ቃል ላይ ለብቻቸው ዓለም ከመፈጠሩ ለብቻቸው አስቀድሞ ተመረጡ የሚል የለም ። “እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው። ኦሪት ዘጸአት 19/6” እያለ ያለው በዚያ ዘመን አህዛብ ሁሉ ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ። ፍጥረት ሁሉ ከእግዚአብሔርም ክብር ከክርስቶስ ተለይቶ ያለ ክርስቶስ ነበረ እስራኤል ብቻ ከአለም ሁሉ ተለይተው ተመርጠው መንግስትነት ተሰጣቸው እነሱ ግን እራስ ወዳዶች ሆነው ቀሩ ፍሬ አላፈሩም ለአንድም የምድር ህዝብ ከክርስቶስ በፊት በረከቱን አካፍለው አያውቁም።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2/11 ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤12 በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ።13 አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።14-15 እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥16 ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።17 መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤18 በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።
የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።የዮሐንስ ወንጌል 1/11 የነሱ ነገር በዛ አበቃ!
Bro. We have to understand the Lord Jesus Christ commissioned His flowers, disciples and apostles to go to the Gentiles. First Peter, and then later Paul. National, racial Israel is a thing of the past as far as God is concerned. The kingdom of God already taken from Israel, and given to a nation bringing forth the fruits thereof, I say unto you, That many already come from the east and west, and already sit down with Abraham, and Isaac, and Jacob, in the kingdom of heaven. But the children of the kingdom of Israel already cast out into outer darkness: there already weeping and gnashing of teeth.They will NOT come back to rule the world under Christ. They are no better (no, they are MUCH WORSE) than even the Gentiles and will be judged just as severely. Forget about “praying for the peace of Jerusalem” as the Christian hucksters charge their followers. THERE WILL BE NO PEACE IN JERUSALEM. Jerusalem is going down.
ክፍል 3
*በዚህ ሃሳብ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ግንኙነት ያስፈልገናል we need Holy Ghost connection ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በክርስቶስ ውስጥ መርጦናልናል ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ ውስጥም አስቀድሞ ፈጥሮናል የሚለውን ማንፀባረቅ ነበረበት። ኢየሱስ በአዲስ ኪዳን ብቻ የመጣ ነው ያልከውን ይህን ስም በብሉይ ቡሃላ እናየዋለን።
1ኛ, *በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን ባቻ ሳይሆን መተርጎም ያለበት በክርስቶስ ኢየሱስ “ውስጥ” ተፈጠርን ነው።[created in(within) Christ Jesus ]
‘ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካም ሥራ እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ “ውስጥ” የተፈጠርን [created in(within) Christ Jesus ]የእግዚአብሔር ፍጥረቱ ነን። ‘ኤፌሶን 2:10
(Eph 2:10 [KJV])For we are his workmanship, created in Christ Jesus unto good works, which God hath before ordained that we should walk in them.
2ኛ, መተርጎም የነበረበት ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በክርስቶስ መርጦናልናል ሳይሆን መተርጎም የነበረበት *ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በክርስቶስ “ውስጥ” [in(within) Christ] መርጦናልና። He chose us “in” Christ before the foundation of the world”
‘በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በክርስቶስ “ውስጥ” [in(within Him) Christ] መርጦናልና። በፍቅር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤ ‘ኤፌሶን 1:4-5
Eph 1:4. even as He chose us out (selects, picks us out), within Him. before [the] casting down (a laying of the foundation; a conception) of [the] ordered system (world), [for] us to continuously be set‑apart (holy) ones and flawless ones (ones without stain; blameless ones) in His sight (presence) [in love; or, putting this phrase at the beginning of vs. 5:]
አባት ምድርን በመሠረተ ጊዜ የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፥ እኛ ወዴት እንደነበርን? እናስታውሳልንን ? ከእግዚአብሔርም ልጆች መካከል አንድስ እንካ የሚያስታውስ የለም። የእግዚአብሔር ክብር ክርስቶስ ጎድሎባቸው ከርመዋል ገና ወደ ክብራቸው ወደ ክርስቶስ በማገገም ላይ ናቸውና።
መጽሐፈ ኢዮብ 38: 4 ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር።5 ብታውቅስ መሠፈሪያዋን የወሰነ፥ በላይዋስ የመለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው? 6-7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፥መሠረቶችዋን በምን ላይ ተተክለው ነበር?የማዕዘንዋንስ ድንጋይ ያቆመ ማን ነው?
ክፍል 4
በተለያዩ ትርጉሞች ለማየት ካስፈለገ ጥቅሶች
‘ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካም ሥራ እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ የተፈጠርን [created in Christ Jesus ]የእግዚአብሔር ፍጥረቱ ነን። ‘ኤፌሶን 2:10
1, ‘በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ ውስጥ [in Christ] መርጦናልና። በፍቅር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤ ‘ኤፌሶን 1:4-5
(Eph 1:4 [AMP])Even as [in His love] He chose us [actually picked us out for Himself as His own] in Christ before the foundation of the world, that we should be holy (consecrated and set apart for Him) and blameless in His sight, even above reproach, before Him in love.
(Eph 1:4 [ESV2011])even as he chose us in him before the foundation of the world, that we should be holy and blameless before him. In love
(Eph 1:4 [HCSB])For He chose us in Him, before the foundation of the world, to be holy and blameless in His sight. In love
2, ‘ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካም ሥራ እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ የተፈጠርን የእግዚአብሔር ፍጥረቱ ነን። ‘ኤፌሶን 2:10
(Eph 2:10 [ESV2011])For we are his workmanship, created in Christ Jesus for good works, which God prepared beforehand, that we should walk in them.
(Eph 2:10 [HCSB])For we are His creation, created in Christ Jesus for good works, which God prepared ahead of time so that we should walk in them.
- for we are (we continually exist being) the result of His work (His creation; the thing He has constructed; what He did; His achievement; His opus; His deed), ones being reduced from a state of disorder and wildness (ones being built, framed, founded, created) “within” Christ Jesus upon good works (deeds) which God made (makes) ready (prepared/prepares) beforehand, to the end that we may walk about (around) within them{JMT] Eph 2:10
(Eph 2:10 [NET])For we are his workmanship, having been created in Christ Jesus for good works that God prepared beforehand so we may do them.
(Eph 2:10 [Webster])For we are his workmanship, created in Christ Jesus to good works, which God hath before ordained that we should walk in them.
(Eph 2:10 [Weymouth])For we are God’s own handiwork, created in Christ Jesus for good works which He has pre-destined us to practise.
(Eph 2:10 [YLT])for of Him we are workmanship, created in Christ Jesus to good works, which God did before prepare, that in them we may walk.
(Eph 2:10 [AMP])For we are God’s [own] handiwork (His workmanship), recreated in Christ Jesus, [born anew] that we may do those good works which God predestined (planned beforehand) for us [taking paths which He prepared ahead of time], that we should walk in them [living the good life which He prearranged and made ready for us to live].
3ኛ, ‘ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በታረደው በግ የሕይወት መጽሐፍ ላይ ስሞቻቸው ያልተጻፈ የምድር ሰዎች ሁሉ ለአውሬው ይሰግዳሉ። ‘ራእይ 13:8
(Rev 13:8 [Weymouth])And all the inhabitants of the earth will be found to be worshipping him: every one whose name is not recorded in the Book of Life—the Book of the Lamb who has been offered in sacrifice ever since the creation of the world.
Rev 13:8. And all those continually dwelling upon the earth (land) will worship it ‑‑ of which ones, the name has not been written within the scroll of “The Life of the little Lamb:” the One having been slaughtered from a casting‑down of [the] ordered arrangement (world) [or: from {the} world’s founding].
ክፍል 5
4ኛ*ኢየሱስ በአዲስ ኪዳን ብቻ የመጣ ነው ያልከውን ይህን ስም በብሉይ እንየው።
ከመጀመርያው የተናገረውና የሙሴን ህግ የሰጠው ማነው? ህግን ለሙሴ የሰጠው እራሱን “ያህዌ (Yahweh)” ብሎ በሚነደው ቁጥቋጦ ጠርተዋል። “ያህዌ” የሚለው የፈጣሪ ስም እ/ር መጀመርያና መጨረሻ የሌለው ዘልአለማዊና እራሱን በራሱ ህላዌ(ህልውና) [self-existent] ያለው መሆኑን የሚያመለክት ነው። ይህ አዲስ ስም ነበር። ለአብርሃም ለይሳቅ ለያቆብ አልተገለጣላቸውም ነበር። “’እግዚአብሔርም (Hebrew፣ ኤሎሂም elohiym el-o-heem) ሙሴን አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) ነኝ። ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም። ‘ ዘፀአት 6:2-3 አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደትረሱ አንዱ እ/ር ኤልሻዳይ፤ያህዌ ብሎ እራሱን ገለጠ ሁለት እግዚአብሔሮች አይደሉም ቡሃላ ነገሩን ስለምናያይዘው ማስተዋሉመልካም ነው።
የህግ ሰጪው ማንነት በዘፀ፤20/2 አስርሩን ትእዛዛት ሲሰጥ በህግ መቅድሙ ላይ ሲናገር ‘“ከግብፅ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ (ያህዌ self-Existent በራሱ የሚኖር ። በራሱ ህልውና ያለው) እኔ ነኝ።” “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። ‘ ዘፀአት 20:2-3”
ለአብርሃም ሲገለጥ እንደ ኤልሻዳይ አወቀው ‘አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ኤልሻዳይ” ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤ ‘ ዘፍጥረት 17:1 ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም የፃፈው ሙሴ ነው። ይህም ማለት እነ አብርሃም ያልበራለቻው ያህዌ የሚለው የእ/ር ስም ከገባው ቡሃላ የፃፈው ስለሆነ ያህዌ እያለ በእብራይስጥ ተጠቅሞበታል ኤልሻዳይ እና ያህዌ አንድ አምላክ እንደሆነ እናያለን ። “እኔ እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) ነኝ። ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም። ‘ ዘፀአት 6:2-3 አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ከዚህ የምንረዳው እ/ር እራሱን በተለያየ ስምና መልክ[ስም በመጽሓፍ ቅዱስ የሚያሳየው የአንድን ነገር ባህርዩን ወይም ተፈጥሮዉን ነው] እራሱን እንዴት እንደሚገልጥ እናስተውላለን። በአዲስ ኪዳን ቃል የነበረው እ/ር ስጋ ሆኖ በክርስቶስ እየሱስ ተገለጠ የእብራይስጥ ስሙ “እያሱ [yashua or Joshua]” ነው። ትርጉሙም “ደህንነት፤አዳኝ [እ/ር ያድናል ]” ማለት ነው። ይከውም በግሪክ ቋንቋ “እየሱስ” ይባላል ትርጉሙም “አዳኝ” ማለት ነው።
ጌታ በሉቃስ ወንጌል 24/27 ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው። እንደ ምናስተውለው ጌታ ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ላይ የተፃፈው ስለሱ መሆኑንና ለመረዳት ግን ጌታ በመንፈሱ ካልተረጎመልና መጻሕፍትን እናስተውል ዘንድ አእምራችን ካልከፈተልን በትዮሎጂ እውቀት ከማበጥ ውጪ እውነትን ለመረዳት ይከብደናል። የሉቃስ ወንጌል 24/45 በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤
ክፍል 6
የዮሐንስ ወንጌል 5/39 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 7/15 አይሁድም፦ ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር።
ጌታ እንዳለው ከሙሴ ዘንድ ስለሱ ተጽፈዋል እስቲ ይህን የሚደንቅ ምጢር እንመልከት። ‘ እግዚአብሔር (ያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱስ በግሪክ] ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ (ኤሎሂም) ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። እግዚአብሔር (ያህዌ) ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው። ‘ ዘፀአት 15:2-3 አስተዋላችሁ ትንቢቱን እግዚአብሔር (ያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱሴም በግሪክ] ሆነልኝ። እንዲገባን በግልጽ አማርኛ እንየው “ያህዌ ደህንነቴ ወይም እየሱሴ ሆነልኝ[“ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ”]” ስለዚህ እየሱስ በእብራይስጥ ቋንቋውስጥ በብሉይ ተደብቆ የነበረ ስም መሆኑን እናያለን።
ይህ የእየሱስ ስጋ የመልበሱ ትንቢት ነው። የአሮጌው ኪዳን እ/ር በአዲስ ኪዳን ሰው ሆኖ ስለመገለጡ ነው። ይህም በኢሳያስ 12/2-3 ‘እነሆ፣ እግዚአብሔር ድነቴ[እየሱሴ] ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም [እየሱሴም]ሆኖአል።” ከድነቴ[እየሱሴ] ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ። ‘ ኢሳይያስ 12:2-3 እንደምናስተውለው ኢሳያስ በሙሴ መጽሐፍ በዘፅአት የተፃፈውን ደግሞ ሲጠቅስ እናስተውላለን። በዚህ አያበቃም እየሱስ ይህን በመጥቀስ አጽንቶታል።
ጌታ እየሱስ ይህን ትንቢት ግልጽ አድርጎ ፈቶታል። ‘የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፤ በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” ‘ ዮሐንስ 7:37-38 በሌላ የእንግሊዝኛ ትርጉም ማንም ከተጠማ ከደህንነት ምንጭ ዉሃ ይጣጣ ይላል።
ይህ ግልጽ ቃል የሚያስረዳን በአሮጌው ኪዳን እየሱስ [በእብራይስጥ እያሱ] ስለ ድነት ወይም ደህንነት ተደብቆ የነበረው ሚስጥር እንደሆነ ነው። ጌታ እየሱስ ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው። “ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ” በቀድሞው ኤልሻዳይ ብሎ እራሱን የጠራው በራእይ[በእየሱስ ክርስቶስ መገለጥ መጽሐፍ] እራሱን በድጋሚ ሲያረጋግጥ ሁሉን ቻይ ብለዋል። ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን አስር ቦታ ላይ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ተብሎ ተጠርተዋል። ልናየው ያልቻልነው ተርጋሚዎቹ ኤልሻዳይ እንደማለት ፈንታ በአማርኛችን ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ በእንግሊዝኛ Almighty ብለው ስለተረጎሙት ነው ። የፃድቅ ሃብቱ ትጋቱ ነውና ማጥናት ትችላላችሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:18 , የዮሐንስ ራእይ 1:8, 4:8, 11:17, 15:3, 16:7, 16:14, 19:6, 19:15, 21:22
ክፍል 7
በአሮጌው ኪዳን ለአብ የተነገሩት በአዲስ ኪዳን ለጌታ እየሱስ ክርስቶስ ስለመነገራቸው የሚያሳዩ ጥቂቶችን ለመጥቀስ ያህል
የዮሐንስ ራእይ 1/8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ(በእብራይስጥ ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee በግሪክ pantokrator pan-tok-rat’-ore፤ the all-ruling, i.e. God (as absolute and universal sovereign):–Almighty, Omnipotent.)፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።
Rev 1/8 I am Alpha and Omega, the beginning and the ending, saith the Lord, which is, and which was, and which is to come, the Almighty. (በእብራይስጥ ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee በግሪክ pantokrator pan-tok-rat’-ore፤ the all-ruling, i.e. God (as absolute and universal sovereign):–Almighty, Omnipotent.)
የዮሐንስ ራእይ 4/8 አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።
Rev 4/8 And the four beasts had each of them six wings about him; and they were full of eyes within: and they rest not day and night, saying, Holy, holy, holy, Lord God Almighty, which was, and is, and is to come.
ጌታ ሙሴ የፃፈው ስለኔ ነው ሙሴን የማያምን መጻሕፍትን አያምንም ጌታንም አያምንም ሙሴ የፃፈው ሁሉስለ ጌታ እየሱስ ትንቢታዊና ገላጭ ቃል ነበረ። “የዮሐንስ ወንጌል 5/46 ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና።47 መጻሕፍትን ካላመናችሁ ግን ቃሌን እንዴት ታምናላችሁ?” ህግ እራሱየሚገልጸወ የህግ ሰጪው አቃምን ነው። አይሁድ ስለ ጌጽእየሱስ ሲያስቡ 33 ½ ዓመት በምድር ላይ ስጋ ለብሶ የተመላለስበትን ብቻ ስለሚያስተውሉ የምሎ ኮታዊምንጭ ማንነት አልተዋጠላቸውም። ለዚህ ነበር ከአብርሃም በፊት ነኝ ሲል ጉድ ጉድ ከአብርሃም በፊት እኔ ነኝ 50 ዓመት እንካ ሳይሞ ላው ምን እያለ ነው እያሉይ መፃደቁ ነበር። የኅይል ሁሉ ራስ እራሱን አርግቶ በፈጠረው በሰው ቅርጽ ወይም መልክ በመሃላቸው ሲከሰት እንዴት ተፈጥራዊው አእምሮ ሊገባው ይችላል?
የዮሐንስ ራእይ 11/17 እንዲህ አሉ፦ ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤
Rev 11/17 Saying, We give thee thanks, O Lord God Almighty, which art, and wast, and art to come; because thou hast taken to thee thy great power, and hast reigned.
የሚገርመው አብርሃም የእምነት ሰው ስለነበር ቀኑን በእምነት አሻግሮ አይቶ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። የዮሐንስ ወንጌል 8/56 አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። እነሱ ደግሞ በምድረበዳ ለነበረችው ቤተ ክርስቲያን አለት ሆኖ ዉሃ ያጠጣቸውን ክርስቶስን ሊያስታውሱት አልቻሉም። ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዐለት አንተ ማነህ ይሉታል? ‘ሁሉም ከአንድ መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዐለት ጠጥተዋልና፤ ያ ዐለት ክርስቶስ ነበረ። ‘ 1 ቆሮንቶስ 10:4
ከላይ ያነሳሁት ሃሳብ አማርኛችን በስተት ማህበሩ ብሎ ተርጉሞታል መተርጎም የነበረበት [የምድረ በዳ ቤተ ክርስቲያን the church in the wilderness] ነበር። ሐዋርያት ሥራ 7/38 ይህ ሰው በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ በማኅበሩ ውስጥ የነበረው ነው፤ ይሰጠንም ዘንድ ሕይወት ያላቸውን ቃላት ተቀበለ፤
Acts 7/38 This is he, that was in the church in the wilderness with the angel which spake to him in the mount Sina, and with our fathers: who received the lively oracles to give unto us:
ክፍል 8 የመጨረሻ
Have to we have to understand our salvation, it is not of works that we return lest we should boast, but grace, “For by (to; in) the Grace you are (you continuously exist being) ones having been delivered (saved; made whole) through [some MSS +: the] Faith, and this not forth from out of you folks, [it is] God’s gift (present associated with sacrifice or offering),”(Ephesians 2:8). Therefore, beloved of brotherns, we do not of our own accord decide that it is time to reconnect to our destiny, that is, unless we are moved by His Spirit and predestined circumstances of life. Neither do we chose to predestine ourselves to the glory of sonship its by him we predestinated to be conformed to the image of his Son; but I can tell you with assurance that when we hear the voice of the Son of God—we will live and be on our way to that end! Although we might be troubled on every side, yet not distressed; we are perplexed, but not in despair; despondent, forlorn, tormented in the lowest reaches of hell, please know that ALL IS WELL! For “God, our Father, even as He chose us out (selects, picks us out), within Him. before [the] casting down (a laying of the foundation; a conception) of [the] ordered system (world), [for] us to continuously be set‑apart (holy) ones and flawless ones (ones without stain; blameless ones) in His sight (presence) [in love; or, putting this phrase at the beginning of vs. 5:]: Having (G3724 horizÇ From G3725; to mark out or bound (“horizon”), that is…to appoint, decree, specify) predestinated us unto the adoption of children (Grk. uihothesia, the placing of sons) by Jesus Christ to Himself, according to the good pleasure of His will.” (Ephesians 1:4-5).