
ጥያቄና/መልስ : ጌታን ሳይቀበሉ በድንገት የሚሞቱትስ እነሱም ይድናሉ?
ክፍል አንድ
ግን አንድ ጥያቄ አለኝ።1,ጌታን ሳይቀበሉ በድንገት የሚሞቱትስ እነሱም ይድናሉ?2,ሁሉም ድነትን ተቀብሎ ከሆነ ምስክር መሆንና ወንጌልን መስበክ ለምን አስፈለገ?
አዎን እህታችን, እኛ የዳነው “በእምነታችን በኩል በጸጋ ነው” (ኤፌ 2 8), ነገር ግን ከእግዚአብሄር እስካልተሰጠን ድረስ እምነት የእኛ አይደለም. ሮሜ. 12: 4, “እግዚአብሔር ለእያንዳንዱም የእምነትን መጠና አካፈለው ለገሰው” እግዚአብሔር ለእኛ እምነት ከሰጠን በኋላ የእኛ ይሆናል! በጣም ቆንጆና ቀላል ሆኖ ልንረዳው ከምንችለው በላይ ባለመፃፉ ደስ ይላል።
‘ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ መጀመሪያ በኵራት የሆነው ክርስቶስ፣ ከዚያም በኋላ እርሱ ሲመጣ የክርስቶስ የሆኑት። ‘ 1 ቆሮንቶስ 15:22-23
አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስ ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል አለው። ‘እኔ ግን ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ[ እጎትታለሁ: በጡንቻ በሃይል to drag , muscular ።” ዮሐንስ12:32
2ኛ ጥያቄ/ሁሉም ድነትን ተቀብሎ ከሆነ ምስክር መሆንና ወንጌልን መስበክ ለምን አስፈለገ? እ/ር ሁሉን የሚያድን ከሆነና ሲኦልም ሞትም በእሳት ባህር የሚደመስሰው ከሆነ ለምን እናመልከዋለን እንደልባችን አንሆንም? የሚሉም አሉ። ይህ የሚያሳየው እ/ርን የሚከተሉት ፍርድና ሲኦልን ፈርተው እንጂ ለእ/ር ፍቅር ስላላቸው እንዳልሆነ ከልባቸው የተገለጠው ሰልፍ ያሳያል።
እያንዳንዱ በራሱ ተራ ስለሚድን ማለትም ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ተራውን ስለማናውቅ ወንጌልን እንሰብካለን።ለሁሉም ሰዎች የእግዚአብሔር ፍቅር ይሰበካል ይታወጃል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፤ የእውነትን ቃል በቅንነት ማስተዋልና መለየት፤ እውነትን በፍቅር ማስተማር፤ በክርስቶስ ተቀባይነትን፤ እና ይቅርታን ለማድረስ እንጥራለን!
የእግዚአብሄር ትግስት ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ እንደሆነ እናውቃለንና። ‘አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንተ ይታገሣል።’2 ጴጥሮስ 3:9
ባለፈው እንዳነሳነው እግዚአብሔር አሁን ሁሉን በአንዴ ማዳን አቅቶት ሳይሆን አሁን እየሰራ ያለው እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ በመውሰድ ላይ ነው። በእቅዱ ሙልአት ጊዜ ግን ሁሉ በአዳም እንደሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉ። ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል። እንደምናውቀው በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ የእቅዱን፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤በዘመን ፍጻሜ ሊያደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።
እግዚአብሔር በአለማመን የዘጋውን ማን ሊከፍተው ይችላል? እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና። [ሰው ሳይሆን ] እራሱ ሉኡል እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ አቅዶ ሁሉን በአለመታዘዝ ከዘጋው የዘጋውን ከመክፈት ማን ያስቆመዋል? እግዚአብሔር ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሊሰጣቸው ይችላልና።የሐዋርያት ሥራ 11/18 ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና፦ እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ። ብዙ ጥቅሶች ቢኖሩም ጥቂቶችን ለመጥቀስ ያህል።
* እግዚአብሔር የሰዎች ሁሉ አዳኝ ነው። 1 ጢሞቴዎስ 4:10
* ጌታ ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደ የእግዚአብሔር በግ ነው.(ዮሐንስ 1:29)
‘እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ለነገሥታትና ለባለ ሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ ይህም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው። ይህ በእግዚአብሔር በአዳኛችን ፊት ደስ የሚያሰኝ ነው፤ እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል[ willing (continuously intending) ]። ‘1 ጢሞቴዎስ 2:1-4
1 Tim 2:3. This [is] beautiful (fine; ideal) and welcomingly received from the presence and in the sight of God, our Deliverer (our Savior; the One Who heals us and makes us whole),
4. Who is constantly willing (continuously intending) all mankind (all men) to be saved (delivered; rescued; made healthy and whole), and (even) to come into a full, accurate, experiential and intimate knowledge of Truth (or: into a realization of [the] Truth),
‘በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደሆኑ፣ በአንዱ ሰው መታዘዝ ደግሞ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። ከእንግዲህ በአንድ ሰው መተላለፍ የተነሣ ኵነኔ በሁሉ ሰው ላይ እንደ መጣ፣ እንዲሁም በአንዱ የጽድቅ ሥራ ለሰው ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ ጽድቅ ተገኘ። ‘
ሮሜ 5:18-19
ክፍል ሁለት
1ኛ ጥያቄ/ለመጀመርያው ጥያቄሽ፡ ጌታን ሳይቀበሉ በድንገት የሚሞቱትስ እነሱም ይድናሉ? እንግዲህ እስካሁን ወንጌልን ከሰማው ያልሰማው ይበዛል 162 ቢልዮን ሰዎች እስካሁን እንደተፈጠሩ ይገመታል ከነዛ ውስጥ ወደ 4 ቢልዮን ሰዎች ክርስቲያን ናቸው ተብለዋል የቀሩት 158 ቢልዮን ህዝቦች ጌታን ሳያውቁ አልፈዋል። በውኑ እ/ር ፍቅር ከሆነ ፍቅር 158 ቢልዮን ህዝቦች ጌታን ሳያውቁ ስለቀሩ ለዘልአለም ያሰቃያቸዋልን? ይህ ከሱ ይራቅ የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን? የእ/ር ፍርድ ለማረም ነው ወይስ ለዘልአለም በእሳት ለማሳቃየት?
እንግዲህ ወንጌሉ ከሞት ቡሃላ ለማዳን ሃይል አለው ወይ? ነው ጥያቄው ለዚህ ጥሩ መልስና ምሳሌ የሚሆነን በኖህ ዘመን የነበሩት የማይታዘዙት እ/ር 120 አመት የታገሳቸው እና
የፈረደባቸው ፍጻሚያቸውን በቃሉ አይተን እንለፍ ። ጌታ እየሱስ ከሞቱና ከትንሳኤው ቡሃላ በኖህ ዘመን አልታዘዝ ያሉት አመጸኞች በእስራት ለነበሩትን ነፍሳትን (spirits መናፍስትን) ሰበከላቸው። ለነሱም የማስታረቁን ቃል ይዞላቸው ወረደ። የሚያሳየንም ክርስቶስ ለሃጢያታቸው መሞቱን ብቻ ሳይሆን መነሳቱም ለመጽደቃቸው መሆኑን ነው።
ይህንን ቃል Weymouth’s translation. ከተባለውን ትርጉም እናስተውል 1Pe
3:18 Christ also once for all died for sins, the
innocent One for the guilty many, in order to bring us to God. He was put to
death in the flesh, but made alive in the spirit, in which He also went and proclaimed His Message to
the spirits that were in prison, 1Pe 3:20 who in ancient times had been disobedient, while God’s longsuffering
was patiently waiting in the days of Noah during the building of the Ark, in
which a few persons–eight in number–were brought safely through the water.”
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3 ፡18 ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን
እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥ 19 በእርሱም ደግሞ
ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤ 20 ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት
በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።
አንድአንዶች ይህንን ቃል ጠምዝዘው ሄዶ የሰበከው ከሱበፊት ለሞቱ ጻድቃን ሰዎች ለማውጣት
ነው ይላሉ። ከቃሉ እዳየነው ግን የሰበከው በእስራት የነበሩትን መናፍስት ነው:: ለሴም ፤ለሄኖክ፤ ለኖህ፤ ለአብርሃም፤ ለያቆብ
፤ለኢሳቅ ወይም ለሙሴ፤ ለእያሱ ወይ ለኤልያስ ወይም ለየትኛውም በቀድሞ ኪዳን አካየዳቸውን ከእ/ር ጋር ያደረጉ ጻድቃን ለማናቸውም አይመለከትም::
እነዚህ ሁሉ ለእ/ር ህያዋን ናቸውና በመንፈሳዊው አለም አለም ሳይፈጠር በፊት የታረደው በግ ታርዶላቸዋልና ከአፈር የተሰራው
ስጋቸው ወደ እፈር ሲመለስ ከእ/ር ያመጣው መንፈሳቸው ወደ እ/ር ተመልሰዋልና ።
የሉቃስ ወንጌል 20፡38 ሁሉ ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም ይለናል። ትንሳኤው በዚህ ምድር ከክርስቶስ ጋር አብረው ይገዙ ዘንድ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰው የሚለብሰው እንጂ እነሱ በመንፈሳዊው አለም ጊዜ ሰለሌ የጊዜ ሃይል ሳይዛቸው ተመልሰውከብረዋል። ለምሳሌ ያህል የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም። ብሎ ጌታ እንደ ተናገረ ሙሴና ኤልያስ ህግንና ነብያትን የሚወክሉት እንዳለ ሆኖ ሙሴ ሞትን አይተው የከበሩትን ኤልያስ ሞትን ሳያዩ የከበሩትን ይወክላሉና ። ከስርየቱ በፊትም ህያዋን ሆነው እናስተውላለን በጉ የታረደውአለም ሳይፈጠር በፊት ነውና። “የዮሐንስ ራእይ 13፡8 ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ…” በዚህም የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን እንዳይደለ እንገነዘባለን።
በጌታ ኢየሱስም የመስቀሉን መከራ ከተቀበለልን ቡሃላ ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን እንደሰጠ።
ሞተው ከነበሩት ከቅዱሳን ብዙ ስጋዎች ተነሱ የሚለው በስብሶ የነበረው ስጋቸው ከትንሳኤው ሃይል አቋድስዋቸው ለምስክርነት ይሆኑ
ዘንድ ስጋቸውን ለብሰው መነሳታቸውን የሚያሳይ ነው እንጂ መንፈሳቸው እማ እስቀድሞ ወደ መጠባት ወደ እ/ር ተመልሶ እንደነበር ግልጽ ነው።
“KJV፣ Eccl 12፡7 Then shall the dust return to the earth as it
was: and the spirit shall return unto God who gave it. መጽሐፈ መክብብ 12፡7 አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም (spirit መንፈስህ) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።” ሰለዚህ የነዚህ ሰዎች ትንሳኤ በስብሶ የነበረው ስጋቸው የማይበሰብሰው ከእ/ር ወጥቶ ወደ እ/ር
የተመለሰው መንፈሳቸውን በትንሳኤው ሃይል እ/ር በማዋሃድ ያስነሳቸው ናቸው። የማይበሰብሰውን ለብሰው ወደ ቅዲስትቱ ከተማ ወደ ሰማያዊትዋ እየሩሳሌም መግባት ቻሉ ከዛም በምድርም ለብዝዎች ተገልጠው መታየት ቻሉ። በራእይ ሂዱና አስተውሉ በፍልስጤም ምድር ያለችው ምድራዊትዋን እየሩሳሎም ምንም ቅዲስትቱ ከተማ የሚያስብላት እንደሌለ
ታያላችሁ ሰማያቱን እየሩሳሌምን ቅድስቲቱም ከተማ ብሎ ሲጠራት እናያለን “የዮሐንስ ራእይ 21፡2 ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥” እንደዚሁ በ(የዮሐንስ ራእይ 21፡10)
ጌታ የተሰቀለባት እና ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደሉት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ ያለባትና የሚደርስባት ምድራዊትዋ እየሩሳሌም እንካንስ ቅድስቲቱም ከተማ ብሎ ሊተራት ቀርቶ በታሪክ ገናና እንደመሆንዋ መጠን ታላቂቱ ከማለት በቀር በስማ ብቻ እንካ አይጠራትም “የዮሐንስ ራእይ 11፡8 በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።”
የሙሴና የኤልያስን ህያውነት እናስተውል
የማቴዎስ ወንጌል 17፡1 ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። 2 በፊታቸውም
ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። 3 እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። 4 ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። 5 እርሱም ገና ሲናገር፥
እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
“መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 2፡11 ሲሄዱም። እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።” እንግዲህ አፈርየሆነው ስጋቸው ወደ ነበረበት ምድር ሲመለስ፥ (spirit መንፈሳቸው) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ተመልስዋልና በመንፈስ ህያዋን ናቸው በዚህም ለጌታ ሁሉ ለእርሱ
ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን እንዳይደለ እወቁያለውን እንገነዘባለን።
ነገር ግን በ “19 በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት(spirit መንፈሳቸው) ሰበከላቸው፤ 20 ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥
የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።” እነዚህ ለየት የሚያደርጋቸው ( spirit መንፈሳቸው) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር እንደ መመለስ ፈንታ እ/ር አሰራቸው። ጌታም ሄዶ በኖህ ዘመን የእግዚአብሔር ትዕግሥት 120 ያስጨረሱትን በኖኅ ዘመን አልታዘዙም ለሚላቸው ወንጌልን ሰበከላቸው። ለምን ወንጌሉን መስበክ አስፈለገው?
እዛው ወረድ ብሎ በ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡6 መልሱን ይነግረናል።
በነገራችን ላይ መጽሐፍ ቅዱስ በብራና መልክ የተዘጋጀ ወጥ ፅሑፍ ነበረ። ለአንባቢያን እንዲመች በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው በ1560 ጄኔቫ መጽሃፍ
ቅዱስ በመባል የሚታወቀው አንድ የሊቃውንት ቡድን በጄነቭ ሆነው ሰሩ። ሁለተኛው እትሙም በ1652 ታተመ ይህ ነበር የመጀመርያው
የእንግሊዝኛ ትርጉም በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡6 ስናስብ የተያያዘ ጽሁፍ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ቃሉም “እንደ ሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና።” “1Pet 4፡6 for this cause was the gospel preached also to them that are dead, that they might be judged according to men in the flesh, but live according to God in the spirit.”
የሃዋሪያው መልእክት ግልጽ ነው። ስጋቸው በተመለከተ ሙታን ናቸው። ህያዋን ሆነው ያሉት በመንፈስ እንደሆነና ታስረውም እንዳሉ ወንጌሉ ተሰበከላቸው። መገንዘብ ያለብን በሲኦል የዘላለም ስቃይ ይጠብቅሃል ተብለው አይደለም የተሰበከላቸው። ነገር ግን ወንጌል የምስራች መልካም ዜና የእ/ር ኁይል ለማዳን ነው የተሰበከላቸው።በስጋቸው ሳሉ ሃጢያታቸው የከፋ ስለ ነበር እ/ር ጎርፍ ልኮ በውሃ በማስጠም በጎርፉጠራርጎ ወደ ሲኦል ወሰዳቸው በዚያም ለዘላለም ሳይሆን ያሰራቸው ለሁለት ሺ ሶስት መቶ ሃምሳ ዘመናት ታሰሩ። “እንደ ሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው የሚለን ያንን ነው ። በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ በሲኦልም ላይ ስልጣን ያለው ጌታ ሄዶ ወንጌልን ሊሰብክ ሄደ እንጂለቫኬሽን አልሄደም ወንጌሉም የእ/ር ታላቅ ስራ ፍርዱ የዘላለም ሳይሆ በዘመናት ወስጥ የተወሰነ እንደሆነ እናስተውላለን ። በዚህም በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ሆኑ። ማንም ሲናገር እንደእ/ር ቃል ይናገር። አሜን!
እንደኖህ ዘመን በመምጣቱም የሚፈረድባቸው በአላማ ለማረም ጽድቅን ለማስተማር ነው። ይህን ሊፈጸም ያለ ትንቢት አስተውሉ!
ኢሳ 29/9 ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩት ጽድቅን ይማራሉና:> በእለም ያሉ ሁሉ ጽድቅ ተምረው ታይቶ ይታወቃልን
ስለዚህ ይህ ገና የሚፈጸም ትንቢት ነው።> when thy judgments are in the earth , the inhabitants of the WORLD will learn righteousness .[uprightness & right standing with GOD.] Isaiah 26/9 አስተዋላቹሁን ፍርዱ በአለም ሲገለጥ ምንን ይማራሉ ይላል? ጽድቅን! ሃሌሉያ!
Ps 130፡4
But there is forgiveness with thee, that thou mayest be feared ትፈራ ዘንድ በአንተ ዘንድ
ይቅርታ አለ። አሜን።