IF THERE IS LACK OF A PROPER TEACHING, THE LAND EXPERIENCE DANGER FROM GOD


IF THERE IS LACK OF A PROPER TEACHING, THE LAND EXPERIENCE DANGER FROM GOD AND THE BENEFITS OF THE LAND IS DEPEND ON THE WORD OF GOD…. Brother Binyam T. Alemayehu 02/16/2018
“መጽሐፈ ምሳሌ 14/34 ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ ኃጢአት ግን ሕዝብን ታስነውራለች።”
“እስራኤል ያለ እውነተኛ አምላክ፣ ያለ አስተማሪ ካህንና ያለ ሕግ ብዙ ዘመን አሳልፈዋል። በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው። በዚያን ዘመን በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታላቅ ሁከት ስለ ነበር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት አስተማማኝ አልነበረም። እግዚአብሔር በተለያየ መከራ ያስጨንቃቸው ስለ ነበር፣ አንዱ መንግሥት በሌላው መንግሥት፣ አንዱም ከተማ በሌላው ከተማ ይደመሰስ ነበር። ‘2 ዜና መዋዕል 15:3-6” In 2Chron 15: 3 we read: “Now for a long season Israel hath been without the true God, and without a teaching priest, and without Law”.

ይህ ማለት በምድሪቱ ላይ የእ/ርን ቃል በትክክል የሚያስተምሩ ካህናት ባለመኖራቸው ምክንያት ስርአት የሌለው ህዝብና መሪዎች ለመፈጠር ምክንያት ይሆናል። ሰው ሁሉ ያሻውን ያደርጋል እግዚያብሔራዊ ያልሆነ አካኤድም ተጠናወቶቸዋል። ደግሞም አብዛኛው ከእ/ር ቃል አእምሮው ጎድሎ እ/ር አጥብቆ ነፍሱ የሚፀየፈውን በወንድማማቾች ወይም በወገኖች መካከል ጠብን ሲዘራም ፈጽሞ አያስተውለውም። ይህንንም ያለገደብ ያደርገዋል። በእስራኤል እደታየው በህዝቡ ላይ በቂ የእ/ር ቃል ካለመንሸራሸሩ የተነሳ ከግለሰብ እስከ መንግስት የባህርይ መዛባት ውስጥ ገብተው ሁሉ ለልቡ ጣኦት ሲወግን ይታያል።

በአንድ ህዝብ ውስጥ የእ/ርን ቃል በትክክል የሚያስተምሩ ካህናት ሳይኖሩ ሲቀሩ ህዝቦች እውቀት አጥተው ይሰናፋሉ። ወገንተኝነት ዘረኝነት ሙስና በስልጣን መባለግም ወዘተ… ይበዛል በእስራኤል የተከሰተው ይከው ነው አንዱ መንግሥት በሌላው መንግሥት፣ አንዱም ከተማ በሌላው ከተማ ሳይቀር እየተነሳ ይደመሰስ ነበር እ/ርን መፍራት ከዓይናቸው ፊት ተሰውሮ ነበር። ይህንን ለማረም እ/ር መፍረድ ሲጀምር ህዝብን ሲያስጨንቅ እናስተውላለን። የሚገርመው ግን ብዙ ሰባክያን እንደሚነግሩን ይህ የሰይጣን ስራ ሳይሆን “እግዚአብሔር እራሱ በተለያየ መከራ ከታናሹ እስከ ታላቁ ድረስ ያስጨንቃቸው ስለ ነበር ወደ እ/ር ለመመለስ ሲገደዱ ይስተዋላል፣”’2 ዜና መዋዕል 15:3-6

ከካህናት እውነተኛ የእ/ር ቃል ካለመምጣቱ የተናሳ እስራኤል ያለ እውነተኛ አምላክ፣ ያለ አስተማሪ ካህንና ያለ ሕግ ብዙ ዘመን አሳልፈዋል ይለናል ነገር ግን በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው። ምድራቸውንም ፈወሰ።

የእ/ር ቃል ከማያውቅ ሰው ላይ የእነዚህ አፀያፊ ባህርያቶች ተጠቂም ይሆናል “መጽሐፈ ምሳሌ 6/16 እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤ 17 ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥ 18 ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥ 19 በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፥ በወንድማማች[በወገኖች፤ በጎሳ፤በነገዶች] መካከልም ጠብን የሚዘራ።”

ህዝብ እ/ር ከሚጠላቸው ባህርያት የሚታረመው ካህናት የእ/ርን ቃል እውቀት በምድሪቱ ላይ ሲያውጁ ነው። የቆሸሸ ህሊና የሚፀዳው በመለኮት ውሃ በእ/ር ቃል ሲረጭና ሲታጠብ ነው። “ካህኑ የሁሉ ገዥ፣ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ስለ ሆነ ከንፈሮቹ ዕውቀትን ሊጠብቁ፣ ሰዎችም ከአንደበቱ ትምህርትን ሊፈልጉ ይገባል፤ ‘ ሚልክያስ 2:7
መቸም እ/ር “ትንቢተ ሆሴዕ 4/6 ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤…።” ሲል ይህ ዉጤት የተከሰተው የእ/ርን ቃል የሚያቀብሉ ቃል አቀባዮቹ ልጆቹ [ካህናት] የልቡን ትርታ እያደመጡ በትክክል የሚያስተምሩ ካህናት በምድሪቱ ባለመኖራቸው ምክንያት ነው።
ለዚህም ነው ይህን የምድሪቱመሰረታዊ የጥፋት ምንጭ ለመድፈን ማስተማር ወሳኝ እንደሆነ ስለገባው በመጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 17 ለትምህርታችን ሲነግረን በአሳም ፋንታ ልጁ ኢዮሳፍጥ ነገሠ፥ ያደረገው አንድ ነገር ነበር በእስራኤልም ላይ ጠነከረባቸው ካህናቱን የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ ያስተምሩ ነበር፤ ወደ ይሁዳም ከተሞች ሁሉ ሄደው ሕዝቡን ያስተምሩ ነበር። በይሁዳም ዙሪያ በነበሩ መንግሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ድንጋጤ የሰው አካሄድ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘው እንደ ሆነ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋልና።

[መጽሐፈ ምሳሌ 16/7] ህዝቡን በማስተማሩ አባት ደስ ሲሰኝ ጭንቀት ከምድራቸው ላይ ሲገፍላቸው ይታያል።
“መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 17/1 በእርሱም ፋንታ ልጁ ኢዮሳፍጥ ነገሠ፥ በእስራኤልም ላይ ጠነከረ። 2 በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወታደሮችን አኖረ፥ በይሁዳም አገር አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች ዘበኞችን አስቀመጠ። 3 እግዚአብሔርም ከኢዮሳፍጥ ጋር ነበረ፥ በፊተኛይቱ በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄዶአልና፥ በኣሊምንም አልፈለገምና፤ 4 ነገር ግን የአባቱን አምላክ ፈለገ፥ በትእዛዙም ሄደ፥ የእስራኤልንም ሥራ አልሠራም። 5 እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸና፤ ይሁዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢዮሳፍጥ አመጣ፤ እጅግም ብዙ ብልጥግናና ክብር ሆነለት።6 ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ ከፍ ከፍ አለ፤ የኮረብታውን መስገጃዎችና የማምለኪያ ዐፀዱንም ከይሁዳ አስወገደ።

7 በነገሠም በሦስተኛው ዓመት በይሁዳ ከተሞች ያስተምሩ ዘንድ መሳፍንቱን፥ ቤንኃይልን፥ አብድያስን፥ ዘካርያስን፥ ናትናኤልን፥ ሚክያስን፥ ሰደደ።8 ከእነርሱም ጋር ሌዋውያንን ሸማያን፥ ነታንያን፥ ዝባድያን፥ አሣሄልን፥ ሰሚራሞትን፥ ዮናትንን፥ አዶንያስን፥ ጦብያን፥ ጦባዶንያን ሰደደ፤ ከእነርሱም ጋር ካህናቱን ኤሊሳማንና ኢዮራምን ሰደደ።9 እነርሱም የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ ያስተምሩ ነበር፤ ወደ ይሁዳም ከተሞች ሁሉ ሄደው ሕዝቡን ያስተምሩ ነበር።10 በይሁዳም ዙሪያ በነበሩ መንግሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ድንጋጤ ሆነ፥ ከኢዮሳፍጥም ጋር አልተዋጉም።”
ከአባት የእ/ር ቃል የሚመጣለት ዛሬ ነቢይ የሚባለው ቀድሞ ባለ ራእይ ይባል ነበር ራእይ ማለት የእ/ር ቃል መገለጥ ነው። ራእይ ማለትም የእ/ር ቃል መገለጥ የሌለው ህዝብ አደጋ ላይ ነው።
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 9/9 ዛሬ ነቢይ የሚባለው ቀድሞ ባለ ራእይ ይባል ነበርና አስቀድሞ በእስራኤል ዘንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፦ ኑ፥ ወደ ባለ ራእይ እንሂድ ይል ነበር።
መጽሐፈ ምሳሌ 29/18 ራእይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተመሰገነ ነው። መኪና ተገለበጠ ሲባል ሰምተን እናውቅ ይሆናል መኪና ብቻ ሳይሆን የሚገለበጠው ራእይ ወይም የእ/ር ቃል የሌለው ሕዝብ ሊገለበጥ ይችላል፤ የእ/ርን ቃል የሚጠብቅ ግን የተባረከ ህዝብ ይሆናል።

Prov 29/18 Where there is no vision, the people perish: but he that keepeth the law, happy is he.
(Prov 29:18 [ESV2011])Where there is no prophetic vision the people cast off restraint, but blessed is he who keeps the law.

(Prov 29:18 [AMP])Where there is no vision [no redemptive revelation of God], the people perish; but he who keeps the law [of God, which includes that of man]—blessed (happy, fortunate, and enviable) is he.

(Prov 29:18 [HCSB])Without revelation people run wild, but one who listens to instruction will be happy.
(Prov 29:18 [KJV])Where there is no vision, the people perish: but he that keepeth the law, happy is he.
(Prov 29:18 [YLT])Without a Vision is a people made naked, And whoso is keeping the law, O his happiness!

እ/ር ሲደሰት የመሪዎችን ልብ ያቀናል። ህዝብንም ይባርካል ለዚህ ሁሉ በረከት ህዝም እንዲበቃ የእ/ር ልጆች ቃሉን ለማስተማር የምንተጋበትን መንፈስ እ/ር እንዲያበዛልን ፀሎቴ ነው። “መጽሐፈ ምሳሌ 21/1 የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።Prov 21/1 The king’s heart is in the hand of the Lord, as the rivers of water: he turneth it whithersoever he will.”

“መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 23/2 የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ ቃሉም በአንደበቴ ላይ ነበረ።3 የእስራኤል አምላክ ተናገረኝ፤ የእስራኤል ጠባቂ እንዲህ አለ፦ በሰው ላይ በጽድቅ የሚሠለጥን፥ በእግዚአብሔርም ፍርሃት የሚነግሥ፥4 እርሱ እንደ ማለዳ ብርሃን እንደ ፀሐይ አወጣጥ፥ በጥዋትም ያለ ደመና እንደሚደምቅ፥ ከዝናብ በኋላ ከምድር እንደሚበቅል ልምላሜ ይሆናል።”

“ትንቢተ ዳንኤል 11/32 ቃል ኪዳኑን የሚበድሉትንም በማታለል ያስታል፤ ነገር ግን አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝብ ይበረታሉ፥ ያደርጋሉም። Dan 11/32 And such as do wickedly against the covenant shall he corrupt by flatteries: but the people that do know their God shall be strong, and do exploits.”
“መጽሐፈ ምሳሌ 14/34 ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ ኃጢአት ግን ሕዝብን ታስነውራለች።” ወንድም ቢኒ

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal