ጥያቄና/ መልስ። መማር ይጠቅማል ወይስ አይጠቅም?


ጥያቄና/ መልስ። መማር ይጠቅማል ወይስ አይጠቅም?
መጀመርያ በእውነት የታጠቀ ፍፁም ትምርት ቤት ካለ ነው። አንድ የድሮ ቀልድ የሚመስል አስተማሪ ታሪክ ትዝ አለኝ አንድ ወንድም በክርስቶስ በስየ ጨርሽሻለሁ ብሎ ገወገኖች ህብረት ጠፋ። የጠፋበትም ምክንያት እውቀት ፍቅር ካልቀደመው ያስታብያልና የሚሰማት ትምህርት ሁሉ ሳያጣራ ያገኘውን እውቀት ስላግበሰበሰ ተወጣጥሮ ነበር። እውቀት ሁሉ እውነትና ብርሃን አይደለምና።

ከዛም አንድ በፀጋ የሸመገሉ ወንድም ነበሩና ወደ ወገኖች ህብረት ቢመለስ ለሌሎችም እንደሚጠቅም ለራሱም እንደሚጠቅም ለእ/ርም ምስጋና እንደሚበዛ ሊነግሩት ሞከሩ። እሱ ግን ተቆጣና እኔ የምፈልገው የፍፁማን ህብረት ካለ ብቻ ነው የምቀላቀለው ብሎ ረጅም መስፈርቱን ሲደረድር ኧቃረጡትና ልጄ እንደ አንተ አባያ ሚዛን ከሆነ እንደዛ አይነት ፍፁም ህብረት ካለና ካገኘከው አንተ ስትገባበት ፍፅምናውን ያጣል። አይዞህ ተስፋ ግን አለ። በመንፈስ ወደ ክርስቶስ አእምሮ ተመለስና የምትፈልገውን ፍፁም ህብረት የት እንደምታገኘው ጌታ ቢረዳኝ አውቀዋለሁና ላሳይህ ባይገርምህ ወገኖችም አንተም እዛ ህብረት ውስጥ አላችሁበት ብለው ይህን ቃል ነገሩት።

ከዚህ ቡሃላ ከክርስቶስ ጋራ የት እንደ ገባህ ካወክ ይህን ጥያቄ ለማንሳት ከሰማይ ወደ መሬት አትወርድም አሁን አንተ በመንፈስ ያለከው በአብ ቀኝ ከክርስቶስ ጋር ተቀምጠካል ከሰማይ ወደ መሬት ዘጭ ብለህ በመቀመጫህ አትውደቅ። ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ገብተሃል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ መግባት መውጣት ብሎም መሰማራት ሆኖልሃል። በደስታም ወደ ከተሰበሰቡት አእላፋት መልእክተኘቹ ጋር በደስታ ሃሴት እያደረክ ነው። በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር ተቀላቅልሃል፥ የሁሉም ዳኛ ወደ ሆነ ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥ ህብረት ገብተሃል። አሉት ልጁም በነፍሱ መስኮት ሾልኮ ወደ ሰጋ ፈቃድ ከወጣበት ከስጋ ድካም ወደ መንፈስ ብርታት ዘወር አለ። ከእ/ር መቅደስ ዘንድም ተመለሰ ንጉስንም እንደገና በውበቱ ማየት ጀመረ።

በእውነት የታጠቀ ፍፁም ትምርት ቤት ካለ መማር ሐጥያት አይደለም። ከእግዚያብሄር በቀጥታ የተማረ ምድረ ገበሬ፤ አርብቶ አደር ፤ቀረጽ ሰብሳቢ ሁሉ በ3 አመት ተኩል በእየሱስ ክርስቶስ ኮሌጅ ተመርቀው ሲወጡ ምድርን እንደ ጌታቸው ሁሉ በአፋቸው ብትር መተዋታልና። ፈቃዱ ከሆነ ብትማሩ እ/ርን ብዙ እንደ ምትጠቅሙት የታወቀ ነው ባትማሩም ይጠቀምባችሃል። ለእ/ር የሚሳነው የለም። ለዚህ ምሳሌ የሁለቱን ሐዋርያቶች ጴጥሮስና ጳውሎስ ህይወት ማነፃፀር በቂ ነው። ጴጥሮስ እ/ር በሚገባ ተጠቅሞበታል ስላልተማረ ግን አገልግሎቱ ከእስራኤልም ወይም ከአይሁድ ክልል አላለፈም።

በአንፃሩ ጳውሎስ በገማሊያ ዩንቨርስቲ የአባቶችን ህግ ማለትም የብሉይ የህግ መጽሐፍትን ጠንቅቆ ተምረዋል። ብዙ የአጎራባች አገሮች ቋንቋዎችንም ይናገር ነበር ። ይህም ባክ ግራውንዱ የጌታ ነገር ሲገለጥለት ጥሩ መዘርጋት ሆነለት አገልግሎቱም እንዳልተማረው ጴጥሮስ በእስራኤል የተወሰነ አልነበረም። ጰውሎስ ግን በእስራኤል፤ በሮም፤ በግሪክ በተለያዩ ነገስታት ወዘተ… በማንም ፊት ለመቆም ብቃቱና አቅሙ ነበረው ጌታን በኅይል ገለጠ። ጌታም የጰውሎስ ያክል ባግራውንድ ጴጥሮስ እንደሌለው ስለሚያውቅ ከእስራኤል ውጪ ሚሽን የሰጠው ለጴጥሮስ ሳይሆን ለተማረው ጰውሎስ ነው።
“ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤”የሐዋርያት ሥራ 9/15

እንግዲህ ይህን ስለ አንዳንድ ወገኖች ስል እጽፋለሁ እንጂ በእግዚያብሄር መንፈስና በልጅነት ውስጥ ይሄ ነው የሚባል ቃሚ መስፈርት ወይም የትምርት ቤት ፈጥም ብሎ ነገር ድንጋጌ የለም ። በእግዚያብሄር ልጅነት ቁልፉ እርሱ የእውነት መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ በመራን ጊዜ ወደ ሚሄድበት እኛም በጉን እንከተለዋለን ትልቁ ነገር ይሄነው። የክርስቶስ አእምሮ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ይሰማል ድል ይነሳል። ከእግዚያብሄር መማር ወሳኝ ነው። የፃድቅ ሃብቱ ትጋቱ ነውና ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፤ የእውነትን ቃል በቅንነት ማስተዋልና መለየት፤ እውነትን በፍቅር ማስተማርም፤ እንዲሁ። ወንድም ቢኒ

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal