
ጥያቄና መልስ [የእግዚአብሔር ፍርድ በብረት እና በእንጨት ቀንበር በህዝቦች ላይ]
ጠያቂ ወንድም ትግስቱ ኀ….
1,.1ሰላም ይብዛ! በትክክል ነጥቡን በጥያቄህ ውስጥ መልሰኸዋል። በቅድምያ እኔ እንደምረዳው “ልጆች በሚያቱና በሚሰሙት ነፍሳቸው ትጨነቃለች” ላልሽው በአንድ መአዝን ሆነን ስናየው ልክ ነው ያስጨንቃል አመጽ በየትኛው ቅርጽና ይዘት ባህሪው ነው። ደስ የሚለው ግን ጌታ እንካን ከፖለቲካ ከዘር ወዘተ… አመጽ እ/ር ከወረደ ከሞራል አመጽ መካከል የተጨነቀውን ጻድቅ አድነዋል፤ “2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2/7-8 ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዓመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥” የዘልአለም አባት ና አምላክ ብርቱ ነው። የነገስታትንም ወገብ የሚፈታ እሱ ነው ጥበብና ኃይልም ለእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ፤ ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያፈልሳል፥ ነገሥታትንም ያስነሣል፤ ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል። የጠለቀውንና የተሠወረውን ይገልጣል፤ በጨለማ ያለውን ያውቃል፥ ብርሃንም ከእርሱ ጋር ነው። እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ያጠፋል፥ የአሕዛብንም አሳብ ይመልሳል። የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘላለም ይኖራል፥ የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው።አሜን።
የተሰጠን የልጅነት መንፈስ እንድንጨነቅ አልተሰጠንም በቅድሚያ የሚያስጨንቀንን ሁሉ በጊዜው ከፍ በሚያደርገው በሱ እግር ስር ማለትም ሁለን ከሚገዛ ከሱ ከስልጣኑ ስር ልንጥለው ይገባል። በዛ ላይ ወደ ክርስቶስ ብስለት ከሳበን እሱ ዓይኑ እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤ ልጅነት የአባትን የልብ ትርታ በማድመጥ በመንፈስ ምሪት በቅንነት ይፈርዳል እንጂ በመልክ አይፈርድምና
“ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4/6 ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። 7 አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።”
ትንቢተ ኢሳይያስ 11/3 እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤
Isa 11/3 And shall make him of quick understanding in the fear of the Lord: and he shall not judge after the sight of his eyes, neither reprove after the hearing of his ears:
የዮሐንስ ወንጌል 7/24 ቅን ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ አትፍረዱ።
2, ትንቢተ ኤርምያስ 9/24 ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡
ማስተዋል ያለብን ህዝቦች ሁሉ የሚረኩት በክርስቶስ ሲገዙ ብቻ ነው። እንደገናም ማስተዋል ያለብን ህዝቦች በክርስቶስም ቢሆንም ቀንበር አይቀርላቸውም ይሄኛው ቀንበር ግን ይለያል ደስ የሚልም ነው ቀንበሩ ልዝብ ሸክሙም ቀሊል ሲሆን የቀንበሩ ተፈጥሮና ባህርይም የዋህነት የተባለ በልብም ትሑትነት የሆነ ፍሬውም ለነፍስ ሁሉ ዕረፍት የሚሰጥ ነው። የበሰሉት የእ/ር ልጆችም ሁሉ በዚህ ባህሪ ነው የሚገለጡት የልጁን መልክ ሊመስሉ የግድ ነውና ።
የማቴዎስ ወንጌል 11/28 እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
29 ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
30 ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።
ሌላው ማስተዋል ያለብን ህዝቤን ልቀቅ ያለው ከፈርኦን አገዛዝ አውጥቶ በራሱ በእግዚአብሔር እንዲገዙ ነው እንጂ ከፈርኦን ወደ ሌላ ፈርኦን [ከአለም ስርአት ወይም በሌላ የባቢሎን ዳይሜንሽን ወይም ሌላ ገጽታ ስርአት(ባቢሎን መንፈሳዊ ዘማዊትዋን እንደ ሚያመለክትም ይገባኛል )] አልነበረም። አሁን ችግሩ በአለም አህጉራት ሁሉ ያለው ስርአት በአጠቃላይ ለፍጥረት እረፍትን በፍፁም አያመጣም። የስልጣን ሽግግሮች ሁሉ ከፈርኦን ወደ ሌላ ፈርኦን ናቸውና። ዲሞክራሲ ማስክ ወይም ጭምብል ነው። Democracy (Greek: δημοκρατία dēmokratía, literally “rule of the people”) ያስቃል ብዙሃኑ ህዝቦች መቼም መርተውም ገዝተው አያውቁም ሹሞኞች እንጂ ሆኖም ይህ ስርአት ከአለም ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ በቅዱሳን አገዛዝ እ/ር እስኪ ተካው ድረስ ለአሁን መቀጠሉ አይቀርም እዚጋ ነው ብዙ ሰው የተላለፈው ለዚህም የሰው ስርአት ቢሆን ጌታ ጌታው እንደሆነ የታወቀ መሆን አለበት። ለወደደው በጽድቅ የሚመሩ መሪዎችን ይሰጣቸዋል ትኩረታቸውን ወደሱ እንዲያደርጉ ንስሃ ሊሰጣቸው ለወደደ የከንፈር አገልግሎት ለሚሰጡ ህዝቦች ደግሞ ለዘመናት የገዝዎቻቸውን ልብ የማን አለብኝነትና የአምባገነን ዳንኪራ ቤት ያደርገዋል።
ጌታ ቢረዳኝ አሁን ወደ ሁለተኛው ጥያቄሽ ድምዳሜ ልመለስና ከላይ እንዳየነው በእ/ር ሉአላዊነት ከተግባባን የሰው አካሄድ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘው እንደ ሆነ እንካንስ በመሪዎችና ብሎም በማህበረሰቡና በወገኖቹ ቀርቶ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን እንደሚያደርግ ማወቁ በረከት ነው ደስ ካላሰኘው ግን ሁከትን ይሰጣዋል። ማ ?እግዚአብሔር ! ለመሆኑ የመሪዎችን ልብ የሚጫወትበት ማነው?በእርግጥም እግዚአብሔር ነው!የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል። ግን ለምን ህዝቦች መንገዱን ሲወዱ በጥሩ መሪዎች ይባረካሉ? ሲክዱትስ ደግሞ በልበ ደንዳና መሪዎች ያስጨንቃቸዋል። አህዛብን የሚገዙት በተፈጥራዊው አእምሮ ና አይን ስናይ የምድር ነገስታትና መሪዎች ናቸው እውነቱ ግን እውነተኛው ከበስተጀርባ ሆኖ የሚገዛው ሃይል እራሱ እ/ር ነው።
አንድ ህዝብ የእ/ር ሉአላዊነት ላልካደ ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። የሚለውን ይቀበላል ከእ/ር ጋር ከተስማም እ/ር እራሱ በጽድቅ የሚመሩት መሪዎች እዲሆኑ ያደርጋል። ከፈለገም የነገስታቱን ወገብ በፍርድ ይፈታል። እሱ ብቻ ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያፈልሳል፥ ነገሥታትንም ያስነሣል፤
መዝሙረ ዳዊት 22/27 የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስቡ፥ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሱ፤ የአሕዛብ ነገዶች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ።
28 መንግሥት ለእግዚአብሔር ነውና፥ እርሱም አሕዛብን ይገዛል።
29 የምድር ደንዳኖች ሁሉ ይበላሉ ይሰግዳሉም፤ ወደ መሬት የሚወርዱት ሁሉ በፊቱ ይንበረከካሉ፤ ነፍሴም ስለ እርሱ በሕይወት ትኖራለች።
30 ዘሬ ይገዛለታል፤ የምትመጣው ትውልድ ለእግዚአብሔር ትነግረዋለች፤
31 ጽድቁንም ለሚወለደው ሕዝብ፥ እግዚአብሔር ያደረገውን ጽድቁን፥ ይነግራሉ።
መዝሙረ ዳዊት 60/1 አቤቱ፥ ጣልኸን አፈረስኸንም፤ ተቈጣኸን ይቅርም አልኸን።
2 ምድርን አናወጥሃት አወክሃትም፤ ተናውጣለችና ቍስልዋን ፈውስ።
3 ለሕዝብህ ጭንቅን አሳየሃቸው፥ አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን።
4 ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው።
ትንቢተ ኢሳይያስ 45/7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
ትንቢተ አሞጽ 3/6 ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ክፉ ነገር በከተማ ላይ የመጣ እንደ ሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?
“Shall a trumpet be blown in the city, and the people not be afraid? Shall there be EVIL in a city, and THE LORD HAS NOT DONE IT?” (Amos 3:6). በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ሁሉም ነገር ከእ/ር ነው ለማለት ይተናነቃቸዋል በተለይም ክፉ ብሎ ነገር ከመልካሙ እ/ር ይወጣል ብለው አያስቡም።
መጽሐፈ ምሳሌ 16/7 የሰው አካሄድ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘው እንደ ሆነ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋል።
Prov 16/7 When a man’s ways please the Lord, he maketh even his enemies to be at peace with him.
መጽሐፈ ምሳሌ 21/1 የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።
Prov 21/1 The king’s heart is in the hand of the Lord, as the rivers of water: he turneth it whithersoever he will.
ወደ ሮሜ ሰዎች 13/1 ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።
2 ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።
3 ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤4 ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።5 ስለዚህ ስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።
መደምደምያ፡
አካለ ክርስቶስ ሁሉ ማለትም የእግዚአብሄር ልጆች በክብር መገለጥ እስከ ሚገለጡበት እስከዛ ጊዜ ድረስ የአመፃ ሚስጥሩ በታላቅ ፍጥነት እንደሚጨምር ሳንደናገጥ መጠበቅ አለብን በዚያው ልክ የሚከለክል አለና። ልጅነት የበላይነት እና ስልጣን ይዞ ለፍጥረት መገለጥ የተከበረውን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ተስፋ ሙሉውን ያስጨብጠናል. “ዮሐንስ ራእይ 2/26-27 ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤ Rev 2/26 And he that overcometh, and keepeth my works unto the end, to him will I give power over the nations:27 And he shall rule them with a rod of iron; as the vessels of a potter shall they be broken to shivers: even as I received of my Father.”
ትንቢተ ዳንኤል 7/18 ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፥ እስከ ዘላለም ዓለምም መንግሥቱን ይወርሳሉ።
ትንቢተ ዳንኤል 7/27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል።
ሌላው በገናናዋ ቤተክርስትያን ብዙ ስተቶች ቢኖሩም ዋናዎቹ ብየ የማስበው መሰረታዊ የሚባሉት ሁለት ታላላቅ ስህተቶች በእ/ር ሉአላዊነት አያምኑም ለታይታ እ/ር ሉኡል ነው ካሉ ቡሃላ ሰው ነፃ ፈቃድ አለው በማለት ልክ እስራኤል የማይወሰነውን እ/ርን በሃሳባቸው ወሰኑት እንደሚል የአምልኮ መልኩን ይተውኑታል ኅይሉን ግን በውስጣቸው በመወሰን ይክዳሉ። እ/ር ግን ለሰው ፈቃድም ጌታዋ ነው። ሁለተኛው እ/ር ፍቅር ነው ካሉ ቡሃላ ያለ ሓፍርት እ/ር ለዘልአለም በትሪሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለዘልአለም የሚያሰቃይ አረመኔ አድርገው በሱ ላይ ይዋሹበታል።
አሁን እኛ በእ/ር ሉአላዊነት ካመንን ተባርከናል ያመነስ ወደ እረፍት ይገባል ነውና። እሱ በነገር ሁሉ ሉኡል ነው ካልን ሉኡል ነው። በመንፈሳዊው አለም ከመሰረትዋ በመውደቅ ላይ ካለችው ከባቢሎን የምነለየው አንዱ በዚህ መሰረታዊ ሃሳብ ነው። ሌላው የእ/ር ፍርድ ሁሉ ከዘመናት ከጊዜ ጋር የተወሰነ ነው እንጂ የዘልአለም ብሎ ነገር ቅጣት የለም
ባለፈው እንዳነሳሁት የዘመን ትርጉም ደግሜ ልጥቀሰውና በመረዳት ብርሃን ማስተዋል ያለብን ዘመን ማለት ዘልአለም ማለት አይደለም። ብዙ ጊዜና ብዙ ወቅቶች አሉ። ነገር ግን አንድ ዘልአለም ብቻ አለ። ዘልአለም ጅማሬ የለው ፍፃሜም ቢሆን የለውም። ነገር ግን ጊዜ ዘመን ወቅቶች ሁሉም ጅማሬ አላቸው ፍፃሜም አላቸው። ጊዜ ሲያበቃ ዘልአለም ይጀምራል የሚለው አባባል ፈጽሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም ዘልአለም ጅማሬ የለውም የሚያበቃም አይደለም። ዘልአለም ጊዜ ሲመጣ የሚጀምር አይደለም። ዘመናት በዘልአለም ውስጥ የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ልክ ሴኮንድ በደቂቃ ውስጥ ቦታ እንዳለው ደቂቃም በሰአት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው ሰአትም በአመታት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው። አመታት እና ዘመናት ያልቃሉ በዘልአለም ውስጥም የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ጊዜ እናስተውል ዘንድ በነዚህ ቃላቶች መካከል ያለው ልዩ ነት ግልጽ እይታ ሊኖረን ወሳኝ ነው። ዘመን የሚመደበው በጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘልአለም ግን ጊዜ አልባ ነው። በመጽሐፍ ስለ ዘመን የተናገሩትንና ሰለ ዘልአለም የተናገሩትን ለይተን ማስተዋሉ የእ/ርን ጠቅላላ ምክር እናስተውል ዘንድ እጅግ ይጠቅመናል።
በጣም የሚያሳዝነው አብዛኛዎቹ የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች ብዙ የሚመሰገኑበት ቢኖርም ዘመንን በተመለከተ ሲተረጉሙ ግድ የለሽ ሆነው ዘልአለም እያሉ በመተርጎማቸው በእ/ር ህዝብ ላይ ለዘመናት ትልቅ ግራ መጋባትን አስከትለዋል። ይህም ብዙ ትውልዶችን ለአያሌ ዘመናት የተዛባ መረዳት ውስጥ ቆልፎ አስቀምጠዋቸዋል። ለመጥቀስ ያህል የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች KJV ላይ እዲሁም በዚህ መጽሐፍ ተጽኖ ስር የተተረጎሙ ሁሉ ላይ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ስለሚሳደብ ሰው የተናገረውን ቃል እንዲህ ያስቀምጡታል። እግዚያብሄር ያሳያችሁ አንዱ ቃል ወደ ስንት ተበታትኖ እንደ ተተረጎመ age {2 ጊዜ beginning of the World {2} ጊዜ, for ever and ever,(8) course{1}ጊዜ World {32} ጊዜ eternal {42}ጊዜ, world began{1}ጊዜ forever{27}, for evermore{2}, እነዚህ ሁሉ ዘመን ወይም እንደ አገባቡ ከዘመን ዘመን፤ ለዘመናት፤ ለዘመኑ፤ ወዛተ ተብሎ በቀላሉ በዚህ መልክ መተርጎም ነበረበት።
“ማርቆ3/29 መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን “የዘልአለም” ሃጥያት ይሆንበታል እንጂ አይሰረይለትም” ከዚህ የተሳሳተ ትርጉም የተነሳ የተሳሳተ ጽንሰ ሃሳብ ተወልደዋል። ለዘልአለም ይቅር የማይባል ሃጥያት አለ ብለን እንድናስብ አድርጎን ነበር። ነገር ግን የቃሉ ፍቺ በትክክል እንዲያቀብል አድርገው ከተረጎሙት ከጥቂት የእንግሊዝኛም ትርጉሞች መካከል Emp hatic Diaglott የተባለው ትርጉም ትክክለኛውን ትርጉምi እዲህ ያስቀምጠዋል። “Whoever may blasphemy the Holy Spirit no forgiveness to the age but is exposed to anian lasting judgment mar3/29” “መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ “ለዘመኑ” ይቅር አይባልም። ነገር ግን ”ለዘመኑ“ ፍርድ ይጋለጣል።“ እንደ ምናስተውለው ይቅር የማይባለው ለፍርድ የሚጋለጠው ለዘመኑ ፍርድ እንጂ ለዘልአለም ፍርድ አይደለም። በማትዮስ 12/32 ያለው ደግሞ እንዲህ ተብሎ ተተርጉመዋል ”በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ ”አለም“ ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም። አለም የሚለው ቃል ከግሪኩaion ማለትም ዘመን age ተብሎ መተርጎም ከነበረበት ቃል የመጣ ነው። ቃሉ መተርጎም የነበረበት “መንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ “ዘመን” ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም” ነው። ጌታ እየሱስ የተወለደው በህግ ዘመን ስለ ነበር በዚህ ዘመንም ቢሆን ማለቱ የህግን ዘመን ለማሳየት ሲሆን በሚመጣው ዘመን ቢሆን ሲል ደግሞ አሁን እኛ ያለንበትን የፀጋውን ዘመን ማለቱ ነው። ይህን ካስተዋልን ስለ ዘመንና ስለ ዘልአለም ያለውን ብዥታ ያጠራልናል። በግሪክ aion(ሰዋሰው noun) በግልጽ “ዘመን ወይም ያልተወሰነ ክፍለ ጊዜ ነው an age or an indefinite period of time, Young’s Concordance”
መደምደምያ፡ ቃል። ትንቢተ ኤርምያስ 9/24 ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ አሜን።