እግዚአብሔር ያለማቃረጥ ማርሽ እየቀያየረ ጊዜያትንና ዘመናትን በመለዋወጥ ላይ ነው።
እ/ር ማርሽ መቀያየሩንና ጊዜያትንና ዘመናትን በመለዋወጥ ላይ መሆኑን ከጥቂቶች በስተቀር ማለትም ሊያስተውሉ ከተሰጣቸው በቀር ለብዙዎች የገባንበት ዘመን የተሰወረባቸው ይመስላል። ቀስ በቀስ ከኤክሌስያ ወደ መንግሥቱ ዘመን ገብተናል። ይህን የመንፈስ እንቅስቃሴ የሚያስተውሉት ምንም እንኳ የተጠሩት ብዙዎች ቢሆኑም የተመረጡት ጥቂቶች እንደሆኑ እና የጊዜን ሚስጥር ያስተውሉ ዘንድ የተሰጣቸው ውስን እንደሆኑ በግልጽ ይስተዋላል።
ግን ይህም የመጨረሻው ዘመን እንዳይደለ ስናስተውል እንገረማለን። በእርግጥ ካስተዋልነው ከፊት ለፊታችን ብዙ ዘመናት እና መንፈሳዊ እድገቶች አዳዲስ ምእራፍ ይዘው እንደሚገለጡ ግልጽ ነው። መቸም እግዚአብሔር ለእኛ ያቀዳቸውን ነገሮች ከአዕምሮአችን በላይ ናቸው። በቸም በዚህ ዘመን መልካሙንና ክፉውን ከሚያበቅለው ዛፍ በሙልአት ዋጅቶን ንቃተ ህሊናችንን በህይወት ከወረስን ወይም ከህይወት ዛፍ ብቻ የምንበላና ደግሞም የበላ ሁሉ ያድጋልና አድገን ለፍጥረትም ህይወትን በእርሱ በሙልአት ለመግለጥ በዚህ ትውልድ ከጀመረ እንደዚህ ትውልድ የታደለ የለም። ይህን ሚስጥር የሚያውቅ አባት ባቻ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ስናስተውል ወደ ሶስት ጊዜ ገና ከ 1,000 ሺ በላይ ትውልድ በዚህች ምድር ላይ እንደ ሚመላለስ እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገብተዋል ይለናል።
መዝሙረ ዳዊት 105/8 ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥Ps 105/8 He hath remembered his covenant for ever, the word which he commanded to a thousand generations.
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 16/14 እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው። ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥1Chr 16/14 He is the Lord our God; his judgments are in all the earth.
ኦሪት ዘጸአት 20/6 ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። Exod 20/6 And shewing mercy unto thousands of them that love me, and keep my commandments.
እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን የገባው ለ1,000 ዓመት ሳይሆን ለ1,000 ትውልድ ነው። በአለማዊ ቀመር የአንድ ትውልድ አማካይ እድሜ 50 አመት ነው እኛ ግን እውነቱን እንድናስተውለው በመጽሐፍ ቅዱስ እንየውና የአንድ ትውልድ አማካይ እድሜ 40 ዓመት ነው። በምድረ በዳ አንዱን አጉረምራዊን ትውልድ ጌታ የተቆጣውና በምድረ በዳ የጨረሰው በአንፃሩም በተመሳሳይ ጊዜ አዲሱ ትውልድም የተተካው በ40 አመት ነበር። በዚህ ስሌት ከአብርሃም ቃል ኪዳን ወዲህ 100 ትውልድ ብቻ ነው ይህም 4,000 ዓመታት ነው። ያም ማለት ለአብርሃም የገባውን የተስፋ ቃል ኪዳን ለመፈፀም ከ 900 መቶ ትውልድ በላይ ይቀራል ማለት ነው። እንደ ምናስተውለው ቀሪው ምን ያህል አመታት እንደሚወስድ ለማወቅ የሮኬት ሳይንቲስት መሆን አይጠይቅም መልሱ ግልጽ ነው 36000ሺ ነው። አሁን ደግሞ ዘመናትን በሰራበት በልጁ እተናገረን እየተናገረንም ነው። …spoke to us in a Son whom He placed …Whom He also made (formed; constructed) the ages (eons).
HEBREWS1/2. upon the last of these days spoke to us in a Son whom He placed [as; to be] Heir of all [ – being both masc. & neut., this could also read: One who receives all men as an allotment; or: heir of all things; One who received everything as his allotted inheritance] through Whom He also made (formed; constructed) the ages (eons).GMT ትንቢተ ዳንኤል 2/21 ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያፈልሳል፥ ነገሥታትንም ያስነሣል፤ ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል። Dan 2/21 And he changeth the times and the seasons: he removeth kings, and setteth up kings: he giveth wisdom unto the wise, and knowledge to them that know understanding:
ሰላም ይሁን
ወገኔ ማብራርያ ስለ ጠየቁ ነው እንጂ በትንሹ መልስ ለመስጠት ሞክሪ ነበር። 2ኛጴጥ3/8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
መቸም የክርስቶስ አእምሮ መቼም አይሰናከልም ብየ አምናለሁ። ይመስለኛል ማታ ስለነበረ ሀሳቡን በእንጥልጥል ተውኩት። መጨመር የነበረብኝ በእግዚአብሔር ዘልአለምነት የጊዜ ገደብ ውስንነት የለም የአሁን አምላክ ነው ወይም ለመንፈሳዊው ነገር የጊዜ ክልከላ አይገድበውም ሰማይ ተከፍተዋል መንፈሳዊ በሩ ወለል ብሎ ተከፍተዋል በመንፈስ በዚህ በር እንገባለን እንወጣለን መሰማሪያም እናገኛለን ያለነው አዳምን አሁን ጨርሶ ክርስቶስን ለመግለጥ የቀን ቀጠሮ የለውም።
36ሺ አመት ለእ/ር 36 ቀን እንደ ማለት ናትና። “8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።”
ተመሳሳይ ጥያቄ አንድ ወንድም ጠይቆኝ የመለስኩለትን በድጋሚ አቅርቤዋለሁ
የተጠቀሰው ከዚህ ይጀምራል
“ጥያቄ ልጠይቅህ እስቲ በ 90 A.D. ከጌታ ትንሳኤ ከ56 አመት ከስድስት ወር ገደማ ቡሃላ አሁን የመጨረሻው ሰአት ነው። ተብሎ ተጽፎ ነበር ከዛ ቡሃላ ሌላ ዘመን ነበረን? ወይም እንደ አንተ እይታ ሌላ ዘልአለም ነው የጀመረው?አዎን ሌላ ዘመን ወይም ዘመኖች እንጂ ሌላ ዘልአለም አልጀመረም እነሆ ቀጠሎማ ከ2000 ሺ ዘመናት ቡሃላም ቢሆን እ/ር የሰጠውን ቃሉን አሁንም የሚያወሩት ብዙ ሰራዊቶቹ ናቸው። በነገራችን ላይ ሌላ ዜና አለኝ የዘመን ፍፃሜ እንጂ የአለም ፍፃሜ የለም። በእርግጥ የመጨረሻው ጠላት ሞት ሲደመሰስ የቀደመው ሥርዓት ሁሉ ያልፋል። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፥18 ልጆች
በቅድምያ የዘመን ፍፃሜ እንጂ የአለም ፍፃሜ የለም። ማለቴ ከእውነት ነው! በክርስቶስ ወንድሜ እንደመሆንህ እልሃለሁ ጊዜ ውሰድና በትኩረት የእ/ርን ቃል እራስህ አጥና ከዛም እኔም ሆነ ሌላ ሰው በሚናገረው አትሰናከልም። የአለም ፍፃሜ ከሚለው ላይ “aion” ከሆነ የትርጉሙ ምንጭ የዘመን ፍፃሜ ብለህ ተረዳው የአለም ፍፃሜ ቢሆን ኖሮ የፀሐፊው መልእክት በ”aion በዘመን” ፈንታ “kosmos አለም” በተጠቀመ ነበርና። “ይሄ የእየሱስ ክርስቶስ ዲክሽነሪ ነው። ኪኪኪ… ”
ለምሳሌ ይህን ክፍል ብታጠናው ሁለቱም ቃላት በልዮኡነት ተጠቅሞባቸው ታገኛቸዋለህ (KJV Matt 13:38 And the field is the world [አለም kosmos]; and as for the good seed, these are the sons of the kingdom; and the tares are the sons of the evil one; 39 and the enemy who sowed them is the devil, and the harvest is the end of the age [ዘመን aion]; and the reapers are angels. 40 “Therefore just as the tares are gathered up and burned with fire, so shall it be at the end of the age [ዘመን aion]..
Strong’s Concordance
kosmos: order, the world
Original Word: κόσμος, ου, ὁ
Part of Speech: Noun, Masculine
Transliteration: kosmos
Phonetic Spelling: (kos’-mos)
Short Definition: the world, universe
Definition: the world, universe; worldly affairs; the inhabitants of the world; adornment.
HELPS Word-studies
2889 kósmos (literally, “something ordered”) – properly, an “ordered system” (like the universe, creation); the world.
[The English term “cosmetic” is derived from 2889 /kósmos, i.e. the order(“ensemble”) used of treating the face as a whole.]
ባለፈው እንደ አነሳሁት እግዚያብሄር ያሳይህ አንዱ ዘመን “aion” የሚለው ቃል ወደ ስንት ተበታትኖ እንደ ተተረጎመ age ዘመን 2 ጊዜ, beginning of the World የአለም ጅማሬ{2} ጊዜ, for ever and everከዘላለም እስከ ዘላለም,(8) course{1}ጊዜWorld አለም{
በአዲስ ኪዳን ”ዘልአለም Eteernal, Everlasting” የሚለው ቃል ከዋናው የግሪኩ ቅጂ ላይ “aionions” ከሚለው ቃል የተረጎመ ነው የቃሉ ስር ወይም፡ ንብረትነቱ “EION” ነው። ትርጉሙም “ዘመን age” ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ናቸው ማለት አይደለም ። aion(the noun form) ሰዋሶው ወይም ነባር ስም ሲሆን aionions (the adjective form ቅጽል ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሶው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንት ሰዋሰው ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት፦ እለታዊ, አመት ፦አመታዊ እንደሚባለው መለት ነው። Greek word “aion” (Strongs #165) or its adjective form “aionios” (#166
እንደ አንድ አንድ ሃሰተኛ ነብያት ትንቢት የአለም ፍፃሜ በዚህና በዛ ዘመን ወይ ቀን ሲል እኛ ካመንአቸው መንፈሳዊ ሚስኪን ነን። እስቲ ይህን እናስተውል። ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም
