ወደ ሮሜ ሰዎች 2 Rom 2
1 ስለዚህ፥
  አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን
  ታደርጋለህና።
1 Therefore thou art
  inexcusable, O man, whosoever thou art that judgest: for wherein thou judgest
  another, thou condemnest thyself; for thou that judgest doest the same
  things.
2 እንደዚህም
  በሚያደርጉት ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ እንደ ሆነ እናውቃለን።
2 But we are sure that the
  judgment of God is according to truth against them which commit such things.
3 አንተም
  እንደዚህ በሚያደርጉ የምትፈርድ ያንም የምታደርግ ሰው ሆይ፥ አንተ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን?
3 And thinkest thou this,
  O man, that judgest them which do such things, and doest the same, that thou
  shalt escape the judgment of God?
4 ወይስ
  የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?
4 Or despisest thou the
  riches of his goodness and forbearance and longsuffering; not knowing that
  the goodness of God leadeth thee to repentance?
5 ነገር
  ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ።
5 But after thy hardness
  and impenitent heart treasurest up unto thyself wrath against the day of
  wrath and revelation of the righteous judgment of God;
6 እርሱ
  ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ያስረክበዋል፤
6 Who will render to every
  man according to his deeds:
7 በበጎ
  ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤
7 To them who by patient
  continuance in well doing seek for glory and honour and immortality, eternal
  life:
8 ለዓመፃ
  በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙትና በአድመኞች ላይ ግን ቍጣና መቅሠፍት ይሆንባቸዋል።
8 But unto them that are
  contentious, and do not obey the truth, but obey unrighteousness, indignation
  and wrath,
9 ክፉውን
  በሚያደርግ ሰው ነፍስ ሁሉ መከራና ጭንቀት ይሆንበታል፥ አስቀድሞ በአይሁዳዊ ደግሞም በግሪክ ሰው፤
9 Tribulation and anguish,
  upon every soul of man that doeth evil, of the Jew first, and also of the
  Gentile;
10 ነገር
  ግን በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፥ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው።
10 But glory, honour, and
  peace, to every man that worketh good, to the Jew first, and also to the
  Gentile:
11 እግዚአብሔር
  ለሰው ፊት አያዳላምና።
11 For there is no respect
  of persons with God.
12 ያለ
  ሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤ ሕግም ሳላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤
12 For as many as have
  sinned without law shall also perish without law: and as many as have sinned
  in the law shall be judged by the law;
13 በእግዚአብሔር
  ፊት ሕግን የሚያደርጉት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ ጻድቃን አይደሉምና።
13 (For not the hearers of
  the law are just before God, but the doers of the law shall be justified.
14 ሕግ
  የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤
14 For when the Gentiles,
  which have not the law, do by nature the things contained in the law, these,
  having not the law, are a law unto themselves:
15 እነርሱም
  ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ።
15 Which shew the work of
  the law written in their hearts, their conscience also bearing witness, and
  their thoughts the mean while accusing or else excusing one another;)
16 ይህም
  እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ በሰው ዘንድ የተሰወረውን በሚፈርድበት ቀን ይሆናል።
16 In the day when God
  shall judge the secrets of men by Jesus Christ according to my gospel.
17 አንተ
  ግን አይሁዳዊ ብትባል በሕግም ብትደገፍ በእግዚአብሔርም ብትመካ፥
17 Behold, thou art called
  a Jew, and restest in the law, and makest thy boast of God,
18 ፈቃዱንም ብታውቅ ከሕግም ተምረህ የሚሻለውን ፈትነህ ብትወድ፤ 18 And knowest his will,
  and approvest the things that are more excellent, being instructed out of the
  law;
19-20 በሕግም የእውቀትና የእውነት መልክ ስላለህ፥ የዕውሮች መሪ፥ በጨለማም ላሉ ብርሃን፥ የሰነፎችም አስተማሪ፥ የሕፃናትም
  መምህር እንደ ሆንህ በራስህ ብትታመን፤
19 And art confident that
  thou thyself art a guide of the blind, a light of them which are in darkness,  20 An instructor of the foolish, a teacher of
  babes, which hast the form of knowledge and of the truth in the law.
21 እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን? 21 Thou therefore which
  teachest another, teachest thou not thyself? thou that preachest a man should
  not steal, dost thou steal?
22 አታመንዝር የምትል ታመነዝራለህን? ጣዖትን የምትጸየፍ ቤተ መቅደስን ትዘርፋለህን? 22 Thou that sayest a man
  should not commit adultery, dost thou commit adultery? thou that abhorrest
  idols, dost thou commit sacrilege?
23 በሕግ  የምትመካ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታሳፍራለህን? 23 Thou that makest thy
  boast of the law, through breaking the law dishonourest thou God?
24 በእናንተ  ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ መካከል ይሰደባልና ተብሎ እንደ ተጻፈ። 24 For the name of God is
  blasphemed among the Gentiles through you, as it is written.
25 ሕግን ብታደርግ መገረዝስ ይጠቅማል፤ ሕግን ተላላፊ ብትሆን ግን መገረዝህ አለ መገረዝ ሆኖአል። 25 For circumcision verily
  profiteth, if thou keep the law: but if thou be a breaker of the law, thy
  circumcision is made uncircumcision.
26 እንግዲህ ያልተገረዘ ሰው የሕግን ሥርዓት ቢጠብቅ አለመገረዙ እንደ መገረዝ ሆኖ አይቈጠርለትምን? 26 Therefore if the
  uncircumcision keep the righteousness of the law, shall not his
  uncircumcision be counted for circumcision?
27 ከፍጥረቱም ያልተገረዘ ሕግን የሚፈጽም ሰው የሕግ መጽሐፍና መገረዝ ሳለህ ሕግን በምትተላለፈው በአንተ ይፈርድብሃል። 27 And shall not
  uncircumcision which is by nature, if it fulfil the law, judge thee, who by
  the letter and circumcision dost transgress the law?
28 በግልጥ አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ አይደለምና፥ በግልጥ በሥጋ የሚደረግ መገረዝም መገረዝ አይደለምና፤ 28 For he is not a Jew,
  which is one outwardly; neither is that circumcision, which is outward in the
  flesh:
29 ዳሩ ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው፥ መገረዝም በመንፈስ የሚደረግ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በመጽሐፍ አይደለም፤ የእርሱ
  ምስጋና ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።
29 But he is a Jew, which
  is one inwardly; and circumcision is that of the heart, in the spirit, and
  not in the letter; whose praise is not of men, but of God.

 

 

፨ወደ ሮሜ ሰዎች 2፡1 ስለዚህ፥ አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ
ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና። 2 እንደዚህም
በሚያደርጉት ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ እንደ ሆነ እናውቃለን። 3 አንተም እንደዚህ በሚያደርጉ የምትፈርድ ያንም የምታደርግ
ሰው ሆይ፥ አንተ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን?

ሐዋርያው በምእራፍ 1 ላይ እግዚአብሔርን ለማወቅ  ባልወደዱ መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን
ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ብሎ ዝርዝር አድርጎ ካስረዳ ቡሃላ ወደፊት ባለ ምእራፍ በእ/ር ፊት አፍ ሁሉ ይዘጋ
ዘንድ ዓለሙ ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች  እንደሆነ ለማሳየት መንገድ
እየጠረገ ነው። “ሮሜ ሰዎች 3፡23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና  የእግዚአብሔርም ክብር
ጎድሎአቸዋል፤”  ነውና  የሚመጻደቁትንም   አፍ ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ
ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር  ይህም የሕግንሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ 

 በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና አንተ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን? እያለ ሁሉ የእ/ር ክብር እንደ ጎደለውና ከእግዚአብሔር
ፍርድ እንደ ማያመልጥ የግዴታ ሁሉም የእ/ር ጸጋ እደሚያስፈልጋቸው እዲረዱ ትኩረታቸውን እያገኘ
ነው።

ምክንያቱም በእ/ር ፊት ሰው በሁለት አልተከፈለም ጻድቅና ጻድቃን ያልሆኑ
አይልም ይልቁኑ “ወደ ሮሜ ሰዎች 3:11 ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥”   ይህም የሆነበት ምክንያት “ወደ ሮሜ ሰዎች 5፡12 ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት
በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤” እንደ ምናስተውለው እ/ር
ሞትን በሰው ሁሉ ላይ በመፍረድ ሰውን ሁሉ ከፍርድ በታች አድርጎታል እና ወደ ሮሜ ሰዎች 6፡23 የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና  ገጽታው ይለያይ እንጂ ሃጢያተኛ ስለሆንክ ሞት የተባለውን ደሞዝህን ተቀብለህ
በልተሀው ሰውነት ሆኖሃል ስለዚህ በሌላው ለመፍረድ ብቃቱ የለህም በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና እያላቸው ነው። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ
የሚሆነን ጌታ በዮሐንስ ወንጌል 8     ማንም ማንንም በድንጋይ መውገር
የማይችልበት ሰአት እንደመጣ የልባቸውን ሃሳብ በመግለጥ ያሳየበት ነው።    

3 ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን
  ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው።
4 መምህር
  ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች።
5 ሙሴም
  እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት።
6 የሚከሱበትንም
  እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤
7 መላልሰው
  በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።
8 ደግሞም
  ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ።
9 እነርሱም
  ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም
  በመካከል ቆማ ነበረች።
10 ኢየሱስም
  ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ። አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት።
11 እርስዋም፦
  ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት።፨ወደ ሮሜ ሰዎች 2፡4 ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ
  ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ፦ ሐዋርያው በሮሜ9 ላይ እ/ር
  በሰው ፈቃድ ላይም ጌታ እንደሆነ እንደሚያስቀምጠው ሁሉ በደህነት ላይ ሁሉን ዋናውን ሚና  የሚጫወተው እራሱ እ/ር እንደሆነ  የሰውን ትምክህት የራሳቸውን ጽድቅ እዳያቆሙ መንገዱን  እየዘጋ እየመጣ ነው። ይህ ትልቅ መልእክት ነው ወደ ንስሐ የሚመራው የእ/ር
  ቸርነት እንደሆነ ያስተምረናል:: ለህይወት የሚሆን ንስሃን እንኴ የሚሰጥ እ/ር እራሱ ነው። “የሐዋርያት ሥራ 11፡18 ይህን
  በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና። እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው እያሉ እግዚአብሔርን
  አከበሩ።” በ “2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡9 ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደ ሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር
  ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።”፨ወደ ሮሜ ሰዎች 2፡5 ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ
  ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ። 6 እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ያስረክበዋል፤

የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን? ነገር ግን
  እንደ ጥንካሬህና  ንስሐ  እንደ ማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን
  በራስህ ላይ ታከማቻለህ። 6 እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ያስረክበዋል፤ ። በትክክልም የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ የሚገለጥበት
  በቍጣ ቀን ቍጣን የሚገልጥበት ጊዜ አለ። የእ/ር የፍርዱን ባህሪ መረዳት አለብን በትንቢተ ኢሳይያስ 26፡9 ፍርድህን በምድር
  ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩት ጽድቅን ይማራሉና” ነብዩ የእ/ር ፍርድ በአለም የመገለጡ ምክንያት ጽድቅን ለማስተማር እደሆነ
  ተረድቶታል:: በየትኛውም የእ/ር ቃል ብታጠኑ ፍርዱ ለዘላለም ዕይደለም 
  በጊዜ ውስጥ የተወሰነ ነው። ለምሳሌ የማቴዎስ ወንጌል 25፡46 እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም
  ሕይወት ይሄዳሉ የሚለው። ዘላለም  የሚለው ቃል ዘመን ተብሎ መተርጎም
  ነበረበት  ከጥቂቶች በቀር ይህን ቀጥተኛ ትርጉም  ባለመከተላቸው የእ/ርን ህዝብ በተሳሳተ መረዳት ውስጥ የሙጭኝ እንዲል
  ማወፈሪያ ግርዶሽ ሆነበታል። በትክክል ለቃሉ እውቅናን ከሰጡት ወስጥ Young’s Literal Translation  Matt. 25:46, 46 And these shall go away to
  punishment age-during, but the righteous to life age-during.  ሲሉ በዘመን ጊዜ ወስጥ መድበውታል።

መረዳት ያለብን በአዲስ ኪዳን “ዘላለም ፣eternal, everlasting የሚለው
  ቃል ከዋናው የግሪኩ ቅጂ ቃል aionions ከሚለው ቃል የተተረጎመ  ሲሆን የቃሉ ስር ወይም
  ንብረትነቱ AION ነው። ትርጉሙም “ዘመን  “ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ
  ትርጉም ያላቸው ቃላት ናቸው ማለት አይደለም። ሰዋሰው ወይም ነባር ስም ሲሆን aionions [the adjective form, ቅጽል ነው። ሁለቱ ቃላቶች ሰዋሰውና ቅጽል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንት ሰዋሰው ሲሆን ሳምንታዊደግሞ ተቀጽላው ነው።
  ልክ እለት እለታዊ አመት አመታዊ እንደ ሚባለው ማለት ነው።  

 

በመረዳት ብርሃን ማስተዋል ያለብን ዘመን ማለት ዘልአለም ማለት አይደለም።
  ብዙ ግዜዎችና ወቅቶች አሉ። ነገር ግን አንድ ዘልአለም ብቻ አለ ። ዘልአለም ጅማሬ የለውም ። ዘልአለም ፍጸሜም ቢሆን የለውም
  ። ነገር ግን ጊዜ፤ ዘመን፤ ወቅቶች ፤ ሁሉም ጅማሬ አላቸው ፍጻሜ አላቸው። ጊዜ ሲያበቃ ዘልአለም ይጀምራል የሚለው አባባል
  ፈጽሞ የተሳሰተ አባባል ነው ::  ምክንያቱም ዘልአለም ጅማሬም  ፍጻሜም የለውም ና። ዘልአለም ጊዜ ሲጀምር የጀመረ አይደለም። ዘመናት
  በዘልአለም ውስጥ የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ልክ ሴኮንድ በደቂቃ ውስጥ ቦታ እንዳለው ደቂቃም በአመት ውስጥ የራሱ የሆነ
  ቦታ እንዳለው ማለት ነው።  አመታት ያልቃሉ ዘልአለም ግን አያበቃም።
  ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ እይታ ይኖረን ዘንድ እጅግ ጠቃሚነው። ዘመን የሚመደበው በጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘልአለም ግን ጊዜ
  አልባ ነው ። በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ውስጥ ስለ ዘመን የተነገሩትንና ስለ ዘመናት የተነገሩት ለይተን ማስተዋሉ የእ/ርን ጠቅላላ
  ምክር በትክክል እናስተውል ዘንድ እጅግ ይጠቅመናል።

 

 

፨ወደ ሮሜ ሰዎች 2፡7 በበጎ
  ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤ 8 ለዓመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት
  በማይታዘዙትና በአድመኞች ላይ ግን ቍጣና መቅሠፍት ይሆንባቸዋል።9 ክፉውን በሚያደርግ ሰው ነፍስ ሁሉ መከራና ጭንቀት ይሆንበታል፥
  አስቀድሞ በአይሁዳዊ ደግሞም በግሪክ ሰው፤” 7 To them who by patient continuance in well
  doing seek for glory and honour and immortality, eternal(aionian) life[“life
  in The Age”];: 8
  But unto them that are contentious, and do not obey the truth, but obey
  unrighteousness, indignation and wrath, 9 Tribulation and anguish, upon every
  soul of man that doeth evil, of the Jew first, and also of the Gentile;  ለእውነት(እኔ እውነት ላለው ጌታ እየሱስ ክርስቶስ) ለሚታዘዙ በበጎ ስራ
  በመጽናት  ምስጋናንና ክብርን ለሚፈልጉ immortality የማይጠፋ
  (የማይበሰብስ)ህይወት ይሰጣሉ።….ይቀጥላል።