ወደ ሮሜ ሰዎች 1
ወደ ሮሜ ሰዎች 1 Rom 1
1-2 ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ። 1 Paul, a servant of Jesus Christ, called to be an apostle, separated unto the gospel of God,
2 (Which he had promised afore by his prophets in the holy scriptures,)
3-4 ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። 3 Concerning his Son Jesus Christ our Lord, which was made of the seed of David according to the flesh;
4 And declared to be the Son of God with power, according to the spirit of holiness, by the resurrection from the dead:
5 በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤ 5 By whom we have received grace and apostleship, for obedience to the faith among all nations, for his name:
6 በእነርሱም መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ ልትሆኑ የተጠራችሁ እናንተ ደግሞ ናችሁ። 6 Among whom are ye also the called of Jesus Christ:
7 በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ በሮሜ ላላችሁት ሁሉ፥ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። 7 To all that be in Rome, beloved of God, called to be saints: Grace to you and peace from God our Father, and the Lord Jesus Christ.
8 እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማች አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ። 8 First, I thank my God through Jesus Christ for you all, that your faith is spoken of throughout the whole world.
9-10 በልጁ ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና፤ ምናልባት ብዙ ቆይቼ ወደ እናንተ አሁን እንድመጣ በእግዚአብሔር ፈቃድ መንገዴን እንዲያቀናልኝ እየለመንሁ ሁልጊዜ ስጸልይ ስለ እናንተ ሳላቋርጥ አሳስባለሁ። 9 For God is my witness, whom I serve with my spirit in the gospel of his Son, that without ceasing I make mention of you always in my prayers;
10 Making request, if by any means now at length I might have a prosperous journey by the will of God to come unto you.
11 ትጸኑ ዘንድ መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁና፤
11 For I long to see you, that I may impart unto you some spiritual gift, to the end ye may be established;
12 ይህንም ማለቴ በመካከላችን ባለች በእናንተና በእኔ እምነት አብረን በእናንተ እንድንጽናና ነው። 12 That is, that I may be comforted together with you by the mutual faith both of you and me.
13 ወንድሞች ሆይ፥ በሌሎቹ አሕዛብ ደግሞ እንደ ሆነ በእናንተም ፍሬ አገኝ ዘንድ ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳሰብሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። 13 Now I would not have you ignorant, brethren, that oftentimes I purposed to come unto you, (but was let hitherto,) that I might have some fruit among you also, even as among other Gentiles.
14 ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም ዕዳ አለብኝ፤
14 I am debtor both to the Greeks, and to the Barbarians; both to the wise, and to the unwise.
15 ስለዚህም በሚቻለኝ መጠን በሮሜ ላላችሁ ለእናንተ ደግሞ ወንጌልን ልሰብክ ተዘጋጅቼአለሁ። 15 So, as much as in me is, I am ready to preach the gospel to you that are at Rome also.
16 በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። 16 For I am not ashamed of the gospel of Christ: for it is the power of God unto salvation to every one that believeth; to the Jew first, and also to the Greek.
17 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና። 17 For therein is the righteousness of God revealed from faith to faith: as it is written, The just shall live by faith.
18 እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤ 18 For the wrath of God is revealed from heaven against all ungodliness and unrighteousness of men, who hold the truth in unrighteousness;
19 እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። 19 Because that which may be known of God is manifest in them; for God hath shewed it unto them.
20-21 የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። 20 For the invisible things of him from the creation of the world are clearly seen, being understood by the things that are made, even his eternal power and Godhead; so that they are without excuse:
21 Because that, when they knew God, they glorified him not as God, neither were thankful; but became vain in their imaginations, and their foolish heart was darkened.
22 ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥
22 Professing themselves to be wise, they became fools,
23 የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ። 23 And changed the glory of the uncorruptible God into an image made like to corruptible man, and to birds, and fourfooted beasts, and creeping things.
24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤ 24 Wherefore God also gave them up to uncleanness through the lusts of their own hearts, to dishonour their own bodies between themselves:
25 ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን። 25 Who changed the truth of God into a lie, and worshipped and served the creature more than the Creator, who is blessed for ever. Amen.
26 ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ 26 For this cause God gave them up unto vile affections: for even their women did change the natural use into that which is against nature:
27 እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። 27 And likewise also the men, leaving the natural use of the woman, burned in their lust one toward another; men with men working that which is unseemly, and receiving in themselves that recompence of their error which was meet.
28 እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ 28 And even as they did not like to retain God in their knowledge, God gave them over to a reprobate mind, to do those things which are not convenient;
29 ዓመፃ ሁሉ፥ ግፍ፥ መመኘት፥ ክፋት ሞላባቸው፤ ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን፥ ክርክርን፥ ተንኰልን፥ ክፉ ጠባይን ተሞሉ፤ የሚያሾከሹኩ፥ 29 Being filled with all unrighteousness, fornication, wickedness, covetousness, maliciousness; full of envy, murder, debate, deceit, malignity; whisperers,
30 ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚያንገላቱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ 30 Backbiters, haters of God, despiteful, proud, boasters, inventors of evil things, disobedient to parents,
31 የማያስተውሉ፥ ውል የሚያፈርሱ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት ያጡ ናቸው፤
31 Without understanding, covenantbreakers, without natural affection, implacable, unmerciful:
32 እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም። 32 Who knowing the judgment of God, that they which commit such things are worthy of death, not only do the same, but have pleasure in them that do them.
ወደ ሮሜ ሰዎች መልክት ጸሐፊው ሐዋሪያው ጳውሎስ ሲሆን የተጻፈበት ዘመንም በ57 ዓ. ም.ነው: : በዚህ ምእራፍ መጀመርያ የክርስቶስን ወንጌል አስተዋውቆ ከዛም ጻድቅ እንዴት በእምነት መኖር እንዳለበትና በእምነት የሚያገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ምን ማለት እንደሆነ በ“ሮሜ1:17 የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ(በእግዚአብሔር) ይገለጣልና።” የሚለውን መሰረት በማድረግ ጽድቅም በእምነት እንደሆነ ያብራራል:: በቀረው በአብዛኛው የትንቢተ እንባቆምን ቃል መሰረት በማድረግ ጻድቁ በህይወት እንዴት መኖር እንዳለበት ግልጽ አድርጎ የጻፈው ነው:: ማለትም አንባቢው በዚህ መንገድ ይሮጥ ይፈጥን ዘንድ ያብራራው ነው ማለት ነው በ“ዕባቆም 2፦2:4 2 እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ፦ አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ራእዩን ጻፍ፥ በጽላትም ላይ ግለጠው (ግልጽ አድርገው)። ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።” Brother Binyam T. Alemayehu / http://www.wongelradio.com
ሮሜ1”1-2 ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ(G, appointed) የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ (G, little) በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።”
፨ሐዋሪያ ሊሆን የተጠራ ሐዋሪ ያ የተላከ ወይም መልክተኛ ማለት ነው:: ይህም ማለት በላኪው ተመርጦ የተጠራና ትእዛዝን የተቀበለ ሲሆን የተቀበለውም ትእዛዝ በራሱ ስልጣንን ይዞ የሚመጣ ነው ይህም ሃላፊነት ያለበት ትዛዙን የሚፈጽም ቧለማል የላከውን እንጂ የራሱን ፈቃድ የማያደርግ እንደራሴ ነው:: የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ እራሱን ባሪያ ብሎ መጥራቱ ምክንያት ህግን ጠንቅቆ የተማረ ሰው ስለ ነበር የህግ ፍጻሜ ወይም ግብ የሆነው በክርስቶስ ዘንድ ያለውን መንፈሳዊ ፍቺ ስለ ሚገነዘብ ነው::
በኛ ዘመን ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ የትምህርት ተቅዋም እንደሆነ ሁሉ በታሪክ መዛግብት ስታስተውሉ በዚያ ዘመንም ገማሊያ ከተባለ በአይሁድ የተከበረ የህግ ትምህርት ቤት አንዱ ወስጥ ተምረዋል:: በመጽሐፍ ቅዱስም ስለዚህ ት/ቤት መስራች ሰው ወጤማታማ የህግ መምህር ዕንደ ነበረ ፍንጭን ይሰጠናል:: “በሐዋ5:32 ነገር ግን በህዝቡ ሁሉ ዘንድ የከበረ የህግ መምህር ገማልያል የሚሉት “ ሲለው እራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ ከዚህ ሰው እግር ስር የአባቶችን ህግ ማለትም የሙሴ ህግን እንደ ተማረ ይናገራል:: “ሐዋ22:3 በገማልያል እግር አጠገብ ያደግኩ: የአባቶችንም ህግ ጠንቅቄ የተመርሁ::” ነኝ ይላል::
መማር መቸም መልካም ነው። ብትማሩ ይበልጥ እ/ርን ትጠቅሙታላቹሁ ጳውሎስ ከነጴጥሮስ ይልቅ የተማረ ስለ ነበር ብዙ ቋንቋም ይናገር ነበርና እ/ር በአይሁድ ላሉ ብቻ ሳይሆን ለአህዛም ጭምር ተጠቀመበት። እ/ር ለነገሩ ሰው ተማረ አልተማረ አላማው በርሱ ላይ ካለ አይገደውም ዋናው ሰውየው ከእ/ር የሰማና የተማረ ይሁን እንጂ የእ/ር ፈቃድ ይፈጸማል። ለነገሩ ሁሉ ከእ/ር የሚሰሙበትና የሚማሩበት ተስፋ እንዳለ እኮ መጽሐፍ በብዙ ቦታ ያስተምራል የእ/ር አላማውና አሰራሩ ጥልቅና ውስብስብ ስለ ሆነ ለማስተዋል ከራሱ ከእ/ር የመጣ መጠነ ሰፊ እገዛ ወሳኝ ነው ውንጂ። “ዮሃ 6:45 ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማ የተማረም ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።”
፨“ህግ ጠንቅቄ የተመርሁ” በዚህም ምክንያት ጳውሎስ የእየሱስ ባሪያ ብሎ እራሱን መጥራቱ አንደኛ እስራኤል ከግብጽ ምድር ከዋጃቸው ቡሃላ በመለኮት ህግ እንዳስረዳቸው ለዋጃቸው ጌታ ብቻ ባሪያዎች እንደሆኑ እንደሚገባ ይገነዘባል:: “ኦሪት ዘሌዋውያን 25:42 ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸውና እንደ ባሪያዎች አይሸጡ።”
ኦሪት ዘሌዋውያን “25፥55 የእስራኤል ልጆች ለእኔ ባሪያዎች ናቸውና ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸው እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።” እ/ር ሃይሉን በመግለጥ ዋጋ ከፍሎ ባርነት ካወጣቸው ቡሃላ ለዋጃቸው ጌታ ብቻ ሊያድሩና ሊያገለግሉ የተገባቸው እንደሆነ ከህጉ ያስተውላል:: በዚህም ጳውሎስ የእየሱስ ባሪያ ብሎ እራሱን መጥራቱ ትህትናውን እናስተውላለን:: ሌላው ወደ ጌታው እንደ ተመለሰ የጌታው ወዳጅ ባሪያ አድርጎ እራሱን መቁጠሩ ነው:: ጆሮው ወደ መንፈሳዊ በሩ ኢየሱስ ክርስቶስ ተደግፈዋል:: ጆሮውም የክርስቶስን ፍቅር ሊሰማና ሊያውቅ ተከፍተዋል:: ይህ ህግ የሚገኘው “በዘጸ21:5 “(ነጻ የወጣው )ባሪያውም :ጌታየን ሚስቴን ልጆቼንም እወዳለሁ አርነት አልወጣም ብሎ ቢናገር ጌታው ወደ ፈራጆች ይውሰደው ወደ ደጁም ወደ መቃኑ አቅርቦ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው ለዘላለምም ባሪያው ይሁን” መጽሐፍ “በ1ቆሮ10:11” በቀደሙት ላይ ይህ ሁሉ እንደ ምሳሌ የደረሰባቸው እኛን በዘመን መጨረሻ ያለነውን ሊናገረን እደሆነ ይናገራል:: ጆሮን ወደ በሩ መደገፍና መበሳት መንፈሳዊ አመልካችነቱ የእ/ር ቃልን ለመስማት መከፈቱን ነው:: “በመዝ 40:6-8 መስዋእትንና ቁርባን አልፈለግክም ጆሮቼን ግን ከፈትክ….አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ ህግህም በልቤ ውስጥ አለ::” ፈቃደኛው ባሪያ የእ/ርን ፈቃድ ሊያደርግ ደስ ይለዋል ጆሮው ተከፍተዋልና ለእ/ር መንፈሳዊ ድምጽ ህያው ነው:: ምክንያቱም ህጉ በልቡ ውስጥ ተጽፈዋል እንጂ በውጪ አይደለም:: ይህ ቃል በጌታ እየሱስ ላይም ተፈጽመዋል:: “ዮሃ4:34 የኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግ ነው ስራውንም መፈጸም ነው”
፨“ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው” መቸም በነብያቱ እ/ር ብዙ ተናግረዋል ለመጥቀስ ያህል በትረ መንግሥቱ ከይሁዳ እንደ ሚመትጣ ከኦሪት ጀምሮ እ/ር ሲናገር ነበረ:: “ኦሪት ዘፍጥረት 49፡10 በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።” ከዳዊት ግንድ እንደ ሚመጣ ደግሞ “መዝሙ89፡29 ዘሩንም ለዓለምና ለዘላለም፥ ዙፋኑንም እንደ ሰማይ ዘመን አደርጋለሁ።” “በኢሳ9: 6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።7 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።”
ትንቢተ ኢሳይያስ 7፥14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
የማቴዎስ ወንጌል 1፥23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው”
፨“ለእግዚአብሔር ወንጌል ”እ/ር እራሱ ይህን የመልካም ዜና ተስፋ ከጥንት ለአብርሃም ሰብኮታል:: “ገለ3:8 በአንተ አህዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ” ለእ/ር ወንጌል መለየቱ የጳውሎስ መላኩ ወይም አምባሳደርነቱ የመለኮት ቃል አቀባይ መሆኑን የሚያሳይ ነው እንጂ የእራሱ ልበ-ወለድ ትንግርት ተራኪ አይደላም። መልቱኩም ወንጌል ነው። ወንጌልም መልካም ዜና ነው። ምንም መጥፎ ዜና በውስጡ የለበትም። gospel ወይም ወንጌል ‘evangel’ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ይህም ሁለት ጥምር ቃላትን በውስጡ ያቀፈ ነው። ‘eu’ኢዩ- good ወይም መልካም እናም ‘angelion’አንጀሊኦን- message ወይም መልክት ማለት ነው። ወንጌሉም ስለ ልጁ ነው። በቀድመው ኪዳን ነብያት ስለ እየሱስ ክርስቶስ ሲተነበዩ ሁሉም ወንጌልን ያማከለ ነበረ። አዳኝ ይወለዳል ህዝቡንም ሁሉ ከሃጢያታቸውና ከዛ ውጤት ተጽኖዎች ሁሉ ያድድናል ይሉ ነበር።
እኛም የዚህን ተስፋ ጨባጮች በክርስቶስ አድርጎናል:: በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን ቡሃላ የማስታረቅንም አገልግሎት ሰጠን “2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:18 ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤19 እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።”
፨“በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ። “ ለብዙዎች ዘመናይ አመለካከት ላላቸው ወንጌል የጀመረው በአዲስ ኪዳን ነው: : በእብራ 4:2 ስናይ በምድረ በዳ ከሙሴ ስር የነበረችው ቤተ ክርስትያን ወንጌል እንደ ተሰበከላቸው ይነግረናል:: ሐዋ7:38“that was in the churcuh in the wildernes” በአማርኛችን ማህበሩ ብሎ ተርጉሞታል:: ወደ እብራ 4:2 ስንመለስ “for indeed we have had gosple preached to us, just as they also…” ለነዛ እንደ ተሰበከ ለእኛም ወንጌሉ ተሰብኮልናልና:: እ/ርም እራሱ ይህን ተስፋ ከጥንት ለአብርሃም ሰብኮታል:: “ገለ3:8 በአንተ አህዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ” አስተዋላቹሁ የእ/ር ወንጌል ማለት አህዛብ ሁሉ ይባረካሉ ! ነው። አጀንዳው ስንቶቹ እንዲባረኩ ነው? አህዛብ ሁሉ! ለማየት ያብቃችሁ እ/ር ተናገረ ማለት ሆነ ማለት ነው። ሁሉን ከክርስቶስ ስልጣኑ ስር ያደርጋቸዋል። የሁሉ ትርጉም በእ/ር ቃል እስቲ እናስተውል።
1ኛ ቆሮ 15:28 ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን። ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት (ከአባት) በቀር መሆኑ ግልጥ ነው። ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል።” አስተዋላቹሁ ሁሉ ተገዝቶለታል ሲል ሁሉን ካስገዛለት ከአባት በቀር መሆኑ ግልጽ ነው። ስለዚህ የሁሉ ትርጉም ከአባት በቀር ያለው ሁሉ ይሸበልላል ወይም ይጠቀልላል ።
፨“ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።” “ተለየ” ፈሪሳዊ ሳለ ለእ/ር ህግ እራሱን ነበር የለየው። የፈሪሳዊ ትርጉም ለእ/ር ህግ መለየት (የሚለዩ)ነውና። አሁን ግን በመጨረሻው ልእለ ተፈጥሮ ስልጣን እ/ር እንዴት እንደ ለራሱ እንደ ለየው እውነቱን እየነገረን ነው። ጳውሎስ መለየቱ ከናቱ ማህጸን ጀምሮ እንደ ሆነም በገላቲያ ላይ ይነግረናል። “ገላ 1:15-16 ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም” ጌታም በደማስቆ ከሾመው ቡሃላ “የሐዋርያት ሥራ 26:16 አገልጋይና ምስክር ትሆን ዘንድ ልሾምህ ታይቼልሃለሁና።” ደግሞም በ“ሐዋርያት ሥራ 9፡15 ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ” ሲል እናስተውላለን። ተለእኮውን የጀመረው ግን ከብዙ አመት ቡሃላ ሁለተኛ ምስክርንትን ከመንፈስ ቅዱስ ከተቀበለ ቡሃላ ነበር። በ “የሐዋርያት ሥራ 13፡2 እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ። በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ።” ከዚያም በቁ.9 “ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን” ይለዋል። ጳውሎስ በክርስቶስ አዲስ ማንነቱ ሲሆን ሳኦል የስጋዊ ማንነቱ ስም ነው። ከዚህ ቁጥር ቡሃላ ሃኪሙ ሉቃስ በአዲስ ማንነቱ ስም ጳውሎስ እያለ ብቻ ይጠራዋል። በሮሜ 7 ላይ ጳውሎስ ስለ ሁለት ማንነቱ ያለውን ትግል ያስረዳናል።
፨“3-4 ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።” ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ
ትንቢተ ኢሳይያስ 11
1 ከእሴይ(ከዳዊት አባት) ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።
2 የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
3 እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም
4 ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
5 የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ፥ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል።
በትረ መንግሥቱ ከይሁዳ እንደ ሚመትጣ ከዳዊት ዘርም እንደሆነ ከኦሪት ጀምሮ እ/ር ሲናገር ነበረ:: “ኦሪት ዘፍጥረት 49፡10 በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።” ከዳዊት ግንድ እንደ ሚመጣ ደግሞ “መዝሙ89፡29 ዘሩንም ለዓለምና ለዘላለም፥ ዙፋኑንም እንደ ሰማይ ዘመን አደርጋለሁ።” ሲል ለባሪያው ለዳዊት ቃል ገብቶለት ነበረ:: የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም በዮሴፍ በኩል በጋብቻ የዳዊት ዘር አድርጎ እ/ር ይቆጥራታል:: መጽሐፍ ዮሴፍ የዳዊት ዘር እደሆነ ያስረዳናል:: “ሉቃ1፡27 ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።” ስለ የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም ትውልድ ከይሁዳ ነገድ መሆንዋን ምንም አይናገርም:: “ሉቃ1፡27 ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።” ሲል ብቻ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ብሎ በእጮኛዋን ነገድ ብቻ ያስተዋውቃታል::
ከየት ነገድ እንደ ሆነች ፍንጭ የምናገኘው መላኩ ገብርኤል ለማሪያም የእ/ርን ቃል ሲያቀብላት ከአሮን ወገን የሆነችውን ኤልሳቤጥን ዘመድሽ ብሎ የጠራትን እናስተውላለን:: የመጥምቁ ዮሃንስ እናትን ከከአሮን ወገን እንደሆነች መጽሐፍ ይናገራል በዚህም የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም እንደ ዘመድዋ ኤልሳቤት ከአሮን ወገን እንደሆነች ግልጽ ነው:: ”ሉቃ1፡ 36 እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤” መላኩ ገብርኤል ለማሪም የእ/ርን ቃል ሲያቀብላት ዘመድሽ ኤልሳቤጥ ብሎ ያረጋግጣል ከዛም ማሪያም ለወራት ከኤልሳቤት ዘመድዋ ዘንድ ተጠልላለች “ሉቃ1፡5 በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።” ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሲል ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።” ይለናል እንደ ምናስተውለው የማሪም ዘመድ ከአሮን ወገን መሆንዋ ብቻ ሳይሆን ከተለያየ ነገድ ጋብቻ ያደርጉ እንደ ነበር እናስተውላለን:: ዘካሪያስ ከአብያ ክፍል ሲሆን ሚስቱም ኤልሳቤጥ ከአሮን ልጆች ነበረች::
በዚህም ከይሁዳ ነገድ የሆነው የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ከአሮን ነገድ የሆነችውን የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም መታጨቱ በዛ ዘመን እንግዳ ነገር እንዳልሆነ እናስተውላለን:: ስለዚህ ጌታ ከይሁዳ ነገድ የዳዊት ዘር የተባለው በዮሴፍ በኩል ነው የዳዊት ልጅ የተባለው እንጂ ከአሮን ወገን ከሆነችው ከናቱ ከማሪም በኩል እይደለም:: ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ብሎ እንደ ተነገረ እ/ር ዮሴፍንና ማሪያምን አንድ ስጋ አድርጎ ስለ ሚቆጥር ከይሁዳ ነገድ አድርጎ ይቆጥራታል በዚህም ጌታ የዳዊት ልጅ ተብሎ ተጠራ :: በጋብቻ ያለው ውህደት በጌታ ፊት ምንኛ ክቡር እንደሆነ ስናስተውል ትህትናን ያስይዛል በአመለካከታችንም ንስሃ ያመጣብናል :: እዚህ ላይ እ/ር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት እጅግ ጥብቅና ሰማይ ከምድር እንደ ሚርቅ ከሰው እመለካከት የራቀ እደሆነ እንረዳለን ::
ጌታ በ “ዘፍ2፡24 ጠቅሶ ሲናገር በ“ማቲ19፡5 አለም። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን?6 ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።” ለዚህም ነው ጌታ ፈሪሳውያንን እንዴት የዳዊት ልጅ ልሆን እችላለሁ ሲል መለኮታዊ ምንጩን እንዲያስተውሉ በማድረግ ዝም ያሰኛቸው:: “የማቴዎስ ወንጌል 22፡41-42 ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ፥ ኢየሱስ፦ ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት።43-44 እርሱም፦ እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?45 ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው።46 አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፥ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።”
፨“እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።” ጳውሎስ ጌታ ከሰው ልጅ በላይ የእ/ር ልጅ እንደ ሆነ ይገነዘባል:: የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ የተገለጠው እንዴት ነው? በቅድስና መንፈስ ከሙታን በመነሳት ሞትን ሽሮ በትንሳኤ የእ/ር ልጅ ሆኖ ተገለጠ:: “የዮሐንስ ወንጌል 10፡17 ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። 18 እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።”
“ወደ ሮሜ ሰዎች6፥4 እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ ” ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን ተነስተዋል የእግዚአብሔርን ክብር እራሱ ኢየሱስ መሆኑ ግልጽ ነው። “የሐዋርያት ሥራ 7፡55 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና።” ይላል። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1 20-21 ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤
የዮሐንስ ወንጌል 14፡8 ፊልጶስ። ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው። 9 ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ? 10 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።
“ወደ ሮሜ ሰዎች8፥11 ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።” “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች15፥45 እንዲሁ ደግሞ። ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።” “የዮሐንስ ወንጌል 11;25 ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ … ይህን ታምኚያለሽን? አላት። “ “2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3;17 ጌታ ግን መንፈስ ነው” “ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3;10-11 እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።”
“የዮሐንስ ራእይ 1;17 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ 18 ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።”
፨“5 በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤”
፨ ስለ ስሙ ፦ “ማቲ1፡ 21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” አስተዋላችሁ ህዝቡ መዳን ያስፈለጋቸው ከሲኦል ሳይሆን ከገዛ ሃጢያታቸው ነው:: “በኢሳ9: 6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።7 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።” “ሐዋ2፡21 የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።” 10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ 11 መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፥3 በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር። ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።
፨ በአሕዛብ ሁሉ፦ “ገለ3:8 በአንተ አህዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ” አስተዋላቹሁ የእ/ር ወንጌል ማለት አህዛብ ሁሉ ይባረካሉ ! ነው። አጀንዳው ስንቶቹ እንዲባረኩ ነው? አህዛብ ሁሉ! ለማየት ያብቃችሁ እ/ር ተናገረ ማለት ሆነ ማለት ነው። “ትንቢተ ኢሳይያስ 25፡6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።”7 በዚህም ተራራ ላይ በወገኖች ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል። 8 ሞትን ለዘላለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል እግዚአብሔር ተናግሮአልና። 9 በዚያም ቀን፦ እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው ተስፋ አድርገነዋል፥ ያድነንማል እግዚአብሔር ይህ ነው ጠብቀነዋል በማዳኑ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን ይባላል።
፨ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤ ከእምነት ይነሳና መታዘዝ ይመጣል ”ሮሜ10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። እምነት በተፈጥሮው የሚመጣው ከሰው ሳይሆን ከእ/ር ነው:: ሮሜ12፡3 እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው አስተዋላችሁ መጀመሪያ እምነትን ለእያንዳዳችን አካፈለን ከዛም የራሳችን አድርገን እንጠቀምበታለን:: ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 21፡3 ስለ በጎ ፈቃዱ(ስለኛ ፈቃድ ሳይሆን) መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። //አንድ እምነት(faith) አለ ኤፌ4፡5// አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ እምነት (faith) እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ:: የይሁዳ መልእክት 1፡3” “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡9 ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት” ይሰጠዋል ፦ ሮሜ16፡25-26 እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥ 27 ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
፨ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤” ፦
፨ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤” ጸጋ the divine influence upon the heart, and its reflection in the life በልብ ውስጥ የተለቀቀ መለኮታዊ ተጽኖ በሂይወትም የሚንጸባረቅ ነው:: የቃሉ ፍቺ ሃብታም ነው ሌላው ትርጉሙ መለኮታዊ አስችሎት፡ መለኮታዊ ስጦታ፡ መለኮታዊ ሞገስ፡ ተቀባይነት የሚያስገኝ “የዮሐንስ ወንጌል 1፡14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ 16 እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና 17 ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ” “ቲቶ2፡11 ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤12-13 ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤”
፨ሐዋርያነትን ተቀበልን፤” ሐዋሪ ያ የተላከ ወይም መልክተኛ ማለት ነው:: ይህም ማለት በላኪው ተመርጦ የተጠራና ትእዛዝን የተቀበለ ሲሆን የተቀበለውም ትእዛዝ በራሱ ስልጣንን ይዞ የሚመጣ ነው ይህም ሃላፊነት ያለበት ትዛዙን የሚፈጽም ቧለማል የላከውን እንጂ የራሱን ፈቃድ የማያደርግ እንደራሴ ነው::
፨6 በእነርሱም መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ ልትሆኑ የተጠራችሁ እናንተ ደግሞ ናችሁ። የእ/ር ፈቃድ ሁሉን ለማዳን ቢሆንም አሁን እያዳነ ያለው በስሙ የሚጠርቱን ከሰዎች መካከል እየለየ ነው:: ከዛ ቡሃላ ነው ወደ ፍጥረት ማዳን ከተመረጡት ጋር ሆኖ ፍጥረትን ሁሉ ከመበስበስ ባርነት ወደ ከበረው የእ/ር ልጅነት የሚያደርሳቸው ሮሜ8፡21 ሁሉን አሁን ባንዴ ለማዳን ቢፈልግ አያቅተውም አላማው ሰፊ ነውና ለሁሉም ጊዜ አለው ከጸሃይ በታች ላለ ነገር ሁሉ አላማና ጊዜ ሰጥቶታል::
ሐዋ 15፡14 እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን ተርኮአል። 15 ከዚህም ጋር የነቢያት ቃል ይሰማማል፥ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ። 16-17 ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ፥” ሁሉ በተራው ነው
“1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡22 ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። 23 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤
፨ 7 በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ በሮሜ ላላችሁት ሁሉ፥ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። በእ/ር ለተወደዱ ለተጠሩ(በመለኮት ለተመደቡ) ቅዱሳን(ለመለኮት አገልግሎት የተለዩ) ሁሉ በሮሜ ላሉ ክርስቶስ ይህ በግሪኩ and የሚለው የእንግሊዝኛ አያያዥ ቃል ሆነ የአማርኛው ሲተረጉሙ የጨመሩት ነው:: ሆኖ መተርጎም የነበረበት ነበር ጳውሎስ ሶስተኛውን ወንበር ባዶውን ለምን ተወው መንፈስ ቅዱስን መጨመር ነበረበትና :: እ/ር አንድ ነው! በወደደው እራሱን ሊገልጥ ይችላል:: ጌታ እኔና አባት አንድ ነን አላለም? ዮሃ1፡1 የእ /ር ቃል ይለው የለን? እንግዲያው ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ቃል ስለ ሆነው እ/ር የሚናገር ነው:: ከጌታ ዘንድ ለተጠሩ(በመለኮት ለተመደቡ) ሁሉ ጸጋና ሰላም ለነሱ ነው:: የእ/ር ጸጋ ሙሉ መገለጥና የሰላም አለቃና ንጉስ ጌታ እየሱስ እራሱ ነው::
፨ 8 እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማች አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።
እምነታችሁ፦ ሲል አንዴ አስቀድመው ከእ/ር የተቀበሉትን የራሳቸው እምነት እንደሆነ በመቁጠር ይናገራቸዋል:: እ/ር በስጦታው አይፀፀትምና ደግሞም ቡሃላ እልፍ ብሎ በሮሜ12፡ 3 የእምነታቸው ምንጭ እ/ር እንደሆነ ይገልጥላቸዋል:: በዚህም ሰው ከላይ ካልተሰጠው በቀር አንዳች ሊያደርግ አይችልም የሚለውን እውነት አያይዘን እናስተውላለን:: በሮሜ12፡ 3 እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ። የእምነትን መጠን ያካፈለው እግዚአብሔር ነው:: በዚህም ስጋ ለባሽ በፊቱ ዕንዳይመካ ትህትናን አስያዘን የሚመካ በእ/ር ብቻ ይመካ! ነውና:: የይሁዳ መልእክት 1፡3 ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ እምነት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ(አዲሱመደበኛ ትርጉም) ከተቀበልን ቡሃላ ግን የራሳችን አድርገን በዛ እምነት ስንኖርበት እ/ርን ደስ ያሰኘዋል:: ያለ እምነት እ/ን ደስ ማሰኘት ማንም አይችልምና::
አንድ ጊዜ ሐዋርያት ጌታን። እምነት ጨምርልን አሉት። ጌታም የእምነት ምንጩ እ/ር አይደለም ብሎ አልተከራከረም የእምነታችን ጀማሪውና ፍጹም አድራጊው እራሱ እንደሆነ ያውቃልና ዕብ 12፡2 የእምነታችንንም ጀማሪና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥(አዲሱ መደበኛ ትርጉም) ይሉቀንም አንድን ነገር እ/ር ሲሰጣችሁ ዘርን እንጂ ዛፉን እንደ ማይሰጣቹሁ ስለሚያውቅ በሉቃ 17፡6 ጌታም አለ። የሰናፍጭ ቅንጣት(ዘር) የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ። ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳ ካፈለው ካለ ደግሞ መጠንዋ ከሰናፍጭ ቅንጣት(ዘር) ታንስ ይሆናል እንጂ ቃሉ እውነት ነው:: ሮሜ 10፥17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። እምነት በባህርዩ የሚመጣው የእግዚአብሔር ቃል(ድምጽ) በመስማት ነው:: “ የዮሐንስ ወንጌል 6፡ 45 ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማ የተማረም ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል” እንግዲህ ሁላችንም ከአብ የሰማነውና የተማርነው ወደ ጌታም የመጣነው መቼ ነው? አብን ያየ አንድ ስንዄ ሰው የለምና መለሱን በመንፈሱ እንጂ በሃይልና በብርታችን ለማይሰራው ሁሉን ለሚያቀው ለእርሱ እተወዋለ ::
፨ እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማች፦ እምነታቸው የተሰማችው አመንኩ ስለዚህም ተናገርኩ ተብሎ እንደተጻፈ እምነት ይናገራልና በሰው ፊት ሁሉ ሳያፍሩበት ስለ ጌታ ስለ ተናገሩለት ነው:: ዓለም የሚለው ቃል kosmos ከሚለው የግሪኩ ቃል የተተረጎመ ሲሆን orderly arrangement የተደራጀውን ስርአት የሚያመለክት ነው:: ያም በዛ ዘመን የገነነውን የሮም ስርአትን የሚያሳይ ነው:: በአለም ሁሉ ስለ ተሰማች በዛን ጊዜ የሮማ ስርወ-መንግስት ተንሰራፍቶ በሜድትራኒያን አከባቢ በቅኝ ግዛት በያዛቸው አገሮች ሁሉ በግዛቶቹ ያካለለውን የሚያመለክት ነው:: ይህም በአለም ሁሉ ማለቱ በሮም ኢምፓየር(ግዛቶች) ሁሉ እምነታቸው መሰማቱን ለማመልከት የተጠቀመበት የብእር አጣጣል የግነት ዘየ ነው:: ለምሳሌ ሌላ ተመሳሳይ ሃሳብ ብናይ” የሉቃስ ወንጌል 2፡1 በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች። 2 ቄሬኔዎስ በሶርያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ። 3 ሁሉም እያንዳንዱ ይጻፍ ዘንድ ወደ ከተማው ሄደ።” አውግስጦስ ቄሣር በዛ ዘመን የነበረውን ህግ አልባነትን ጦርነትን ሁከትን አመጽን ሁሉ በሃይል አንበርክኮ ድል ካደረገ ስርአትን ካደሰ ቡሃላ በሜድትራኒያን ብዙ ግዛቶችን ይዞ ነበር። የህዝብ ቆጠራ የተደረገውም በግዛቶቹ ሁሉ ነው እንጂ አለምን ሁሉ ያካለለ ነው ማለት አይደለም:: ሌሎች አገራት ከስልጣኑ ስር አልነበሩምና::
ሌላው መንገድ የእ/ር ታላቅ ስራ ዝናው በምድር ሁሉ የተነገረበት መንገድ በዚህም መልኩም እናስተውላለን የሐዋርያት ሥራ 2፡4 በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር። ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤ ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ። እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? 8 እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን? 1 የጳርቴና 2የሜድ3 የኢላሜጤም ሰዎች፥ በሁለት ወንዝም መካከል 3በይሁዳም 4በቀጰዶቅያም5 በጳንጦስም 6በእስያም፥ 7 በፍርግያም 8በጵንፍልያም 9በግብፅም19 በቀሬናም በኩል ባሉት 11በሊቢያ ወረዳዎች የምንኖር፥ 12በሮሜም የምንቀመጥ፥ አይሁድም ወደ ይሁዲነትም የገባን፥ 113 የቀርጤስና14 የዓረብ ሰዎች፥ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን። 12 ሁሉም ተገረሙና አመንትተው እርስ በርሳቸው። እንጃ ይህ ምን ይሆን? አሉ። እነዚህ ከነገድ ከቋንቋ ከየአገሩ የተሰበሰቡት የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ ወደየ አገራቸው አስራጭተዋል::
አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ፦ ጌታ ለሁሉም ነገር በተመለከተ ወደ መንፈሳዊው ግዛት ለመግባት ብቸኛው መንፈሳዊ በር ነው::
የዮሐንስ ወንጌል 10፥9 በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።” በዚህ መንፈሳዊ በር ሰው ወደ መዳን ይገባል ይወጣልም መሰማሪም ያገኛል:: ወንድማችን ጳውሎስ ስለ ሁሉ እናመሰግን፤ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እኛ እንደሆነም ይገነዘባል።” “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፥20 ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።”
“ 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፥17-18 ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።”
፨“ ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡9-10 በልጁ ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና፤ ምናልባት ብዙ ቆይቼ ወደ እናንተ አሁን እንድመጣ በእግዚአብሔር ፈቃድ መንገዴን እንዲያቀናልኝ እየለመንሁ ሁልጊዜ ስጸልይ ስለ እናንተ ሳላቋርጥ አሳስባለሁ።
በልጁ ወንጌል ፦ የልጁ ወንጌል እንደዚህ ነው:: የሉቃስ ወንጌል 4፡17-19 የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ። የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። 20 መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። 21 እርሱም፦ ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ ይላቸው ጀመር። እንዳስተዋልነው የልጁ ወንጌል ይህን መንፈሳዊ ትይንት ያዘለ ነው:: ለድሆች ወንጌልን(የምስራቹን) መስበክ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን መስብክ የተጠቁትንም ነጻ ማውጣት የተወደደችውንም የጌታን ዓመት መስበክ ነው:: “ወደ ገላትያ ሰዎች 3፡8 መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ። በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ።… 14 የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ።”
በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና፤፦ “In my spirit” (NASB) means “with my whole heart” (NIV). “የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው የሆዱን ጕርጆች ሁሉ የሚመረምር።መጽሐፈ ምሳሌ 20፡27” “መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16፡7 …..ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው።” “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡11 በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው?” መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 28፥9 አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና፥ የአባትህን አምላክ እወቅ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው ብትፈልገው ታገኘዋለህ ብትተወው ግን ለዘላለም ይጥልሃል። “መጽሐፈ ምሳሌ 21፡2 የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።” “የዮሐንስ ወንጌል 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።”
እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና፤፦ ጳውሎስ ምስክሩ እ/ር እንደሆነ ይታመናል “የሉቃስ ወንጌል 12፡8 እላችሁማለሁ፥ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል፤ 9 በሰውም ፊት የሚክደኝ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይካዳል።” እንደምናስተውለው በሰው ፊት የሚመሰክር ሁሉ በእ/ ር መልአክት በ(Gr. aggello) a messenger መልክተኞች ፊት እ/ር ይመስክርለታል በሰው ፊት የሚክደው በአንጻሩ በእ/ር መልክተኞች ፊት ይካዳል :: ጳውሎስ በሮሜ ላሉት ምስክሩ እ/ር እንደሆነ በመታመን ይናገራል::
ወደ እናንተ አሁን እንድመጣ በእግዚአብሔር ፈቃድ መንገዴን እንዲያቀናልኝ እየለመንሁ፦ ሐዋሪያው ጳውሎስ የነገሮች ሁሉ የበላይ ሉኡሉ እንደሆነ ያውቃል:: በእግዚአብሔር ፈቃድ ማለቱ ወደ እነሱ ለመሄድ ቢፈልግም ለአካየዱ እንካን እ/ር የበላይ ሉኡሉ እንደሆነ ያውቃል::
“መጽሐፈ ምሳሌ 3፡5 በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ 6 በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።”
“ትንቢተ ኤርምያስ 10፥23 አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም። “
“መጽሐፈ ምሳሌ 5፥21 የሰው መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና። “ ”መጽሐፈ ምሳሌ 16፥9 የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቀናለታል።” “መጽሐፈ ምሳሌ 20፥24 የሰው አካሄዱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው እንግዲያስ ሰው መንገዱን እንዴት ያስተውላል?”
ሁል ጊዜ ስጸልይ ስለ እናንተ ሳላቋርጥ አሳስባለሁ፦ሁል ጊዜ ስጸልይ ወንድማችን ጳውሎስ ስለ ሁሉ ሁል ጊዜ መጸለይ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እኛ እንደሆነም ይገነዘባል “ 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፥17-18 ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።” ወንድማችን ጳውሎስ ስለ ሁሉ ሁል ጊዜ መጸለዩ ለጸሎት ቀመር እንደ ሌለው ያውቃል :: ሰው ተንበርክኮ ሊጸልይ ይችላል:: ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ ቆሞም መጸለይ ይቻላል:: በአልጋ ላይ የወደቁትንም ሰምተዋል ምክንያቱም እ/ር መንፈሱ የተሰበረውን እራሱን ያረደውን ትሁቱን ያየዋል እ/ር ታላቅ ነው ማንንም ግን አይንቅምና:: በዚያም ወራት ሕዝቅያስ እስከ ሞት ድረስ ታመመ…..ፊቱንም ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ….. 5 ተመልሰህ የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው። የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ እነሆ፥ እፈውስሃለሁ በሦስተኛውም ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ። 6 በዕድሜህም ላይ አሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ ……መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 20፡1 ነህምያም እየሰራ ወይን ጠጅ እያሳለፈ ጸለየ እ/ርም አላሳፈረውም ሞገስን ሰጠው ተከናወነለት::
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6፥18 በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤” በመንፈስ ጸልዩ፤ ጸሎት በቀላሉ በመንፈስ ነው:: በመንፈስ ከሆነ ደግሞ ጊዜና ቦታ አይወስነውም:: ጸሎትና አምልኮ ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው በመንፈስና በእውነት እንደ እ/ር ፈቃድ ከሆኑ ከጣራ አልፈው በእ/ር ፊት መለካም መአዛ ያላቸው ህያው መስዋት ናቸው::
፨ “ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡11 ትጸኑ ዘንድ መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁና፤ 12 ይህንም ማለቴ በመካከላችን ባለች በእናንተና በእኔ እምነት አብረን በእናንተ እንድንጽናና ነው።” ወንድማችን ጳውሎስ ወገኖች ሲገናኙ እ/ር በረከትን በዚያ እንዳዘዘ ለመጽናትም ጌታ እንደ ሚጠቀምበት ያውቃል:: በይሁዳ መልእክት 1፡3 እንደ ሚናገር ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ የተሰጠ እምነት ለሁሉም እንዳላቸው ያውቃል:: በዚህም መንፈሳዊ ስጦታ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለመቀበልም ዝግጁነው:: 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡21 ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። በሚለው መልክቱ እምነትን ጭምር በአጠቃላይ ሁሉም መንፈሳዊ ነገር ስጦታ እንደሆነ ይነግረናል። እንካን እምነት መጽሃፍ ጌታ እየሱስ እራሱ የእ/ር ስጦታ እንደሆነ ያስተምረናል። “የዮሐንስ ወንጌል 4፡10 ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና። ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት”
በ“መዝሙረ ዳዊት 133፡1 ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው። 2 ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው። 3 በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና።”
“ የማቴዎስ ወንጌል 18፡20 ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።” “ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡ 17 ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።” በእ/ር ህልውና መገኘት የደስታ ሙልአት አለና አሜን! እንላለን።
፨ 13 ወንድሞች ሆይ፥ በሌሎቹ አሕዛብ ደግሞ እንደ ሆነ በእናንተም ፍሬ አገኝ ዘንድ ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳሰብሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።
ወንድማችን ጳውሎስ ለሌሎች አህዛብ ወንጌልን በመስበክ እጅግ ደክመዋል። በድካም ሁሉ ልማት (ፍሪ)አለና ፍሪም አግኝቶባቸዋል:: የሮሜ ሰዎችም መልካም መሬት እንደሆኑ ስለ ሚገነዘብ ዘር ዘሪ ዘርን ሊዘራ ወጣ ዘሩም የእ/ር ቃው ነው ዘሩም በቀለ አንዱ 30፡60፣ 100 አፈራ ተብሎ እንደ ተጻፈ በእነሱም ይህን የማይለወጥ መንፈሳዊ መመርያ ተጠቅሞ ፍሬን ሊያይ ወደ እነሱ ሊሄድ ያስባል:: ሆኖም ቡሃላ በምእራፍ 15 እንዳስረዳቸው “ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ያያሉ፥ ያልሰሙም ያስተውላሉ ተብሎ እንደ ተጻፈ ።” የክርስቶስ ስም በተጠራበት ስፍራ ሳይሆን ባልተጠራበት አህዛብ ወንጌልን ለመስበክ ሲጣጣር ወደ ሮሜ እንዳይመጣ ስራ በዝቶበት እንደተለከለ ይናገራል::
“ወደ ሮሜ ሰዎች 15 ፡20 እንዲሁም በሌላው ሰው መሠረት ላይ እንዳልሠራ የክርስቶስ ስም በተጠራበት ስፍራ ሳይሆን ወንጌልን ለመስበክ ተጣጣርሁ፤ 21 ነገር ግን። ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ያያሉ፥ ያልሰሙም ያስተውላሉ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። 22 ስለዚህ ደግሞ ወደ እናንተ እንዳልመጣ ብዙ ጊዜ ተከለከልሁ። 23 አሁን ግን በዚህ አገር ስፍራ ወደ ፊት ስለሌለኝ፥ ከብዙ ዓመትም ጀምሬ ወደ እናንተ ልመጣ ናፍቆት ስላለኝ፥ 24 ወደ እስጳንያ በሄድሁ ጊዜ ሳልፍ እናንተን እንዳይ፥ አስቀድሜም ጥቂት ብጠግባችሁ ወደዚያ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ።” “የሐዋርያት ሥራ 1921 ይህም በተፈጸመ ጊዜ ጳውሎስ፦ ወደዚያ ደርሼ ሮሜን ደግሞ አይ ዘንድ ይገባኛል ብሎ በመቄዶንያና በአካይያ አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ በመንፈስ አሰበ።”
፨14 ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም ዕዳ አለብኝ፤ 15 ስለዚህም በሚቻለኝ መጠን በሮሜ ላላችሁ ለእናንተ ደግሞ ወንጌልን ልሰብክ ተዘጋጅቼአለሁ።
ለግሪክ ሰዎችና ፦ይህ ቃል የሚያመለክተው በሜዲትራንያን አከባቢ ለነበሩ ለግሪክ ቋንቋ ተናጋሪዎች ነው:: በዛ ዘመን ፍልስና የበዛውና የስልጣኔ ቁንጮ ተደርገው ከሚታሰቡት መካከል ነበሩ:: ታላቁ አሌክሳንደር ከግሪክ ተነስቶ ቅኝግዛቱን በሰፊው አድርጎ ተያይዞት ነበር:: ከሱ ውድቀት ቡሃላ ግን ግሪኮች በዛመልኩ አልቀጠሉም። ሮማዊያን የሚያተኩሩት ህግና ስርአት ላይ ሲሆን ግሪኮች ፍልስፍናን ይወዱ ነበር:: የመከላከያ ሃይላቸውም ግንባታ ለስለስ ያለ ስለ ነበር በዚህ ምክንያት ግሪኮች ለቅንኝ ግዛት የተጋለጡ ነበሩ::
ላልተማሩም፦ የሚላቸው የክሪክ ቋንቌ የማይናገሩትን ሌሎች ህዝቦችን ነው::
ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም፦ለጥበበኞች ግሪኮችን የሚወክል ሲሆን በ “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፥22 መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥ ተብሎ እንደተጻፈው ነው።”
ለማያስተውሉም፦የሚላቸው የክሪክ ቋንቌ የማይናገሩትን ሌሎች ህዝቦችን በዛን ዘመን ከጥበብ የራቁ ተደርገው ይታሰቡ ስለ ነበር ነው::
ዕዳ አለብኝ፤፦ ጌታም በደማስቆ ከሾመው ቡሃላ ሃላፊነት ይሰማዋል፤ “የሐዋርያት ሥራ 26:16 አገልጋይና ምስክር ትሆን ዘንድ ልሾምህ ታይቼልሃለሁና።” ደግሞም በ“ሐዋርያት ሥራ 9፡15 ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ” ሲል እናስተውላለን።47 የጌታውንም ፈቃድ ካወቀ ቡሃላ መንፈሳዊ ስልጣን ሃላፊነቱንም ይዞ እንደሚመጣ ያውቃል። ደጎሞም ጌታችን ብዙ ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል። ብሎ እንደተናገረው ነው። “የሉቃስ ወንጌል 12፡47 የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል፤ 48 ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።”
ስለዚህም በሚቻለኝ መጠን በሮሜ ላላችሁ ለእናንተ ደግሞ ወንጌልን ልሰብክ ተዘጋጅቼአለሁ።፦ ሁሌም ዝግጁ መሆኑን እናስተውላለን “2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፥16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” የመከረውን እራሱየሚኖሮወን እንደሆነ እንረዳለን::
፨16 በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።
በወንጌል አላፍርምና :፦ ጳውሎስ ስለእውነት ሲል እስከ ሞት ድረስ የታመነ እንደ ሆነና እንደ ማያፍር ጌታውን ሊያከብር እንደቆረጠ ደጋግሞ በሌላ ስፍራም ይነግረናል ።“ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1፥20 ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በአንድ ነገር እንኳ አላፍርም ነገር ግን በህይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ በግልጥነት ሁሉ እንደ ወትሮው አሁን ደግሞ በስጋዬ ይከብራል።” በወንጌል አላፍርምና ሲል ወንጌልም መልካም ዜና ነው። ምንም መጥፎ ዜና በውስጡ የለበትም። gospel ወይም ወንጌል ‘evangel’ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ይህም ሁለት ጥምር ቃላትን በውስጡ ያቀፈ ነው። ‘eu’ኢዩ- good ወይም መልካም እናም ‘angelion’አንጀሊኦን- message ወይም መልክት ማለት ነው። የምስራቹም ስለ ልጁ ነው ስለ አዳጁ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ስለ መሆኑ ነው። አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ከዛም ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።ለሚያምኑ ሁሉ ሲል በእ/ር ለተጠሩ ማለቱ ሲሆን የእ/ር ሃይል የሚለው ደግሞ ክርስቶስን ነው “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡23 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥ 24 ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።” እንዳስተዋልነው ላልተጠሩት ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ሲሆን ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው “የሐዋርያት ሥራ 13፡48 አሕዛብም ሰምተው ደስ አላቸው የእግዚአብሔርንም ቃል አከበሩ፥ ለዘላለም ሕይወትም የተዘጋጁ ሁሉ አመኑ፤” የተዘጋጁ የሚለው ከግሪኩ ቃል tas’-so ከሚለው የተተረጎመ ሲሆን ordained የሆኑ በመለኮት የተመደቡ ስለመሆናቸው ያመለክታል።
የKJV በትክል ተርጉሞታል Acts 13፡48 And when the Gentiles heard this, they were glad, and glorified the word of the Lord: and as many as were ordained to eternal life believed.
“የይሁዳ መልእክት 1፡1 ….. በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤ 2 ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ 3 ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት(faith እምነት) እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።” እንዳስተዋልነው በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠቸው (faith እምነት) እንዲጋደሉ ይመክራቸዋል:: ከዝም አዛምደን አብ ከሳበው በቀር ወደኔ ሊመጣ የሚችል የለም ያለውን እውነት እናስተውላለን።
አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ፦ “ወደ ሮሜ ሰዎች 2፡9 ክፉውን በሚያደርግ ሰው ነፍስ ሁሉ መከራና ጭንቀት ይሆንበታል፥ አስቀድሞ በአይሁዳዊ ደግሞም በግሪክ ሰው፤ 10 ነገር ግን በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፥ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው። 11 እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።” “የሐዋርያት ሥራ 3፡26 ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።”
ለማዳን ነውና።፦ ከላይ እንዳየነው
፨17 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።
ጻድቅ በእምነት ይኖራል፦ ይህን ቃል የጠቀሰው ከ “ትንቢተ ዕንባቆም 2፡4 እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል” ከሚለው ነው ስላልጽደቀ ሰው እንጂ ስለሃጥእ የተናገረ አይደለም። የጸደቀ ሰው በህይወት የሚኖረው በእምነት እንደሆነ የሚያሳይ ነው:: ሰው እራሱን አያጸድቅምና። “የሚያጸድቅ እ/ር ነው” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።፦ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ማለትም በ እ/ር የሚገለጥበት ምክንያት እምነት የእ/ርን ቃል ወይም ድምጽን ከመስማት የሚመጣ ሥለሆነ እርሱ ይናገራል እኛም በሰማነውና በታዘዝነው ልክ ከእምነት ወደ እምነት እንሻገራለን::
፨”18 እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤ 19 እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። Brother Binyam T. Alemayehu Wongel Radio
እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ የመገለጡ ምክንያት እውነትን ስለማያቁ ሳይሆን እውነትን ስለሚያውቁ ላወቁት እውነት በእ/ር ፊት ተጠያቂ ናቸውና ለዚህምም ምላሽ የእ/ር ቁጣ ተገለጠ። እውነትን ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊያውቁት የሚገባቸውን እውነት በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ሆነ ሳለ እውነትን በዓመፃ ስለከለክሉ ነው። ያወቅነው እውቀት እ/ርን እንድናከብረው ካላደረገን ከንቱ ነውና ፍርድን ያመጣል። ከመጽሃፍ ስናስተውል እውቀት ሁለት ውጤት አለው። 1ኛ እውቀት ያስታብያል ተብሎ እንደ ተጻፈ ወደ ትቢት ሰፈር ያሳድጋል ይህ ጠማማ እድገት ደግም ዘሞ አይቀርም በመጨረሻው ይወድቃል። ከውድቀት በፊት ትቢት ይቀድማል ተብሎ እንደተጻፈው ማለት ነው። 2ኞው ጤናማው እውቀት ያድናል ወደ ክርስቶስ መልክና አምሳል ደግሞም ወደ ትህትና ሰፈር ያሳድገናል። ለዚህ ትልቁ ምሳሌ ጌታ እየሱስ እራሱ ነው እርሱ የእውቀት ራስ ሆኖ ሳለ እኔ በልቤ ትሁትና የዋህ ነኝ ከኔ ተማሩ አለ የእ/ር ፈቃድ ፈጽሞ ያደርግ ነበረ። ስለዚህ እኛም በጤናማ እውቀት ወደ ትህትና ሰፈር ካላደግን ቆም ብለን እራሳችንን መመርመር ይገባናል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡31 ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤ ተብሎ እንደተጻፈው ነውና።
፨“ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡20-21 የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ።”
የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤፦ የማይታየው ባሕርይ እ/ር መንፈስ ስለሆነ በመጀመሪያ ደረጃ መንፈስ በስጋ አይን አይታይም የዮሐንስ ወንጌል 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የዘላለም [aidios, “perpetual” የመያልቅ(ወሰን የሌለው) ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ በፍጡራኑ ላይ የአምላክነቱ ወይም የመለኮትነቱ መልክት አስቀምጥዋልና ሰው ፍጡራኑን በማየት ፈጣሪውን ያያል።
“መዝሙረ ዳዊት 19፡1 ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል። 2 ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች። 3 ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም። 4 ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።” ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ ምን የሚል ድምጽ ነው ? የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ:: ኦሪት ዘፍጥረት 1፡14 እግዚአብሔርም አለ፦ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ አለ ይህን ቃል ስናስተውል ለምልክቶች፤ ለዘመኖች፤ለዕለታት፤ ለዓመታትም ስናስተውል ሶስቱ ለዘመኖች፤ለዕለታት፤ ለዓመታትም የጊዜ መለያ አድርጎ በአላማ ሰራቸው 4ኞው ለምልክቶች signs ያለው ምንን የሚያመለክቱ ናቸው? አዎን ግልጽ ነው የእ/ርን ክብር አመልካቾች ናቸው:: ቡሃላም ፉጥራኑ ሁሉ ሲያከብሩት ይስተዋላል። በየዮሐንስ ራእይ 5፡13 በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ። በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ።
ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ።” ለኛም ቢሆን ያወቅነው እውቀት እ/ርን እንድናከብረው እና እንድናመሰግነው ካላደረገን ከንቱ እንደሆነ ከቀደሙት እናስተውላለን።
፨22 ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ Rom 1፡22 Professing themselves to be wise, th ey became fools, ባወቁት እውቀት እ/ርን እንዳያከብሩ እና እንዳያመሰግኑ በሃሳባቸው ከንቱ በልባቸውም ጨለማ ሆነ ጥበበኞች ነን ሲሉ ሞኞች ሆኑ፥ የሞኝ መጨረሻው ግልጽ ነው መዝሙረ ዳዊት 14፡1 ሰነፍ(ሞኝ) በልቡ። አምላክ የለም ይላል። በልቡ ይጀምራል ከዛ ልቡ ከሞላው በአፉ ይፈሳል።
፨23 የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ።
የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር ፦ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4-18 የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው የሚታየው ሁሉ በጊዜ የተወሰነ ነው ክብሩየሚጠፋነው። የማይታየው እ/ር ግን ዘላለማዊ ነው::
በሚጠፋ ሰውና በወፎች፦ በግብጻዊያን Bird Headed Gods የወፍ እራስ ያላቸው የሰዎች ጣኦታት ይመለኩ ነበር።
አራት እግር ባላቸውም፦ አራት እግር ባላቸውም ምስሎች ግብጻዊያን ያመልኩ ነበር እስራኤል የግብጽን አማልክት በማምለክ ባሪያውን ሙሴንና እ/ርን በምድረበዳ አስቆጥተውታል። “ኦሪት ዘጸአት 32፡8 ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ለራሳቸው አደረጉ፥ ሰገዱለትም፥ ሠዉለትም። እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አሉ ሲል ተናገረው።” “መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 17፡9 የእስራኤልም ልጆች በአምላካቸው በእግዚአብሔር ላይ ቅን ያልሆነን ነገር በስውር አደረጉ በከተሞቻቸውም ሁሉ ከዘበኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ተመሸገች ከተማ ድረስ በከፍታዎቹ ላይ መስገጃዎችን ሠሩ።….12 እግዚአብሔርም የከለከላቸውን ጣዖቶች አመለኩ።” Brother Binyam T. Alemayehu Wongel Radio
፨24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤25 ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን።
24 እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር ጥበቃውን በማንሳት ለክፉ ልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው ምክንያት ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በዚህ ዘመንም እንደሚታየው ለፈጣሪ የተገባውን አምልኮ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እነርሱ ቀረባቸው እንጂ እርሱ ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን
፨26 ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ 27 እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። 28 እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው
እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት ና ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው የማይረባ አእምሮ ደግሞ የተዛባ ባህሪ ያመጣል። በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በስጋቸው ተቀበሉ። የሰዶምና የገሞራ የሃጢያት ጩኸት እጅግ በዝቶና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳ ስለ ነበር ለንስሃም እድል ሳይሰጣቸው በስጋቸው ብድራት እዲቀበሉ ወስኖ ነበር::
“ኦሪት ዘፍጥረት 18፡ 20 እግዚአብሔርም አለ፦ የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና፥”
ኦሪት ዘፍጥረት 19፡24 እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ 25 እነዚያንም ከተሞች፥ በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ፥ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ። ከጌታ እየሱስ ንግር እንደምንረዳው ለንስሃም እድል ሳይሰጣቸው በስጋቸው ብድራት እዲቀበሉ ወስኖ ነበር ነው እንጂ እድሉ ቢሰጣቸው እስከ ዛሬ ባልጠፉ ነበር ብለዋል። የማቴዎስ ወንጌል 11፡23 አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና።
የ እ/ር ህግ በዚህ ጉዳይ ላይ አቋሙ ግልጽ ነው። ኦሪት ዘሌዋውያን 18፡22 ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ ጸያፍ ነገር ነውና። 23 እንዳትረክስባትም ከእንሰሳ ጋር አትተኛ ሴት ከእርሱ ጋር ትተኛ ዘንድ በእንስሳ ፊት አትቁም የተጠላ ነገር ነውና። 24 በእነዚህ ሁሉ ከፊታችሁ የማሳድዳቸው አሕዛብ ረክሰዋልና በእነዚህ ነገሮች ሁሉ አትርከሱ። 25 ምድሪቱም ረከሰች ስለዚህ ኃጢአትዋን በእርስዋ ላይ እመልሳለሁ፥ ምድሪቱም የሚኖሩባትን ሰዎች ትተፋለች። በህሊና ህግ ይ ሁን በሙሴ ህግ መልክ እወነትን የግለጠላቸው ለህግ እርግማን ተጋልጠዋል እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት ና ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው (ለህግ እርግማን) አጋለጣቸው የማይረባ አእምሮ ደግሞ የተዛባ ባህሪ ያመጣል። Deut 28፡28 The LORD will also subject you to confusion of mind. እግዚአብሔር በዕብደት(በአይምሮ መዛባት)፥ ይመታሃል። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ የሰጣቸው በዚህ መልኩ ነው።
እ/ር በሰው አይሞሮ ላይም ጌታዋ እንደሆነ ናቡክነደጸርን ሚሞሪውን ዋይፕ አድርጎ የእንስሳ አይምሮ እንደሰጠውና ቡሃላም አይምሮውን በመመለስ ትህትናን ሲያስተምረው ከታሪኩ አስፈሪ አምላክ እንደሆነ ልንማር እንችላለን ።
“ትንቢተ ዳንኤል 4፡32 ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፥ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ፥ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል አለው። 33 በዚያም ሰዓት ነገሩ በናቡከደነፆር ላይ ደረሰ ጠጕሩም እንደ ንስር፥ ጥፍሩም እንደ ወፎች እስኪረዝም ድረስ ከሰዎች ተለይቶ ተሰደደ፥ እንደ በሬም ሣር በላ፥ አካሉም በሰማይ ጠል ረሰረሰ። 34 ዘመኑም ከተፈጸመ በኋላ እኔ ናቡከደነፆር ዓይኔን ወደ ሰማይ አነሣሁ፥ አእምሮዬም ተመለሰልኝ ልዑሉንም ባረክሁ፥ ለዘላለምም የሚኖረውን አመሰገንሁ አከበርሁትም ግዛቱ የዘላለም ግዛት ነውና፥ መንግሥቱም ለልጅ ልጅ ነውና። 35 በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቈጠራሉ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል እጁንም የሚከለክላት ወይም። ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም። 36 በዚያን ጊዜም አእምሮዬ ተመለሰልኝ፥ ለመንግሥቴም ክብር ግርማዬና ውበቴ ወደ እኔ ተመለሰ አማካሪዎቼና መኳንንቶቼም ፈለጉኝ፥ በመንግሥቴም ውስጥ ጸናሁ፥ ብዙም ክብር ተጨመረልኝ። 37 አሁንም እኔ ናቡከደነፆር የሰማይን ንጉሥ አመሰግናለሁ፥ ታላቅም አደርገዋለሁ፥ አከብረውማለሁ። ሥራው ሁሉ እውነት፥ መንገዱም ፍርድ ነውና፥ በትዕቢትም የሚሄዱትን ያዋርድ ዘንድ ይችላልና።”
፨29 ዓመፃ ሁሉ፥ ግፍ፥ መመኘት፥ ክፋት ሞላባቸው፤ ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን፥ ክርክርን፥ ተንኰልን፥ ክፉ ጠባይን ተሞሉ፤ የሚያሾከሹኩ፥ 30 ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚያንገላቱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ 31 የማያስተውሉ፥ ውል የሚያፈርሱ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት ያጡ ናቸው፤ 32 እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም።
ወንድማችን ጳውሎስ ወደ ገላትያ ሰዎች በጻፈው መልክት 5፡19 የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው ሲል የእ/ር ጠላት የሆነው ለእ/ር ህግ የማይገዛው ያልታደሰው ስጋዊ አይምሮ ስራዎች አከታትሎ ያስረዳናል ከላይ የተጠቀሰውም በስጋ ስራ የሚመደብ ነው። በዚህም በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በስጋቸው የተቀበሉት። ትህትናን እንማራለን። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡8 በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። በመንፈስ ዘርተን ህይወትንና ሰላምን እንድናጭድ የእ/ር ጸጋ ሁላችንንም ይርዳን። ወደ ሮሜ ሰዎች 9፡16 እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። ተብሎ እንደ ተጻፈ በክርስቶስ እየሱስ ወደ ምህረቱ ዙፋን ያቀረበን የሚያስፈልገንን ጸጋ ለሰጠን ለቅዱስ ስሙ ለዘላለም ብሩክ ይሁን:: አሜን!